ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
በአሜሪካ ለምትኖሩ ብቻ https://www.tiktok.com/t/ZTYA7qvyr/
መስከረም አበራ ጥፋተኛ በተባለችባቸው የኮምፒውተር ወንጀሎች እስር ተፈረደባት
“ኢትዮ ንቃት” የተሰኘው የማኅበራዊ ሚዲያ መሥራች እና ባለቤት መስከረም አበራ ከሦስት ሳምንት በፊት ጥፋተኛ በተባለችበት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የአንድ ዓመት ከአራት ወር እስራት ተፈረደባት።
የቅጣት ውሳኔው በፍርድ ቤት ሲገለጽ መስከረም አበራ ችሎት አለመገኘቷን ጠበቃዋ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በመስከረም አበራ ላይ የቅጣት ውሳኔውን ያስተላለፈው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀሎች ችሎት ነው።
ፍርድ ቤቱ መስከረምን ጥፋተኛ ያላት “በኮምፒውተር ተጠቅማ በኅብረተሰብ መካከል አመጽ፣ ሁከት እና ግጭት ለማነሳሳት ሞክራለች” በሚል ክስ ነው።
መስከረም ጥፋተኛ የተባለችው በባለቤትነት በምታስተዳደረው ‘ኢትዮ ንቃት’ የዩቱዩብ ገጽ ላይ በተላለፉ ሁለት ፕሮግራሞች ምክንያት ነው።
ቀዳሚው ፕሮግራም ሚያዝያ 4/2014 ዓ.ም. “መልዕክት ለጄኔራል አበባው ታደሰ” በሚል ርዕስ የቀረበ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከሦስት ቀናት በኋላ በተመሳሳይ የዩቲዩብ ገጽ ሚያዝያ 7/2014 “አማራ ክልል ምን እየተደረገ ነው?” በሚል ርዕስ የተላለፈ ነው።
ባለፈው ጥቅምት ወር የዋለው ችሎት መስከረም አበራ ጥፋተኛ መሆኗን በመግለጽ የቅጣት ውሳኔ ለማስተላለፍ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር።
ከተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮዎች በኋላ ዛሬ ሰኞ ኅዳር 16/2017 ዓ.ም. የዋለው ችሎት የቅጣት ውሳኔውን ማስተላለፉን ጠበቃ ሄኖክ ገልጸዋል።
ጠበቃ ሄኖክ አክለውም “ይህ ውሳኔ የተላለፈው መስከረም አበራ ቅሬታ አለኝ ብላ ችሎት ባልቀረበችበት ሁኔታ ነው” ብለዋል።
አቶ ሄኖክ “ከዚህ ቀደም ያቀረብኳቸው መከላከያ ምስክሮቹ በአግባቡ ያልታዩልኝ ስለሆነ ከዚህ ችሎት ፍትህ አልጠብቅም፤ እናንተ ተገቢ ነው የምትሉትን ቅጣት ወስኑ፤ ከዚህ በኋላ በችሎት አልገኝም ብላ ገልጻለች ይሄንንም ለፍርድ ቤት በጽሁፍ አሳውቃለች” ሲሉ የደንበኛቸውን ቅሬታ ለቢቢሲ አስረድተዋል።
የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ተከትሎ የይግባኝ አቤቱታ ያቀረቡ እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠበቃው፤ “ከእሷ ጋር በተነጋገርነው መሠረት ቅጣቱ ላይ ሳይሆን መስከረም ጥፋተኛ የተባለችባቸው ሥራዎች ምንም ዓይነት የማነሳሳት፣ ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ባህሪ የሌላቸው እና በወንጀል የሚያስቀጡ ስላልሆኑ ፍርዱን ብቻ በተመለከተ ለፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛችንን አዘጋጅተን እናቀርባለን” ሲሉ መልሰዋል።
“ከዚያ በተረፈ ግን የቅጣቱ መብዛት ወይም ማነስን በተመለከተ [ይግባኝ] አናቀርብም” ብለዋል።
መስከረም ታኅሣሥ 2015 ዓ.ም. ለተመሠረተባት እና አሁን እስር ለተፈረደባት የኮምፒውተር ወንጀል ክስ የጦር ኃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አበባው ታደሰ እና የቀድሞውን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ይልቃል ከፋለን በመከላከያ ምስክርነት እንዲጠሩላት መጠየቋ ይታወሳል።
እነዚህ ምስክሮች የሚያስረዱላት ጉዳይ ምን እንደሆነ በአስረጂነት ካቀረበች በኋላ መጥሪያ እንደሚደርሳቸው ተገልጾላት የነበረ ሲሆን፣ እሷ ግን ምስክሮቹ ከቀረበ በኋላ ምን እንደሚያስረዳ ነጥብ የሚያስይዙት በሚል ብትከራከርም ተቀባይነት ሳታገኝ መቅረቷን በወቅቱ ጠበቃዋ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።
መስከረም አበራ አሁን የአንድ ዓመት ከአራት ወራት እስር ካስፈረደባት ክስ በተጨማሪ በእነ ዶክተር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ፣ ከዳዊት በጋሻው፣ ከጎበዜ ሲሳይ እና ከገነት አስማማው ጋር “የሽብር ድርጊት በመፈጸም” ሌላ የወንጀል ክስ እንደቀረበባት ይታወቃል።
@ቢቢሲ
የዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ እና የዶ/ር ነገሪ ሌንጮን የፓርላማ ፍጥጫ ተመልከቱት https://youtu.be/FXKDbaxFLyg
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago