Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)

Description
እንኳን ደህና መጡ‼

✔ማስታወቂያ ለማሰራት እና ጥቆማ ለመስጠት በዚህ ይጠቀሙ ☞https://t.me/WasuMohammed

✔ ቻናሉን ለመቀላቀል Join ☞http://t.me/Wasulife

ከልብ አመሰግናለሁ♥🙏
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 15 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 6 days, 1 hour ago

Last updated 2 months ago

5 days, 13 hours ago

ለጥንቃቄ ተጠቀሙበት

" ትላንት ማታ ሚያዚያ 13 ከምሽቱ 2:30 አካባቢ እኔና ባለቤቴ ዘመድ ጥየቃ ቆይተን ጉዞአችንን ከቄራ ወደ ወሎ ሰፈር አድርገን ስንሄድ ድንገት ጎተራ ማሳለጫ መንገድ ላይ አስደንጋጭ ክስተት ተመለከትን።

ጎተራ ማሳለጫ በላይኛው መስመር አንድ ሰው ከሶስት ሰዎች ጋ ሲታገል ተመለከትን። ቦታው እና ሁኔታው እጅግ አደገኛ ነው።

እግረኛ የማይጓዝበት እና መኪኖች በፍጥነት የሚያልፉበት መንገድ ከመሆኑ የተነሳ ለኛ በዚህ ሁኔታ መቆም እጅግ ፈተኝ ነበር።

ነገር ግን ቢያንስ የተጎጂው ሰው ሕይወት ለማትረፍ በቦታው ቀድመን የደረስን እኛ ብቻ መስሎ ስለታየን እና መኪና አስቁሞ በዚህ ልክ ይዘርፋሉ ብለን ስላልገመትን 7 ሜትር በሚሆን ርቀት ላይ ቆምን።

ይህን ሰው አንዱ መሬት ላይ አስተኝቶ አንቆታል ፤ ሌላኛው በተደጋጋሚ ይደበድበዋ አንደኛው በእጁ በያዘው ስለት ያለው መሳርያ ደጋግሞ ሲወጋው ተመለከትን።

ሰውዬው በዚህ መሀል ከፍ ባለ ድምፅ የሰቀቀን ጩኸት ያሰማ ነበር።

ከመኪናችን መውረድ ስለማንችል ያለን አማራጭ ሀዛርድ አብርተን ያለማቋረጥ ክላክስ ማድረግ ብቻ ነበር። ከኋላ ሌሎች መኪኖች ደረሱብን እነሱም ሁኔታው በግልፅ ስለሚታይ ከመኪናቸው ሳይወርዱ ያለማቋረጥ ክላክ ማድረግ ጀመሩ።

ያኔ ነው ከሌቤቹ/ነብሰ በላዎቹ አንዱ ወደ እኛ መቶ ጮኸብን በእግሩ መኪናውን ደበደበ ፊቱ በደንብ ይታያል። ሌሎች 2ቱ ሰውዬውን ይታገሉታል።

ሪስክ ወስጄ መኪናዬን በጣም ሳቀርብባቸው ሰውዬውን ለቀውት ሶስቱም መንገድ ዳር ያስቀመጡትን ድንጋይ አንስተው ሲያስፈራሩኝ መኪናዬ እንዳይጎዳብኝ ፈጣሪን እየተማፀንኩ በፍጥነት አለፍኩ። ነገር ግን በቀላሉ መስታወቱ ላይ ጉዳት ማድረስ ይችሉ ነበር።

ሰውዬውም ከወደቀበት ተነስቶ በተቃራኒ መስመር እየተንገዳገደ ለመሸሽ ሲሞክር በስፖኪዬ ተመለከትኩት።

ክስተቱን መረጃ ለመስጠት ለፌዴራል ፖሊስ ስንደውል አዲስ አበባ ፖሊስ ጋር መረጃ ስጡ ባሉን መሰረት በ +251111110111 ደውለን አሳወቅን። ቤት ደርሰን ሁኔታው በጣም ስለረበሸን በድጋሚ ስንደውል ፖሊሶች ተልከው " በአከባቢው ምንም የተፈጠረ ነገር የለም " ተባልን።

ይህን ከሰማን በኋላ ሁለት ሀሳብ መጣብን ፤
° ምናልባት ተበዳዩ ሰውዬ የነሱ ተባባሪ እና ግርግር ፈጥረው ከመኪና የወረደ አሽከርካሪ ላይ ጉዳት ለማድረስ እና መኪና እና ሌሎች ንብረቶችን ለመስረቅ ታቅዶ የተሰራ ይሆን ?
° ምናልባት ያለምህረት ሲደበድቡት ሱወጉት እውነትም ተበዳይ ይሆን ?

የሚመለከተው የፀጥታ አካል ትኩረት ሰጥቶ ቢሰራበት እንለለን። የደህንነት ካሜራዎችም የህብረተሰቡን ስጋት መከታተል አለባቸው።

ጎተራ አከባቢ እና ሌሎች ተጋላጭ ቦታዎች ላይ በምሽት የምታሽከረክሩት ጥንቃቄ አይለያችሁ!
(አንተነህ ክ.)ከቲክቫህ ገፅየተወሰደ)
==========================
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇      
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

5 days, 13 hours ago
Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)
5 days, 15 hours ago

በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገኘው ሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አምባራስ ቀበሌ ግፍ በተሰኘዉ አካባቢ ከ4 ቀናት በፊት ያጋጠመው የእሳት አደጋ ተባብሶ በርካታ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ ተሰምቷል።ህዝቡ በባህላዊ መንገድ እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ እያደረገ ቢሆንም ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ ከስፍራው የወጡ ረጃዎች ይጠቁማሉ።በጊዜ መፍትሄው ላይ ቢሰራ መልካም ነው።

2 months ago
**"…ሊሳካ አልቻለም "**

"…ሊሳካ አልቻለም "

ከ12 ቀናት በፊት በደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ፤ የኦፓል ማዕድን ለማውጣት ቁፋሮ ላይ እያሉ ዋሻ የተናደባቸው ሰዎች የሚወጡበት መፍትሔ አሁንም ድረስ አለመገኘቱን የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር እና የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር ተናግሯል።
ትላንት የመከላከያ ሠራዊት በአካባቢው በመገኘት የዋሻውን የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ፈንጂ ቢጠቀምም፤ ሙከራው እንዳልተሳካ የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳደር ገልጿል።
የመከላከያ ሠራዊት መሀንዲሶች በአካባቢው ላይ የተሰማሩ ሲሆን ፤ ዋሻው የሚገኝበትን ቦታ ተመልክተው " ፈንጂ እና ድማሚት " በመጠቀም የዋሻው የላይኛው ክፍል ለማፍረስ ሙከራ ቢያደርጉም አልተሳካም ተብሏል።
የተንጠለጠውን ገደል ለመናድ አልተቻለም።ይህ ሙከራ ከከሸፈ በኋላ እንዲወገድ የሚፈለገውን የዋሻ ክፍል " በታንክ የመምታት " ሀሳብ ከመሀንዲሶቹ በኩል መቅረቡን ቀርቧል።
ያቺ ቦታ ብትመታ እና ብትናድ ሰዎቹን ቆፍሮ የማውጣት እድል እንደሚኖር ማህበሩ ገልጿል።ይሁንና " በታንክ መምታት " የሚለው ሀሳብን በተመለከተ እስካሁን ድረስ ውሳኔ ላይ እንዳልተደረሰ ተነግሯል።
የመከላከያ ሠራዊት አባላት መውጫ ያጡትን የማዕድን ቆፋሪዎች ለማውጣት አሁንም በአካባቢው እንደሚገኙ ተገልጿል።በዋሻው ውስጥ መውጫ ካጡ 12 ቀናት ያስቆጠሩት የማዕድን አውጪዎች ያለ ምግብ " እስካሁን መቆየት ይችላሉ ? " ለሚለው ጥያቄ የከበሩ ማዕድናት አምራቾች ማኅበር አሁንም ተስፋ እንዳለ አመልክቷል።
"ይኖራሉ። እስከ 15 ቀን ድረስ የመቆየት እድል አላቸው። ዋሻው ውስጥ ውሃ ስላለ፤ አፈር በሉ ምንም አሉ ዞሮ ዞሮ የመቆየት እድላቸው አለ " በማለት ግለሰቦቹ በህይወት ይገኛሉ የሚል ተስፋ እንዳለው ማህበሩ ገልጿል።(BBC)Subscribe👇****           
https://bit.ly/3PYWA12

2 months ago
ይሄ ***👆***በውስጥ የደረሰኝ ጉዳይ እውነት ነው።ዛሬ …

ይሄ 👆በውስጥ የደረሰኝ ጉዳይ እውነት ነው።ዛሬ ከአዲስ አበባ በአፋር ኮምቦልቻ ደሴን አልፎ ወደ ወልዲያ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ይጓዙ የነበሩ መንገደኞች ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ተሰምቷል።ሰንበቴና አጣዬ የብሔር ጉዳይ እንደ ምክንያት ተነስቷል።ውርጌሳስ ምክንያቱ ምንድነው?? ትንንሽ የዝርፊያ ቡድኖች በየሰፈሩ ተፈልፍለዋል።ውጤቱም እየታዬ ነው።ህዝቡ መፍትሄ እየጠየቀ ነው።

ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇*    
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
*ተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎችእንዲደርስዎ Join አድርገው
👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

2 months ago

ዛሬ ከአዲስ አበባ ደሴ የየብስ ትራንስፖርት መቋረጡ ታውቋል።በዋናው መንገድ ላይ የሚታይ ተሽከርካሪ የለም ሲሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።ምክንያቱ👇እዚህ አለ።
https://t.me/wasulife/27119

2 months, 1 week ago

የአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ እንደገለፀው

በዞኑ ውስጥ 1 ሺህ 80 የአንደኛ እና መካከለኛ፣
65 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሲኖሩ አሁን ላይ 353 የአንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቻ ስራ ላይ ናቸው። ከ65 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የሚሰሩት 23ቱ ብቻ ናቸው። በተፈጠረው የጸጥታ ችግር 137 ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇*    
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
*ተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎችእንዲደርስዎ Join አድርገው
👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ
https://t.me/wasumohammed

2 months, 1 week ago
Update

Update

ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደው የአንድ ወር የምግብ ድጋፍ ተደረገላቸው

ከተለያዩ ቦታዎች  ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ጃራ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ 10ሺ ተፈናቃዮች ያለምንም የምግብ እርዳታ ለሁለት ወራትቢቆዩም በዛሬው ዕለት ለአንድ ወር የሚሆን የምግብ እርዳታ ተደርጎላቸዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለሙ ይመር እንደተናገሩት 820 ኩንታል እህል  ድጋፉ የተደረገው ከፌደራል አደጋ ስጋት ነው።ከነገ ጀምሮም ለተፈናቃዮች መከፋፈል ይጀምራል ብለዋል።

ተፈናቃዮች ፈጣን የሆነ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸው ስለነበር ለክልሉ ማሳወቃቸውን እና ክልሉም ለፌደራል ድጋፍ በመጠየቁ የፌደራል አደጋ  ስጋት ለተፈናቃዮች 820 ኩንታል እህል ድጋፍ እንዳደረገ እና ድጋፉም ለአንድ ወር የሚሆን እንደሆነ ተናግረዋል።

ሀላፊው ከኑሮ ውድነት ጋር ለተፈናቃዮች እርዳታ ማድረስ ፈታኝ ሆኖባቸው እንደ ነበር እና አሁን  ላይ በዋነኝነት ተፈናቃዮችን ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ ከመንግስት ጋር በመሆን እየሰሩ እንዳለ ገልፀዋል።

እነዚህ ተፈናቃዮች ከ2 ዓመት  እስከ 3ዓመት  በካምፑ የቆዪ ናቸው። ከዚህ ቀደም ድጋፍ ያደርጉ የነበሩ ከ40 በላይ የሚሆኑ ድርጅቶች  በፀጥታው ችግር  ምክንያት አቋርጠው ከአካባቢው መውጣታቸውን ለችግር እንደዳረጋቸውም ገልፀዋል።አሁን ላይ ግን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ለተፈናቃዮቹ እንደሚደረግም አቶ አለሙ ይመር ነግረውኛል ሲል ብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ዘግቧል።
ቤተሰብ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇*    
https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g
*ተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎችእንዲደርስዎ Join አድርገው
👇በዚህ ይከታተሉ
https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4

2 months, 1 week ago
Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)
2 months, 2 weeks ago
Wasu Mohammed(ዋሱ መሀመድ)
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 days, 15 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 6 days, 1 hour ago

Last updated 2 months ago