ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
«ወደ ጥንታዊያን አበው
ሐይማኖት እንመለስ »
-------
"ንግባእኬ ኀበ ሃይማኖተ
አበዊነ ጥንታውያን።"
ትምህርተ ሥላሴና የቤተክርስቲያን ታሪክ
ረዘም ባለ ዝግጅ የተዘጋጀ ነው(የ1ሰዓት ከ25 ደቂቃ ትምህርት) ገብታችሁ ኮምኩሙ እንግዲህ😁
👉https://youtu.be/lQ84Tf3OGag?si=2nXrA5AARiP4QYXF
በቪዲዮ ላይ የተዳሰሱት፦
ቃሉን ለምን? ፣ ምሥጢር ማለትስ?
የቤተክርስቲያን አባቶች? ፣ ኒቂያ ጉባኤ?
እና ሌሎችም.... ሼር አድርጓት።
ታንቆ ወይስ ተሰቅሎ?
ሙስሊም ወገኖች ኢየሱስ አልተሰቀለም በማለት ሲሞግቱ ይስተዋላል። ነገር ግን እንደ ፓሪሽ ሳንደርስ የመሳሰሉ ሙህራን የክርስቶስን ታሪክ ዙሪያ ገባውን ሁሉ ካጠና በኋላ <<ጥርጣሬ አልቦ ወይም የማይካዱ ሐቆች>> ብሎ ከዘረዘራቸው 8 ነጥቦች መካከል አንደኛው የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሞት እንደሆነ ይገልጽልናል[1]። ጆን ዶሚኒክ ክሮሳን የተባለው ምሁር ደግሞ በጴንጤናዊው ጲላጦስ ዘመን የክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት ታሪክ እንደ ማንኛውም እውናዊ ታሪካዊ ክስተት እርግጠኛ የምንሆንበት ክስተት እንደሆነ ይነግረናል[2]። በነገረ መለኮት ትንታኔውና በምንባባዌ ህያሴው የሚታወቀው ስመጥሩ ኤቲስቱ ባርት ኧርማን የክርስቶስ ሞትን በተመለከተ በመጽሐፉም ሆነ በቃለ መጠይቆቹ ሞቱ እውነተኛ ታሪካዊ ሀቅ መሆኑን ይናገራል(ከአፖስቴት ፕሮፌት ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ መመለልከት ያሻል)[3]። ነገር ግን የሀገራችን ሙስሊም አቃቤያን በእነ አህመድ ዲዳት እና መሰሎቻቸው ሙግት እስከዛሬ ሲሞግቱ ይስተውላል። አንድ አብዱል እንዲህ ሲል ይጽፋል፦
አብዱል፦
" እናንተ በእንጨት ላይ ሰቅላችሁ የገደላችሁትን ኢየሱስን የአባቶቻችን አምላክ አስነሣው፤" (የሐዋርያት ሥራ 5: 30)
የአማርኛ ተርጓሚዎች ይህንን የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ሲተረጉሙ በአማኙ ላይ ማታለያ ፈፅመዋል። የእንግሊዝኛውም ሆነ የግሪኩ ቃል "ሰቅላችሁ" አይልም። ይልቅስ የሚለው "አንቃችሁ" ወይንም "Hanged" አልያም በግሪከኛው "κρεμάννυμι" ነው። ለማስረጃነት ከታች ሁለቱንም ትርጉሞች አስቀምጥላችኃለው።"
መልስ
በመጀመሪያ ደረጃ፣ "ታንቆ መሞት" ለሚለው ቃል የምንጠቀመው የጽርዕ(የግሪክ) ቃል κρεμάννυμι(ክሬማኑሚ) ሳይሆን ἀπάγχω (አፓግኾ) ነው። ለምሳሌ ስለ ይሁዳ ሲያወራ:-
" ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና #ታንቆ ሞተ።" የማቴዎስ ወንጌል 27:5
καὶ ῥίψας τὰ ἀργύρια εἰς τὸν ναὸν ἀνεχώρησεν, καὶ ἀπελθὼν #ἀπήγξατο.(አፔግሳቶ) የሚለውን ይጠቀማል።
ነገር ግን κρεμάννυμι/ክሬማኑሚ የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም አለው። መስቀል(ለምሳሌ፦ ጃኬቴን እንጨቱ ላይ ሰቀልኩት ማለት ከፈለግኩ በጽርዕ(በግሪክ) ይህን ቃል ነው የምጠቀመው(ጃኬቴን እንጨት ላይ አነቅኩት አይባልም) ምናልባት ሙስሊሙ ወዳጄ ጃኬቴን አነኩት ይለን ይኾን?
ሌላው ኢየሱስም የተሰቀለው እንጨት ላይ ተንጠልጥሎ ነው(κρεμάννυμι) እንጂ እንጨት ላይ እንደ አልጋ ተኝቶ አይደለም። ለዛ ነው ይህን ቃል የተጠቀመው። ስለዚህ κρεμάννυμι "depend" (የተመረኮዘ) (hangs on) የሚል ትርጉምም ሊሰጠን ይችላል።
ይሄንንም በምሳሌ ስንመለከተው፦
" በእነዚህ በሁለቱ ትእዛዛት ሕጉም ሁሉ ነቢያትም ተሰቅለዋል(κρέμαται/ክሬማታይ)።"
"40 On these two commandments the whole law #hangeth(depends), and the prophets."
(Matthew 22:40)
ስለዚህ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው በእንጨት ላይ ተንጠልጥሎ ስለሆነ(κρεμάννυμι/ክሬማኑሚ) ተብሎ ተነገረ እንጂ እንጨት ላይ እንደ አልጋ ተኝቶ ነው ብለን ስለማናምን ግዴታ አነቀው ማለት አይቻልም። ለዚህም ነው ይህን የጽርዕ ቃል የተጠቀመው። ስለዚህ κρεμάννυμι/ክሬማኑሚ "depend" በአማርኛው የተመረኮዘ(hangs on) የሚል ትርጉምም ሊሰጠን ይችላል።
በመጨረሻም ሙስሊም ወገኖቼ ይሄን አይነቱን ተራና ለሙግት የማይቀርብን ሙግት እየቀዳችሁ ባታቀርቡና ለእውነተኛው ጌታ ኢየሱስ ነብሳችሁን አሳልፋችሁ ብትሰጡ እያልን እንዘጋለን።
ማጣቀሻዎች
[1] E.P Sanders, Jesus & Judaism, p.11
[2] John Dominic Crossan, Jesus:A Revolutionary Biography, p.145
ይህም ልዩነት ቤተ ክርስቲያንን የከዱት (referred to as the lapsi) የቀደሙት ክርስቲያኖች በአንዱ ጎራ ቢመለሱም ችግር የለውም ሲሉ በአንዱ ጎራ በፍጹም እነዚህ ከሐዲያን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን መመለስ የለባቸውም ብለው ራሳቸውን በአቋመ ተአቅቦ አገለሉ። በተለይም Novatian የተባለ የRoman presbyter የዚህ እንቅስቃሴ ጠንሳሽ ነበር። እሱ እና ተከታዮቹ (Novatianists) ከቤተ ክርስቲያን ራሳቸውን በመለየት የራሳቸውን የእምነት ተቋም መሰረቱ። Novatian በሶስት ጳጳሳት ተሹሞ ራሱን እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን ጳጳስ መሆኑን እንዲታወጅለት አስደረገ። የዛኔ ነው ቅዱስ ቆጵርያኖስ ብዕር እና ብራናውን በማገናኘት የቤተ ክርስቲያን ከፋፋይ ቡድኖች ማለትም Novatianistsቶች ላይ የግሳጼ እና የውግዘት ጡመራ በድርሳኑ ላይ የተገለጠው። የሮሜ ቤተ ክርስቲያንም Novatianistsቶችን መናፍቃን ብላ በመጥራት አዋጅን በሮሜ ባለው synod አሳወጀች። ይህንን ሐሳብ በመደገፍ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሚላኑ ቅዱስ አምብሮስ ተቃውሞውን በNovatianistsቶች ላይ ገልጿል። ወደ ዋናው ነጥባችን ስናልፍ schismatics ራሳቸውን በፈቃዳቸው ከክርስቶስ አካል ቆርጠው ማውጣታቸው ድነታቸውን እንዲሁ መተዋቸውን የሚያሳይ ነው በማለት ይናገራል (በምዕራፍ 5 ላይ ይመልከቱ) እንደ Novatians ያሉ ቅዱስ ቆጵርያኖስ ለቤተክርስቲያኗ አላማ እና ለነፍሳት ድነት አስፈላጊ እንደሆነ የተገነዘበውን የቤተክርስቲያንን ለተመላሾች ምህረትን የማድረግ እና የመስጠት ስልጣንን ክደው የቤተክርስቲያንን አንድነት የአወኩትን ሁሉ መናፍቃን በማለት ይጠራቸዋል። በዚህም ምክንያት ቤተ ክርስቲያንን እናት ያልሆነችላቸው ከፋፋይ ቡድኖች እግዚአብሔርም አባት እንደማይሆንላቸው በምዕራፍ 6 ላይ ሲናገር እንመለከተዋለን። በ3ኛው መቶ ክ/ዘ የአርጌንስ ደቀመዝሙር እንደነበር የሚነገርለት የቂሳርያው ጳጳስ ፊርሚሊያኖስ እነዚህ ከቤተ ክርስቲያን ራሳቸውን የቆረጡ መናፍቃን መንፈስ ቅዱስ የሌላቸው እና ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ጋር ምንም አይነት መንፈሳዊ ግንኙነት እንደማይኖራቸው ይናገራል (Firmilian, Bishop of Caesarea in Cappadocia, to Cyprian, Against the Letter of Stephen, Epistle 74)
ስለዚህ የቅዱስ ቆጵርያኖስ ሐሳብ በቀጥታ ስለ Ecclesiological Exclusivism ወይም salvation is attainable only within the visible bounds of a specific institutional Church እያለ ሳይሆን ድነት ከእውነተኛው፣ ከሐዋርያት አስተምህሮ እና ከቃሉ ባፈነገጠ መልኩ ሊገኝ እንደማይችል እና እነዚህ ሐይሎች ራሳቸውን ሲቆርጡ ከሆነች specific institutional Church ብቻ ሳይሆን በምንፍቅናቸው እና በከፋፋይነታቸው ከክርስቶስ አካልም ራሳቸውን እንዳገለሉ የሚገልጽ ሐሳብ ነው። በዛው ክፍል ላይ ቅዱስ ቆጵርያኖስ ሁሉን አቀፋዊቷ በኖህ መርከብ በተመሰለችው ቤተ ክርስቲያን (mystical assembly) እንኳን እንደማይኖሩ የሚያስረዳ ሐሳብ የያዘ ነው። ስለዚህ የNovatianistsቶች ጥምቀት ሆነ ቅዱስ ቁርባን validity እንደሌለው የሚያሳይ ድርሳን ሁኖ እናገኘዋለን።
ይቀጥላል.......
« ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ድነት የለም/extra Ecclesiam nulla salus »
ድነት ከቤተክርስቲያን ውጭ የለም የሚለውን ሐሳብ ከመመልከታችን በፊት ቤተ ክርስቲያን የሚለውን አገላለጽ መመልከቱ ጥሩ ነው። በAugsburg Confession(Part 11 Articles VII and VIII: Of the Church) ላይ ቸርች የቅዱሳን ስብስብ ወይም ጉባኤ እንደሆነች ይናገራል። ነገር ግን ይቺ ቤተ ክርስቲያን የምትታይ ወይም የማትታይ ልትሆን ትችላለች። የምትታየዋ ቤተክርስቲያን earthly manifest ያደረገች እና የእግዚያብሔር means of grace proclaimed የሚሆንባት እና administered የሆነች ነች። የማትታየዋ ቤተክርስቲያን ግን መንፈሳዊ የሆነች እና በእግዚአብሔር ብቻ የተገለጠች በ denominational lines በgeography ወይም time bound ያልተደረገችም ጭምር ናት። ቃሉ እና ቅዱሳት ምስጢራቶቹ ውጫዊ እና የሚታዩ ስለሆኑ የማትታየዋ ቤተክርስቲያን የምትመሠረትው እና የምትጸናው በምትታየዋ ቤተክርስቲያን ነው። ይህም ደግሞ በሁለቱ ስብስቦች መሐል ያለውን ጥብቅ ትስስር የሚያሳይ ሁኖ እናገኘዋለን። ሉተራኑ ቴዎሎጂያን Johann Gerhard ቤተክርስቲያንን በሁለት አይነት መገለጫዎች ይጠራታል። አንደኛ ሚስጥራዊ ወይም መንፈሳዊ አካል ያላት ወይም corpus mysticum እና ቅልቅላዊ አካል ወይም corpus permixtum በማለት ለሁለት አይነት መደቦች ያስቀምጣታል። የማትታየዋ ቤተክርስቲያን (corpus mysticum) ፍጹማዊት እና ከክርስቶስ ጋር እውነተኛ ህብረት ያላት ስትሆን ምትታየዋ ቤተክርስቲያን (corpus permixtum) ግን የእውነተኛ አማኞች እና የግብዞች (hypocrites) ወይም የከሐዲያን ቅልቅል ልትሆን ትችላለች። ስለዚህ ድነት necessarily በምትታየዋ ቤተክርስቲያን ብቻ አባል በመሆን ነው ማለት አይቻልም። በምትታየዋ ቤተክርስቲያን አባል መሆን ለድነት ዋስትና አይሰጥም። በምትታየዋ ቤተክርስቲያን ሁለቱም አባል ሊሆኑ ይችላሉ (both true believers and hypocrites) በማቴዎስ ወንጌል 13:24–30 ላይ እንክርዳዱም ሆነ ስዴውም በአንድ ቦታ ሲበቅሉና የእርሻው ባለቤት በቁጥር 30 ላይ "እስከ መከር ጊዜ አብረው ይደጉ" ሲል እንመልከታለን። ነገር ግን የሚለዩበት ዘመን በደረሰ ጊዜ እንክርዳዱን በእሳት አቃጥሉት ስንዴውን ግን ለይታችሁ በጎተራ አስገቡት በማለት ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ስለፍርድ ቀን ሊሆን የሚችለውን በParable of the Wheat and Tares analogy ሰርቶ ሲያስረዳቸው እንመለከታለን። ይህም ማለት በአንዲት በምትታይ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ True Believers አይደሉም። ባጭሩ Just because someone is a member of a visible congregation does not guarantee they belong to the invisible Church (the true community of believers). Therefore, church membership should be viewed as a step toward Christian maturity, not a guarantee of salvation.
ይሄን ያህል ስለ ቤተ ክርስቲያን ካየን አሁን ደግሞ አከራካሪ ስለሆነው ጉዳይ ማለትም “extra Ecclesiam nulla salus” ("outside the Church there is no salvation") የሚለውን መርህ ጠለቅ ባለ ዳሰሳ ለመመልከት እንሞክር። ይህ አይነቱ ሐሳብ ለመጀመሪያ ጊዜ explicitly articulated የሆነው በካርቴጁ ቆጵርያኖስ (Cyprian of Carthage ድርሳን መሰረት ነው። ቅዱስ ቆጵርያኖስ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት በተሰኘው ድርሳኑ (De Unitate Ecclesiae) ምዕራፍ 6 ላይ « ቤተ ክርስቲያን እናት ያልሆነችለት እግዚአብሔር አባቱ ሊሆን አይችልም »
« No one can have God for his Father, who does not have the Church for his mother » -—De Unitate Ecclesiae, Chapter 6—-
ይሄንን ክፍል በመውሰድ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ተቋማት (በተለይ የCatholic እና የEastern Orthodox Church) dogmatic interpretation ሲሰሩበት ይስተዋላሉ። «ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ድነት የለም/ extra Ecclesiam nulla salus» የሚለው term በራሱ አከራካሪ እና አወዛጋቢ ሐሳብን የያዘ term ነው። An Introductory Dictionary of Theology and Religious Studies በሚለው መጽሐፍ ገጽ 439 ላይ Gary Macy የተባለ scholar ቤተ ክርስቲያን የሚለውን የቅዱስ ቆጵርያኖስን ሀረግ ለብዙ መቶ ዘመናት ቤተክርስቲያን ከድነት ጋር ያላትን ግንኙነት ለመግለጽ በተለይ በሁለት አይነት ፍታቴ ሲጠቀሙበት እንደቆዩ ይናገራል። ቅዱስ ቆጵርያኖስን እየተናገረ ያለው ስለ "Body of the Saved" ወይም the mystical assembly of all who are saved by God's grace ነው ወይስ The Church as a Specific Institution ነው እየጠቀሰልን ያለው የሚለው ሐሳብ እንደተጠቃሚው እየተተረጎመ የመጣ ሐሳብ ነው ይለናል። ስለዚህ አንዳንዶች Ecclesiam ወይም ቤተክርስቲያን የሚለው ሐሳብ የምትታየዋ ቤተክርስቲያን የሚገልጽ ነው ሲሉ አንዳንዶች ደግሞ የለም የማትታየዋ ቤተክርስቲያን ነው የሚገልጸው ብለው ያምናሉ። ይሄንን ውዝግብ ለጊዜው እናስቀምጠው እና ቅዱስ ቆጵርያኖስ ምን ለማለት ፈልጎ ነው የሚለውን ለመመልከት እንሞክር፣
ቅዱስ ቆጵርያኖስ ይህንን ድርሳን ሲከትብ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሮም ግዛት በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ስደትና በቤተክርስቲያን ውስጥ በተፈጠሩ ግጭቶች ወቅት ነበር። ቅዱስ ቆጵርያኖስ የቤተ ክርስቲያን አንድነት እጂጉን ያሳሰበው ጉዳይ ነበር። ከዚህም ረገድ አንድ እምነት ነበረው እሱም ከቤተ ክርስቲያን ተለይቶ መውጣት ማለት ልክ ከክርስቶስ አካል እንደመለየት መሆኑን ይናገራል። በዛን ዘመን Schism አንዱ አስጊ እና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ትልቅ ቁርሾ ፈጣሪ እንቅስቃሴ እንደሆነ ያምንም ነበር። በተለይ 249–251 ዓ.ም በንጉሠ ነገሥት Decius የግዛት ዘመን ክርስቲያኖች ከባድ ስደት ገጥሟቸው ነበር፣ ይህም በብዙዎች ላይ የደረሰው መከራ እና ስደት ብዙ ክርስቲያኖች ወደ ክህደት መንገድ እንዲያመሩ አድርጓቸዋል። ስደቱ ከቀዘቀዘ በኋላ ቤተ ክርስቲያን በዘመኑ ትልቅ መናወጥን አስከትሎ ነበር።
ያለ ፍቃዷ የተደፈረች ሴት እና መጽሐፍ ቅዱስ?
ሙስሊም ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስን ለመተቸት እና የአምላክ ቃል ላለማድረግ በብዙ ሲሟገቱ ይስተዋላል። ይሄን ሰሞን አንድ ኡስታዝ ከአንዲት ክርስቲያን ጋር ሙግት ሲያደርግና በዛው በሚወያዩበት ጥቅስ ላይ በመመርኮዝ የተጻፈ ጽሑፍ በማህበራዊ ድረገጾች ላይ ሲዘዋወር አየሁ። ሙግቱ በብዙ ወፍሮ ከውስጥ የከሰመ ሙግት እንደሆነ የጠያቂያችንን ሙግት ያየ ሰው የሚያስተውለው ነገር ነው። እንዲህ ሲል ይጀምራል፦
ጠያቂው
መጽሐፍ ቅዱስ ሴቶችን ዝቅ ያደርጋል። እንደ እቃም ያያቸዋል። ለምሳሌ፦ በዘዳግም መጽሐፍ ላይ ስለ አንዲት የታጨች ሴት ያወራናል። እንዲህ ይላል፦
ዘዳግም 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁷ በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ጮኻለችና፥ የሚታደጋትም አልነበረምና።
²⁸ ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ያልታጨች ልጃገረድ ቢያገኝ፥ ወስዶም ቢደርስባት፥ ቢያገኙትም፥
²⁹ ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፤ አስነውሮአታልና ሚስት ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ ሊፈታት አይገባውም።
➨በዚህ ክፍል ላይ እንደምናየው ከሆነ ይህቺ ልጅ ቆንጆ ብትሆንና ያሰው ደግሞ ብር ኖሮት ሊያገባት ተመኝቶ ቢደርስባት ያለ ምንም የቤተስብ ፍቃድ ይህ ሰው ልጅቷን ያገባል። እርሷንም ለመውሰድ ገንዘቡን ብቻ ለቤተሰቧ ሰጥቶ ያገባታል። እውነት ይህ የአምላክ ፍትህ መጽሐፍ ቃል ነው ወይ? ይህቺ ልጅ ከተደፈች በኋላ ታገባዋለች አልፈልግም የማለትም ብቃት የላትም? ፍትህ የለበትም ይገርማል!?
መልስ
ይህ ኡስታዝ ያነሳው ሙግት የመጽሐፍ ቅዱስን የአውድ ሥነ-አፈታት መርሖን ካለማወቅ የተፈጠረበት ጥያቄ መሆኑን እናያለን። የእርሱም ጥያቄ በእውነቱ ከጠቀሰው ጥቅስ ጋር ይያያዛልን? የሚለውን ራሱ የጠቀሰውን የመጽሐፍ ክፍል በማብራራት እንጀምራለን። ክፍሉ እንዲህ ይላል፦
ዘዳግም 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁷ በሜዳ ባገኛት ጊዜ የታጨችው ልጃገረድ ጮኻለችና፥ የሚታደጋትም አልነበረምና።
²⁸ ማናቸውም ሰው ድንግልና ያላትን ያልታጨች ልጃገረድ ቢያገኝ፥ ወስዶም ቢደርስባት፥ ቢያገኙትም፥
²⁹ ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ #አባት#ይስጥ፤ #አስነውሮአታልና ሚስት #ትሁነው፤ በዕድሜውም ዘመን ሁሉ #ሊፈታት አይገባውም።
➨ይህ ክፍል እየተናገረ ያለው ከእርስዋም ጋር የተኛ ሰው ልጅቷን አስነውረሯታል። ታዲያ ስላስነወራት ለአባቷ አምሳ ሰቅል(ማለት 800 ግራም ብር ማለት ነው። ይህ ክፍያ በዚያ ዘመን ለነበረ ሰው እጅግ ውድ ክፍያ ነው፡፡) ይሄ ክፍያ ግን የሚተገበረው ለአባቷ ስም መጥፋት እንጂ እርሱ ሀብታም ሆኖ ልጅቷን ለመውሰድ (ለማግባት) የሚደረግ ክፍያ አይደለም። ለዛም ነው በጥቅሱ ላይ <<“ያ የደረሰባት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብላቴናይቱ አባት ይስጥ፤>> ብሎ አስደንግጎ ነገረን። ታዲያ ይህ ክፍያ በዚያን ዘመን ለነበረና በህጉ ለሚተዳደር ሰው ግዴታ ለአባቷ ሴት ልጁን ስለደረሰባት ይሄን ያህል ብር ይሰጥ ነበር። የክፍሉ ጥቅስ ክፍያው ለአባቷ ነው ብሎ ሳለ፤ ለጋብቻ ፍቃድ ለልጅቷ ነው ክፍያው ማለት ትዝብት ውስጥ አይከተንም ወይ ኡስታዝ?
🚩ሁለተኛው ጥያቄው፦
ሙሉ የመጽሐፍ ቅዱስን አስተምሮ ካለማገናዘብ እንደመነጨ እንመለከታለን። ሚስት ትሆነዋለች የሚለው አገላለፅን በተመለከተ በህጉ መሠረት አባቷ እና እሷ ከተስማሙ ብቻ እንደሆነ በሌሎች ተመሳሳይ ክፍሎች ላይ እንመለከታለን። ለፍትህ ፍትህ እንደሚባለው ይህንን ክፍል ከዛው ከሙሴ መጽሐፍ ህግ ከሆነው ዘጸአት 22:16-17 ጋር በማነፃፀር እንመልከት።እንዲህ ይላል፦
ዘጸአት 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ሰው ያልታጨችውን ድንግል ቢያስታት፥ ከእርስዋም ጋር ቢተኛ፥ ማጫዋን ሰጥቶ ሚስት ያድርጋት።
¹⁷ አባትዋም እርስዋን እንዳይሰጠው ፈጽሞ እንቢ ቢል እንደ ደናግል ማጫ ያህል ብር ይክፈላት።
➨ከዘዳግም 22፥27-29 ጋር ተመሳሳይ ድርጊት በዘጸአት መጽሐፍ ላይ እንመለከታለን። በጥንት ዘመን አንድ ሰው አንዲትን ድንግል ሴት ለማግኘት ብሎ ያለ ጋብቻ ቢገናኛት የስም ካሳ ገንዘብ ለወላጆቿ ይከፍላል፤ ከዛም በፍቃድ እንደ ስርአቱ ይጋባሉ። ይሄ ህግ ግን የሚፀናው የአታላዩ ጉዳይ ተመርምሮ በቤተሰቡ ውስጥ የፈቃደኛነት ስሜት ከተፀባረቀ ብቻ ልጅቷን በአባት በኩል እንዲያገባ ይደረጋል፥ ምክንያቱም አባት የቤቱ ራስ ነበረና። ለምሳሌ፦ አንዲት ሸጋ ድንግል ሴት አይቶ ቢደርስባት ለስም መካሻ ይሆን ዘንድ የሀገሩ ሽማግሌዎችና ታላላቅ የሐይማኖት አባቶች ተሰብስበው እንደ ባህሉ እና እንደ ወጉ መቀጫውን እንዲከፍል ለአባቷም እንዲያቀርብ ያደረጋሉ። ውሳኔውም የልጅቷ ፍቃድ በአባቷ በኩል ይጠየቃል፤ በመጨረሻ በህዝቡ ዘንድ ይነገራል። ይህ ስርአት በሀገሬ ገጠራማው አካባቢ ላይ ይገኛል።
➨ታዲያ ክፍሉ እንደሚለው ከሆነ ጋብቻው የልጅቷ ፍቃድ በአባቷ በኩል እንደሚገኝ ነግሮን ሃቁ ይህ ሆኖ ሳለ የኡስታዙ ቅጥፈት ምን የሚሉት ነው?..የልጅቷም ፍቃድ የለበትም ማለቱስ ኪስ ወለድ ሙግት አይሆንበትምን? ትዝብቱን ለአንባቢው ተዋለሁ።
"እኛ ግን እግዚአብሔር ልባቸው ለታወረባቸው ሰዎች ብርሃኑን ይገልጥላቸው ዘንድ እንጸልይ።"
ተባረኩ።
እስኪ ጥቆማ እናድርግ!
የወንድማችንን ቃል የቴሌግራምና ዩቱዩብ ቻናል በመቀላቀል አባል ይሁኑ። ወንድማችን ቃል በክርስትናው ነገረ መለኮት ዙሪያ ከእግዚአብሔር ዘንድ ባለ እውቀት ተደርገው ከተሰጡን ስጦታዎች መካከል አንዱ ነው። ስለሱ ብዙ የምንላችሁ ነገር ወደ ፊት ይኖረናል።
ለአሁኑ ግን የወንድማችንን ቃሌን ኦፊሻል ቴሌግራም ቻናልና ዩቱዩብ አካውንት ተቀላቀሉ(አባል) ኹኑ ወገኖች፦
ቴሌግራም፦ https://t.me/hokhmahchristianstudies
ዩቱዩብ፦ https://youtube.com/@hokhmah-y7y?si=6on3drQJvMhf-W3W
ሼር አድርጉት ተባረኩ።
@Yeshua_Apologetics_Ministry
የሙስሊሞች አዲሱ ሲስተም hey chatGpt I need a very quick answer. ብለው ስለ ክርስትና ይጠይቁና የሚፈልጉትን መልስ chatGpt ይሰጣቸዋል..😁
እኛ ደሞ እስኪ ይሄን አርጊውመንት እናፍርስ፦
Hey chatGpt👉 https://vm.tiktok.com/ZMhtgrq6j/
ከዛሬው ከተሰበከው ስብከት ከወደድኩት ሃሳብ ላጋራችሁ፦
መጋቢው፦
"...ጦርን አዘጋጁ ሃጢአትን ግደሉ። ምክንያቱም ሃጢአት ለሞት የሚዳርግ ነው። ለቅድስና ሕይወት መቀጠል አንዱ ይህ የሃጢአትን ጦርነት መጋፈጥ ነው። የዘላለም ሕይወት መገኛው መንገዱ አንድና አንድ ብቻ ነው። እርሱም፦ እውነተኛ ፍቅር፣ በክርስቶስ መታመን፣ በእግዚአብሔር መደሰት፣ በመንፈስ ቅዱስ መደገፍና ሃጢአትን በመግደል ነው። ይህ ነው መንገዱ፤ ከዚህ መንገድ ከወጣ አንድ ሰው ለዘላለሙ ሕይወት አንዳች ዋስትና የለውም።..."
ጦርን አዘጋጁ ሃጢአትን ግደሉት!
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana