ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
ለ54 ዓመታት ድጓ ያስተማሩት መልአከ ብርሃን ነጋ ተገኘ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ !
ነሐሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
ለ54 ዓመታት ድጓ ያስተማሩት መልአከ ብርሃን ነጋ ተገኘ በተወለዱ በ84 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል ፤ ሥርዓተ ቀብራቸውም በአንዳቤት ወረዳ ውንጅ መካነ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ተፈጽሟል።
የመልአከ ብርሃን የኔታ ነጋ ተገኘ አጭር የሕይወት ታሪክ እንደሚከተለው ቀርቧል
መልአከ ብርሃን የኔታ ነጋ ተገኘ ከአባታችው ተገኘ በላይ ከእናታችው ወ/ሮ ስለአለሽ ዘለቀ በ1933 ዓ.ም በህየ ምድር አንዳቤት ውጅ መካነ ብርሃን ቅድስት ማርያም ድብር ተወለዱ።
ዕድሚያችው ለትምህርት ሲደርስ በደብሩ ከነበሩት ከመዘምር አበበ እሽቴ ፊደልና ንባብን ጀምረው በመቀጠል ሙቀጭ ሐና በመሔድ መዝሙረ ዳዊትና ዜማን በመቀጠል ጎንጅ ጽላሎ ከሊቁ የኔታ ጥላሁን ቅኔን ከነ ሙሉ አገባቡ ተምረዋል። በመቀጥልም ጎንደር ደንቢያ በመሄድ ከታላቁ ሊቅና ባሕታዊ የኔታ አክሊሉ ቅኔን እስከ አገባቡ ተምረው አስመስክረዋል።
ለትምህርት ደከመኝ ሰለችኝ የማያውቁት ሊቁ መልአከ ብርሃን ነጋ ተገኘ ጸዋትወ ዜማን ቨ ጾመ ድጓንና አቋቋም ላይ ቤትና ታች ቤትን ጠንቅቀው ተምረዋል ።
ከየኔታ መንክር ምቅዋመ ማርያም አርበያ መድኃኔዓለም።
(ሰሜን ጎንደር) ከየኔታ አምደ ጽዮን ዝማሬ መዋሥዕት ተምረዋል። ድጓን በደቡብ ጎንደር ደራ ሐሙሲት ቆራጣ ወለተ ጴጥሮስ ከየኔታ መንግሥቱ ተምረው ከአጠናቀቁ በኋላ ጾመ ድጓንና ድጓውን ብራና ዳምጠው ቀለም በጥብጠው ብዕር ቀርጸው ጽፈው ደጉሰው የዓለም ብቸኛ የድጓ ማስመስከሪያ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሆነችው ቅድስት ቤተልሄም በመሄድ ድጓን በ1962 ዓ.ም አስመስክረዋል።
ሊቁ መልአከ ብርሃን ነጋ ተገኘ የተማሩትን ለማስተማር ሳይውሉ ሳያድሩ ወደ ታላቁ ደብር አቸፈር አንባ ጊዮርጊስ በድጓ መምህርነት ለ 3 ዓመታት አስተምረው 28 የድጓ መምህራንን አውጥተው ለደብሩም ተክተው ወደ ሌላ ቦታ ተዘዋውረው ወደ በህየ ምድር አንዳቤት ውጅ መካነ ብርሃን ቅ ማርያም ከ1965 ዓ.ም እስከ 1971 ዓ.ም ድረስ 32 የድጓ መምህራንን አስተምረዋል። በመቀጠል በመካነ ሥላሴና በአፄ ናዖድ ደብር ደብረ ሰላም ወፍጫሜ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ 1971 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ለ 35 ዓመታት በማስተማር 210 የድጓ መምህራንን ወደ ምስክር ጉባኤ ቤት ልከዋል።
ከ2006 ዓ.ም እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ በአንዳቤት ወረዳ ጃራገዶ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ለ10 ዓመት በአጠቃላይ ለ54 ዓመታት ወንበር ዘርግተው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን በርካታ ሊቃውንትን አስተምረዋል።
ወላዴ ሊቃውንት መልአከ ብርሃን የኔታ ነጋ ተገኘ በሕይወት ዘመናቸው በጸሎት የበረቱ አስታራቂ እና ተወዳጅ ካህን ነበሩ።
መልአከ ብርሃን የኔታ ነጋ ተገኘ ባደረባቸው ሕመም ከዚህ ዓለም ድካም በተወለዱ በ84 ዓመታችው አርፈዋል።
የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም ባስተማሩበት በአንዳቤት ወረዳ ውንጅ መካነ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም ተማሪዎቻቸው ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በተገኙበት ተፈጽሟል።
ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል በመልአከ ብርሃን የኔታ ነጋ ተገኘ ዕረፍት የተሰማውን ኃዘን እየገለጸ ለውሉደ ያሬድ ሊቃውንተ ፣ ለተማሪዎቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን ይመኛል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago