𝔂𝓮𝓫𝓮𝓴𝓾𝓵𝓮𝓷 የበኩሌን

Description
የበኩሌን.... ግጥም +
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 months, 3 weeks ago

.....እነሆ የእውቀት ጮራ ሲደበዝዝ የጥይ ብልጭታ ይሆናል....ብረቶችን ማጭድ አድርጎ የሚያበጃቸው አንጥረኛ ጩቤ አቅላጭ ጎራዴ ቀጥቃጭ ጦረኛ በመሆን ለከንቱ ይለፋል። ገበሬም አውድማ ላይ አይታይም።ነጋዴም መሳሪያ ያዘዋውራል።ሀኪምም ቁስለኛ ጠጋኝ ..መካነ መቃብራትም ሙታኖቻቸውን ለመቀበል አፎቻቸውን ከፍተው ሽርጉድ ይላሉ.....✍️

ሕዋ

3 months, 4 weeks ago

የሀሳብ ውልብታ ፥ ቅጽበተ ሽውታ
ፍጡነ ብልጭታ ፥ ድንገቴ ኮሽታ
ላንደኛው በረከት ፥ ለሌላው በሽታ
✍️ሕዌ..ቴ

3 months, 4 weeks ago

አንተ የኔ አለቃ ገብረሃና ነህ የጥርሶቼን ሸለፈት የምታስወግድ አለችኝ...እኔም አንቺ የችግሮቼ ሁሉ ማዘንጊያ ልዕልቴ ነሽ አልኳት.....✍️**

ሕዋ 

3 months, 4 weeks ago

ህልሜን ስጠነስስ-መጥመቂያ ገንቦዬን ሳላጥን
ለትልሜ ማስቀመጫ - ሳላበጃጅ
ሰንዱቅ-ሳጥን
ምኞቴን ሳንተከትክ - በቅጥ ሳልከድን በራዴን
እንጀራዬን ስጋግር - ሳላሟሸው ምጣዴን
አይን አዋጅ ሆኖብኝ አለም - በሁሉ አስገባሁ እጄን
ያልተቋጨ ነገር አብዝቼ -በጅምር አበዛሁ ደጄን!

ህዋ......✍️

4 months ago

በጉዞዬ ፦
አቅጣጫ እንኳን አልጠይቅም
ለምን ቢሉ መሄጃዬን ከቶ
አላውቅም
የሚጠፋኝ መዳረሻ ስለሌለኝ አልጨናነቅም?

4 months ago

''አይነጋ መስሏት''
ነውሯን ''በቋት'' ተጠዳዳችው
በፅልመት ተገን
ረስታ ነገን
ጭንቋን አራግፋ ገላገለችው
ጎህ ቲቀድማ ተዋረደችው
ወቸው ጉድ ?

✍️

4 months ago

አዲስ ዘ አሮጌ

አዲሱ ጫማዬ ገና ከወዲሁ ርዕደ ጫማ ተከስቶበታል
መርዶ ምሰማበት ያ ተለቭዥኔም መብራት ጠፍቶበታል
አስቤዛ ለቤቴ የሚያስገባው እጄም እጅግ እጅ አጥሮታል
ዋጋ ንሮበታል
በጅማሬ ቀኔ ብዙ ብዘረዝር ምንስ ግብ ይመታል
ብቻ ያምናው አመት እጁን ባውዳመቴ አስገብቶበታል?


መ1

4 months ago

....ደግሞ አንቺ ኢትዮጵያ የበጋው ወር መስከረም ክረምቱን ሸኝቶ በፀሐዩ ፀዳል ታጅቦ የአደይ አክሊል ደፍቶ ብሩህ ሆኖ ሲመጣልሽ... አንቺ ግን የጥይቶች እንጉርጉሮ፣
የመፈናቀል ነጠላ ዜማ፣የዘረኝነት አልበምሽን ፣የድህነትን ቀረርቶ የምትለቂበት ተሆነ ግን እውነት እውነት እልሻለሁ ያስገባሽው ወር 2017 ሳይሆን ....የ1977 ማስታወሻ እንደሆነ ከወዲሁ ልገልጥልሽ እፈልጋለሁ።?

መ1

4 months ago

መስከረም ?

ወርሃ መስከረም አበባው

      ን
           ድ
                 ቆ

አዳፋውን ጥሎ አዲስ ካባ

      ጥ
             ል
                   ቆ

የተስፈኛውን ጧፍ
የህልመኛን ፋኖስ
በፅናት ለኩሶ*

የምድሪቱን ንጣፍ
በአደይ አልብሶ*

ሞቆ

ደምቆ

አሸብርቆ

ስቆ
ደመና ቀንሶ ፀሀይ እያበዛ
ኪነ ፍጥረታቱን አድምቆ እያወዛ
ወርሀ መስከረም
በኩር ለወራቱ
ሽክ ብሎ መጣ
በሐበሻ ኩራቱ
መስከረም ሲመጣ ለበኩርነቱ
ለክቡርነቱ ፍሪዳው ተጣለ
ዶሮውም ተባርኮ በሐዋሪያት ቁጥር ተገነጣጠለ
ሀገር ሙክት ጠቦት ቁርጡን ሲቆርጥ ዋለ
ቋንጣ ዘለዘለ....
ለምለም ሳር ቄጠማ ተጎዘጎዘ ተነሰነሰ
ቡናው ተፈልቶ
ፈንዲሻው ፈክቶ
ሉባንጃው ጬሰ
አረቄ ጠጁ ጠላ መውደዱ
ህጣን አዋቂ ሴትና ወንዱ
ተሰባሰበ ዘመድ አዝማዱ
የሩቅ ባዕዱ...
እንደ ልማዱ እንደመንገዱ
ተዘጋጀለት ሁሉ እንደሆዱ
ዘፈን በአይነት ቅኔም ጎረፈ
በአል በሙላት ተትረፈረፈ
አደይ መስከረም ኢዮሀ አበባ
እየተባለ መስከረም ገባ
መስከረም ጠባ.....

( ) ቴዎድሮስ

እሰይ !
አሹ !
እንኳን !
በሰላም አደረሳችሁ

4 months ago
*"እውነቱን ለመናገር ቀን በበቀን ዓመትባ'ል ነው

"እውነቱን ለመናገር ቀን በበቀን ዓመትባ'ል ነው
ፀሐይ በምስራቅ ወጣ በምዕራብ እስከምትገባ... ."

፦ Pamfalone ቀዳማዊ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana