ሳሙኤል በለጠ(ባማ)

Description
የሐሳብ ነገር
| @wosdomati |
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

12 months ago

አልተዛወረችምና እውናዊ ልብ ወለድ
[ኂሳዊ ዳሰሳ]
በሳሙኤል በለጠ

"የልብ ወለድ ደራሲ ወይ ነገር ተመልካች ወይም ደግሞ አመላካች ነው። በተጨማሪም በልብ ወለዱ በሬካታ ተሞካሪ ነገሮች አሉ፥ ወይ እውነት ይሰጥሃል ወይ የእውነቱን መነሻ ነጥብ ታገኝበታለህ፥ ገጸ ባህሪያት የረገጡትን ምድር አልፎም ማለዳና ጨለማውን ለማሳየት ገጸ-ባህሪ ፈጥሮ የሰውንና የተፈጥሮን ምስል ያሳይሃል።"( Émile Zola, The Experimental Novel, p. 8 )

ደራሲ ገጣሚና ኀያሲ በዮሐንስ አድማሱ በ1961 ዓ.ም በጻፉት "የልብ ወለድ ሥነ ጽሑፍ ጉዞ" በሚለው ኂሳቸው ላይ በዘመኑ የነበሩ የልቦ-ለድ መጽሐፎች በሦስት መሰረታዊ ምክንያት ጥሩ እንዳልነበሩ ይነግሩናል።

ሀ/ በቴክኒክ ጉድለት፤
ለ/ በሒስና በሐያሲ እጦት፤
ሐ/ በደራስያኑ አማርኛ መበላሸት።

የነፍቅር እስከ መቃብር ዘመን አልፎ ያልተቀበልናቸው እነ ዳኛቸው መጥተው ልቦለዳችን ወደ ድህረ-ዘመናዊው አጻጻፍ በነ አዳም ረታ፣ በነ ስንቅነህ እሸቱ(ኦ ታም ፕልቶ)፣ በነ ሌሊሳ ሲተካ የልብ ወለዱ ዘርፍ አበበ ነገር ግን አሁንም ዮሐንስ አድማሱ ያነሱት ጉድለቶች ነበሩ ወደ ተነሳንበት እንምጣ አሌክስ አብርሃም በሥስት የሥነ-ጥበብ ዘርፍ ማለትም በግጥም፣ በአጫጭር ልብ ወለድ፣ አሁን ደግሞ በረጅም ልብ ወለድ በዚህ ዘመን ብዕራቸው ከደመቀላቸው እንዲሁም ሠፊ አንባቢ ማግኘት ከቻሉ ደራሲዎች ተርታ ለመሰለፍ ችሏል።

ለዛሬ በሁለት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ገጽ በአራት ክፍል የተከፈለውን "አልተዛወረችም" ሲል አሌክስ ርዕስ የሸለመውን መጽሐፉን ከእውናዊ(Realism Literature) የሥነ-ጽሑፍ አጻጻፍ ይትብሃል አንጻር እንመልከተው ሁሌም እንደምጽፈው ሥነ-ጽሑፍ በተለያየ ዲሲፕሊን ሲኄስ የኀያሲው ምልከታ እንጂ ደራሲው እንደዛ አስቦ ላይጽፈው ይችላል።

እንሂድ ዳኛቸው ወርቁ ከሞልቬር ጋር በነበረው ቃለ-ምልልስ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር "Good Literature reflects the life and spirit of a people"¹ (ደገኛ ሥነ-ጽሑፍ የሚህበረሰቡን መንፈስና ሕይወት የሚያንጸባርቅ ነው።) የአሌክስ አልተዛወረችም የማሕበረሰቡን መንፈስና ሕይወት በማንጸባረቁ ደገኛ ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ ይካተታል እንበልና ወደተነሳንበት ጉዳይ እንዝለቅ:-

ሀ.የአጻጻፉ ይትባህሉ ምንነት!

ሪያሊዚዝም በአሌክሳንደር ሹሽኪን የተዋወቀ ርዕዮተ ዓለማዊ የአጻጻፍ ፍልስፍና ሲሆን በራሺያ በሥፋት የተሰራጨ እንደሆነ ታሪክ ይነግረናል። ሪያሊዝምን ያጠኑት ደራሲና ኀያሲ ኤምሊ ዞላ እንደሚሉት ከሆነ የአጻጻፍ ይትብሃሉ እሙናዊ(faithful) በሆነ መልኩ ሕይወትን ድጋሚ መግለጽ ነው።² እውናዊ ሥነ-ጽሁፍ እንዲህ ይተረጎማል።

ለ. ጭብጥ (Themes)

አንድ ልቦ-ለድ ልብ ወለድ ከሚያስብሉት አንዱ ጭብጥ ነው። ነገር ግን በእውናዊ (Realism) አጻጻፍ ጊዜ ጭብጡ ሊያንስ ይችላል።³ "ዓይኖቿን ጨፍና ዕንባዋ ጠይም ጉንጮቿ ላይ ግራና ቀኝ ወደ ጆሮዋ እየፈሰሰ ነበር"(©አልተዛወረችም ገጽ-31) ይሁንና የሥነልቦና መደፍረስ፣ የሰውነት ግንብ በሌላ ሲናድ፣ ፍቅር፣ ጥላቻና ብቸኝነት ተራኪውን አብርሃምን የልቡ ጓዳ ገብተው የሚጎበኙት ስሜቱች ሲሆኑ ማህደርና ዮናስም የሚታመሱበት ትራውማ(ሽብር) በመጽሐፉ ተተርኳል።

ሐ.መቼት(Setting)

እውናዊ የሥነ-ጽሑፍ አጻጻፍ ይትብሃልን ያጠኑ ምሁራን እንደሚሉት ከሆነ መቼና የቱ ተለምዷዊ(ordinary) ነው ይላሉ "ግድግዳው፣ ጣሪያው፣ መኝታ ቤቱ፣ ሳሎኑ፣ መታጠቢያ ቤቱና ማብሰያ ቤቱ ሁሉ ቁጥር ስፍር በሌለው ትዝታዬ ተሞልቶ፣ ገና ሳምንት ሳይሞላኝ አዲሱ ቤት ዕድሜ ልኬን የኖርኩበት አሮጌ ዋሻ መስሎ ተሰማኝ"(©አልተዛወረችም ገጽ-54) የአልተዛወረችም መቼት ቀለል ያለና ተለምዷዊ ነው። ደምሥራ ሳይቀር ውበት የሞላባት ማህደር ከንፈሯ የማደንስበት ካፍቴሪያ እንዲሁም የአብርሃም ቤት የልብ ወለዱ ተለምቶሻዊ መቼና የቶች ናቸው።

መ. Causality built into text

የሠው ልጅ የኅላዌ ጣጣ አያበቃም⁴ ከዚህም አልፍ በጥላ(shadowed) ውስጥ ተደብቀው የሚገኙ ግን የሰውን ዘለለት ያበራያሉ⁵ ወይም ያፈካሉ ይሄንን መመርመር የሥነ-ጽሑፍ በተለይም የእውናዊ አጻጻፍ ይትብሃል መገለጫው ነው። "ባሌ ዕረፍቱን ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሊመለስ ሲዘጋጅ፣ በመለያዬታችን እንደ ሴት ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።"(©አልተዛወረችም ገጽ-68) ማህደር የአብርሃምን የዕድሞ⁶ ጫፍ ጣቱ ሲነካው ተራኪው አብርሃም የነፍሱ ጫፍ ላይ ሲደርስ መልኳን ተመልክቶ ብቻ ለመኖር ሲጓጓ የኦሄነሪን "The last leaf" ያስታውሰናል። ኦ ሄነሪ ጆንሲን ገጸ ባህሪ አድርጎ በተረከው ትረካ ጆንሲ የሚረግፉ ቅጠሎችን ስታይ የመኖር ነገሯ እየጠወለገ ሲመጣ መጨረሻ ቅጠል ቀረች እሱን እያየች መኖር ቀጠለች ይሄንን ሥዕል ሲስል የነበረው በህርማን በበሽታ ይሞታል። የማህደር የሕልሟ መክሰምና የልጅነት ትራውማ(ሽብር) የአገር እንደ ጀንበር መንጋደድ የተደበቁ የሁላችንም ጥላ ታሪኮች የዛሬ አካላችንን የሠሩ ናቸው። አሌክስ ይሄንን በደንብ ተርኮልናል።

ሠ.ፍልስፍና (Emphasis on morality)

ማህበራዊነት ፍልስፍናና ፍልሱፋን የተብሰከሰኩበት የፍልስፍና ዐይነት ነው። እውናዊ አሳቢያን ደግሞ ለሥነ ምግባር አጽንዖት ሲሰጡ ውስጣዊ አንጻራዊ ነው። ይላሉ ሆኖም ይህ አስተሳሰብ ማሕበረሰብን በደገኛ ይሰራል። እውናዊ ሥነ ጽሑፍ ውስጥ ያሉ ገጸ-ባህሪዎች መዳረሻቸውን ጨብጠው ማህበረ-ከባቢውን ያሳዩናል። ነገር ግን ልብ ወለዱ ሲያልቅ ለአፍቃሬ አንባቢው ሐሳቡም፣ ስሜቱም፣ እውነቱም፣ እምነቱም፣ ክፍት ነው። "ትንሽ ሐውልት ውለታቸው ባረፈበት ሰው ልብ ቢቀር ምኑ ነው ክፋቱ!?" (©አልተዛወረችም ገጽ-239)

ማጠቃለያ

ይኽ የአሌክስ የመጀመሪያ የረጅም ልብ ወለድ ሥራው ነው። እውናዊ አጻጻፍ ይትብሃል(Realism Literature) በአልተዛወረችም ልብ ወለድ ውስጥ እንዴት ስላለው ተጽኖ የተሰማኝ ይህ ነው። ሌሎች የሥነ-አዕምሮ፣ የፍልስፍና፣ የሥነ-ጽሑፍ ሰዎችም ልብ ወለዱን ወደራሳችሁ ቤት ብትጋብዙት እላለሁ!

የሕዳግ ማስታወሻዎች

1.Dannyachew Worku in "Black Lion" -An Overview By Sebhat G/Egziabher p.2

2.ከፀሐይ በታች አዲስ ነገር የለም እንዲል መጽሐፉ የሥነ-ጽሑፍ ሰው የሚታወቅን እንደማይታወቅ የማይታወቅን ደግሞ እንዲታወቅ አድርጎ መጻፍ እንዳለበት ይላል ደራሲ ሳሙኤል ጆንሰን

3.Themes are less obvious Indira Gandhi National Open University American Drama P.128

4.ኀያሲ ዓብደላ እዝራ

5.why something happens foreshadowed Foreshadowing in everyday

1 year ago

ክረምት ነበር ፥ ርጥብ ዝናብ ከንፋስ ጋራ
(ከላይ ወረደ ፥ አወናወነኝ¹ ሊጥለኝ)
'ርቃን ገላዬ ቀለም የነካካው ጣቴ
ጸጉርሽን ሊጎትት፥ ሲጥር
(ገለሽ ከምስሉ አመለጠኝ)
"ትንሽ አመመኝ
ለምን? ሰዓሊ ነኝ"
ውሽንፍር ዝናቡ ዓይኔን እየጠበሰው
አማልዕክት-መሳይ ገላሽን ለመሳል
(ስታገል ዓይንሽ ዓይኔን እየፈጀው)
ምስልሽን ለመስራት ታገልኩኝ
በክረምት ታገልኩኝ በበጋ
(እየመሸ ነጋ)
ይሄ ሁሉ መጣር ይሄ ሁሉ መጋር
አንቺን ለመሳል ነው?
(አይደለም አይደለም)
ሥዕልሽ ያደርሳል ከሕይወት ዳር²
(እውነት)
(እውነት)
(እውነት)

  1. መወዛወዝ፣ መንገዳገድ፣ ወደግራ ወደቀኝ ማለት
  2. ዝመዳ In The Midst Of Winter Albert Camu
1 year ago

ከአዳማ ወደ ድሬ ዳዋ የሚወስድ መኪና ውስጥ ... ላብ ካቸፈቸፈበት አየር ስር አንዲት ሴት ተቀምጣለች ። ጸጉሯ ተበታትኑዋል። ፊቷ ላይ ማዲያት ጥላውን ጥሏል። ለንቦጩን የጣለው መኪና የሁሉንም ጩኸት አፍኖ ይዟል። ከሁሉም ሰዎች ይቺ ሴት ደመቅ ብላ ትታያለች ። በዛለ ክንዷ ሮዛ የሚል መጽሐፍ ይዛ : በመጽሐፉ መሃል ጠቋሚ ጣቷን ከታ መጽሐፉን ቆልፋዋለች ። ከውልደት እስከ አሁን ያለው ኅዘኗ አካሏን ሰርቷል ? ...2

ሳን ሚጉኤል የጻፈውን 'voices from silence' ን እየባከንሁበት : የልብ - መልኳን እያሰስሁበት : የሴቲቷን አይኖች ለማዬት ቀናሁ ። ታሪክ ድጋሚ ተፈጠረ ። የሰው ቀለሙ በቀን : አካሉም በፀሐይ ይሳላል ። የተናገርነው ጭምር የቃላት ቀለም ነው ። እነዚህ ናፍቆት ይሆናሉ ። አንዳንዴ ቢጫ ጥላ አያጠላም ። ተስፋ ማጣት : ተስፋ አለማዬት---ሕይወት--- ሳይወድ በግዱ ሰው ፈሳሽ ጨለማውን ተግቶ ያጋሳል ። ጥጋብ አይደለም---።

"የት ነው የምትሄደው?"

"ጨለንቆ ! አንቺስ?"

"ድሬ ዳዋ" መርጋት ተደላድሏል በድምጿ ::

"ለሥራ ነው?"

"አዎ ! አንቺስ ?''

"እኔም"

"ምን ትሰሪያለሽ ?"

ዝም .....

መኪናው በፍጥነት ይጓዛል ። መኪና ውስጥ ባሉ ሰዎች ሕመም ተደብቋል ። በወና ህዋ የተንሳፈፉ ቀለማት አርፈውባቸዋል ። በአበባና በአበባ መካከል እንዳለ ፈገግታ ፈገግ ብላ ጥርሷን ገለጠች ።በእርግጥም የስዕልን ርቃቄ ነች ።----

"ምንድነው? የምታነበው?"

"ሳን ሚጉኤልን ታውቂዋለሽ?"

" የሚወራለት ንባብ የለኝም :: አንድ ...አንድ ...ከሁለት አይበልጡም ያነበብኋቸው ። ምን ፃፈ ያንተስ ሰውዬ ?"

"ስለ አርጀንቲናዎች የጻፈው ነው።" ነገር በእንጥልጥል ...

ከንፈሮቿን በአይኔ ሰሳምኩ ...

''ሮዛ ደስ ይለኛል ። ይሄ መጽሐፍ ብዙ ጣእሞች አሉበት ። ቡዙ እጆች ፣ ብዙ ገላዎች ፣ ተነክተውበታል ። አፎች ተጣመዋል ። ድምጾች ሰልለው ፣ ጸጉሮች ጸጥ : ጭጭ : ረጭ : ብለውበታል። ብዙ ሕመሞች ...! ትራስ ላይ ተንሰቅስቀው ፣ ሲያለቅሱም ፡ ሳያለቅሱም ፡ ሳግ ፡ ሲያንቃቸው ጭምር አይበታለሁ... ። አንዳንዴኮ... አንዳንድ አካሎችም : አእምሮ ላይ እንደ በረዶ ይረጋሉ ። ደስ አይልም ? አንዳንድ አካሎች ደግሞ በሌላ ይሰንፋሉ ። ሲያስጠላ ! ይሄ ፍቅር ። የሰው ልጅ ተጫውቶ የሚሸነፍበት ካርታ ። ጦር ያለው ። የሚዋጋ ። የሚያቃጥል ...''3

"ካነበብሁት ቆዬሁ ። በለኮስሽኝ ... እስካልበርድ : እስካልረግብ : በትውስታ ምሪት እንደ አጥቢያ ኮከብ እንዳልበርቅ ፈራሁ ። ሃሃሃ ... "

'' ጥሩ ታወራለህ ። ድምፅህ መግራት አለው ።''

'' መኖርን አታስመስግኝኝ ! ''
.
.
.

ለፀሐይ እንደተተወ ውጥር ቆዳ : የሁሉም ሰው ፊት ሲቃጠል : ዜማም : ግጥምም : እንደ ሌለው ሙዚቃ ነገሮች ዝም ሲሉ : ብልቶች እንቅስቃሴ ሲያቆሙ----- ልቦች በልቦች ሲጎዱ : ቀጭን ሰይጣን ግንባሩ ላይ በለኮሳት እሳት ሲነድ----- በመጽሐፍ መልካ - መልክ ላይ ተዘበራርቆ ተደርሷል። ስለ ቀለም : ማንም... ስለሌላቸው ነፍሶች : ተወግረው እንደጎበጡ አካሎች : እንደተዘበራረቀው ተፈጥሮ : መኪናው ጥሎ እንዳለፋቸው የትላንት መንገዶች : እንዳልተከፈተ ሙዚቃ : ቅላጼ እንደሌለው ሕመም : በውስጥ እንደሚመላለስ : የሚንሴጠሰጥ ጩኸተ - ራስ : የማይያዝ : የማይጨበጥ : የማይደረስበት : የራቀ : በጣቶቼ ልጨብጠው ስል ...ሲያዳልጠኝ : በቃ! በቃ ! ይሄም ...ትንሽ ትንሽ ያማል።''---4

"የት ደረስን?"

"አዋሽ 40"

ካንቀላፉ ትላንቶች ቅዠት ...ቀለም ሲውለበለብ...! ረጋ ካለ የአዋሽ ተንሳፋፊ ሐይቅ : ሙቀት የሚያነጥባቸው ላቦች... በገላ : በገጻችን ሲሰፉ : በቃ! ----አይኗ ተስለመለመ ። ቅንድቧ ስር ላብ አቸፈ---።

"እምልሽ ለምን ሮዛን ወደድሽ ?"

"እኔ እንጃ ! ምናልባት ታሪኬን ስለሚነግረኝ ?።"

" ብዙ ኖርሽለት ለሃዘን ? ተጎናበስሽለት ለደስታ ?"

ምኑ ይነገራል ብለህ ?

እዚህ ጥያቄ ምልክት ላይ! ብዙ አዳፋ ታሪኮች አሉ ። ቢጻፉ የማይጠሩ ። ሸፋፋነታቸው በጫማ የማይሸፈን ። መንገድ የጠፋባቸው የታሪክ እግሮች : አቅጣጫ የሌላቸው : ቀለም የሌላቸው : ስሜት የሌላቸው : ብዙ ምንም የለሾች -----ያልተሞሸሩ ሕመሞች : ማንም ያልካደመላቸው : የበለዘ ወዝ : ጠረን የሌለው ሰመመን : ምጽአት የራቀው በድን : በአይን ቆብ ተጠቅልሎ ያሸለበ አይን : በጨረር የተጠቀጠቀ አይን ... ለህመሟ ስታሸልብ እያያሁዋት ...! ---- ከተከፈተው ጭኗ ጠባሳዋን ማዬት : ለአዋሽ እንደ ገባር የገባ ዕንባዋን ማለቂያውን ማዬት ፈለግሁ ። ኦ ! አንተ አላህ ። ኦ ! ያንተ ያለህ ...።

ከታሪኳ : ከነካካችው ገላዋ : ከነኳት ገላዎች : የሚነሱ ታሪኮች ታሪክ ለመሆን ሲጣጣሩ : ሲጥሩ : ሲፈጉ : ዝም ብለው ዝም አስባሏት ። የወገገ ታሪኳን ሲያርመጠምጡት : በጣታቸው ሲያጨማልቁት---- የማያውቋት : የማታቃቸው : ደሟን : ደም ግባቷን : ከደምስሯ ሰርገው ሲጠቡት : አያውቁ ይሄን መከራ---- አያውቁ ይህንን ሕይወት ---- ልስልስ ሞትና ---ከራስ መለየት ነው የሕይወት ኋላና ፊቷ ።

"እኔ እምልሽ ድሬ ዳዋ ለምን ነው ምትሄጅው!"

"ቁልቢ ነኝ"

" ኧረ ? ዘመድ ጥዬቃ ? ወይስ... ?"

" አይ ! ለንግስ... ስዕለት አለብኝ ። ዘቢብ መልኬን : ፀጋ ወዜን አደርሳለሁ ። "

" ስለ ቀደስሻት ቀኔ : ሌሊቶቼን ሰዉቼ እጎናበስልሻለሁ ። ሃሌታን እወጣልሽም ዘንድ አስብሻለሁ ። ''

'' ሃዘን ተቃመስን አይደል ? በደስታህ በኩል ተጋደምኩ ?''

'' የዕንባ መና የሕይወት ችሮታም ነው :: ''

ከተሳፈርኩበት ወረድኩ :: የሳን ሚጎኤልን መጽሐፍ ጨርሼ እጄላይ ተዝረክርኳል :: ጨረቃ ... ከርቀት ተቀበለችኝ ። ባለንጀራዬ ከሩቅ ጨረቃዋን ቀድሟት ይመጣል። የምናየው የማይታየውን ቀለም ነው ? የምናየው የኛ ቀለም ነጸብራቁ አይናችን እንዳልሆነስ ? የደም ዝውውራችን የተደበቀ ሌላ ቀይ ቀለም ይሰጣል ። የኖርነው ዛሬ : የዛሬ ቀለም ነው ። የናፍቆት ቀለሙ - መለያዬት ነው ? የተለዬኋትን ? የተነጠልኳቸውን አሰብሁ ።

ዞር ብዬ መኪናውን አየሁት ። የተጫነበት ሃሳብ እንደሚያንገዳግደው : ወደ ቀኙ : ወደ ግራው እንደሚያስዘምመው ይሆናል ::

1.The color introduced by daylight ግጥም ፓሬ
2.ግራ ገብ በሆነ ዓለም አንዳንዴ ክምችት(restኸ mass) በሐዘን ሊፈጠር ይችላል አካልም
3. እንቅልፍ አሸለብ አረጋት የሚዘንበው የኃዘን ዝናብ ቆመ
4.የመንገድ ኃሳቦቸ
6.የሚቀጥ[...]

1 year ago

የውስጥ ቀለሞች ...
:

ቀና አለ ። ግራጫው ሰማይ ላይ የተሰመሩት ወፎች ቁልቁል : ወደ ታች : ይወርዳሉ ። ዝቅ ሲል ...ከከንፈሩ የሚያፈተልከው የሲጋራ ጢስ ፊቱ ላይ ብን : ብን : ይላል ። አእምሮው ውስጥ ቀይ - ቢጫ - ነጭ - ቀለሞች ተፈጥረዋል:: -----1

1 year, 1 month ago

ከልብ ወለድ ባሻገር ባሻገር
”ሀገር ያጣ ሞት ሂሳዊ” ንባብ
ክፍል አንድ
ሳሙኤል በለጠ
አለመታደል ሆነና አንዱን ዘመን ሳናጣጥም ወደ አንዱ አዘመምን ልብ ወለዳችን ዘመናዊ ሆን ስንል ዮሃንስ አድማሱ ዘመናዊ ልብ ወለዳችን በጣት የሚቆጠሩ እንደሆኑ ነገሩን እንዲህ እንዲህ እያልን በገድምዳሜው ድህረ ዘመናዊ ድርሰቶች ላይ ደረስን ነገሩ እንዲህ ነው። ድህረ ዘመናዊ ድርሰት በሥነ ግጥሙ እነ ሰለሞን ደሬሳና ሌሎችም በድርሰቱ አዳም ረታ ከተዋወቀ ወዲህ መልኩንና ቅርጹን እየቀያየረ አሁን ላይ የደረሰ ሲሆን የአጻጻፍ ይትብሃሉን ወጣት ደራሲያንም እያዘወተሩት መጡ በቅርብ አመታት ለንባብ ከበቁ መጽሃፍቶች ድህረ ዘመናዊ የድርሰት አጻጻፍ ይትብሃልን የደገበረው የሄኖክ በቀለ ለማ ”ሀገር ያጣ ሞት” አንዱ ነው።
ለመሆኑ ድህረ ዘመናዊ ድርሰት ምንድነው? ከዘመናዊ ድርሰትስ የሚለየወ ጠባዩ ምንድነው? የሥነ ጽሁፍ ሃያሲው ሺቫ ኪርካህ ”Alienation and Loneliness of American Postmodern Characters in Salinger’s Masterpiece Catcher in The Rye” በሚለው የጥናቱ መግቢያ ላይ እንዲህ ይላል ”The postmodern texts reveal skepticism about the ability of art to create meaning, the ability of history to reveal truth, and the ability of language to convey reality. All that skepticism led to fragmented, open-ended, self-reflexive stories that are intellectually fascinating but often difficult to grasp. The stylistic techniques of postmodernism include the frequent use of intersexuality, Metafiction, temporal distortion, magical realism, faction, reader involvement and minimalist techniques of reduction, omission and suggestion.” ድህረ ዘመናዊ አጻጻፍ በእነዚህ ጠባዮች ከዘመናዊ አጻጻፍ ተቃርኖ የቆመ እንደሆነ ይነግረናል። ሳሙኤል ቤኬት፣ ኩርት ቮኔጉት፣ ጆን ባርት፣ ሳልማን ሩሽዲና ሌሎች ድህረ ዘመናዊ የድርሰት አጻጻፍ ይትብሃል የሚከተሉ ደራሲዎች ናቸው ይላል።
የሄኖክ በቀለ ለማ ”ሀገር ያጣ ሞት” ከላይ ሃያሲ ሺቫ ኪርካህ የገለጸውን የድህረ ዘመናዊ የአጻጻፍ ይትበሃል መለያ ጠባይ ያለው መሆኑን እንረዳለን magical realism - አስማታዊ እውነታ የሄኖክ በቀለ ለማ በእያንዳንዶቹ ገጸ ባህሪያት እንዲሁም Self-reflexive Stories - የራስ ልዋጤ ታሪኮች አስማታዊ እውነታዎችን ይነግረናል። የህላዌ ስንክሳርን ለመፈከር ይጠይቃል ፍቅር፣ ክህደት፥ ወሲብና መቀማማት፥ ፀፀትና መስዋዕት፥ የትዝታ፣ ሞት፣ ህይወት ተስፋን መቀማት፣ በገጸ ባህሪዎቹ በዱና፣ በሊቀ መኩዋስ፣ በጸሎት በስዕለ፣ የተተወሩ - Plot- በጊዜ ውስጥ የተሰነጉ የተፈቱ፣ ያልተፈቱ፣ የሚያስቃትቱ፣ የሚያስነቡ የሚመስጡ የህላዌ ስንክሳር ናቸው። -Reader involvement- አፍቃሬ አንባቢን ማሳተፍ የድህረ ዘመናዊ የአጻጻፍ ይትብሃል አንዱ መንገድ ነው። ”ሳቁን ተሻምቼ አልጽፍለትም። ታዲያ ዛሬ በምን እዳው? እንደልጆቹ በቻለው ቋንቋ አፍ ላስፈታው። ከዛስ? ነፍስ እስከፈቀደ ይጨመርለታላ ይህ እንዲህ በሚያልፍ ዛሬ ላይ የተቃጣ ቅናት ነው። የቃል ፍቅር እዳው ምን ድረስ ነው?” (ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 200) ሄኖክ በቀለ ለማ በድርሰቱ በእያንዳንዱ መሥመር የአንባቢን ምናብ እየፈተነ ያሳትፋል። በእነዚህና መሌሎች መስፈርቶች ”ሀገር ያጣ ሞት” ድህረ ዘመናዊ ድርሰት ነው ማለት እንችላለን።
”ሰማይ በደመና ጭረት ፊቱ ተዥጎርጉሮ በዋለበት፤ የልጅገረድ ቅንድብ በመሰች ጭረት ጨረቃ በተኩዋለበት፤ በክዋክብት ውቅራት ስግግ ገላውን ባቀፈበት፤ የምድር ብሌን በስልችት ቁልቁል ካፈጠጠበት፤ የሀገር ሰው ሰነፍ ቆሎውን እያሻመደ ኩታውን እየተከናነበ የመከኑ ሕልሞቼን በሚከልስበት፤ ከጣሪያው ሥር ጥላሸትና ጠረን የጠገበ መረባ የተተከሉትን አይኖች በሚጠየፍበት፤ ግዑዛን አፋቸውን በምጥን ሃሌታ በሚፈቱበት፤ ወጣት ለቂሙ መቁዋጫ ቀጠሮ መሚቀጥርበት፤ የሃዋዝ መሰንቆ ሳይታለብ.....”(ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 10) ሁሉም የድህረ ዘመናዊ ሃያሲዎች እኔም የምስማማበት አንድ ነገር አለ ለድህረ ዘመናዊ ድርሰት የቋንቋ አጠቃቀም ቅጥ ራሱን ችሎ ገጸ ባህሪ ይሆናል። (the language style has become a characteristic of the novel) ሄኖክ ይህንን በድርሰት የሞከረ ብርቱ ደራሲ ነው።
”ባለ መሰንቆውን ሐዋዝ ተጫወት ቢሉት....
”ሞት ይቅርይላሉ ሞት ቢቀር አልወድም
ድንጋዩም አፈሩም ከሰው ፊት አይከብድም”ብሎ ነው። አይንህን ያሳየኝ ያሉት።
”ይሄ ምላስህ አንድ ቀን ይጠልፍሃል። የለፈለፍከው እርጥብ ገመድ ሆኖ ያንቅሃል” ብለውት መርቀውታል።(ሀገር ያጣ ሞት ገጽ - 39) ሥነ ጽሁፍ ከተለያዩ የህይወት የህይወት ህላዌ ጥያቄዎች ጋር ትስስር ይፈጥራል የሥነጽሁፍ ዳርዊኒዝም ሊቁ ጆሴፍ ካሮል ”literature deals with death in relation to three specifc themes in human life history: imminent threats to survival, childhood, and pair bonding” የሚል አጽኖት አለው ሥነ ጽሁፍ ከተለያዩ የህላዌ ጣጣዎች ጋር አጣምሮ መጻፍ ለጽሁፍ ፍካሬም ውበትም አውንታዊ ተጽኖ አለው ”ሀገር ያጣ ሞት” በጽሞና ላነበበው የሊቀ መኩዋስንና የሐዋዝን ነገረ ሞት ብቻ ሳይሆን የተዋቡን መቃተት በራስ ለዋጤ ታሪኮች የሚነገሩ ታሪኮች ውስጥ ሀገር የሚያህል የህላዌ ጣጣና ጥያቄ ያገኛል።
ታላቁ ዕዝራ አብደላ እንደሚለው ደግሞ ”በአንድምታ የተለበለብ የቋንቋ ትርታና ንዝረት ነው።” ሄኖክ ገጸ ባህሪን፣ ከህላዌ ጣጣ የህላዌ ጣጣን ከሃሳብ ሃሳብን ከ ግዜ ጋር ጊዜን ከሃገር ጋር አገርን ከህልውና ጋር አሹዋርቦ ነው የጻፈው ይች አገር ግን ሞቱን አልተቀበለችውም ወለፈንዳድ ህላዌአችንን ያሳያል በዕውቀቱ በአንድ ግጥሙ እንዳለው ”መንሳፈፉስ ይቅር እንዴት መስጠም ያቅተዋል ሰው?” ይህ የባይተዋር ገድላችን ነው መሰል ሄኖክ ይሄን ሁሉ አጣምሮ አንድ ተስማሚ አጽኖት ሳልሰጠው ባልፍ ትውልድ ይቅር አይለኝም ሂሴም ውሃ አያነሳም ብዙ ቲዎሪዎች ያሉትና የሥነጽሁፍ ሃያሲው ብራያን ማከል ”POSTMODERNIST FICTION” በሚለው መጽሃፉ ዋቢ ያደረገውን ሃሳብ ላንሳ ልሰናበት ”The skeleton of the layers and the structural order of sequence a literary work of art are of neutral artistic value; they form the axiologically neutral foundation of the work of art in which the artistically valent elements…of the work are grounded”
ክፍል ሁለት ይቀጥላል።

1 year, 1 month ago

የመጨረሻው ናፍቆት

ካይኔ ዋሻ ተደብቄ ፣ ከል ሳለቅስ
የህጻንነቴን እርጥብ ዝምታ...
በመናፈቅ ባሁን መዳፍ ፣ ስደባብስ
ካይኔ ዋሻ እንዳለሁ
ነፍሴን እጠይቃለሁ?
ናፍቆት ትንሳኤ አለው?
“የናፍቆትን ክራር
በጣትህ ብቃኘው
ይጠዘጥዛል እንጂ
ዜማ አይሆንም ምነው?”

ጌታሆይ
በሰማዬ ላይ ያንዣበበው ፣ እዥ የደመና ቁስል
በጽሃይህ አታጥገው ፣ ላንተ ናፍቆት መቃጥያ ይሆነኛል።
ካሻት ህጻን ማለዳ ፣ የብርሃን ልሃጭ አትትፋ
የጽሃይም እግር ይሰበር ፣ ተስፋም ከማዕከሉ ይጥፋ።

ጌታሆይ
ናፍቆቴን መናገር ፣ ሞት ይወልዳል
የህጻንነቴን ለጋ ዝምታ ፣ መልስልኝ
የናፍቆቴ ትንሳኤ ፣ እሱ ይሆናል
ማን ያውቃል?

1 year, 2 months ago

የአንዲት ሴት መከራ የወሲብ ቅድስናን ፍለጋ
?? ?????? ?? ?????? ????????
ሰው ለመከራ ነው የተፈጠረው የሚለው የነቪክቶር ሁግ አባባላዊ አጽንኦት አንዳንዴ ዋጋውን ያጣል ለምሳሌ የነቪክቶር ሁግ ሌስሚዘረብል ልብወለድ ላይ ፈንቲ ከጎረቤት እንዴት ያለስራ መኖር እንዳለባት ትማራለች፣ መከራ ሲቀጥል እንዴት ያለ ምግብ መኖር እንዳለባት ልትማር ትችላለች እነዚህ ሁሉ የመከራ ምሳሌዋች ትክክለኛ መከራን ለመፈከር አይሆኑም መከራ የሚመዘነው በሆነብን ነገር ክብደት ላይሆን በስሜቱ ጥልቀት ነው። ፓብሎ ኮሄልዮ “Eleven Minutes” የሚል ዝነኛ መጽሃፍ አለው እሲ ይህን መጽሃፍ እንዳሰው መጽሃፉ በብዙ ሺህ ኮፒዎች ከመታተም በላይ አልፎ በበርካታ ትርጉም ተሰርቶለታል።
እውቁ ሃያሲ ናስረላህ ናምቦሮል ከአመታት በፊት በመጽሃፉ ዙሪያ በሰራው ሂስ “ይህ ልብ ወለድ ውሎ አድሮ እውነተኛ ፍቅር ያገኘች ይህንን ለማግኘት ብዙ መስዋዕትነት የከፈለች የአንዲት ወጣት የዝሙት አዳሪነት ታሪክ ነው። ታሪኩን ስንገልጠው የወሲብ ቅድስናን ጭብጥ ላይ ያጠነጥናል። ለቁሳዊ ጥቅም ሲባል ወሲብ ርኩስ መሆኑን ያስገነዝባል፣ የወሲብ ጥምረት ወደ ቅዱስ ድርጊት የሚል አንደምታንም እናገኛለን” የሚል ምስክርነት ስለ መጽሃፉ ይሰጣል።
ደራሲው ለመጽሃፉ ካራክተር ያረጋት አንዲት ብራሊላዊት ሴት ሲሆን ማርያ ትባላለች ማርያ በወሲብ ንግድ ውስጥ የሰራች፣ የተሰደደችም ጭምር መከረኛ ናት እኔ ያለኝ የእንግሊዘኛው ቅጂ ላይ የማርያ የእለት እለት ባስታወሻዎች ከጀርባው አሉበት ኮሄሎ ታሪኩን ሲጀምር በአንድ ወቅት በአንድ ከተማ የምትኖር አንዲት ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች ይነግረናል ታሪኩ ለማመን የሚቸግር በመሆኑ ተጨባጭ ለማድረግ ሲጥር ደራሲው ከፍተኛ ሥነ ውበት ያለው የአጻጻፍ ይትብሃልን ይጠቀማል። ማሪያ ፍቅር ለማግኘት ያደረገችውን ጥረትና ስቃይ በደንብ ይተረካል። ማርያ የልጅነት ሽብር ወይም ትራውማ አለባት በዚህም ሰበብ የህልውና ስቃይ ውስጥ ገብታለች ገንዘብን ፍቅርን በየዳንኪራ ቤት ስትፈልግ የነበረችው ማርያ ያሳለፈችው መከራ ቀላል የሚባል አልነበረም።
የዕለት እለት ማስታወሻዋን ያነበበ አንባቢ ደራሲው በዘይቤ የካራክተሩዋን ፍለጋ ለማወቅ ይረዳል። ሁዋላ ላይ ይችው ገጽ ባህሪ “an adventurer in search of treasure,” ትሆናለች ፍለጋዋ አበቃ የፈለገችውን ፍቅርና አፍቃሪ አገኘች በመንገዶቹዋ ብዙ የፍትወት እግሮች ተራምደዋል። ረካች ረኩባት? ግድ ሊሰጣትም ላይሰጣትም ይችላል እያንዳንዱ ነገር ቅድስናም ርኩሰትም አለው በህይወት አጋጣሚ ማርያ የፍቅርንና የወሲብን ቅድስና በመከራ ውስጥ ፈልጋነው ያገኘችው የመከራ መዳፍ ቅድሳን ፈልቀቀች ሃያሲያን ማሪያን አልኬሚስት ላይ እንዳለው ሳንቲያጎ ጀብደኛ ናት ይላሉ የወሲብንም የፍቅርንም ቅድስና ከመከራ አውጥላለችና መከራ ይቅጥላል ከመከራው ሊመለክ የሚችል አንድ ቅዱስ ነገር አንድ ቀን ይወጣል። እዚሁ መጽሃፍ ላይ እንዲህ ብላለች “When I had nothing to lose When I stopped being who I am, I found myself.” መከራ ወደ ቅድስና መውጫ መሰላል የሚሆንበት አጋጣሚ በየታሪኩ ቢፈለግ ታሪክ ይጠፋል?