ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ተው በሉት ይሄን ሰው ይላሉ ብዙዎች
እኔ ብቻ አድናቂክ ካንተ ተፈታኞች
ኢንትራንስን በኮድ አስረህ አጅበኸው
ጭራሽ ዘንሮማ ኦንላይን አርገኸው
ስንቱ ተስፋ ቆርጦ ስራውን መረጠ
አልሞት ባዩም ደሞ በንባብ ቀለጠ
በአሳይቶ መንሳት በእቁልልጭ ጭዌ
በቀደሙት አየን አርገሀቸው ቀዌ
ጊቢ ቂቤ ሆኖ እሳት ላይ የጣዱት
እንዳማረው ቀረ ስንቱ ባንተ ምክንያት
እኔ ግን የምልህ
ሁሉ እንዳለ ሆኖ አጀብ ቁጥጥሩ
መለየቱም መልካም ደካማን
ከጥሩ
ቢሆንም ቢሆንም እንዳናጣ ተስፋ
በሁኔታዎች ላይ ወይ እንዳንከፋ
ለተከርባች ሁሉ ይዘጋጅ ማረፍያ
በአጉል አወዳደቅ ደሞ እንዳንደፋ
ለብርዬ ቃል አጥሮኝ ለቃቅሜ የፃፍኩት ማመልከቻ?
✍️የተክልዬዋ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm
የተማሪ ሚዛን በጣም ረቀቀ..
..
ለገበሬ ሰብል፡ ተሠራ ኮባይነር፣
ለተማሪ ደግሞ፡ታብሌት 'ሚባል ነገር፣
..
ኮባይነር ሲለያይ፡ ምርትን ከገለባ፣
የታብሌት ክፋቱ፡ ያበዛል ጠረባ፣
ኦንላይን ነው ፈተናው፡ ለተማሪ እርዳታ??
እንግዲህ ተፈታኝ፡ዐይንህን አፍታታ፣
..
ታብ ታብ ማድረግ ነው፡ዘንድሮ ፈተና፣
እርሳስ ለመዋዋስ፡የለም ጎንበስ ቀና፣
..
የሀገርን ዕድገት ለማየት አሻግሮ፣
ፈተና ያወጣውም፡ይፈተን ዘንድሮ?
..
መስመር ተዘርግቷል፡አዕምሮ ሊመዘን፣
ተሜም ጠንክርና፡ፈጣሪን ተማፀን!!
መልካም ፈተና ለተፈተኞች በሙሉ!!
ኤርሚ ግርማ
@semetnbegtm
@semetnbegtm
@semetnbegtm
"ወደድኩህ " ያልሽኝ ቀን?****
መንገድሽን ሔጄ ፣ ሸኝቼሽ ስመለስ
ዳግም ተገናኝተን ፣ እስካወራሽ ድረሰ
ያልሽኝን እያሰብሁ☺️
ስሔድ ስሔድ ስሔድ?፣ አልፌው ሰፈሬን
አልፌው መንደሬን
አልፌው ብሔሬን
ላልፋት ስል ሀገሬን?
መንገድ የሚዘጉት ፣ በዱላ ግንባሬን?
ነርተው ዘረሩኝ ፣ ከሀሳቤ አነቁኝ
"ወደት ነው ምትሔደው?" ፣
በማለት ጠየቁኝ
ወዴት ልበላቸው??
ተደቅነውብኝ ፣ ሽመልና ፍርጃ
ያልሽኝ ተዘነጋኝ ፣
መንገድ የሚያሳስት ፣
ምን እንዳልሽኝ እንጃ።?
ብቻ ሰምቻለሁ
ብቻ ግን አውቃለሁ❤️
" ወደ ተለየ አለም
ፍቅር ይወስዳል" ይላል ፣
ያፍቃሪ አፍ መፍቻ
እዚ እንዳይሆን ብቻ ?
?
አምላክ አድሎሻል ገፀ በረከቱን
ብልሃት የመኖር የማግኘት ማጣቱን
እንደ ሴትነትሽ ብዙ ተጋፍጠሻል
ትላንት ሳይበግርሽ ከዛሬ ደርሰሻል
ፈጣሪ ጠብቆ እንደ ቸርነቱ
ለዛሬ በቅተሻል
.
ዘውትር በክፉዬ ቀርበሽ ያፅናናሽኝ
በፈጣሪ ልሳን በፈጣሪ ቃላት
ሰርክ 'የደገፍሽኝ
ተስፋ እንዳልቆርጥ ሆነሽኝ ብርታቴ
ከጎኔ አልጠፋሽም የምወድሽ እህቴ
አንድ ስደናቀፍ አይዞህ በርታ ብለሽ
ውስጥሽ ከፍቶት እንኳን እኔን ታፅናኛለሽ
ብዙ ያስተማርሽኝ ገፀ በረከቴ
አንቺን ሚገልፅበት ቃል የለው አንደበቴ
ብቻ መልካም ልደት አመት አድሎሻል
ገና የምትኖሪው ብዙ ይቀርሻል
አያልፉ ሚመስሉ ብዙውን ተራምደሽ
በሰው የማይቻል ለብቻሽ ተጉዘሽ
በከፍታም ቢሆን አልያም በዝቅታ
የጥንካሬሽ ገፅ መቼም አልተረታ
.
መልካም ልደት ይሁን ላንቺ እህትዓለሜ
ሚስጥረኛዬ ነሽ ጓዳ የህመሜ
መልካም ልደት ወይዘሪት ፋሲካ????? እንኳን ተወለድሽ
??ታናሽሽ??
?
የፈሰሰ አይታፈስም
ትላንትና አይመለስም
ስኖር ያኔ ከጎናቹ
ውል ጥቅሜ ያልገባቹ
ምን ፍለጋ ምን ቀረና
ከደጃፌ ተገኛቹ?
.
በትላንቴ ሳልበገር
ወደፊቴ ገስግሻለው
የራስ ዋጋ ሚገባኝን
አሁን በደንብ አውቂያለው
እንደ ወትሮው ላልጎተት
ለአንድ እራሴ ቃል ገብቼ
ሚገባኝን ስላወኩኝ
አልፊያለው ሁሉን ትቼ
.
ባለሁበት ስላልቆምኩኝ
ተጨንቃቹ ተጠባቹ
ካመለጥኩት ትላንትና
ልትመልሱኝ ላሰባቹ
.
የጣልኩትን ዞሬም አላይ
እንኳን ቀርቶ ልመለከት
በመጣ እግር ተመለሱ
ደስተኛ ነኝ ባለሁበት
በኪሩቤል አሰፋ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana