ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
( ርዕስ - ና! ከደብረዘይት )
የሰው ልጅ ፍቅር ከዙፍን ከሰማያት ከከብርህ ወደ ምድር ስቦህ
የኛን ስጋ ለብሰህ ደዌያችንን ተቀብለህ
ህማማችንን ተሸክመህ
በጲላጦስ አደባባይ ቀራንዮ በመስቀል ላይ
እየሞትክ ያነጽካት ደም የከፈልክላት
ቤዛ የሆንክላት
የሲኦል ሃያላን የዲያብሎስ ጭፍሮች ያልተገዳደሩአት
በደምህ ነጠብጣብ በዋጋ የገዛሃት
ቤትህ አድፋለች ወንበዴዎች ከበዋት
ሻጮች ሰፍረውባት ገበያ ሆኖባት
ሸመታው ደርቶባት በአህዛብ ተንቃለች
በርግብ ሻጮች ወንበር ቤትህ ቆሽሻለች
በለዋጮች ዕቃ በዕዳ ተይዛለች
https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
ወደ እየሩሳሌም ስትገባ ያጀቡክ
ቁልቁል ደብረ ዘይት ስትወርድ የከበቡክ
ልብሳቸውን ጥለው ሆሳእና ዛሬ የዳዊት ልጅ ያሉ
ማለዳ ተነስቶ በቅዳሴ ስምህ ክበር ያሉህ ሁሉ
በምስጋና ፍክተው በልልታ በሆታ
መድሃኒት ነክ ያሉ
አረፋፋዱ ላይ መቅደስ ውስጥ ገብተው
ቤትህ ተመልሰው ቅዱሳቱን ከበው
በአገልግሎት ዕቃ ገቢያ ይዘዋል
ገዢና ሻጭ ሆነው ሁሉም ርቀዋል
የጦፈ ገበያ የደራ ሸመታ
የሌቦች ትርምስ የለዋጮች ወይታ
መልኳን ቀይሯታል ያለስሟ ስም ስም አሰጥቷታል።
ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
የፖለቲካው ንግድ መቅደስክ ውስጥ ሆኗል
ያኛው ይራገማል ይህኛው ያወግዛል
ዘር ቡድን ለይቷል ልዩነቱ ሰፍቷል
የኬፋ ነን ያሉ በአንድ ወገን ሆነው
መደብር አቁመው ወንዝ ጎሳ ጠርተው ገብያ ሰርተዋል
ሌሎች ከዛ ማዶ ከመቅደሱ መሃል
አጥንት የቆጠሩ ደም የመረመሩ ዘር የዘረዘሩ
የአጵሎስ ነን ያሉ ሌላ ንግድ አላቸው ሸመታ ይዘዋል
የሚሸጥ ይሸጣል የሚገዛም በስቷል
የገቢያው ጩኸት የሌቦች ኹካታ
ቤትህን ሞልቷታል የመንደር ጨዋታ
ሰላሟን ነስቷታል ክብሯን አዋርዷታል
በተቀደሰው ቤት በደጀ ሰላሙ እርኩሰቱ ገኗል
የቤቱ ባለቤት ማንነት ተረስቷል የቅዱሳን ህይወት ታሪክ ብቻ ሆኗል
የምድራዊው ነገር በዝቶ ይነገራል
ግማሹ ከጳውሎስ ነን ብሎ ይቆማል
ቀሪው ከኬፋ ጋር ብሎ ይቧደናል
በክርስቶስ ህብረት አንድነት ቦታ አጥቷል
ቋንቋ ደም ዘረ ሆኗል ቅድሚያ የሚሰጠው
ማነህ ከወዴት ነክ ከነማነህ ሆኗል አቋቋሙ ቅኔው
መስቀል ተሸክመህ ቀራንዮ ውለህ
ደምህን አፍስህ
አጥንትህን እስኪታይ ስጋህ እስኪደማ ግርፋቱን ችለህ
የሁሉን ሰው ደዌ ህማም ተሸክመህ
ስለሚተላለፍ ስለ በደል ቆስለህ
በመከራ መስቀል ህይወትኽን ሰጠህ
የከፈልከው ዋጋ ሁሉ ተዘንግቶ
መሞትህ ተረስቶ
ከፊት ተደርድርው ወንዝ ጎሳ መንደር
ገበያ ሰርተዋል በማስመሰል ፍቅር
በእንግድነቱ አለም በዚህ ከንቱ ምድር
ጥለን የምንሄደው የዘር የወንዝ ክብር
በቤተክርስቲያን በመቅደሱ ስፍራ የደራ ንግድ ነው የሚያተረፍ ስራ
ቋንቋም ሆኗል ገንዘብ የመግባቢያው በሩ
ወይንም ዘር መቁጠር ነው ወንዝ እየከተሩ
.
ና ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
ና ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና
https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
አፍኒን እና ፊናስ መቅደስህን ደፍረው
ኤሊን አስቆጥተው ህዝቡን አስመርረው
በከበረው ነዋይ ጨዋታ ይዘዋል
በቅዱስ ቁርባኑም ማፌዝ ጀምረዋል
ግዴለሾች ሆነው ግልጋሎት እረስተው
የእግዚአብሔርን ቁርባን ንቀው አቃለዋል
በድንኳኑ ደጃፍ በአገልግሎት ካሉት ከሴት ተኝተዋል
የካህኑ ኤሊ ድምፁ አልተሰማም
የልጆቹን በደል አይቶ አልተናገረም
የቤተመቅደሱ የጦፈ ገቢያ ዝም ብሏል እያየ የንግዱን መዋያ
ሳሙኤል ተኝቷል እግዚአብሔር ይጣራል
ደጋግሞ እስኪሰማ ድምጹን እያጣራ ሳሙኤል ተኝቷል
እግዚአብሔር ይጣራል
ሳሙኤል ሳሙኤል የሰው ያለህ ይላል
እግዚአብሔር ይጣራል
ከአፋኒን እና ፊናስ በደል ከፍ ብሎ
ከነጋዴዎች ጩኽት ከነጋዴዎች ሁከት ድምጽ ሁሉ አይሎ
እግዚአብሔር ይጣራል ሳሙኤል ብሎ
በቤተመቅደሱ ድምጹ ያስተጋባል
የጅራፉ ጩኸት ድምጹ ቋንቋ ፈጥሯል
ሳሙኤል ሳሙኤል እግዚአብሔር ይጣራል
ኤሊም ዝም ብሏል
የቤተመቅደሱን ንግድ አልተቃወመም
በቅዱሱ ስፍራ የማይገባውን አልተከላከለም
ተው አላለም ኤሊ እንደ ክህነቱ
ተው አላለም ኤሊ እንደ ስርዓቱ
መቅደሱ ሲደፈር ልጆቹ ሲስቱ
ንግዱ ተጧጥፏል ኤሊም ዝም ብሏል
ይሄ በደል ከብዶ ፀጋህ ሳትወሰድ
መቀጣጫ ሆኖ አህዛብ ሳይለብሱ
እውነት ሳይጋረድ
ምህረት ሳይርቀን ጥበቃህን ሳተው
ጽዮን ሳትማረክ ፊትህን ሳታዞረው
.
ና! ከደብረ ዘይት ቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና።
https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
ኑፋቄ የሚያቀርቡ ክህደት የሚዘሩ
በመቅደስ ሆነው እየተዟዟሩ
የሚሸጡም አሉ ንፍቅና ሚሰፍሩ
መግባት ያቃታቸው ከውጭ ያቀርባሉ
ችርቻሮ ጅምላ ዱቤ ዋጋ እያሉ
ውስጥ ያሉ በርካሽ ከመቅደሱ ሆነው
ይቸበችቡታል የኑፋቄውን ንግድ
ቤቱን ለመቦርቦር መቅደሱን ለመናድ
አስመጪ አከፋፋይ ሆነዋል ብዙዎች
ኑፋቄ እየሸጡ ሃጢአት ማከፋፈል
ገንዘብ እየሰጡ ቅድስናን ማስጣል
https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
ናት ከደብረ ዘይት ቁል ቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና
አውሬው ተደስቷል ገብያው ሰምሮለት
ሰርግና ምላሽ ነው መቅደስ እረክሶለት
አንድ ዕቃ ለገዛ ሁለት አለን ነፃ
ማስታወቂያው በስቷል በየጥጋጥጉ
መክፈልም ካቃተ ዱቤ አለን አትስጉ
የትኛው ያተርፋል ይሄ ስንት ያወጣል
ይኽን የሚገዛ ያንን የሚለውጥ
ይኼ ሆኗል በቋንቋው በቤተመቅደስ ውስጥ
ውጡ እናንት ሸማቾች
ውጡ እናንት ነጋዴዎች
ገበያ ሰሪዎች
በተቀደሰው ላይ ገንዘያ የምትሰሩ
በምስጋናው ዕቃ ሸቀጥ የምትሰፍሩ
ነፃውን ግልጋሎት ገቢያ ያወጣቹ
በጸሎት ስፍራዬ ሱቅ የከፈታቹ
ውጡ እናንት ሸማቾች ቤቴን የለዋጮች ስፍራ ያረጋቹ
በተቀደሰው ላይ መደብ የሰራቹ
የነጋዲያኑ መደርደርያ የእርግብ ሻጮቹ ወንበር
የሻጭ የለዋጩን የሱቁን መደብር
በትን ብራቸውን ግረፍ በጅራፍህ አርቅ ከደጃፍህ
ውጡ እናንት ሸማቾች ቤቴ የጸሎት ነው
ቤቴ የአምልኮ ነው
ቤቴ ለስግደት ነው
አንሱ ይኽን ወንበር ውሰዱ ከፊቴ
የምስጋና ስፍራ የጸሎት ነው ቤቴ
የገበያ ሃሳብ የሌባ ሸመታ
አይሆንም ከዚህ ውስጥ ውጡ ከዚህ ቦታ
ለሌላ አሳልፈህ ለአህዛብ አትስጠን
ቤቱ ያንተ ቤት ነው እኛም ያንተው ነን
እንደ አባትነትህ እራስህ ገስጸን
እጠባት ቤትህን እጠብቃለሁ ሁላችንን
አጽዳ መቅደስህን ፍታው ገቢያውን
ያንተ ግርፊያ ይሁን ለሌላ አትተወን
ስለ ቅዱሳንህ ብለህ ተለመነን
ቤቴየሰ ብለህ አንተው አስተካክለን
.https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
ና ከደብረ ዘይት ከቁልቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ አለንጋ ያዝና
ና ከደብረ ዘይት ቁል ቁል ውረድና
መቅደስህን አጽዳ ጅራፍ አበጅና።
ተፈፀመ !
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ይቆየን !https://t.me/httpsGibiGubayeMikael
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana