🖊ብዕራችን🎤

Description
🎤ይህ ቻናል የተለያዩ ግጥሞች፣ድርሰቶች እንዲሁም የተለያዩ ፅሁፎችን ወደእናንተ ያደርሳል።ስለቻናሉ ለሚኖራችሁ ማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ፅሁፍ ከፈለጋችሁ
🖊 @Hamenrama19
@Tsi_2127
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

9 months ago
9 months, 4 weeks ago

"ቢጫ ሞት"
ኤልያስ ሽታኹን
~        ~       ~       ~      ~
ቢጫ አበባ ቆርጠን አደይ ቀነጠስን
ለወረት ገላችን ተስፋ ነሠነሥን....

እንዲያው ይመስል በዓል
የውሸት ከነዓን
ሀሰት ወለደ ነዌ
የውሸት ነነዌ
ለሀሰት ወጋችን ለውሸት ማዕረግ
ስንት አደይ ስንት በግ?

እኛ
የማይጠብቀንን ወቅት እየጠበቅን
ተስፋን ሰበብ አርግን ስንቱን አረገፍን?
ጥያቄ?
ከስሩ ገንደሰን
ከግንዱ ቀንጠሰን ለኛ ተስፋ ያልነው
ለአደዩ ምንድነው?

ሞት::

10 months, 2 weeks ago

*እሷ....ግድ የላትም

ነግሬሽ አልነበር.....
ያየሻቸው ሁሉ እውነት እንዳልነበር
የሰማሻቸውም የሀሰት ክስና ምስክር
በዕንባ ተሞልተው የተስረቀረቁ
በቁጣ ታጅበው የተወረወሩ...( ቃላት)
በደስታ ያዜሙ.... አንደበቶች
እውነት እንዳይመስሉሽ እነዚያ ጊዜያቶች።

ከመሰሉሽ እንኳን.....
ይህንን አትርሽ
             እኝህን አስታውሽ
አበቦች እረግፈው
ዛፎች ሌላ አቅጥለው
ለምለም ሳሮች ደርቀው
........ እንደምታያቸው።

ደግሞ
ግዜ መጥቶላቸው
ዳግም ተጸንሰው
ያጌጣሉ አብበው።

ጣፋጭ ፤ ለመራራም....(እንዳለው)
የዋሸ አንደበት እውነት ይናገራል
እውነትም ያወራ በሀሰት ይያዛል
ብቻ ምን አለፋሽ....
ፃድቅ ነኝም ያለ ጽድቁ ሳይገለጥ
ርኩሰቱ ቀድሞ በሀፍረቱ ሲዋጥ
ሃጥዕ ነኝም ያለ ሀጥያቱ በዝቶበት
ምህረትን ሊለምን ወደ አምላኩ ሲሮጥ

ሕይወት መስታወት ናት ታያለሽ ሁሉንም
          እሷ....ግድ የላትም ።

ተፃፈ በብርሀነአብ@L_Rabbi@arthophia ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት@Hamenrama19@Tsi_2127 ይቀላቀሉን።*@THartandliterature

10 months, 3 weeks ago

በተሰጠህ መክሊት - በተሰጠህ መፍቻ
ደጋግመህ ካልከፈትክ - ለድልህ መባቻ
የዘንዶው ጭንቅላት - ካልተቀጠቀጠ
ሲወፍር ይኖራል - አንተን እየዋጠ

ዣንቶዣራ
(ይስማዕከ ወርቁ)
ለሚመለከተው በሙሉ . . .

10 months, 4 weeks ago

እሳት ወይ አበባ*
..........
ይቅር ብቻ አንናገርም፥
እኔና አንቺ አንወያይም፥
ለውይይት አልታደልንም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም.....ዝም፡፡
አበባ አንሆን ወይም እሳት
ተጠምደን በምኞት ቅጣት
ሰመመን ባጫረው መአት
እድሜአችንን እንዳማጥናት....
እሳት አንሆን ወይ አበባ
በሕቅ -እንቅ ስንባባ
ባከነች ልጅነታችን ፥ እየቃተትን ስናነባ፡፡......
ፈራን፤ አዎን ፍቅር ፈራን፥
የነፍስን አንደበት ዘጋን፥
የእድሜ ጠብታችንን ምጥ፥ የጣር ፅንሳችንን ልሣን፥
ልጅነት የለገሠንን
በመለኮት የቀባንን
በእሳቱ ያጠመቀንን
የፍቅር አምላክ በጥበቡ፥ በሥልጣን ያላበሰንን
ፈራን፥ አዎን እውነት ፈራን
የስሜት እስትንፋስ ነሳን፡፡ ....
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን**

ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት@Hamenrama19@Tsi_2127 ይቀላቀሉን።*@THartandliterature

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana