ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month, 3 weeks ago
Last updated 2 days, 20 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 1 week ago
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 5፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሕንጻ ዲዛይን አማካሪ ተወዳዳሪ ድርጅቶች የፋይናንስ ሰነድ ተከፈተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሚያስገነባው ባለ 2 ምድር ቤት እና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ ተጫራች የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ያቀረቡት የፋይናንስ ሰነድ በዛሬው ዕለት በተጫራቾችና በታዛቢዎች ፊት ተነበበ።
በዛሬው ዕለት የፋይናንስ ሰነዳቸው በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተከፍቶ የተነበበው የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ጥቅምት 21፣ 2017 ዓ.ል. በዚሁ አዳራሽ በይፋ በተከፈቱ የቴክኒክ ሰነድ : ሰነዶቻቸው መስፈርቶቹን ማሟላታቸው በቴክኒክ ኮሚቴ የተረጋገጠላቸው ድርጅቶች መኾናቸው ተነግሯል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ፅ/ቤት አማካሪዎች ጠቋሚነት በፕሮጀክት አፈጻጸማቸው መልካም ስም ካላቸው የመንግሥት እና የግል ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ሰነድ ውድድር ምዕራፍ ካለፉት ተወዳዳሪዎች መካከል አንደኛውየመወዳደሪያ ሰነድ ማቅረቢያ መስፈርቱን ባለሟሟላቱ ከጨረታው መሰረዙ ተነግሯል።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባው ባለ 2 ምድር ቤት (B2)፣ 13 ወለል (G+13) የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች ጨረታ በተመረጡ ድርጅቶች መካከል ብቻ የተከናወነ እንደኾነ መነገሩ ይታወሳል።
የጨረታውን ሂደት አስመልክቶ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልዓዚዝ አሎ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የፋይናንስ ግልፀኝነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የአሠራር ሂደቶችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደኾነ ተናግረዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ሕግን መሠረት አድርጎ እየሠራ ለመሆኑ ይህኛውን ጨምሮ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች እየወጡ ያሉ ጨረታዎች እየተካሄዱ ያሉበት ሂደት አመላካች እንደኾነ አቶ አብዱልዓዚዝ ተናግረዋል።
ዛሬ በተጫራቾችና በታዛቢዎች ፊት በይፋ ተከፍቶ የተነበበው የዲዛይን አማካሪ ድርጅቶች የፋይናንስ ሰነድ ተጣርቶ ከቀናት በኋላ አሸናፊው ድርጅት ለሕዝብ ይፋ እንደሚሆን ምክትል ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።
========
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 28፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 6፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የዓረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊ የኾኑትን ሰዒዳ (Saida) ሙሐመድ ዑመር በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ፕሬዚደንቱ የዓረብ ሊግ ተወካይን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው ሲያነጋግሩ የአሁኑ የመጀመሪያቸው መኾኑ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል።
በአፍሪካ ሕብረት እና በተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የዓረብ ሊግ ተወካይ የሆኑት ሰዒዳ ሙሐመድ ዑመር የዓረብ ሊግ ጽሕፈት ቤት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በትምህርት፣ በማኀበራዊ ጉዳይ እና በልማት አብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል።
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት ጽሕፈት ቤት በተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የዓረብ ሊግ አባል በምትኾንበት መንገድ ጉዳይ ዙርያ ሐሳብ ተነስቷል።
የዐረብ ሊግ ተጠባባቂ ኃላፊዋ ጥያቄው ተገቢውን መስፈርት አሟልቶ በኢትዮጵያ መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ከቀረበ ሁኔታዎችን በቅርበት ለመከታተል ያስችላል ብለዋል።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የክብር ዶክተር ሐጂ ኢብራሂም የውይይቱን በጎነት ገልፀው፣ የተፈጠረውን ዕድል ተጠቅመን መስሊሙን እና ሀገርን በሚጠቅም መልኩ ከዐረብ ሊግ ጋር ተቀራርቦ ለመሥራት የሚታየው ፍላጎት አበረታች እንደኾነ ተናግረዋል።
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 27፣ 2017 ዓ.ል | ጁማዱል ኡላ 4፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ የሥራ ግምገማ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ (ተቅዪም) ጋምቤላ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የምክር ቤቱ ጽሕፈት ቤት አካሄደ።
ትላንት የተጀመረው የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ በተከናወኑ ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉን የግምገማ መድረኩን የመሩት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ተጠሪ ሸይኽ ሑሴን ሐሰን ተናግረዋል።
ዛሬ የተጠናቀቀው የጋምቤላ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ዓመታዊ ግምገማ በ2016 ዓ.ል በምክር ቤቱ የተመዘገቡ ውጤቶችን በማስቀጠል፣ በታዩ ውሱንነቶች ላይ የማስተካከያ እርምጃ እንደሚወሰድ ሸይኽ ሑሴን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ነሐሴ 18፣ 2016 ዓ.ል በአዲስ አበባ ባደረገው የ2ኛ ዓመት፣ 4ኛ መደበኛ ጉባዔ፣ የክልልና የከተማ አሥተዳደር የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች የ2016 ዓ.ል የሥራ አፈጻጸማቸውን እንዲገመግሙ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል።
የጋምቤላ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የሥራ አፈጻጸም ገምጋሚ ቡድን በዛሬ ውሎው በከፍተኛ ምክር ቤቱ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውሮ መጎብኘቱን ከሸይኽ ሑሴን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 22፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 29፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በአዲስ አበባ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ሊካሄድ ነዉ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የሰላም ሚኒስቴር ከሙሐመድ ቢን ዛይድ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በአዲስ አበባ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ጉባዔ ሊያካሂድ መሆኑን ተናገረ።
ጥቅምት 25 እና 26፣ 2017 ዓ.ል (ሰኞና ማክሰኞ) በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሪዞርት የሚካሄደውን ይህን ዓለምአቀፍ ጉባዔ አስመልክቶ ሚኒስቴሩ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
በሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ደዔታ ዶክተር ኸይረዲን ተዘራ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ ቀደምት የሰዎች መገኛ ብቻ ሳትሆን፣ እስልምናና ክርስትና ለዘመናት በሰላምና በሃገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉባት ታሪካዊ ሀገር መሆኗን አውስተዋል።
በዓይነቱ የመጀመሪያ የኾነው ይህ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ሃይማኖቶች ለሀገራችን ሰላምና አብሮነት ያደረጉትን ጉልህ አስተዋፅዖ ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዝ መሆኑን ሚኒስትር ደዔታው ተናግረዋል።
ለዚህም ዓላማ መሳካት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር ተቀራርቦ እየሠራ እንደሚቀጥል ሚኒስትር ደዔታው ተናግረዋል።
ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዓለምአቀፍ ጉባዔ ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል ቤተ እምነት አባቶች፣ አውሮጳና ኤዥያን ጨምሮ ከአሥራ ሦስት ሀገራት የሚመጡ የሃይማኖት ሊቃውንት፣ አሥራ አምስት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ሦስት መቶ ሰዎች በጉባዔው ላይ እንደሚሳተፉ ተነግሯል።
በጉባዔው ላይ በምሑራን የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች እንደሚቀርቡ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
ጥቅምት 21፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 28፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ሊገነባ ለታቀደ ው ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ ጨረታ በይፋ ተከፈተ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሊያስገነባ ላቀደው ባለ 2 መሠረትና ባለ 13 ወለል የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የኮንትራት አማካሪ ጨረታ በይፋ ከፈተ።
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱልሃዲ ሙሐመድ በጠቅላይ ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባው B+2፣ G+13 የአፓርትመንት ሕንጻ የዲዛይን እና የአማካሪ ጨረታ በተመረጡ ድርጅቶች መካከል ብቻ የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ስምንት (8) ድርጅቶች የተመረጡ ሲኾን፣ ከመንግሥት ድርጅቶች ሦስት (3)፣ ከግል አምስት (5) መሆናቸውን ኃላፊው ተናግረዋል።
በጨረታ መክፈቻ ስነ ሥርዓቱ ላይ ከስምንቱ (8) ድርጅቶች አራቱ (4) የተገኙ ሲኾን፣ ጨረታው ታዛቢዎች በተገኙበት ተከፍቷል።
ድርጅቶቹ በፕሮጀክት አማካሪዎች የተጠቆሙና በፕሮጀክት አፈጻጸም ጥሩ ስም ያላቸው መሆናቸውንም ኃላፊው ተናግረዋል።
ጥቅምት 20፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በሐጅ ወቅት በጀዳ አውሮፕላን ማረፊያ #ሻንጣ_ለጠፋባችሁ የ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) ሐጃጆች።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በ1445 ዓ.ሒ (2016 ዓ.ል) የዘመነ መስተንግዶ ለአል ረሕማን እንግዶች በሚል መሪ ሐሳብ ሐጃጆችን ማስተናገዱ ይታወሳል።
የሐጅ ሥርዓታችሁን አጠናቅቃችሁ ሻንጣችሁን ከመካ ወደ ሀገር ቤት ለመላክ ከመካ የሽኝት አስተባባሪ የሻንጣ ታግ ወስዳችሁ፣ ነገር ግን ሻንጣችሁ በጀዳ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የጠፋባችሁ ሐጃጆች፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጀዳ አውሮፕላን ማረፊያ የተገኙ የኢትዮጵያውያን ሐጃጆች ሻንጣዎችን ወደ አገር ቤት አምጥቶ ለጠቅላይ ምክር ቤታችን ያስረከበ በመሆኑ፣ ሻንጣ የጠፋባችሁ ሐጃጆች የፓስፖርታችሁን ቅጂ (ኮፒ) እና የሻንጣችሁን ታግ ቅጂ ከዚህ በታች በተቀመጠው ስልክ ቁጥር 0911 82 19 15 (በቴሌግራም) እንድትልኩ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሐጅና ዑምራ ጉዞ ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት።
ጥቅምት 20፣ 2017 ዓ.ል | ረቢዑል ሳኒ 26፣ 1446 ዓ.ሒ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month, 3 weeks ago
Last updated 2 days, 20 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 1 week ago