ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month, 3 weeks ago
Last updated 1 day, 20 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months ago
ለ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች አድርሱልኝ
!!!!
#አደራ ይህን መልዕክት ያልደረሰው አንድም ተማሪ እንዳይኖር
እባካችሁ ይህንን ፅሁፍ በተመስጦ እራሳችሁን አረጋግታችሁ አንብቡት
ትምህርት ማለት ህይወታችን ላይ ጀምረን ካልተሳካ እንደምንቀይራቸው ቢዝነሶች እንጂ ሌላ አይደለም።እያንዳንዱ ውድቀት ለስኬት መወጣጫ ብቻ ነው። ከስህተቶችህ ተምረህ በርትተህ ትመለሳለህ።አንተ በጣም ጠንካራ እና ያሰብከውን ማንኛውንም ነገር ማሳካት የምትችል ነህ። መቀጠል ከባድ እንደሆነ አውቃለሁ፣ ግን በመጨረሻው ዋጋ እንደሚሆንህ ቃል እገባልሃለሁ።አስተውል! ህይወት ሌላ እድል እየሰጠችህ ነው
ፈጣሪህ አይሳሳትም
የሰው ልጅ ፍላጎት ሁሌም ቢሆን ያልተገደበ ነው።እኛ እንደሆንን ሁሌም ቢሆን ማማረራችን አይቀርም። ሞልቶ ሰጥቶንም እናማርረዋለን ሲጎድልብንም እናማርረዋለን።ፈጣሪ እኛ ህይወት ላይ በፍፁም አይሳሳትም።ከእኛ የሚነጥቀን ነገሮች እኛ እየነጠቀን ቢመስለንም ነገር ግን የኛ ስላልሆነና ፈጣሪ የተሻለ ነገር አዘጋጅቶልን ነው።
አንዳንዴ ለምንፈልጋቸው ነገሮች ምንም ያክል ብንለፋም ውጤታቸው ደግሞ እኛ እንዳሰብነው ሳይሆን ይቀራል።አብዛኛው ጊዜ ደግሞ እንደዚህ አይነት ነገሮች የሚፈጠሩት ከራሳችን ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ምክንያቶች ነው።ሰለዚህ ምን ማድረግ ይኖርብናል?
1.የመጀመሪያው ነገር ለምትፈልጉት ነገር የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ።መፍትሄ ሆኖ ያገኛችሁትና ልፋታችሁ የተሳካ እንዲሆን ሊያደርግ የሚችል ምንም አይነት ነገር ማድረግ።2.የቻላችሁትን ያክል ከለፋችሁ በኋላ የምትጠብቁት ውጤት የመሳካትና ያለመሳካት እድል ሊኖረው እንደሚችል አስቡ።እራሳችሁን በዚህ ልክ ካዘጋጃችሁ በሚመጣው ውጤት የማትጎዱ ይሆናል።
ሁሉንም ነገር በምክንያት ነው
እኛ ህይወት የሚፈጠሩ ሁሉንም ነገሮች ምክንያት አላቸው።ዋናው ነገር ያንተ ለምን? ብሎ መጠየቅ ነው።ለምን ብለህ ስትጠይቅ ህይወትህ ላይ የተፈጠሩና እየተፈጠሩ ያሉ ነገሮች ሁሉ መፈጠር ሰላለባቸው እንደሆነ ይገባሀል።ስለዚህ በእያንዳንዱ የህይወትህ ክስተቶች ውስጥ ደስተኛ ለመሆን ሞክር።
ሁሌም ህይወቴን የምመራባቸው ሁለት ህጎች አሉኝ1.እየተፈጠሩብኝ ያሉ ነገሮችን ለማስተካከልም ይሁን ወደፊት በሚኖረኝ ህይወቴም የምፈልገውን ለመኖር የማደርገው አንድ ነገር ቢቻ ነው።እሱንም #ከተመቻቹልኝ እድሎች ጋር የአቅሜን መሞከር,ከዚያም የሚመጣውን ውጤት በደስታ መቀበል ምክንያቱም የቻልኩትን ከሞከርኩኝ በኋላ የሚመጣው ውጤት ከእኔ ቁጥጥር ውጪ የሆነ ነገር ስለሆነ።2.ምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብሆን ለራሴአንድም መጥፎ ንግግርአልናገረውም።ምክንያቱም ይህቺ ህይወት በራሷ ከእኔ ማንነት በታች ነች።እኔ ከተፈጠሩብኝም ከተፈጠሩልኝም ወደፊትም ከሚፈጠሩብኝ እና ከሚፈጠሩልኝ ነገሮች ሁሉ በላይ ነኝ።
ህይወት ሌላ እድል እየሰጠችህ ነው
ህይወት ማለት አንድ በተቀደድችልን መንገድ ቢቻ መንገዷን ተከትሎ መሄድ አይደለም።ህይወት ሁሌም ምርጫ ትሰጥሀለች።አንደኛው በር ስትዘጋ ሌላ በር ትከፍትልሀለች።ዋናው ነገር ያንተ ብስለትና ዙርያህን በደንብ ማሰስህ ነው።
ህይወት ለደካሞች ቦታ የላትም ሲባል እንዲሁ ተረት ብቻ አይምሰልህ።አዎ በህይወትህ ተስፋ ስትቆርጥ, የምትሰራቸው ነገሮች አይሳኩልኝም ስለዚህ መተው አለብኝ ብለህ እጅ ስተሰጥ,ሁሉንም ነገር ከሰዎች መጠበቅ ስትጀምር ህይወት በዙርያህ ባሉ ነገሮች ትቀጣሀለች።እንዴት ካልከኝ
ጓደኞችህ ሁሌም እንደማትችልና ሀሉንም ነገር ላይ ተስፋ እንደሌለህ ይነግሩሀል።
ቤተሰቦችህ አንተ ላይ ተስፋ እንደቆረጡና አንተ በቤተሰብህ ዘንድ ምንም አይነት ትርጉም እንደሌለህ ይነገሩሀል። እና
አዕምሮህ ደግሞ ምንም የማትረባ ደካማ እንደሆንክና እራስህን ጠልተህ ህይወትህ ላይ አላስፈላጊ ውሳኔዎችን እንድትወስን ታደርግሀለች።
መቀየር ማትችለው ነገር ላይ ችክ አትበል
ህይወታችን ላይ ሁለት አይነት ክስተቶች ይፈጠራሉ
1.ምንም ብናደርግ ልንመልሰው(ልናስተካክለው) የማንችለው ጉዳይ።
2.ከተወሰኑ ጥረቶች በኋላ ልናስተካክለው እና ወደነበረበት ልንመልሰው የምንችለው ጉዳይ።
ስለዚህ ወዳጄ ህይወት ሁሌም ቢሆን ሩጫ ናት መቀየር የማትችለው ላይ ቆመህ ስታማርር ህይወትህን ሳትቀይር አትኑር
ህይወትህ ለማስተካከል ወይም ከነበርክበት ተሽለህ ለመገኘት በምታደርጋቸው ሩጫዎች ውስጥ ሁሉ የምትፈልጋቸውን ነገሮች በምትፈልገው ልክ ወይም ደግሞ ባሰብከው ፍጥነት ላይሳካልህ ይችላል።ምናልባትም ውድድር ላይ ከሆንክ ካንተ የበለጠ ልምድ ባላቸውና ውድድሩን በደንብ በሚያውቁት ሰዎች ልትቀደም ትችላለህ።
ህይወት እንዲህ ነች ወይ ትሸልምሀለች ወይ ደግሞ ከህይወት ሩጫህ አስተምራህ ታጠነክርሀለች።ስለዚህ የምትፈልገውን ለማግኘት ባደረግካቸው የህይወት ሩጫዎች ሁሉ ከስህተት መማርንና ጥንካሬን አትርፈሀል እንጂ አልባከንክም።አትጨነቅ
ምክንያቱም መጨነቅ እድሜህን ከማሳጠር እና ደስታህን ከመንጠቅ ውጪ አንድም ቀን መፍትሄ ሆኖ አያውቅም።የሚፈጠሩብህን ነገሮች ለማስተካከል የምትችለውን,መፍትሄ ሆኖ ያገኘኸውን ሁሉ አድርግ።እመነኝ ይህን ማድረግ ስትጀምር የህይወትን ትርጉም ይገባሀል።
መልካም ቀን
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
የ2016 የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መለቀቂያ ሰዓቱ አሁን ነው ፤ ለመመልከት
1.በዌብሳይት - http://result.neaea.gov.et
2. በ6284 - SMS
3. በቴሌግራም ቦት - @eaesbot መጠቀም ትችላላችሁ።
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
አለመኖርን እየኖርን ነው!
“በሕይወታችን መጀመርያ ላይ እንዲሁም በእርጅና ዘመናችን የሌሎችን እርዳታ እና ፍቅር የተሞላበት እንክብካቤ እንሻለን። ይኹንና በእነዚህ ሁለት የእድሜ ሁነቶች መካከል ባለው ሰፊ ጊዜ ፥ ጥንካሬ ሳይከዳን እና ራሳችንን ማቆምም ሳይሳነን ለሌሎች እገዛ እና ፍቅር ብዙም ስፍራ አንሰጥም።
የራሳችንም ሕይወት የሚጀምረው እና የሚገባደደው እንክብካቤን በመሻት እንደመኾኑ በጉብዝናችን ወራት ለሌሎች ርህራሄ እና እንክብካቤ ብንሰጥ የተገባ አይደለምን?”
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
ለበጎ ነው!!
አንድ ሰው በባህር ብቻውን በጀልባ እየተጓዘ በማዕበል ተመታና ጀልባው ተሰባብራ በባህሩ ውስጥ ሰጠመች። ሰውዬው እንደምንም እራሱን አድኖ አንድ ደሴት ላይ ያርፍና ጎጆ ነገር ሰርቶ ለቀናት ለብቻው እዛች ደሴት ላይ ይኖራል።
ምግቡን ዓሳ አያጠመደ እየተመገበ
ብዙ ቆየ።
አንድ ቀን ለምግብ የሚሆነው አሳ ሊያጠምድ ባህሩ ዳርቻ ላይ መንጠቆውን ይዞ ለረጅም ሰአት እየጠበቀ እያለ በድንገት ጭስ ሸተተው። ዞር ብሎ ሲያይ ያቺ ጎጆው እየነደደች ነው። እየሮጠ ቢመለስም ጎጆዋን ሊያድናት አልቻለም።
ለካ ዓሳ ለማብሰል ያቀጣጠለው እሳት ተያይዞ ጎጆውን አንድዷታል አለቀሰ፤ ፈጠሪውን ወቀሰ፤ እንዴት እዚህ ባህር ላይ ብቻዬን ጥለኸኝ ከቤተሰቦቼ ነጥለኸኝ ስታበቃ በስንት ልፋት የሰራኋትን ጎጆ ታቃጥልብኛለህ ብሎ አለቀሰ፤ አማረረ።
ከደቂቃዎች በኃላ አንድ ድምፅ ሰማ፤ ወደ ድምፁ ፊቱን ሲያዞር አንድ ትልቅ መርከብ አየ፤ ተደሰተ። የመርከቡ ሰዎች መጥተው ጭነው ወሰዱት። ከዚያም ለመርከቡ ሰዎች ጠየቃቸው! እንዴት አገኛቹኝ?
እዚህ አካባቢ እዚህ ባህር ላይ ማንም አይመጣም እኮ እናንተ እንዴት አገኛቹኝ?
አላቸው። መርከበኞቹም "እኛማ በዛኛው በኩል ዞረን እየሄድን ነበር። ከዚህ በኩል ጭስ አየንና እዚህ ሰዉ ይኖራል ብለን መጣን፤" አንተ አገኘን አሉት።
አቤት ጌታዬ ለካ ከዚህ ከስቃዬ ልታውጣኝ ፈልገህ ነው ትንሿ ጎጆዬን ያፍርስከው፤ ወደ ትልቁ ቤት ልትውሰደኝ ነው አለ።
✍አንዳንዴ የሆነ ነገር ስናጣና ሲበላሽብን ሰውንም ፈጣሪንም ስናማርር እንኖራለን። ግን ካጣነው እና ከጎደለብን ነገር ጀርባ ብዙ ጥሩ ነገር ልናገኝ እንደምንችል እንዘነጋለን። በችግራችን ጊዜ መጠጋት ያለብንን ፈጣሪያችን እንረሳዋለን። ከዚያም አልፈን የሁሉ ነገር ፈጣሪ የሆነውን አምላክ እንወቅሳለን።
ወዳጄ ሆይ ሁሌም ቢሆን በማንኛውም መጥፎ አጋጣሚ ውስጥ ሁነንም መልካም ነገሮችን ማሰብና በፈጠረን አምላክ ተስፋ ማድረግን ልማድ እናድርገው፡፡
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
ጊዜ
"ጊዜ የዘላለም አሽከር ሲሆን፣ ሰው ደግሞ የጊዜ ባሪያ ነው።ሰው ጊዜን በደቂቃና በሰአት፣ በወራትና በዓመታት ሸንሽኖ፣ ከግድግዳው ላይ ሰቅሎ በእጁ ላይ ጠፍሮ ሊገዛው ሊቆጣጠረው ይሞክራል። ጊዜ ደግሞ ሰውን ከልጅነት ወደ ወጣትነት ከጉልምስና ወደ እርጅና እያክለፈለፈ ከሞት ደጃፍ ያደርስና መቃብር ይጨምረዋል።
በክረምትና በበጋ ፣በጸደይና በመጸው እየተመሰለ መልኩን እየቀየረ ሲመጣና ሲሄድ ሲዞርና ሲፈራረቅ፣.... የጊዜ ጉዞ ያዙሪት እንጂ የወደፊት አይመስልም። በድል ፈረስ ላይ ተቆናጦ በስኬትና በውድቀት፣ በቀጠሮና በድንገት በጥበቃ እና በጥድፊያ ተጠቅሞ የሰውን እጣፈንታ የሚወስን ጊዜ መሆኑን በቀላሉ እንዘነጋለን። ጊዜን መግዛት ሲባል ራስን እንጂ ጊዜን ማስገዛት አይደለም።
"በጊዜ ውስጥ ትናንት የትዝታ ፣ነገ ደግሞ የተስፋ ጎተራ ናቸው። ካመለጠ ትናንት....ያልመጣ ነገ ይሻላል። በእጅ ያለ ዛሬ ግን ከሁሉም ይበልጣል። ዛሬ ሁሌም ያለ እየመሰለ የማይደገም... ተመልሶ የማይመጣ .....ላንድ አፍታ ለቅፅበት ታይቶ ዳርቻ ከሌለው የዘላለም ጠፈር ገብቶ የሚሰወር...
በትናንትናና በነገ መሃል የተሰነቋረ እንቁ ነው። የዛሬ ሚስጢሩ ና ጉልበቱ ያለው ደግሞ "አሁን" ነው። "ቅድም" እና "በኃላ" ግን ያለ ቦታቸው ዛሬ ውስጥ የተደነቀሩ የትናንትናና የነገ ሽርፍራፊዎች ናቸው።
ምንጭ ? ሌላ ሰው (ዶ/ር ምህረት ደበበ)
መልካም አዳር
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
ፅናት!!
"በዓለም ላይ የፅናትን ቦታ የሚተካ ምንም ነገር የለም። ብቃትም አይደለም። እንደውም ብቃት ያላቸው ስኬታማ እንዳልሆኑ ብዙ ቁጥር ያለው የለም። የረቀቀ ዕውቀትም አይደለም እንደውም ሰዎች እንደማወቃቸው ስኬታማ አለመሆናቸው ቢታይ አስገራሚ ትዕይንት ነው።መማርም አይደለም።
ዓለማችን በተማሩና በማይሰሩ ሰዎች የተሞላች ናት። ጽናትና ቁርጠኝነት ግን ሁሉንም ነገሮች ናቸው።የአላማ ፅናት ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ቦታ ተነስተው ያሰቡት ቦታ ለመድረስ ሊያቆማቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።"
ካልቬን ኮሌጅ
"እያንዳንዱ ታላላቅ የስኬት ታሪክ የትልልቅ ውድቀቶች ውጤት ነው ። ልዩነቱ ተሸናፊዎች በወደቁበት ተኝተው ሲቀሩ አሸናፊዎች ግን ከያንዳንዱ ውድቀታቸው በኀላ ዳግመኛ በታላቅ ብርታት መነሳተቸው ነው"
-ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
ከራስህ ጀምር!
የሚከተሉት ቃላት በአንድ ሰው መቃብር ላይ የተፃፋ ናቸው።
ወጣትና ነፃ ሳለሁ ና ምናቤ ገደብ በሌለው ወቅት አለምን ስለመለወጥ አልም ነበር። እያደግኩና እየበሰልኩ ስመጣ ግን እንደማትለወጥ አወቅኩ፣ ስለዚህ ምኞቴን አጠር አደረኩና ሀገሬን ለመለወጥ ወሰንኩ። ነገር ግን እሱም የሚሳካ አልመሰለኝም።ወደ መጨረሻ እድሜዬ እየደረስኩ ስመጣ በአንድ የመጨረሻ ተስፋ የመቁሩጥ ሙከራ ፣ የራሴን ቤተሰቤን ብቻ ፣ ለእኔ ቅርብ የሆኑትን ለመለወጥ ወሰንኩ ፤ እሱም አልሆነም።
እና አሁን በምሞትበት አልጋ ላይ ተጋድሜ ድንገት ይህንን አስተዋልኩ፤ ራሴን ለውጬ ቢሆን ኖሮ ፣ ምሳሌ በመሆን ቤተሰቤን መለወጥ እችል ነበር። ከእነርሱ ምሳሌነት ማበረታቻ የተነሳ ፣ ሀገሬን የተሻለ ማድረግና ማን ያውቃል አለምንም መቀየር እችል ይሆን ነበር።
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
ፈተናዎች ሲበዙብህ
ተስፋ ስትቆርጥ በሕይወትህ ውስጥ የሽንፈት’ አስተሳሰብን ትጋብዛለህ። ይልቁንም ችግሩን ለመፍታት የተለያዩ መንገዶችን ፈልግ እና ችግሩን እስክታሸንፍ ድረስ ስልቶችህን መቀየርህን ቀጥል።
እያንዳንዱ ችግር የራሱ የሆነ የመፍትሔ ዘር ይዟል። ይህ ማለት በአንተ ላይ የሚመጣ ችግር ሁሉ የራሱን መፍትሄ ይዞ ይመጣል ማለት ነው። ሰለዚህ የሚመጣውን ማንኛውንም ችግር መቋቋም እችላለሁ ብለህ ካሰብክ የማትፈታው ችግር አይኖርም።
በራስ መተማመን ችግሮችህን እና ዓለምን በድፍረት ለመጋፈጥ መቻልህን ያረጋግጣል። ሕይወትን ለመጋፈጥ በውስጥህ የሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ እንዳለህ እመን።
4. ፍርሃትን ስታስወግድ ስኬት ወደ አንተ ይመጣል
ፍርሃት በተለይም ውድቀትን መፍራት ብዙ ሰዎች በልበ ሙሉነት ችግራቸውን ለመፍታት እንዳይችሉ የሚያደርጋቸው መሰናክል ነው።
ፍርሃት ችግሮች ሲያጋጥሙህ ከሚያጋጥምህ ውጤት ይልቅ አሁን ያለው ሁኔታ የተሻለ እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል። ፍርሃት በአንተ እና በስኬት መካከል ያለ እንቅፋት ወይም መሰናክል ነው። ስለዚህ ፍርሃትን ስታስወግድ ስኬት ወደ አንተ ይመጣል።
አንዳንድ ጊዜ ተአምራት እንደሚፈጸሙ ማወቅ እና ማመን በጣም አስፈላጊ ነው። ሆኖም፣ ተአምራት በህይወትህ ውስጥ የሚከሰቱት አንተ ድርሻህን ስትወጣ ብቻ ነው። ማድረግ ያለብህን ሁሉ አድርግ፣ እናም ተአምራት በአንተ ላይ ይከሰታሉ።6. አእምሮህ አንተ ከምታስበው በላይ ሊሠራ የሚችል ታላቅ ሃብት ነው። ስኬታማ ሰው ለመሆን የሚያስፈልጉህ ግብዓቶች በሙሉ በአእምሮህ ውስጥ ናቸው - ታላቅነትን ለማግኘት እና ያሉብህን ችግሮች ለመፍታት የሚያስፈልግህ ነገር ሁሉ በአእምሮህ ውስጥ ነው። መፍትሄዎችን እንዳታይ የሚያደርጉህን እና ትኩረትህን የሚከፋፍሉ ነገሮችን በሙሉ ስታስወግድ፣ ያኔ ነገሮች ቀላል ይሆናሉ።
መልካም ቀን
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
Telegram?
@bright_ethiopia1
▓▒F░O░L░L░O░W▒▓█
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month, 3 weeks ago
Last updated 1 day, 20 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months ago