ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 1 week ago
Last updated 4 months ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months ago
"....ዑለሞችና የዒልም ተማሪዎች መስጂድ ውስጥ ተቀምጠው ከመቅራት ባለፈ ስለህዝቡ ፈሳድ ደንታ ቢስ ሆነዋል..."
📚ያስተነትኑም ዘንድ ታሪኮችን ተርክላቸው
ለቀቅ ስል ስንትና ስንት አላደርገውም ብሎ የሚያስበውን የማይጣስ ህጎቹን እንደማስፈታው.......የጨዋ ክልል የመሰለው ዝምታዬ ብልግናን የማፈን ጦርነት ውጤት እንደሆነ......<<ቆይ ግን አንቺ ስለራስሽ ምንም አትነግሪኝም እንዴ? >> የሚል ጥያቄው መልስ እኔ.....በተባለ የወሬ ሞቅታዬ ውስጥ ያለመደው የሴትነት ወዝ እየተተፋ ሄዶ ድንግል ልቡ እንዳይከረፋ እንደምለፋ.....<<ለምን እንደሆነ እኔጃ ግን አንቺ ጋር ብቻ ነው የምስቀውም የማወራውም>> ሲለኝ ምን ያህል ያዳመጠውን ጆሮዬን እንደረገምኩኝ..... ምንም አይገባውም!
ኦህ አምላኬ
ዱርዬ ነገር ነኝ ግን ብዙ አትዳፈረኝ ብዬው ነበር መተናነስ መሰለው እንጂ ይሔን ባሪያህን ከኔ ጠብቀው እባክህ መሄጃዬ እየደረሰ ነው💔
Glamor
ልክ ስለእሱ ሳስብ የሆነ የሚያቅለበልበኝ ነገር አለ። ራሴን መቆጣጠር በጣም ይከብደኛል....በአላህ ግሌክስ ተይ ደግመሽ አጠገቡ እንደማትደርሺ ትናንት ቃል ገብተሽ አልነበር በውስጤ እላለው ግን እንደዛ ከውስጤ ጋር ጦርነት ከፍቼ እንኳን እዛው አጠገቡ ነኝ። በጤና ነው ግን እንደሚጎዳኝ እያወኩ እንኳን እንዲህ የምወደው? እላለው ከዛ ዋጋውን ባውቅም ስንት ነው ? እላለው ሁሌም ቢጨምር እየተመኘሁ( ብር የለኝም ብዬ እንድሄድ እኮ ነው) ሀያ ብርየሚል መልስ እንደተሰማ በቃ እጄ ከአዕምሮዬ ውትወታና እረፍ ትዕዛዝ አፈትልኮ ይወጣና ብሩን ከፍሎ ሳንቡሳውን ለአፌ እያጎረሰ ይሄዳል....በልቼ እስክጨርስ እጄን ማንም አያዘውም።
ከሳንቡሳ ጋር ምን እንዳዋሀደኝ እንጃ
Glex
ግድ የለም ባካችሁ አጎብጦ የሚያስጉዛችሁን ሸክም ከትከሻችሁ ላይ አውርዱት.....ሀዘን ይዞ ቡዝዝ ያለው አይናችሁን በመፍነክነክ የሚመጣን እንባ አስታቅፉት አትያዙት ይፍሰስ.....እንደድንጋይ ከብዶ እንዳረጀ የሰው ቆዶ ጨምድዶ የያዛችሁን ስንክሳር ለሰከንድ በሚያስደስታችሁ ነገር አለስልሱት።
ህይወት ውስጥ ብዙ ነገር ያምራል እኮ!
ግድየለም ቁስላችሁን ለጥቂት ጊዜ ችላ ብላችሁ ብትፈግጉ ማንም አይሰርቃችሁም እመኑኝ ሁሉም በየመንገዱ ትግል ላይ ነው።
እያረፋችሁ....ህፃን ልጅ በመኮርኮርም ቢሆን ?[ሳቅ ይጋባል ]
Glamor
ወላሂ ጌታችን እኮ በዳዮችንም ተበዳይንም አይረሳም ? አልሀምዱሊላህ ?
አሄሄ አንዳንድ ማዕበሎቻችን ሲንጡን ፊታችን መናወጣችንን ሁሌ ያሳያል ብለሽ? በጭራሽ!
እንዲህ እየተመሰቃቀልን ምነው ምን ሆናችኋል? የሚለን እንኳን የጠፋው እያወቁ ነው? የለም! እኔ እንደዛ አላስብም
ባይሆን ፊታችን ውስጣችን የደረሰበትን መንኮታኮት መረዳትና ለሌሎች ማስነበብ ጠፍቶበት ይሆናል እንጂ እንዴት ሁላችንም በደስታችን ችርስ ብሉ ጠጡ ሆኖ ህይወታችን አብሮ ያጫፈረን ሁላ በጭንቃችን እለት እንደ ጉም ሊበተን ይችላል? ግድ የለሽም ምን እንደሆንንማ አያውቁም !
[ለኛ ግድ የላቸውም ከሚለው ይኼ ያፅናናን እንደሆን
እንዲህ እየፃፍን እንሞክረው ይሆን❔]
©Glamor
ቀዳዳችን በዛ አልሞላ አለን አደል..?
ተስፋ ቆርጠን ሞትም ተመኝተን ይሆናል
ሂወት ምን እንደያዘችልን ግን ማናችንም አናቅም
የባሰም እንዳለ እ፡ልፍ ስንል እልፍም እንዳለ
#እየቆየ_ነው_የሚገባን
✍️Mewla
እናውቃቸዋለን፣ ሸምድደናቸዋል፣ ሙሉ ነን ያልንባቸው ግንዛቤዎች ከአለም እና ውስጧ ከያዘችው ጉራማይሌ አንፃር ምንም እንደሆነ፤ ለካ ምንም አላውቅም የምንልበት
ድንገት ባዶነት የሚሰማን ጊዜ እንደሚመጣ #እየቆየ_ነው_የሚገባን
©glamor
« ግለት ያለው ኃይለኝነት እንደ ህፃን ልጅ ገላ ከለሰለሰ እዝነት ጋር፣ በጀግንነት የተሞላ ግርማ ሞገስ ለማመን ከሚቸግር መተናነስ ጋር፣ ታላቅ ቆራጥነት ከፍትሀዊነት ጋር፣ እውነተኝነት፣ ጥልቅ አፍቃሪነትን መመልከትን የምትሹ ከሆነ እንያን ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ከኔ በኋላ ነብይ የሚመጣ ቢሆን ኖሮ ዑመር ይሆን ነበር ያሏቸውን ዑመር ኢብኑል ኸጣብን ተመልከቱ።
ለእነዝያ ያለፈው መጥፎ ማንነታቸው፣ ብዙ ወንጀሎችን ሰርተው ከአላህ እዝነት ተስፋ ለቆረጡት ስለ ታላቁ የነብዩ ባልደረባ ስለ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ንገሯቸው።
ከችግር በኋላ ድሎት ለመኖሩ፣ ከተውበት በኋላ እጅጉን ያማረና የተዋበ ደስታ እንዳለ ለማመን ለከበዳቸው ስለ አል ፋሩቅ ንገሯቸው።
የጅህልና(የመሀይምነት) ዘመንን በደንብ ማጤን የፈለገ ዑመር ከመስለማቸው በፊት ያለውን ይመርምር፣ የእስልምናን ውበት መመልከትን የፈለገ ዑመር እስልምናን ከተቀበሉ በኋላ ያላውን ህይወታቸውን ይመልከት።
አንዲት ሴት ስለ ዑመር ተጠየቀችና እንዲህ አለች። ዑመር ሲያበላ ያጠግባል፣ ሲማታ ያሳምማል፣ ሲራመድ ያፈጥናል ትላለች።
በእርግጥም እውነት ተናገረች። ዑመር በእዝነታቸው ልቦችን አጠገቡ፣ በፍትሀዊነታቸው የበዳዮችን አቅም መቱ፣ በእውነተኝነታቸው ወደ ሀቅ ብዙዎችን አመለካቱ።
የተውበትን ፀዳል ውበት ማየትን ካሻችሁ ዑመርን ተመልከቱ። ትላንታችሁ ስለጨለመ ፈፅሞ የተሻለ ነገር እንደማታገኙ ከተሰማችሁ ዑመርን ተመልከቱ።
ለማን ማዘን ለማን ደግሞ ኃይለኛ መሆን እንዳለባችሁ ከጠፋባችሁ ዑመርን ተመልከቱ።
አላህ መሀሪና አዛኝ፣ ወደርሱ የተመለሰን እንደሚያልቅ ምሳሌን ካሻችሁ ስለ ሁለተኛው የምዕመናን መሪ ስለ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ በጥልቀት መርምሩ። መገን አላህ! የወደደውን ማስወደድ ከአላህ የበለጠ ማን ያውቅበታል?(ማንም) »
[ አብዱልሀኪም ሰፋ ]
:
ኡመሬ❤️❤️❤️
በዱንያ ፍቅር አይናችን ሲቅበዘበዝ አራዳነት መስሎን ያንንም ያንንም ስንይዝ እና ስንለቅ.. ከተፃፈው ከሪዝቃችን ውጪ ምንም ነገር ማድረግም መያዝም እንደማንችል...
#እየቆየ_ነው_የሚገባን
✍️Mewla
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 4 months, 1 week ago
Last updated 4 months ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 3 months ago