AddisWalta - AW

Description
This is Walta Media and Communication Corporate’s official Telegram channel.

For more updates please visit https://shorturl.at/ehosX https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 2 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

2 months, 1 week ago
ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ …

ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ አሸናፊ ሆነ

ነሀሴ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተካሄደ የአውሮፓ ሱፐር ካፕ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ አታላንታን 2 ለ 0 በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆነ።

ጎሎቹን ቫልቨርዴ በ58ኛው እንዲሁም ዘንድሮ ቡድኑን የተቀላቀለው ፈረንሳያዊው ክሊያን ምባፔ በ69ኛው ደቂቃ ለማድሪድ አስቆጥረዋል።

ምባፔ በማድሪድ ማሊያ የመጀመሪያውን ዋንጫ ለማንሳት ችሏል።

ዛሬ ዋንጫ ማሸነፉን ተከትሎ ሪያል ማድሪድ የአውሮፓ ሱፐር ካፕን ስድስት ጊዜ በማንሳት በታሪክ የመጀመሪያው ቡድን ሆኗል።

2 months, 1 week ago
AddisWalta - AW
2 months, 1 week ago
AddisWalta - AW
2 months, 2 weeks ago
**ፓስፖርትን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በዓለም ገበያ …

ፓስፖርትን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በዓለም ገበያ በሶስት እጥፍ ጨምረዋል - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ነሐሴ 1/2016 (አዲስ ዋልታ) ፓስፖርትን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች በዓለም አቀፍ ገበያ በሶስት እጥፍ ገደማ ጭማሪ እንደታየባቸው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጎሳ ደምሴ ገለጹ።

የፓስፖርት ዋጋ ማሻሻያው ለዜጎች የፓስፖርት አገልግሎት አማራጮችን ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሊታይ ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል።

የዋጋ ማሻሻያው ከሶስት ወር በፊት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀ መሆኑንም አስረድተዋል።

ፓስፖርትን በቀደመው የገበያ ሁኔታ ለዜጎች ማቅረብ መንግስት እንደ ሌሎች ሸቀጦች ሁሉ ለፓስፖርት ጭምር ድጎማ ያድርግ እንደማለት መሆኑን ከአዲስ ዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የዋጋ ማሻሻያው ከክልከላዎች፣ ከእጥረት እንዲሁም ከተደራሽነት የመነጩ ውስንነቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በዘላቂነት የውጭ ምንዛሪ ወጪን ለማስቀረት የፓስፖርትና ምስጢራዊ ህትመቶችን በሀገር ውስጥ እንዲከናወን ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንም አብራርተዋል፡፡

በሰለሞን በየነ

2 months, 2 weeks ago
**በጥቁርና ነጭ ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት …

በጥቁርና ነጭ ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ በማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራው ለማሳካት የታሰበ ነው - የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ

ነሐሴ 1/2016 (አዲስ ዋልታ) በጥቁርና ነጭ ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ በማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራው ለማሳካት የታሰበ ነው ሲሉ የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ ገለጹ።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው 27 ባንኮች የተሳተፉበት የልዩ የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አንድ የአሜሪካ ዶላር 107.9 ብር እንደተሸጠ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ በጥቁር እና ነጭ ገበያው መካከል ያለው ልዩነት መጥበብ እና የምንዛሪ ተመን መረጋጋት በአንድ ሳምንት ውስጥ ልዩነት ማሳየቱን ገልጸው ኢትዮጵያ በጀመረችው የማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ ለማሳካት የታሰበውም ይህ ነው ብለዋል።

የዛሬው አማካይ ዋጋ የነገ የውጭ ምንዛሬ ዋጋ ጠቋሚ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ባንኩ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

2 months, 2 weeks ago
በ33ኛው የኦሊምፒክ ውድድር በ3 ሺህ ሜትር …

በ33ኛው የኦሊምፒክ ውድድር በ3 ሺህ ሜትር የወንዶች መሰናክል የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ማታ 4:43 ላይ ይካሄዳል፡፡

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን!

2 months, 2 weeks ago
AddisWalta - AW
2 months, 2 weeks ago
AddisWalta - AW
2 months, 2 weeks ago
"ያለማሰለስ መሥራት ለስኬት ቁልፍ ነው" ይባላል። …

"ያለማሰለስ መሥራት ለስኬት ቁልፍ ነው" ይባላል። የኢትዮጵያ የደን ሽፋን የ#አረንጓዴዓሻራ ንቅናቄ ከተጀመረበት በ2011 ከነበረበት 17.2 በመቶ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ የቻለው ባላሰለሰ ጽኑ ጥረት ነው።

በክረምቱ የችግኝ ሥራ መሪዎን ይከተሉ። አሻራዎን ይትከሉ። ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም ምስሎች።
??
https://www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate/posts/pfbid02cnHZbu2FWKrvApsPmqgKR3bez5V255ZBbkTDb9xyjLPsKQ56g7gUiNjtah9jwTLnl

2 months, 2 weeks ago
**የልብ ድካም ህመምን የሚለይ ቴክኖሎጂ**[**#ቴክኖ\_ቅምሻ**](?q=%23%E1%89%B4%E1%8A%AD%E1%8A%96_%E1%89%85%E1%88%9D%E1%88%BB)

የልብ ድካም ህመምን የሚለይ ቴክኖሎጂ#ቴክኖ_ቅምሻ

በሳይንቲስቶች ዘንድ ጨዋታ ቀያሪ (Game changer) የሚል ስያሜ የተሰጠው በልብ ድካም የመጠቃት አደጋ የተጋረጠባቸውን ሰዎች ለይቶ የሚያሳውቅ ቴክኖሎጂ ይፋ ሆኗል፡፡

ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴል የተሰራው በሲቲ ስካን ላይ የማይታይ የልብ ቁስለት መኖሩን ለይቶ የሚጠቁም ሲሆን ይህም የኤክስሬይና የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን ያጠቃልላል።

ቴክኖሎጂው ተለዋዋጭና ጨዋታ ቀያሪ ነው ያሉት የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ባልደረባ ፕሮፍ ኬት ቻነን ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ዓይን የማይታዩትን ባዮሎጂያዊ ሂደቶች ማወቅ እንድንችል ያደርጋል ብለዋል፡፡

በኤን ኤስ ኤስ ኢንግላንድ የሚደገፈው ፕሮጀክት በኦክስፎርድ፣ በሚልተን ኬይንስ፣ በሌስተር፣ በሊቨርፑልና በዎልቨርሃምፕተን በሚገኙ አምስት ሆስፒታሎች ላይ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች በልብ በሽታና ለሞት በሚያደርስ የልብ ድካም የመያዝ አጋጣሚያቸው ከፍ ያለ ነው። በዩናይትድ ስቴትስ በየዓመቱ 350 ሺሕ የሚጠጉ ታካሚዎች የልብ ምርመራ የሚያደርጉ ሲሆን ከእነዚህ ታካሚዎች መካከል 45 በመቶ የሚሆኑት በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አማካኝነት በሽታቸው ታውቆ መድኃኒት ታዞላቸው ህክምናቸውን እያደረጉ እንደሚገኙ የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ቴክኖሎጂው ታካሚዎች የከፋ ደረጃ ላይ ሳይደርሱ ህክምናቸውን እንዲያደርጉና ከህመማቸው እንዲፈወሱ እያደረገ ይገኛል፡፡

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 1 month, 2 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago