ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የምወዳቸውን ሰዎች ሌሎች ሰዎች እንዲወዷቸው ማድረግ ይሆንልኛል።
ልደቱ አያሌውን በኔ የተነሳ የወደዱት ጓደኞች አሉኝ። የተስፋዬ ጫላን መዝሙሮች አስወድጃቸው ከተስፋዬ መዝሙሮች በፍቅር የወደቁ ጓደኞች አሉኝ።
አርሰን ቬንገርን እና ሊዮ ሜሲን በእኔ የተነሳ የወደደች ልጅ አለች። ፊልፕ ያንሲን በኔ የተነሳ የወደደ ጓደኛ አለኝ።
የምወዳቸውን ሰዎች ሌሎች ሰዎች እንዲወዱ ማድረግ ይቀናኛል።
የጌታሁን ሄራሞን የፌስቡክ ፅሁፎች በእኔ የተነሳ አድኖ ማንበብ የጀመሩ አሉ። ሀውለትን ስለምወዳት የወደዳት ሰው አለ።
(
በዘመነ ሚኒሊክ ረሃብ አለንጋውን አነሳ። የሚበሉት የቸገራቸው በየአቅጣጫው ይወድቁ ጀመር። ዜጎች በረሃብ ሞቱ።
በዛን ወቅት አንዲት እናት ያልተለመደ ነገር አደረገች ተባለ። ከሰውነት ወደ አውሬነት ተለወጠች። ህፃን ልጅን ለመብልነት አዋለች። አዎን ህፃን ልጅ በላች። (ባልሳሳት የጳውሎስ ኞኞ መፅሐፍ ላይ ይመስለኛል ይህን ያነበብኩት)
ያኔ አስችሏቸው ሰውን ያህል ነገር መመገብ ባይሆንላቸውም፥ በደህናው ጊዜ ለመብልነት የማይውሉ ባዕድ ነገሮችን የተመገቡ ሰዎች ነበሩ። የሞቱ እንስሳትን ፥ የአእፋትን ኩስ ወዘተ በመመገብ ረሃብን ለማምለጥ የሞከሩ ነበሩ።
እንደ ሐገር የተራብነው ትላንት ብቻ አይደለም። ረሃብ እየደጋገመ ጎብኝቶናል ፥ ጠኔ ደጋግሞ ረግጥናል። የሚበላ ማጣት አዋርዶናል።
በዘመናዊ አለም ረሃብ የመንግስት ጥፋት ውጤት ነው። ረሃብን የተሳሳተ ፖሊሲ ያዋልዳል።
በንጉሱ ዘመን ረሃብ ነበር። ያኔ የንጉሱ ተቃዋሚዎች "ህዝብ ተርቦ ንጉሱ ለውሻቸው ይደግሱ ነበር" አሉ። ዛሬም ድረስ ጃንሆይን የሚቃወሙ ሰዎች "በ66ቱ ረሃብ ሃይለስላሴ ጥፋት ሰርተዋል። ህዝብ ተርቦ እሳቸው የቅንጦት ጉዳይ ላይ አተኩረዋል" በማለት ያብጠለጥሏቸዋል።
በ ዘመነ ደርግ 19 77 ብሔራዊ ውርደትን የሚያከናንብ ረሃብ ተከሰተ። ዜጎች የሚበሉትን አጥተው በመደዳ ሞቱ።
ያኔ ህዝብ በረሃብ አለንጋ ሲገረፍ ደርግ የአብዮቱን አስረኛ አመት ያከብር ነበር። ከፍተኛ በጀት መድቦ ስልጣን የያዘበትን አስረኛ አመት መታሰቢያ ደግሷል።
ሹሟምንቶቻችን ህዝብን መናቅ መለያቸው ነው። የህዝብ ሞት ግድ አይሰጣቸውም።
ዛሬም ዜጎቻችን በረሃብ እየተቀጠፉ ነው። ጦርነት እና የፖሊሲ ውድቀት የፈጠረው ችግር ዜጎችን ለችግር ዳርጓል። በዚህ ሁሉ መሐል መንግስታችን ትኩረቱ ሌላ ነው።
ዜጎች የሚበሉትን አጥተው ሳለ መንግስት ገንዘቡን ከተማን ለማስዋብ እና ቤተመንግሥት ለማደስ እያዋለው ነው።
በተመሳሳይ እንቅፋት መመታት እጣፈንታችን ሆኗል። አባቶቻችን የወደቁትን አወዳደቅ እንድንደግመው ተፈርዶብናል።
Via ተስፋአብ ተሾመ
መፅሐፍ ማንበብ በጣም ጥሩ ነገር ነው። ይህ አንድ እና ሁለት የለውም።
ቀላል ቁጥር የሌላቸው መፅሐፍ አንባቢያን መመፃደቃቸው አሳሳቢ ነው። የማያነቡ ሰዎችን መናቅ እና ማሳነስ ያምራቸዋል።
እውቀት ትሁት ሊያደርግ ይገባል። (ወይም ትሁት ቢያደርግ መልካም ነው)
ማንበብ ፥ ማሰላሰል ፥ ማወቅ ወዘተ ሊሰጠን ከሚገባ ፀጋዎች መከል አንዱ ቀላል አቀራረብ ነው ብዬ አምናለሁ።
በተረፈ መፅሐፍ በማንበባቸው የሚመፃደቁ ሰዎች ነገር ያበሳጨኛል
ስለ ጋብቻ ምን ታስባላችሁ?
የእኔ ትውልድ ከትዳር የተኳረፈ ይመስላል። ቤተሰብ መመስረት ባለብን እድሜ ፀረ ጋብቻ ልምምድ ላይ ተጠምደናል። በቀልዶቻችን ክቡሩን ትዳር እናዋርዳለን።
ከደቂቃዎች በፊት ከአንዲት ጓደኛዬ ጋር ረዘም ያለ የስልክ ወሬ ነበረን። ወሬያችን ሳናስበው ወደ ትዳር አጀንዳ ገባ።
ስለራሳችን አቋም ፥ በዙሪያችን ስላሉ ሰዎች አስተሳሰብ ፥ ስለ ትውልድ አባሎቻችን እምነት አወራን።
"የኛ ትውልድ ትዳር ጠል እየሆነ ነው" አለችኝ።
ቀላል ቁጥር የሌለው ወጣት ትዳር ጠል እየሆነ ነው። ትዳር የማይጠላው ደግሞ ጋብቻን ይሸሻል። ሰላሳዎቹ ውስጥ ሆኖ ቤተሰብ ለመመስረት እድሜው ገና እንደሆነ የሚያስበው ብዙ ነው።
ይህ አለምክኒያት አልመጣም። ከልጅት ጋር ስለ ጉዳዩ አውርተን እንደ ጨረስን "ምንድነው ያገኘን? ትውልዳችንን ምን ነካው?" ብዬ ሳስብ ነበር።
የተወሰኑ ምክኒያቶችን ገመትኩ
(ለፅሁፉ ሳልጠነቀቅ እንደ ወረደ ግምቴን ላስቀምጥ)
ሀ፥ በርካታ ወጣቶች ስራ አጥ ናቸው። ስራ ያላቸው ደግሞ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ ነው። በዚህ ሁኔታ ቤተሰብ መመስረት ማሰብ ውስብስብ ነው።
ለ፥ አሉታዊ ታሪኮች ተሰራጭተዋል። በትዳራቸው የሚማግጡ ሰዎችን ታሪክ ደጋግመን ሰምተናል። የታመመ ቤተሰብ የመሰረቱቱ ተቆጥረው አያልቁም። አንዳንዱ ወላጆቹ ጭምር ጤና ያጣ ትዳር ነው ያላቸው። ይህ ትዳር የሚሸሽ ትውልድ እንዲበዛ ሰበብ ሆኗል።
ሐ፥ የሰዎች ፍላጎት ጣሪያው ሰማይ ደርሷል። ፊልሞች ምናባዊ የሆነ የፍቅር ህይወትን አስለምደውናል። ማህበራዊ ገፆች ከእውነታ የተፋቱ እና የተጋነኑ ግኑኝነትን ግተውናል። ይህ ሰዎች ከእውነታው የተጣላ ምኞት ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል።
ሴቷ በፊልም ያየችውን አይነት ወንድ ትፈልጋለች። ቲክቶክ ሰፈር የተነገረለትን የምናብ ወንድ ታልማለች። ወንዱ የፊልም ሴት ይመኛል። ማህበራዊ ገፆች የሷላትን ሴት ለማግኘት ይጓጓል።
በእውነተኛው አለም ግን ምናባችን ላይ የሳልናቸውን ፍፁም ሰዎች አናገኝም።
አሳዛኙ ነገር ብዙሃኑ እጅግ የላቀ ግኑኝነትን እየፈለገ ቆሞ ቀርቷል።
በነገራችን ላይ ፍፁም የሆነ አጣማሪ የሚፈልግ ሰው ራሱም ፍፁም መሆን አለበት።
መ፥ የዚህ ዘመን ትውልድ የተቃራኒ ፆታ ህይወቱ ብዙ ንክኪ ያለው ነው። በሃያዎቹ አጋማሽ ያሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የፍቅር ግኑኝነት ጀምረው አቋርጠዋል። ይህ አይነት ልምምድ ግኑኝነትን ዋጋ እንዳንሰጠው ያደርጋል። ትዕግሥት ይነጥቃል። ስሜትን ያኮላሻል።
ሠ፥ ትዳር ጠል ቀልዶች እና ንግግሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ትዳር ነፃነትን የሚነጥቅ ተቋም እንደሆነ ነግረውናል።
ረ፥ የእምነት ተቋማት ተዳክመዋል። በዛው መጠን ወጣቱ ከእምነቱ ሸሽቷል። ሀይማኖቶች ለትዳር የሚሰጡትን ክብር ወጣቱ በአግባቡ መገንዘብ የማይችልበት ሁኔታ ላይ ይገኛል። ይህም ሌላ ችግር ይሆናል
...
ብዙ ግምት ማስቀመጥ ይቻላል። ከልጅቷ ጋር ካወራሁ በኋላ ስለ ጉዳዩ ሳስብ ወደ አእምሮዬ የመጣውን እንደወረደ ፃፍኩት።
ዋናው ቁም ነገር ፥ ጋብቻ ክቡር ነው።
Via ተስፋኣብ ተሾመ
ስለ ጀዋር መሐመድ መፅሐፍ
(ተስፋአብ ተሾመ)
ጥቂት ሰዎች መፅሐፍ እንዲፅፉ እመኛለሁ። ገዱ አንዳርጋቸው ፥ሳሞራው የኑስ ፥ ለማ መገርሳ ፥ በረከት ስምኦን ፥ ጌታቸው ረዳ ፥ ሀይለማርያም ደሳለኝ ፥ ጀዋር መሐመድ፥ ጃል መሮ.... መፅሐፍ እንዲፅፉ የምመኝ ነኝ።
ጀዋር መሐመድ በአዲስ መፅሐፍ ሊመጣ እንደሆነ ሰምተናል። እውነት ለመናገር መረጃውን ከሰማሁ ቀን ጀምሮ በጉጉት ስጠብቅ ነበር።
ከላይ የጠቀስኳቸው ሰዎች እንዲፅፉ የምመኘው በምክኒያት ነው።
ሐገራችን በተወሳሰበ ችግር ውስጥ ገብታለች። እንደ ሐገር የምናልፍበት መንገድ ነገ በታሪክ ፊት በልዩ ሁኔታ ትኩረት የሚስብ ይመስለኛል።
የእርስ በእርስ ጦርነት ፥ የመፍረስ ስጋት ፥ አይገመቴ እጣ ፈንታ ፥ ረሃብ ፥ ተደጋጋሚ መፈናቀል እየጎበኘን ነው። ያለፉት ጥቂት አመታት ክፍለ ዘመን ያክላሉ። ሰባቱ አመታት ሰባ አመት ይመስላሉ።
ካለንበት ምስቅልቅል ጀርባ ፖለቲካ አለ። ፖለቲካ ወለድ ቀውስ እየናጠን ነው። ምን እየሆነ እንዳለ ሁላችንም እናውቃለን። ነገር ከድርጊቱ ጀርባ ያለውን ነገር በጥልቀት መረዳት አዳጋች ነው። ይህን መረዳት ለመፍትሄ ይረዳናል።
ጃዋር መሐመድ በኦሮሞ ፖለቲካ ግዙፍ ስም ነው። በአንድ ወቅት "የለውጡን ኳልኩሌተር ሰራሁት" ብሎን ነበር።
አንዳርጋቸው ፅጌ "የለውጡ ሮድ ማፕ ባለቤት ነኝ" ማለቱን አንረሳም። በአንድ ወቅት ለBbc በሰጠው ቃለ መጠይቅ የአብይ እና የኢሳያስ ዋነኛ አገናኝ መሆኑን ተናግሯል። ኢሳያስ ባለፉት አመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለው ሚና ይታወቃል።
ጃል መሮ "ኦነግ እና የኢትዮጵያ መንግስት ተስማሙ" ተብሎ ተነግሮ ዜናው ከአየር ሳይወርድ ከፌደራል መንግስት ለመፋለም ነፍጥን አንስቷል። ከኦነግ ጋር ግልፅነት የጎደለው ስምምነት በተደረገ ማግስት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት "መንግስት ክዶናል" ብሏል። ኦላ ምን እንደተካደ ጃል መሮ ቢነግረን ይገቅማል።
ለማ መገርሳ ለውጡ በስሙ ተሰይሞለት ነበር። "ቲም ለማ" ስለሚባል ቡድን ደጋግመን ሰምተናል። ቀጥሎ የኢህአደግን መፍረስ ተቃውሞ ከመደመር ቡድን ወጥቷል። ከዛ በፊት ግን ከለውጡ አክተሮች መካከል ነበር።
የብአዴኑ ገዱ አንዳርጋቸው የለውጡ እሳት ከበላቸው የለውጡ አቀጣጣዮች መካከል ነው። ዛሬ ብአዴን ከሕወሓት ተላላኪነት ወደ ኦህዴድ ተላላኪነት ተቀይሯል።
በረከት ስምኦን ከለውጡ በፊት "ትንሳኤ ዘ ኢትዮጵያ" የሚል መፅሐፍ ፅፎ ነበር። በመፅሐፉ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ልዩነቶችን በአግባቡ ካልስተዳደረች ሐብቷን እንደምታወድም ፅፎ ነበር። ከለውጡጋ ቀድመው ከተላተሙ ሰዎች መካከል አንዱ በረከት ነው።
የህወሐቶቹ ደብረፂዮን እና ጌታቸው ረዳ ዛሬ ላይ ጎራ ላይተው ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል። ከዛ በፊት ግን ከለውጡ ተቃራኒ ሆነው ለውጡን ተፋልመዋል።
እንዲህ እንዲህ እያልን መቀጠል እንችላለን...
ለውጥ ተብዬው ነውጥ ከመምጣቱ በፊት ጀምሮ በተለያየ አሰላለፍ ውስጥ የነበሩቱ ከእነርሱ አንፃር ያለውን መረጃ በመፅሐፍ ቢያጋሩን እወዳለሁ። የቆሙበትን መሰረት ፥ አሰላለፋቸውን እንዲመርጡ ያስቻላቸውን ገፊ ምክኒያት ፥ የተራመዱበትን መንገድ ሊነግሩን ይገባል።
በሚሰጡን መረጃ ላይ ተመርኩዘን እውነትን እንፈልግበታለን።
ያለንበትን ቀውስ የወለደውን እውነተኛ ምክኒያት መረዳት ለእውነተኛ መፍትሄ ይጠቅማል።
የጀዋር መሐመድን "አልፀፀትም" የተሰኘ መፅሐፍ በከፍተኛ ጉጉት እጠብቃለሁ
በዛሬው ሰንበት ከእንግሊዝ ሀገር የሚተላለፍ አንድ ስብከት ስሰማ ነበር። ሰባኪው ስብከቱን ያጠነጠነው በፈላስፋው ኒቼ አባባል ዙሪያ ነበር። ፈላስፋው “God is dead, we have killed him” በሚለው አባባሉ በጣም ይታወቃል። ሰባኪው እግዜብሔር ሊሞት ይችላል? እኛስ ልንገለው እንችላለን? ልንገለው ከቻልንስ በምን መሳርያ ወይስ በምን መነገድ ነው ልንገለው የምንችለው? እያለ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ወደ ስብከቱ ዝርዝር ገበ። እኔ ግን በጥያቄው fascinated ስለ ሆንኩ በራሴ የስብከት ሀሳብ ውስጥ ገባሁና ብዙም ስብከቱን በቅጡ አልሰማሁትም።
እግዜብሔር ሊሞት ይችላል? አዎ ሊሞት ይችላል። በግለሰብ ሆነ በማሕበረ ሰብ ውስጥ ሊሞት ይችላል። ግለሰብ ፈጣሪውን አልፈልግህም ብሎ ከሕይወቱ ሊያወጣው ይችላል። በዛ ሰው ሕይወት ውስጥ ምንም ትርጉም የለውም። ለዛ ሰው እግዜሩ ሞቷል። ይህ ማለት ግን ሰውየው (ሴትየዋ) ሞተዋል ማለት ነው? በጭራሽ። ሰው ያለፈጣሪው ደስተኛ፣ ጤነኛ፣ ሀብታም፣ ደግ፣ አስተዋይ፣ ለሰው አሳቢ፣ ሆኖ መኖር ይችላል። በምሕበረ ሰቡም ውስጥ እንዲሁ ነው። እግዜብሔር አያስፈልገንም ብለው ከማሕበረ ሰብ እንቅስቃሴ ውስጥ ያስወጡ በርካታ ማሕበረሰቦች በአለም ላይ አሉ። እነዚህ ማሕበረሰቦች ይህን በማድረጋቸው ጠፍተዋል? በጭራሽ። እኛ ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት በፈጣሪ አማኝ ነን ከምንል ማሕበረሰቦች የተሻለ ሰላም፣ ሀብት፣ ፍትህ፣ ትምሕርት፣ ጤና በነዚህ ማህበረሰቦች (ሀገራት) ወስጥ ይገኛል። ለዚህ ይመስለኛል ሁሉም በቦሌም ሆነ በባሌ ካልወጣሁ ብሎ በጾም በጾለት ሆነ በጉቦም ሲዋትር የሚውለው። ለተሻለ ሰላም፣ ሀብት፣ ፍትህ፣ ትምሕርት፣ ጤና።
ኒቼ “እግዜሩ ሞቷል” ብቻ አይደለም ያለው፣ “ገለንዋል” (we have killed him) ብሏል። ከግለሰብ ሆነ ከማሕበረሰብ ሕይወት ውስጥ ለማውጣት እግዜብሔርን በምን ገደልንው? የመግደያው መሳርያ ምን ነበር? ክርስትናው እራሱ የመግደያውን መሳርያ ወልውሎ፣ ቀምሞና አመቻችቶ አቅርቦ ይሆን? በአብዛኛው የምዕራቡ አለም አብዛኛው ሕዝብ የለየለት ከሀዲ አይደለም። ግን ለፈጣሪ መኖር ወይም አለምኖር ግድ የለውም። “ቢኖር የራሱ ጉዳይ፣ ባይኖር የራሱ ጉዳይ” ባይ አይነት ነው። ለዚህ እግዜሩ በግለሰብ ሆነ በማሕበረ ሰብ ውስጥ ለመሞት ምክንያት የክርስትና አስተምህሮቱ እንዲህ የጦዘ ድብልቅልቅ ውስጥ ለዘመናት መግባቱ ለብዙ አምላካቸውን በውስጣቸው ለገደሉ ግለሰቦች ይሁን ማሕበረሰቦች እንደ ዋና የመግደያ መሳርያ የተጠቀሙበት ይመስላል። ኒቼ we have killed him ሲል በምን ይሆን?
እኔ ይህን ሳውጠነጥን ሰባኪው ስብከቱን ጨርሶ መዝሙሩ ሲመጣ ከራሴ ስብከተ ፍልስፍና ነቃሁ። እንዲህ አይነት ሰንበትም አለ። አሜን!!
ከዮናስ ጎርፌ የፌስቡክ ገፅ የተወሰደ
አዲሳባ እየፈረሰች ነው። ደሰሳ ቤቶች "አዲሳባን አይመጥኑም" ተብለው እየፈረሱ ነው።
አዲሳባን ዘመናዊ ህንፃ ሳይሆን ደሳሳ ቤት ነው የሚመጥናት። ኢትዮጵያ የደሐ ሐገር ናት። አዲሳባ ደግሞ የድሆች መኖሪያ ነው። ሚሊዮኖ ድሆችን እያስተዳደሩ "የደሀ ቤት ከተማችንን አይመጥንም" ማለት አሳፋሪ ስላቅ ነው።
ደሳሳ ቤቶችን ማስወገድ መፍትሔ አይሆንም። ድህነታችንን የሚመጥነውን የደሐ ቤት ማፍረስ ትርፉ ሌላ መከራ ነው።
መፍትሔው የደሐውን ኑሮ ማሻሻል ነው። የደሐ ኑሮ ሲሻሻል ደሳሳ ቤቶች በራሳቸው ጊዜ በዘመናዊ ቤት ይተካሉ።
ቅድሚያ ለድህነት ቅነሳ ፖሊሲ!
ከጋፋት እስከ መቅደላ
ቴዎድሮስ ያሰሩትን 8 ሺ ኪሎግራም የሚመዝን መድፍ ከተሰራበት ስፍራ እስከ መቅደላ ያስወሰዱበት መንገድ ድራማዊ ነው። ነገሩ ትኩረት የተነፈገው ቢሆንም አግራሞትን የሚፈጥር እና ሰባት ወራት ግድም የፈጀ ነበር።
ንጉስ ቴዎድሮስ ከእለታት በአንዱ "መድፍ ስሩልኝ" የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ለፈረንጆች አስተላለፉ። ትዕዛዙ 'እምቢ' ሊሉት የማይችሉት ከአለት የጠጠረ ነበርና የንጉሱን ፈቃድ ለመፈፀም ሩጫ ተጀመረ።
አላማው ብረት ማቅለጥ የሆነ ግዙፍ ምድጃ ከተዘጋጀ በኋለ ብረት ቀለጦ የእሳት ፈሳሽም ሆነ። ብረት ቀልጦ የተዘጋጀው የእሳት ፈሳሽ ለሞዴልነት ወደ ተዘጋጀው ጉድጓድ እንዲፈስ ተደረገ፤ የማፍሰስ ሂደቱ 20 ደቂቃ የወሰደ ነበር።
በዚህ መንገድ የተጀመረው የመድፍ ስራ ከተገባደደ በኋላ በስራው ለተሰማሩ አውሮፓውያን የክብር ቀሚስ ፥ በብር እና በወርቅ ያጌጠ ፈረስ እና በቅሎ በተጨማሪም ለእያንዳንዳቸው 1 ሺ ብር በሽልማት ተሰጠ።
መድፉ ከጋፋት እስከመቅደላ የሄደበት መንገድ በብዙ የሚያስገርም ፥ ትኩረትን የሚሰርቅ ነበር።
አስቀድሞ መድፉን ለማጓጓዝ አላማ የሚውሉ በአይነታቸው ልዩ የሆኑ ጋሪዎች ተሰሩ፥የጋሪዎቹ ብዛት 14 ነበር።
መድፉ ግዙፍ ነው፥ ግዙፍ ሲባል ለግነት ያህል ሳይሆን ክበደቱ 80 ኩንታል ወይንም 8 ሺ ኪሎግራም የሚመዝን ነው።
ግዙፉን ቁስ ከጋፋት ወደ መቅደላ ማጓጓዙ መስከረም 21 ፥1860 አ.ም ተጀመረ።
ከጋፋት እስከ መቅደላ ያለው ርቀት 320 ኪሎ ሜትር ነው፥ ደግሞ ስፍራው መንገድ አልተበጀለትም።
የቴዎድሮስ ሰራዊት ከፊሉ ከፊት እየቀደመ መንገድ ሲሰራ ቀሪዎቹ መድፉን በማጓጓዝ ተግባር ይሰማራሉ።
መድፉን መቅደላ ለማድረስ የሚረዳ መጎተቻ በጥንቃቄ ተዘጋጅቷል። በዳገት ላይ ወደኋላ እንዳይንሸራተት ደግሞ ማገጃ ተሰርቷል።
800 ጋሪ ጎታች ሰዎች ተልእኮውን በድል ለመፈፀም ተመድበዋል። በመጎተቻው ከፊት ከሚጎትቱት በተጨማሪ ከኋላ የሚገፉ ሰዎቸ አሉ።
ይህ ሁሉ ዝግጅት ቢደረግም ጉዞው ደህንነቱ የተጠበቀ አልነበረም፥ መንገዱ ሽፍቶች ነበሩበት።
ሽፍቶች መሳናክል እንዳይፈጥሩ ሲባል ከሽፍቶች እየተፋለሙ መንገድ የሚያስለቅቁ ተዋጊዎች ተዘጋጁ።
ጥሻውን እየመነጠሩ መንገድ ማዘጋጀት ፥ ከሽፍታ እየተፋለሙ የደህንነት ስጋት ማስወገዱ ጉዞውን አዝጋሚ በማድረጉ የተነሳ ፥ በቀን የሚደረገው አማካይ ጉዞ ከ3 -4 ኪሎሜትር ብቻ ነበር
እመው "በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ" እንዲሉ የስንቅ እጥረት ተከሰተ። ይሄኔ ቆፍጣናው ንጉስ አፄ ቴዎድሮስ በመንገድ ወዳለ ሰብል በማቅናት እሸት በመብላት ለሰራዊታቸው 'ያደረግኩትን አድርጉ' የሚል ተግባራዊ መልእክትን አሰተላለፉ።
ቴዎድሮስ በጉዞ ወቅት አረአያ ሆነዋል። ዳገታማ ቦታዎች ላይ ቀልጠፍ ብሎ በመንገድ ስራ ይሰማራሉ፥ ጥሻ ይመነጥራሉ፥ አፈር ይደለድላሉ፥ ድንጋይ ይፈነቅላሉ።
6 ወር ተኩል ከፈጀ አድካሚ ጉዞ በኋላ መድፉ ከመቅደላ ግርጌ ደረሰ።
ከዚህ በኋላ ከቀደመው የላቀ ጥንቃቄ የታከለበት ስራ ተጀመረ። ወደ መቅደላ አምባ የሚያደርስ መንገድ እጅግ ከፍተኛ በሆነ ጥንቃቄ ተሰራ።
መድፉ ከመቅደላ ግርጌ እየተጎተተ ሽቅብ መውጣት ሲጀመር ብርቱ ስጋት ነበር። በመጨረሻው ሰኣት መጎተቻው ተበጥሶ አደጋ እንዳይደርስ እና የተለፋው ሁሉ ከንቱ እንዳይቀር ተፈርቷል!
ከሰራዊቱ መሃል ከፊሉ 8 ሺ ኪሎ ጎራም የሚመዝነውን ግዙፍ መድፍ ይጎትታል፥ የተቀሩቱ ደግሞ ከኋላ ይገፉታል። ይሄን የሚያደርጉት በህብረት ድምፅ በማውጣት ስለሆነ የንጉሱን ድምፅ የሚሰማ የለም። ቴዎድሮስ መልእክት ማስተላለፍ ሲፈልጉ እጃቸውን ብድግ ያደርጉታል፥ ያኔ ሁሉም ፀጥ ይላል።
አድካሚ የነበረው የመድፍ ጉዞ ሰባት ወራት የተጠጋ ግዜን ፈጅቶ ከጋፋት ተነስቶ መቅደላ ደረሰ። ያኔ ንጉሱ ቦረቁ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana