ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
????♂️ሁለቱም ወገኖች ልዩነትን ሲቀበሉ እና የባህል ልዩነቶችን ለመፈተሽ ጥረት ሲያደርጉ፣ የባህል ልዩነቶች ግንኙነቱን ለማበልጸግ እና ለማሳደግ ያገለግላሉ።
????♂️ሁለቱም ሰዎች ከአንድ ሀገር የመጡ ቢሆኑም፣ በግንኙነት ሂደት ውስጥ የባህል ልዩነቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። ንዑስ ባህሎች በከፍተኛ ሁኔታ ሊለያዩ ይችላሉ፣ ለምሳሌ፣ በተለያዩ የዘር ቡድኖች፣ በገጠር እና በከተማ አካባቢዎች፣ በማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ደረጃዎች እና በሀገሪቱ አካባቢዎች።
?እያንዳንዱ ቤተሰብ ድርጊቶችን፣ ስሜቶችን፣ የንግግር እና የአለባበስ ዘይቤን፣ የቤተሰብ ትስስርን እና ሌሎች ገጽታዎችን በተመለከተ የራሱ የሆነ ባህላዊ ደንቦች አሉት።
?በባህሎች መካከል የተለያዩ የልዩነት ደረጃዎች አሉ፡ ጎሳ + ደረጃ + የጠባቂነት ደረጃ።
?በባህል ልዩነት ምክንያት ግጭቶች ወይም መሰናክሎች በትዳር ህይወት ዑደት ውስጥ በተለያዩ ወቅቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ።
?አንድ ሰው ባህሉን እንዲተው ከመጠበቅ፣ እርስ በርስ ለመማማር እና ባህሎችን ለመጋራት መልካም አስተሳሰብን መቀጠል አስፈላጊ ነው። የሌላውን ሰው ባህል ካልተቀበልክ ወይም ከራስህ ባህል የሆነን ሰው እንደምትመርጥ በልብህ ሀሳቡ ካለብህ ከራስህ ባህል የሆነን ሰው ማግባት ተገቢ ነው።
??የትዳር ጓደኛዎ የሚስማማቸውን እና መቀበል የሚፈልጉትን የባህልዎን ክፍሎች እንዲመርጥ ይፍቀዱለት።
ይቀጥላል…
በኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሚንበር ቲቪ ዘወትር ማክሰኞ
ምሽት 2:30-3:30
በአላህ ስም እጅግ አዛኝ ሩህሩህ በሆነው
ተጣማሪን መምረጫ መስፈርቶች
ክፍል (6)
6ኛ፤ ውበት
☪️እስልምና ውበትን እንደ አንድ ለጋብቻ ቀስቃሽ አጋጣሚ ያደርገዋል፡፡ ?መልክተኛው (ሰዐወ) ቡካሪና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲሳቸው እንዲህ ማለታቸው ተወርቷል፡፡
??አንዲት ሴት ለአራት ምክንያት ትገባለች፡ ለገንዘቧ፤ ለቤተሰቧ ክብር፤ ለቁንጅናዋና ለዲኗ፤እጅህ አፈር ይዘገንና ዲን ያላትን ምረጥ)፡፡
?ውበት ወይም ቁንጅና አንጻራዊ ነገር እንጂ ቋሚ መለኪያ የለውም፡፡ አንድ ሰው ከሚስቱ ላይ የሚያየውን ውበት ሌላን ሰው በፍጹም አይዋጥለት ይሆናል፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው የራሱን የውበት መስፈሪያ እንዲጠቀም ቢፈቀድለት መልካም ነው፡፡ መልክተኛውም ከላይ ያነሱት ሲያያት የምታምረው ነው ያሉት፡
•እይታው የሚፈጥረው ስሜት ለግለሰቡ ነው የተተወው፡፡
??እዚህም ጋር ማስታወሻ ለእናቶችና እህቶች ባስቀምጥ ደስ ይለኛል፡፡ እሱም ለልጃችሁ ቆንጆ ሚስት መረጥንልህ አግባት ስትሉ ካልታየው ባትጫኑና ባታስገድዱ መልካም ነው፡፡ የሚያገባት እሱ ነውና ውበቷን ካደነቀና ስሜት ከሰጠው መልካም፡ ካልሆነ ግን እሱ ስለሆነ የሚያገባት በእናንተ መስፈርት ቆንጆም ብትሆን ገፋፍቶ ማስገባቱን ብትተውት ትመከራላችሁ፡፡
??♂️ወጣት ወንዶችም ውበት ላይ ከፍተኛውን ትኩረት ስታደርጉ የሚከተሉትን ሀሳቦች ከግምት ማስገባት ያስፈልጋል፡
??አንደኛ፡ ውበቷ ለአንተና ለቤቷ መሆኑን ብታረጋግጥ ፡ የሴት ልጅ ውበት ለአደባባይ፡ ለጎዳናና ለሰርግ ቤት ወይም በተለያዩ መድረኮች ላይ መፎካከሪያ ተደርጎ መቅረብ የለበትም፡፡ ይህ በፍጹም ተቀባይት ያለው ስነምግባር አይደለም፡ ኢስላማዊ ሸሪዓንም ይጋፋል፡፡ ለሚስትህ ቁንጅና የጓደኞችህን ምስክርነት አትፈልግ፡ ይህ አካሄድህ ኋላ ላይ ዋጋ ሊያስከፍልህ ይችላል፡፡
??ሁለተኛ፡ በቁንጅናዋ የተፈተነች መሆን የለባትም፡ እራሷን ከፍጥረት ሁሉ በላጭ አድርጋ በመመልከት የምትኩራራ እንዳትሆን ያስፈልጋል፡ ባሎችን በጣም ከሚደብራቸው (ከሚያስቆጣቸው) የሚስት ባህሪ አንዱ ደግሞ ኩራት ነው፡
?ይህ ስሜት ሌሎችን ዝቅ አድርጎ መመልከትና መሬት አይንካኝ ካስባላት ይህ ውበት ለሚስትነት አያገለግልም፡ ሲጀምር ባልለፉበት ነገር የሚኩራሩ ሰዎች ግብዞች ናቸው፡፡
??በነገራችን ላይ ወንዶችም በውበታቸው የሚኩራሩ ከሆነ ዋጋቸው ይወርዳል፡፡
?አላህ ሰርቶ በሰጠን ነገር ላይ አመስጋኝ እንጂ ትእቢተኛ መሆን አይገባም፡ በእርግጥ እራሳችንም ለፍተን አግኝተነዋል ብለን በምናስበውም ነገር መኩራራት ተገቢ አይደለም፡ ጸጋዎች ሁሉ ባለቤትነታቸው ለአላህ ነው የሚመለሰው፡፡
?እንደ ተረት አንድ አይነስውር ሰው አንዲት አይናማ ሴትን አግብቶ ይኖር ነበር፡፡ ሚስቱም የአይነስውርነቱን አጋጣሚ እንደ እድል በመጠቀም ዘወትር ልትኩራራ ትሞክራለች፡፡ አይኔን፤ ቅንድቤ፡ ሽፋሽፍቴ፡ ማማር የጥርሴን አደራደር፡ የጉንጬን አወራረድ ወዘተ ብታይ ውበቱ ለጉድ እኮ ነው፡ እያለች ጉራዋን እየነዛች አስቸገሪቺውና አንድ ቀን አንቺ ሴትዮ እስኪ ተይኝ ባክሽ እንደምትይው ወደር የለሽ ቆንጆ ብትሆኝ እኮ አይናማዎቹ ለኔ አይነቱ አይተውሽም ነበር አላት ይባላል፡፡
??ሶስተኛው፡ ዉበቷ በዲን መርሆዎች የተጠበቀ መሆን አለበት፡፡ ውበት በሴቶች ላይ በጣም ያምርባቸዋል፡ የበለጠ የሚያምረውና የሚደምቀው ደግሞ በኢስላማዊ ስረአት ሲሸፈን፡ በጥብቅነት ሲሞሸር ነው፡ ለአደባባይ የማይቀርብ ውድና ብርቅ ጌጥ መሆኑ ታውቆ ጥበቃና ከለላ ሲደረግለት፡ በጨዋነት ሲከሸን፤ በእርግጥ ጸጋ ይሆናል፡፡ ተቃራኒው ገዳይ መርዝ ስለሆነ መራቁን እንመክራለን፡፡
??♂️ወንዱንም በተመለከተ ሰይዲና ዑመር ረአ ሴት ልጃችሁን ፉንጋና ወራዳ ለሆነ ሰው አትዳሩ፡ እናንተ የምትወዱትን ውበት እነሱም ይወዳሉና ብለዋል፡፡ (ሀዲሱ ደኢፍ ነው ተብሎዋል) ወንዶች ለራሳችን የምንወደውን ለሴት ልጆቻችንና እህቶቻችን መውደዱ ፍትሃዊ የመሆን ምልክትም ነው፡፡
7ኛ፡ የቤተሰብ ክብር
?ይህ የቤተሰብና የአያት ቅድመ አያቶች ክብር ነው፡፡ በቤተሰቡ መካከል ቤተሰባዊ ትስስር፡ የተቅዋና ኢማን ቤተሰብ የመሆን ታሪክ ማለቴ ነው፡ ማግባት የሚፈልግ ሰው የተከበረ ቤተሰብን፡ በታላላቅ እሴቶች (እንደ ኢማን ተቅዋ፡ ዒልም፡ ጥብቅነት፡ መተባበር እና ቤተሰባዊ ትስስራቸው፡) የታወቁ ቤተሰብ ልጅ ካገኘህ አትልቀቅ፡፡
?የሰው ልጅ የሚኖርበት ከባቢ ልጅ ነው ይላሉ አረቦች፡ ከላይ ያነሳናቸው እሴቶች መሀል ያደገ ሰው ምንም ቢሆን የተወሰነውን ያህል መውረሱ አይቀርም፡ መልክተኛውም ለዘር ፍሬያችሁ ማረፊያውን ቦታ በጥንቃቄ ምረጡ ብለዋል፡ (ዘር ከልጉዋም ይስባልና) ሴቶች እህቶቻቸውንና ወንድሞቻቸውን አምሳያ ይወልዳሉና፡
?በታወቀው ሀዲሳቸውም፡ አንዲት ሴት ሚስት ተደርጋ ከምትወሰድበት ምክንያት አንዱም ከተከበረ ቤተሰብ መምጣቷን አድርገውታል፡፡ በጋብቻ የምንጣመረውን ሰው ምንጩን በደንብ ማጣራት ጥሩ ነው፡ ክብር አደብ፤ እውቀት፡ ጠንካራ የዝምድና ትስስርና የመተባበር ባህል ያለበት፡ ወዘተ ጉዳዮች በአግባቡ ቢታዩ አይከፋም፡
?ብልግና፡ ዝርክርክነት፡ መቆራረጥና መበጣበጥ፡ ፍችና መለያየት ባህላቸው የሆኑ ቤተሰቦች ውስጥ ያደጉ ሰዎች አዙሪቱ ውስጥ የመግባት እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ ሰው ከቤተሰቦቹ ብዙ ነገር የሚማር ፍጡር ነው፡ ሳያውቀው ጭምር፡ (አንዳንዴ ልክ መስሎት ሊያድግ ይችላል)፡ መቼም ከዚህ አይነት ቤተሰብም አላህ መልካሞችን ሊፈጥር እንደሚችል ጥርጥር የለውም፡ እኔ ግን የማወራው እንደአጠቃላይ መርህ ነው፡ ዩክሪጁል ሀየ ሚነል መይት ነውና፡፡
?አናሱ ከማዓዲኒ ዘሃቢ ወልፊደቲ፡ ሰዎች እንደ ማእድናት ናቸው፡ ወርቅና ብር እንዳለበት፡፡ ከማእድናት ውስጥ እጅግ በጣም ውድና ብርቅ የሆኑ አሉ፡ መካከለኛም አሉ ዝቅተኛም አሉ፡ (ወርቅ እንኳ ባለ 14፤18፤24 ካራት አለው እኮ) ከቻልክ ውድና ብርቅ የሆነውን አይነት ሰው ካገኘህ እንዳትለቅ፡ ህይወትህን በሙሉ የምታጌጥበት ነውና፡፡
??የትዳር አጋርህን ስትመርጥ ከምርጥ ቤተሰቦች የተቀዳች መሆኗን ከግምት አስገባ፡፡ ከተከበረ ቤተሰብ የመጣች ልጅ ከቤተሰቧ የወረሰችው መልካም ነገር ይከተላታል፡ አንድ አባት ለልጁ እንዲህ አላት፡ ልጄ ሆይ ባልሽን በክብርና ፍቅር ያዢ፡ ከቤተሰባችን መዝገበ ቃላት ውስጥ ፍቺ የሚል ቃል የለም፡፡
?ሌላኛዋ እናት ደግሞ ልጄ ሆይ ለባልሽ ባሪያ ሁኚለት፤ ሎሌ ይሆንልሻልና፡፡
?በተቃራኒው ሲሆንም አይተናል፡ የልጃቸውን ባል የሚንቁ ደፍረው የሚያስደፍሩ ቤተሰቦች አሉ፡ ከማህበረሰቡም ጋር ያላቸው የሻከረ ግንኙነት ቤተሰቡ ውስጥ ያለውን የስነምግባር ልኬት ያሳብቅባቸዋል፡፡
??ይህ ሁሉ ነገር ልጅቱን በቀጥታ ሊወክላትም ላይወክላትም ይችላል፡ ግና ማንኛውም ሰው ከቤተሰቡና ከኖረበት ማህበረሰብ የሚወርሰው ባህሪ መኖሩ አይቀርምና በአንክሮ መመልከት መልካም ነው፡፡ ይህን ጉዳይ ቀጥታ ለወንዱም እኩል በኩል የሚገለበጥ መሆኑ እንዳይረሳ፡ ሁሉም የተቀዳበትን ምንጭ መምሰሉ አይቀርምና፡
??ወንድሞችና አባቶች ለሴት ልጃችሁና እህታችሁ መጥቶ የሚጠይቀውን ሰው ከዚህ አንጻር መገምገም ጥሩ ነው፡፡ ምንጩ ጥርት ያለ ክብርና ማእረግ፡ እምነትና ተቅዋ፡ አደብና አኽላቅ፡ ካለበት ቤት የመጣውን ጎረምሳ ቅድሚያ መስጠት ብልህነት ነው፡
8ኛ ባህል
?እኛ ያደግንበት የሥልጣኔ ውጤቶች ነን፣ እናም በተለያዩ ባህሎች ባህሪያት ተጽዕኖ ይደረግብናል።
በአላህ ስም እጅግ አዛኝ ሩህሩህ በሆነው
ተጣማሪን መምረጫ መስፈርቶች
ክፍል (5)
4ኛ:ሀያዕ (ጨዋነት)
?ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) “ለሁሉም ሀይማኖቶች የራሳቸው መገለጫ የሆነ ስነ-ምግባር አላቸው የኢስላም ባህሪ (የተለየ) ሃያዕ ነው” ብለዋል፡፡ በሌላም ዘገባ “የማታፍር ከሆነ የፈለከውን ስራ” ብለዋል፡፡
??ሃያዕ ከሴት ልጅ በእጅጉ የሚፈለግ element ነው፡፡ ሃያዕ በወንዶችም ላይ የሚያምር ቢሆንም በሴቶች ላይ ደግሞ እጅግ በጣም የሚያምር ምግባር ነው፡፡
??በእውነት ለሴት ልጅ በተለይ እጅግ ድንቅና ውብ ነገር ነው፡፡ የሴት ውበትዋ በሃያዕዋ ውስጥ ነው ይባላል፡፡ ወንዳወንዷን ሴት፣ እንደ ወንዶች ጮኻ የምትስቅ አካሔዷም አወጣጥ አገባብዋም ከወንዶች ጋር የተመሳሰለች ከሆነ ልክ አይመጣም፡፡
??በአላህ መልዕክተኛም አንደበትም ተረግማለች፡፡ አብደላህ ኢብኑ ኡበይዱላህ ኢብኑ አቢ መሊከተ እንዳወሩት “ለአይሻ እንዲህ ብለው ተጠየቁ ሴት ልጅ የወንድን ጫማ ትጫማለች? ሲመልሱም በርግጥ ወንዳ ወንዷን ሴት መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ረግመዋል” አለች፡፡
?ከቂያማ ምልክቶችም አንዱ ወንዶች ሴቶችን፤ እና ሴቶችም ወንዶችን መመሳሰላቸው ነው፡
?በጨዋነትና በእራስ አለመተማመን (ለራስ ዝቅተኛ ግምት በመስጠት) መካከል ከፍተኛ ልዩነት አለ፡፡ የደካማ ስብእና ባለቤት በመሆን የሚመጣው ልፍስፍስነት ሃያዕ አይባልም የዚህ ባህሪ ምንጩም ፍርሃትና ድክመት በመሆኑ ነው፡፡
??ፈሪና ልፍስፍስ ሰው መብቱን ከመጠየቅ ይቆጠባል ይህ ደግሞ ተፈላጊ ምግባር አይደለም፡፡
?ሃያዕ (ጨዋነት) ምስጉን ባህሪ ሲሆን የጥንካሬ ምልክትም ነው፡፡ ፈሪ እና ልፍስፍስ መሆን የማይፈለግ ምግባር እና የደካማነት ምልክት ነው፡፡
?የአንዲት ሴት ሃያዕ እንዴት ሊታወቅ ይችላል? የሚታወቀውማ በአኗኗር ዘይቤዋ ነው፡፡ ከሌሎች ጋር ባላት ግንኙነት፤ በተለይም ከቤተሰቦቿ (አባቷ፤ወንድሟ በተለይ በአንተ ፊት የምታሳየቸው ተግባራትና የምትጠቀማቸው ቃላት ስለ ሀያእዋ ሊያሳብቁባት ይችላል፡
?የሰው ልጅ ሲናገር እና ሲናደድ አስተሳሰቡና ስነምግባሩ ይጋለጣል፡ ይባላል፡ ስለዚህ በተለያዩ አጋጣሚዎች ይህን ወሳኝ ባህሪ ማረጋገጡ መልካም ነው፡
??ለአንዲት ሴት ሀያእ እጅግ በጣም አስፈላጊ መገለጫዋ ነው፡ ይህን ማጣት አጉል ነው፡ ከቤት ስትወጣ፡ ከወንዶች ጋር ያላት ቅርበት፡ የአነጋገር ስታይሏ፡ ባእድ ከሆኑ ሰዎችም ጭምር ያላት የመግባባትና ድንበርን ያለመጠበቅ፡ ቅጥ ያጣ ድፍረት ከሰው መሀል (በተለይ በወንዶች) ማሳየት፤ ለሴት ልጅ፡ ከአለባበስ ከአረማመድና ከአጠቃላይ የላይፍ ስታይሏ፡ ይህን እሴት መገመት ይቻላል፡፡
?እሴቱ ለሌሎች የስነምግባር መርሆዎችም መገለጫና ማሳያ በመሆኑ ቸል መባል የለበትም፡፡ አብደላ ኢብኑ ኡመር እንደዘገቡት አንድ ቀን ረሱሉ (ሰዐወ) ከሰዎች አጠገብ ሲያልፉ አንደኛው ወንድሙን ስለሀያእ (አታብዛ) በሚል ሲመክረው ሰሙና ተወው ሀያእ ከኢማን ነው፡ አሉት፡ ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል፡፡
5ኛ፡ መታዘዝ
??ከላይ እንዳነሳነው ረሱሉ (ሰዐወ) የመልካም ሴትን መገለጫዎች ሲጠቅሱ፡ ለባሏ ታዛዥ መሆኗን አንዱ አድርገው ገልጸዋል፡፡ ሚስት በሏን የምትታዘዘው የቤቱ አስተዳዳሪ (መሪ) በመሆኑ ነው፡፡መሪ ደግሞ ይታዘዙታል፡ የትኛውም ስብስብ መሪውን ካልታዘዙት ስረአት አልበኝነት መንገሱ አይቀርም፡ ስብስቡም አይቀጥልም፡፡
?የሚገርመው ሚስቶች ባሎቻቸውን እንዲታዘዙ ስናስተምር ቅር የሚላቸውና ሴቶችን እንደመጫን የሚቆጥሩ ሰዎች መከሰታቸው፤ ነው፡ እነዚህ ሰዎች የትኛውም ተቋም ሄደው አብሮ ለመስራት ታዛዥና አዛዥ መኖሩን መቀበላቸው አይቀርም፡ ቤትም ተቋም ነው እስካልን ድረስ የእዝ ሰንሰለት ያስፈልገዋልና እንግዳ የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም።
?ባይሆን ቤቱ የተመሰረተበትን አላማ ለማሳካትና በቤተሰቡ መካከል ያለውን የስራ ክፍፍል አሳልጦ ውጤታማ ለመሆን መልካሞቹ ሴቶች ባሎቻቸውን በመልካም ነገር እስካዘዙዋቸው ድረስ መታዘዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እዚህም ጋ ጥያቄው የአንዲት ወጣት ሴት ለባሏ ታዛዥነት እንዴት ይታወቃል የሚለው ነው፡፡
??ከልምድና ተሞክሮ የተወሰደው ቤተሰቦቿን በመመልከት መሆኑ ነው፡፡ በእርግጥ ሰዎች አንድ አይነት አይደለንም፡ ነገር ግን ሴቶች በእናቶቻቸው ተጽእኖ ስር መኖራቸውና አርአያ አድርገው እንደሚከተሏቸው ልንክደው አንችልም።
ይቀጥላል…
በኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሚንበር ቲቪ ዘወትር ማክሰኞ
ምሽት 2:30-3:30
በአላህ ስም እጅግ አዛኝ ሩህሩህ በሆነው
ተጣማሪን መምረጫ መስፈርቶች
ክፍል (4)
3ኛ፡ ንቃተ ህሊና
??♂️ንቃተ ህሊናዋ ከፍ ያለችዋን ብትመርጥ በትዳርህ ዕረፍት ለማግኘት ይረዳሃል፡፡
??ይህቺ አይነት ሴት (ንቃተ ህሊናዋ ከፍ ያለችዋ) ማለት ስለ ቤት አያያዝ፣ ስለ ገንዘብ አወጣጥና አገባብ፣ ስለ ልጆች ተርቢያ ስለ ባል እንክብካቤ ስለ ጠቅላላ ዕውቀት የተወሰነ ግንዛቤ ያላት ማለት ነው፡፡ ይህቺ ሴት አዕምሮዋን የምታሰራ እና የምትሰጣቸውን ውሳኔዎችም ተቀባይነት የሚኖራቸው አይነት ናት፡፡ እንደዚህ አይነት አቅለኛ ሴት ካልሆነች ግን እራሷንም ባሏንም ብዙ ችግር ውስጥ ልትከት ትችላለች፡፡በርካቶችን ልታስቀይም ትችላለች፡፡ ይህ የሚሆነው አውቃም ሳታውቅም ሊሆን ይችላል፡፡ ??♂️በተመሳሳይ የወንዱም ያው ነው፡ ብስለት የማይታይባቸውን ሰዎች ለትዳር መገፋፋት ተገቢ አይደለም፡ ቀድሞ እንዲበስሉና፡ ሃላፊነት ለመሸከም እንዲችሉ ማብቃት ያስፈልጋል፡፡እንዴት ታውቃለህ የግንዛቤዋን መጠን (አቂል መሆኗን) ይህ የሚታወቀው በተወሰነ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ የተወሰኑ ጥያቄዎችን በማንሳት ስለ ሕይወት እና ተያያዥ ጉዳዮች ያላትን ምልከታ መረዳት ይቻላል፡፡ ስለ ትዳር፣ ስለ ዕውቀት፡ ከሰዎች ጋር ስላላት ግንኙነት፡ ስለሀገርና፡ አካባቢዋ ወዘተ… ጉዳይ በማንሳት መጠያየቅ አቅማችንን መተዋወቅ እንችላለን፡፡
?ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ እና አስተያየትዋን በጥንቃቄ አዳምጥ፡፡
?ስለ ት/ቷ፣ ስለ ምትወዳቸው ጉዳዮች ስለ ዲንና ስለ ጓደኞቿ ወዘተ… በማንሳት የአዕምሮዋን የብስለት ደረጃ መገመት ትችላለህ፡፡
??ሞኛ ሞኝ ሰው ጋር መጋባት በጣም አድካሚ የቤት ስራ የመውሰድ ያህል ነው፡፡ በአባባል ከሞኝ ጋር አትወዳጅ ሊጠቅምህ ፈልጎ ይጎዳሃልና ይባላል፡፡?ይህንን ስንል ራሳችንን በማጥራራትና ለሌሎች ዝቅ ያለ አመለካከት በማሳየት መሆን መሆን የለበትም እራሳችንም መለስ ብለን መፈተሸ ተገቢ ነው፡፡
?ረሱሉ (ሰ.ዐ.ወ) አላህ የሰጣቸውን እልቅናና ደረጃ በሌሎች ላይ የበላይ ለመሆን ወይም ሌሎችን ለማግለል አልተጠቀሙበትም። ብዙ ጊዜ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ባልደረቦቻቸውን እና ሚስቶቻቸውን ያማክሩ ነበር። ቤታቸው ሲገቡ እንደ ባል (መሐመድ )ነበር የሚሆኑት።የእሳቸው አስተያየት በወህይ ባልተነሳባቸው ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሚስቶቻቸውን በክርክር ውስጥ ያሳትፉ ነበር። በተለይ ሀፍሳ በጠንካራ አስተያየት እና ሀሳቧን ለመግለጽ ፈቃደኛ በመሆን ትታወቅ ነበር።
??♂️??በተመሳሳይ፣ አጋሮች ሌላውን ለመቆጣጠር ዲግሪ፣ እድሜ ወይም ሌላ ሁኔታዎችን መጠቀም የለባቸውም።
?"እኔ የበለጠ አውቃለሁ" የሚለው አመለካከት ወደ ኃይልና ግጭት ሊያመራ ይችላል፡ የስልጣን የበላይነትን ለማሳየት አላስፈላጊ ፉክክር ውስጥ ሊከት ይችላል፡???ብዙ የተማሩ ሴቶች ባለሙያ የመሆን ፍላጎት አላቸው፤ አንዳንዶች ደግሞ ፍላጎት የላቸውም፡፡ አንዳንድ ሴቶች እቤት ውስጥ መቆየታቸው ስራቸውን/ትምህርታቸውን እንደሚያባክን ያምናሉ እናም እርካታ እንዲሰማቸው ለማድረግ መስራት ይፈልጉ ይሆናል፡፡ ሌሎች የተማሩ ሴቶች ከቤት ውጭ ለመስራት ፍላጎት ላይኖራቸው ይችላል።
??♂️ብዙ ወንዶች የተማረች ሴት ቢፈልጉም፣ እሷ ግን ባለሙያ (ፕሮፌሽናል) እንድትሆን ላይፈልጉ ይችላሉ። ሌሎች ወንዶች ሚስታቸው ከመጀመሪያው ጀምሮ ባለሙያ ትሆናለች የሚል ጠንካራ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል። ሁሉም የበላይነት ስሜትን ሳያንፀባርቁ ማስኬድ ይቻላል። ??ለዚህም ነው የትዳር አጋርን ለመምረጥ ስናስብ በዚህ ጉዳይ ላይ ልናተኩር የሚገባው።
ይቀጥላል…
በኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሚንበር ቲቪ ዘወትር ማክሰኞ
ምሽት 2:30-3:30
?ሌላው የምንኖርበት ማህበረሰብም መረሳት የለበትም፡ አንድ ከመቶ ሙስሊም በሆነበት ሀገር የሚኖሩ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች 99 ከመቶ ሙስሊም ማህበረሰብ እንዳለበት አካባቢ እኩል የኢማን ደረጃ (እኛ ደረጃ መዳቢ ባንሆንም) ልንጠብቅባቸው አንችልም፡ መሰረታዊ የኢስላም መርሆዎች ግን ለምሳሌ ፈርድን (ግዴታዎችን) መስራትና ከባኢረዙኑብን (ታላላቅና አጥፊ ወንጀሎችን) መቆጠብ፡ ትንሹ ስታንዳርድ ተደርጎ ሊወስድ ይችላል፡፡
?ሌላው ሙስሊሞች በጣም አናሳ ቁጥር ባላቸው አካባቢ የሚኖሩና ሊጋቡ የሚያስቡ ወንድምና እህቶች በዚህ የዲን ግንዛቤ ላይ በአግባቡ ቢነጋገሩና ቢግባቡ መልካም ነው፡፡ እኔ ይህን ያህል አጥባቂ አልመሰለቺኝም፤ አልመሰለኝም በማለት የሚያማርሩ ሰዎችን ማግኘት ሊያስደነግጥ ይችላል፡፡ እኔ የምፈልገው ለዘብተኛ ሙስሊም እንጂ ሁሉንም ነገር የሚያጠባብቅ መሆኑን ብረዳ አልገባበትም ነበር የሚሉ ባለትደሮች ተገኝተዋል፡ ስለሆነም መርሆዎቹን በግልጽ ማስቀመጥና የት ድረስ እንደምንጠብቅ ማሳወቅ ቀድሞ ነው፡
??ከላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ወንዱንም ሴቱንም መመልከታቻቸው እንዳለ ሆኖ የሴት ልጅ ቤተሰቦች በተለይ ወንዱን ለማወቅና ስለ ባህሪው ለመረዳት ልጃቸውን ሊያግዙ ይገባል፡ ኢማም ሻእፊይ ፡ ፋሲቅ ሰውን ልጁን የዳረለት ከሆን በእርግጥ ዝምድናዋን ቆርጦዋል ብለዋል፡፡ ፋሲቅ (አመጸኛ) ሰው ደግሞ ባል መሆን አይችልም፡ ፊስቁ መከራዋን ነው የሚያበላትና የወልዮች ሚና በተለይ በዚህ ቦታ ይፈለጋል፡፡
ይቀጥላል…
በኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሚንበር ቲቪ ዘወትር ማክሰኞ
ምሽት 2:30-3:30
በአላህ ስም እጅግ አዛኝ ሩህሩህ በሆነው
ተጣማሪን መምረጫ መስፈርቶቸ
ክፍል(3)
2ኛ፡- ሳሊህ መሆን
•??♂️??ሙስሊሞች የትዳር ጓደኛ ከማግኘታቸው በፊት ሃይማኖታዊ ማንነትን ቅድሚያ እንዲሰጡ መልክተኛው (ሶ.ዐ.ወ) በአበክሮ ተናግረዋል።
??አንድ ወንድ ሴት ልጅዎን ለማግባት ቢፈልግ እና ስነምግባሩ ጥሩ ከሆነ እና ለሃይማኖቱ ያለውን ታማኝነት ካረጋገጣችሁ ዳሩለት ያለበለዚያ ፈተናዎች እና ጉልህ የሆነ ብክለት በአለም ላይ ይሰራጫል ብለዋል።
?ይህ ሐዲሥ አላህን የመፍራት እና የመልካም ባህሪ አስፈላጊነትን አጉልቶ የሚያሳይና አንድ ሰው ሙሉ በሙሉ ህይወቱን ወደ ወዲያኛው ዓለም በትኩረት መምራት እንዳለበት ያሳያል።
?ብዙ ሙስሊሞች ሃይማኖትን ከአምልኮ ጋር በተያያዙ ውጫዊ ድርጊቶች ለምሳሌ እንደ ሰላት ወይም ልብስ ስለመልበስ ብቻ አድርገው አቅልለው ያዩታል።
??♂️??ጥሩ ሙስሊም መሆን የእስልምናን ህግ ከመከተል ያለፈ ነገርን ይጨምራል።
?ጠንካራ መንፈሳዊ መሠረት መያዝንም ይጨምራል። ከአላህ (ሱ.ወ) ጋር ያለን ግንኙነት እና “መንፈሳዊነት” የሚለው ቃል ሁለቱም የሚያመለክተው የአምልኮን ውስጣዊ ገጽታ ነው። እርስ በርስ መተሳሰርን የሚገነዘቡ እና አላህን (ሱ.ወ) ለማስደሰት የሚጥሩ ሰዎች ደግ፣ አሳቢ እና አፍቃሪ በመሆን ግንኙነቶችን ለመፍጠር እና ለማጠናከር ይረዳሉ።
?ጋብቻን በተመለከተ ሰዎች ለሃይማኖታዊ እሴቶቻቸው ምን ያህል ትልቅ ቦታ እንደሚሰጡ እና ሃይማኖትን የሚገልፁበት መንገድ ይለያያል፡፡. ?አንዳንድ ሰዎች ማንኛውም ሁለት "ጥሩ" ሙስሊሞች መጋባት ደስተኛ ትዳር ሊኖራቸው ይችላል ብለው ያስባሉ፡፡ እውን ነገሩ ሁሉ እንደዚያ ነው ወይ የሚል ጥያቄ ማንሳታችን ግን አይቀርም።
⚖️የአንድን ሰው የመንፈሳዊነት (የኢማን) ደረጃ ለመለካት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል ምክንያቱም የልብ ጉዳይ ስለሆነ፡፡
?አብረው ጊዜ ማሳለፍ፣ የአንድን ሰው አመለካከት እና እምነት ለመወሰን የሚረዱ ጥያቄዎችን መጠየቅ እና ስለዚህ ሰው የሚያውቁትን ሌሎችን መጠየቅ የአንድን ሰው ባህሪ እና የሞራል ሁኔታ ለመገምገም ብቸኛው መንገዶች ናቸው።
?ውጫዊ ገጽታ ባህሪያትን እና አመለካከቶችን ከሚቀርፀው ውስጣዊ ኮምፓስ ጋር መመሳሰል አለበት።
??አንድ ሰው ከእስልምና ስርዓቶች (ኢባዳዎች ) አንፃር ሲታይ ሀይማኖተኛ ሆኖ ከስነምግባር አንፃር ግን ተሳዳቢ፣ ግትር፣ ስስታም ወይም ትምክህተኛ ሊሆን ይችላል።
?እንደ አለመታደል ሆኖ፣ በጣም ብዙ ሰዎች የኢስላም ውጫዊ ገጽታዎች ከእውነተኛው እስላማዊ ባህሪ ጋር ሲምታታባቸው እናያለን። ሙስበሀን መያዝ፣ ጀለቢያና ኮፊያ ማድረግ፡ ሂጃብ መልበስ ወይም ረጅም ፂም መያዝ አንድ ሰው ጥሩ ባህሪ እንዲኖረው ዋስትና አይሆንም።
?አንዳንድ ሰዎች ከእውነተኛው ኢስላማዊ ባህሪ ይልቅ እነዚህን ውጫዊ የእስልምና ገጽታዎች መተግበር በጣም ቀላል ሆኖ አግኝተውታል።
?እስልምና እንደማንኛውም ሀይማኖት በተለያየ ዲግሪ እና በተለያዩ ትርጓሜዎች ሊተገበር ይችላል። በሙስሊሞች መካከል እንኳን ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ።ትዳር ቀጥተኛ አመለካከት ባለው ሰው እና የበለጠ ሚስጥራዊ አመለካከት ባለው ሰው መካከል በአኗኗር ምርጫዎች ልዩነት የተነሳ እንዲሁም እርስ በርስ ሊጋጩ በሚችሉ አመለካከቶች እና እምነቶች የተነሳ አንዱ ለአንዱ ጥሩ ምርጫ ላይሆን ይችላል።
?ከኛ ጋር ተስማሚ ሊሆኑ ስለሚችሉ የትዳር ጓደኞች ሁሉንም ነገር ማወቅ ከጋብቻ በኋላ ምንም አይነት አስደንጋጭ ነገር እንደማይኖር ዋስትና አይሆንም። ምክንያቱም ስለ አንድ ሰው አንዳንድ ነገሮችን የሚማሩት ከእነሱ ጋር ሲኖሩ ብቻ ነው። ነገር ግን ከቅርብ ቤተሰብ እና ጓደኞች ዘንድ ስለነሱ መጠየቅ ትልቅና ድንገተኛ የብስጭት እድልን ለመቀነስ ይረዳል።
?በመሰረቱ በሙስሊም ህይወት ውስጥ ከሀይማኖት አንፃር ጥሩ ሙስሊም እንደሆኑ ለማወቅ በጣም አስፈላጊው ነገር ሁለት ነገሮች ናቸው።
?ኢስላማዊ መስፈርቶችን (እንደ ሰላት እና ፆም) ማሟላት እና ከባድ የሆኑ ወንጀሎችን ማስወገድ (እንደ ሽርክ፣ ግድያ፣ ዝሙት፣ ወዘተ)
??መልካም ሴት ለባሏ ጌጥ ናት ጀርባው ጥብቅ ነው መልእክተኛው ሰ.አ.ወ እጅህ አፈር ይንካና ዲን ያላትን ምረጥ ማለታቸው ለዚህ ነው “ዱኒያ በሙሉ መጠቀሚያ ናት ከነዚህ መልካሙ ወይም በላጩ ደግሞ መልካም ሴት ወይም ሚስት ናት ብለዋል
??ከዱንያ ምርጡ ወይም በላጩ መጠቀሚያ ሲባል ከስራህም ከዩኒቨርስቲ ዲግሪዎችህ ወይም ሰርተኪፌቶችህ፡ ከድርጅትህ፣ ከካምፓኒህ ከገንዘብህ ሁሉ መልካም ሚስት ትበልጣለች ማለት ነው፡፡
??አንድ የአላህ ባሪያ ከተቅዋ ቀጥሎ የሚጠቅመው ነገር ካለ ካዘዛት መርሀባ የምትለው፣ ሲያያት የምታስደስተው ቢምልባት የምታጠራው፣ርቆ ቢሄድ ነብሷንም ገንዘቡንም በታማኝነት የምትጠብቅ ሴት ብትሆን እንጂ፡፡
??♂️አንድ ወጣት አንዲት እኩያው ጋር ተዋደዱ እና አገባት እየዘረዘርን ያለውን ጉዳይ ባብዛኛው ከግምት አልከተተም ነበርና ከጥቂት ጊዜ ቆይታ በኋላ ከጎረቤቱ ሰውዬ ጋር ትስስር እንዳላት አወቀና በድንጋጤም ተዋጠ፡ እናም የታለ ታዲያ ፍቅራቸው የጠቀማቸው? ?ለሚስትነት አፍቃሪ መሆን ብቻ አይበቃም የራሷንም የባሏንም ክብር የምትጠብቅበት የበጎነት ባህሪ ሊኖራት ይገባል፡፡
?ከላይ ያለውን መስፈርት (መልካም ሴት) ብዙዎቻችን ጋር ፈጥኖ የሚመጣው ሀሳብ ሂጃቧን በደንብ የምትለብስ ሰላት እና ፆም ላይ ጎበዝ፣ቁርአን እና አዝካር የምትለዋን ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡ በመልክተኛው ሀዲስ ላይ በዝርዝር የተቀመጡ አራት መስፈሪያዎች ናቸው፡፡
?ሲያዛት የምትታዘዝ
?ሲያያት የምታስደስተው
?ሲምልባት የምታጠራው
?ርቆ ሲሄድ በነብሷም በገንዘቡም ታማኙ ናት (እምነት የማታጓድለው፡)፡ ስለሆነም ሁሉም ሙስሊም ሴት መረዳት ያለባት እውነታ የሷ መልካምነት መገለጫዎች ከላይ የተጠቀሱት ነጥቦች ናቸው፡፡ ማለትም ለባሏ ታዛዥ የምትሳመር፡ መሃላውን የምትሞላለትና ነፍሷና ገንዘቡን ባለበትም በሌለበትም የምትጠብቅ ታማኝ መሆኗ ነው፡፡ በእርግጥ ሒጃብ ሰላት ፆምና ባጠቃላይ የግዴታ ኢባዳዋን የምትተገብር መሆኗ ሳይረሳ ማለት ነው፡፡
??እዚህ ጋር ትኩረት የሚያሻው ነጥብ አለ፡ ማናችንም ብንሆን የመልካም ሰውነት ጥጉን አንደርስም፡ ኢማን የምንለው ነገርም ፕሮሰስ (ሂደት እንጂ፡ ሙስሊም ስለሆንን ሙእሚን አውቶማቲካሊ አንሆንም፡
•قَالَتِ الْاَعْرَابُ اٰمَنَّا ۗ قُلْ لَّمْ تُؤْمِنُوْا وَلٰكِنْ قُوْلُوْٓا اَسْلَمْنَا وَلَمَّا يَدْخُلِ الْاِيْمَانُ فِيْ قُلُوْبِكُمْ ۗوَاِنْ تُطِيْعُوا اللّٰهَ وَرَسُوْلَهٗ لَا يَلِتْكُمْ مِّنْ اَعْمَالِكُمْ شَيْـًٔا ۗاِنَّ اللّٰهَ غَفُوْرٌ رَّحِيْمٌ ا:
•የዐረብ ዘላኖች «አምነናል» አሉ፡፡ «አላመናችሁም፤ ግን ሰልመናል በሉ፡፡ «እምነቱም በልቦቻችሁ ውስጥ ገና (ጠልቆ) አልገባም፡፡ አላህንና መልክተኛውንም ብትታዘዙ ከሥራዎቻችሁ ምንንም አያጎድልባችሁም፡፡ አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና» በላቸው፡፡[ሱረቱል ሁጁራት ፡ 14]
??♂️??ወደ ኢማንናኢህሳን ደረጃ መድረስ ገና ወጣት ለሆኑ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁ ቀላል አይመስለኝም፤ የኢስላም የመነከር ጉዳይ እድሜ ልክ የሚሰራ፤ ልፋትና ጥረት ከፍላጎት ጋር የሚፈልግ ነገር ነው፡፡
በአላህ ስም እጅግ አዛኝ ሩህሩህ በሆነው
ተጣማሪን መምረጫ መስፈርቶች
ክፍል(2)
1. ኢስላም
•ሙስሊም የሆነ ግለሰብ ሙሽሪክ (ጣኦት አምላኪ) ሴትንም ሆነ ወንድን ማግባት ፈፅሞ አይፈቀድለትም፤ የፈለገውን ያህል ውብና ድንቅ ብትሆንም ንግግሯ ጣፋጭ ፈገግታዋም ማራኪ ቢሆንም፡
•وَلَا تَنكِحُوا۟ ٱلْمُشْرِكَـٰتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ وَلَأَمَةٌۭ مُّؤْمِنَةٌ خَيْرٌۭ مِّن مُّشْرِكَةٍۢ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ ۗ وَلَا تُنكِحُوا۟ ٱلْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا۟ ۚ وَلَعَبْدٌۭ مُّؤْمِنٌ خَيْرٌۭ مِّن مُّشْرِكٍۢ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ ۗ أُو۟لَـٰٓئِكَ يَدْعُونَ إِلَى ٱلنَّارِ ۖ وَٱللَّهُ يَدْعُوٓا۟ إِلَى ٱلْجَنَّةِ وَٱلْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِۦ ۖ وَيُبَيِّنُ ءَايَـٰتِهِۦ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ
•(በአላህ) አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው፡፡ ከአጋሪው (ጌታ) ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው፡፡ እነዚያ (አጋሪዎች) ወደ እሳት ይጣራሉ፡፡ አላህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምሕረት ይጠራል፡፡ ሕግጋቱንም ለሰዎች ይገልጻል እነርሱ ሊገሰጹ ይከጀላልና፡፡ በቀራ ፡- 221
•እናም አንድ ሙስሊም ወጣት ከጣኦት አምላኪ ወይም እምነት አልባ ከሆነች ሴት ጋር የትም ቢሆን መጋባት አይሆንም፡፡
•ለምሳሌ ለት/ትም ይሁን ለስራ ወደ ተለያየ ዓለም የሚጓዙ ወንድሞች ይህ ጉዳይ ሊገጥማቸው ይችላል በስራ/ በት/ት ምክንያት መቀራረቡ ቢከሰትና ላግባት/ላግባው ብሎ ማሰብ ይፈጠራል፡፡ ምንም ያህል ብትስብህና ብትማርክህ (ለሴትም ቢሆን) ከኢስላም አንጻር ከባድና ስህተት የሞላበት ውሳኔ ነው የሚሆነው፡፡
•መርሰደል ገነዊ ደስ የሚል ታሪክ አለው እዚህ ጋር ጠቀስ ብናደርገው ያስተምራል፡፡ ትልቁ ሰው መርሰድ ከመስለሙ በፊት አናቅ ከምትባል የመካ ሴት ጋር ትስስር (ግንኙነት) ነበረው፡፡)፡፡
•ቲርሚዝ አብደላ ኢብኑ አምር ኢብኑል አስን ጠቅሰው ታሪኩን እንዲህ ዘግበውታል፡፡ መርሰድ ኢብኑ አቢ መርሰድ የሚባል ሰው ነበር የመካ ምርኮኞችን በለሊት እየገባ በማስመልጥ መዲና ድረስ ይዟቸው ይመጣ ነበር፡ በመካ ሲኖር አንዲት አናቅ የምትባል ሴተኛ አዳሪ ሴት ጓደኛው ነበረች፡፡ አንድ ቀን አንድ ምርኮኛ ሰውን ሊያስመልጠው ቀጥሮት ነበርና ወደዚያው ሰፈር አቅንቶ ሳለ የገጠመውን ሁኔታ እራሱ ይተርካል፡-
•በአንድ ጨረቃማ ሌሊት ከመካ ቤቶች (ግድግዳ) በአንዱ ተጠልዬ ሰውዬዬን እየጠበኩት ሳለ በድንገት ወደ ቆምኩበት አናቅ መጣችና በጥላዬ አወቀቺኝና
??♀️መርሰድ
ብላ ተጠራች
??አቤት መርሰድ ነኝ
አልኳት
??♀️እንኳን ደህና መጣህ (አህለን ወመርሀበን) እኛ ቤት እንሂድና ማደር አለብህ
አለችኝ እኔም
??አናቅ ሆይ አላህ ዚናን እርም አድርጎታል አልኳት፡፡
ከዚያም
??♀️እናንተ ሰዎች ሆይ ይሄ ሰውዬ ምርኮኞቻችሁን ይዞ ሊጠፋ ነው
ብላ ጮኸች
ስምንት ሰዎች ይከታተሉኝ ጀመር ኸንዳማ ከሚባለው ተራራማ መንገድ ሮጬ አንድ ዋሻማ ጉድጓድ ውስጥ ገባሁ እየተሯሯጡ መጡና ከጉድጓዱ ጫፍ ላይ ቆመው ሽንታቸውን በአናቴ ላይ ለቀቁት እኔን ከማየት ግን አላህ ጋረዳቸውና አመለጥኩኝ፡ ከዚያም ወደ ቄያቸው ተመለሱ እኔም ወደ ቀጠርኩት ወፍራም ሰውዬ ተመልሼ እያደከመኝም ቢሆን መዲና አደረስኩት።
•ከዚያም ወደ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ሄድኩና
??አናቅን ላግባት አልኳቸው
መልስ ሳይሰጡኝ ቀሩ ወድያው መጡና ያመርሰድ
•اَلزَّانِيْ لَا يَنْكِحُ اِلَّا زَانِيَةً اَوْ مُشْرِكَةً ۖوَّالزَّانِيَةُ لَا يَنْكِحُهَآ اِلَّا زَانٍ اَوْ مُشْرِكٌۚ وَحُرِّمَ ذٰلِكَ عَلَى الْمُؤْمِنِيْنَ
•ዝሙተኛው ዝሙተኛይቱን ወይም አጋሪይቱን እንጂ አያገባም፡፡ ዝሙተኛይቱንም ዝሙተኛ ወይም አጋሪ እንጂ አያገባትም፡፡ ይህም በምእምናን ላይ ተከልክሏል፡፡[ሱረቱል ኑር ፡ 14]
የሚለውን ቀሩና እንዳታገባት አሉኝ፡፡
•ስለዚህ ለአንድ ሙስሊም ሙሽሪክ ወይም እምነት የለሽ ሰውን ማግባት እርም ሆኖበታል፡፡
•እዚህ ጋር የአህለል ኪታብ (የአይሁዳና የክርስታኖች ጉዳይ መነሳቱ አይቀርም እንደተጠቀሰው ፍቃድ ስላለበት ማለት ነው፡፡
•يٰٓاَيُّهَا الَّذِيْنَ اٰمَنُوْٓا اَوْفُوْا بِالْعُقُوْدِۗ اُحِلَّتْ لَكُمْ بَهِيْمَةُ الْاَنْعَامِ اِلَّا مَا يُتْلٰى عَلَيْكُمْ غَيْرَ مُحِلِّى الصَّيْدِ وَاَنْتُمْ حُرُمٌۗ اِنَّ اللّٰهَ يَحْكُمُ مَا يُرِيْدُ
•ዛሬ መልካሞች ሁሉ ለናንተ ተፈቀዱ፡፡ የእነዚያም መጽሐፍን የተሰጡት ሰዎች ምግብ (ያረዱት) ለእናንተ የተፈቀደ ነው፡፡ ምግባችሁም ለነሱ የተፈቀደ ነው፡፡ ከምእመናት ጥብቆቹም ከእነዚያ ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡት ሴቶች ጥብቆቹም፤ ዘማዊዎችና (ዝሙተኞች) የምስጢር ወዳጅ ያዢዎች ሳትኾኑ ጥብቆች ኾናችሁ መህሮቻቸውን በሰጣችኋቸው ጊዜ (ልታገቡዋቸው የተፈቀዱ ናቸው)፡፡ ከእምነትም የሚመለስ ሰው በእርግጥ ሥራው ተበላሸ፡፡ በመጨረሻም ቀን እርሱ ከከሳሪዎቹ ነው፡፡[ሱረቱል ማኢዳህ 5]
ይቀጥላል…
በኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሚንበር ቲቪ ዘወትር ማክሰኞ
ምሽት 2:30-3:30
በአላህ ስም እጅግ አዛኝ ሩህሩህ በሆነው ተጣማሪን መምረጫ መስፈርቶች
መግቢያ ክፍል(1)
ለራስህ ጥሩ አጋር የማግኘት ሂደቱን ለመጀመር በአንተ/ቺ መርሆች እና ቅድሚያ በምትሰጣቸው ነገሮች ላይ ለማሰብ ብቻ ጊዜ ማሳለፍ አስፈላጊ ነው።
?ከአንተ/ቺ ጋር በጣም ሊስማሙ የሚችሉ የሰው ዓይነቶች እና በጣም ምቹ የሆኑትን የስብዕና ዓይነቶችን ግምት ውስጥ አስገባ/ቢ።
?የአንተን/ቺን እሴቶች እያሰብክ ከትልቁ ጀምራችሁ በቅደም ተከተል ጻፉት፤የማትደራደሩበትን ወይም ያለሱ መኖር የማትችሉትን እሴቶች (ኮር ቫልዩስ) ያድምቁ።
?በመቀጠል በትዳር ጓደኛህ ውስጥ የምትፈልጓቸውን ባህሪያት ዝርዝር አዘጋጁ ደረጃም አውጡላቸው እና አስፈላጊ የሆኑትን ጎላጎላ ባለ መስመር ጻፉት.
?ከዚያም፣ በደንብ ከሚያውቃችሁ የቤተሰብ አባላት እና ጓደኞች ጋር ተነጋገሩ፡ ስለአንተ/ቺ ያላቸውን ስሜት እንዲገልጹ ጠይቋቸው፣ በተለይም አንተ ከፍተኛ ዋጋ ስለሰጠሃቸው ገዳዮች ያላቸውን አስተያየት ጠይቅና ግብረመልሳቸውን ውሰድ፡ በእርግጥስ ለአቅመትዳር የደረስክ/የደረሽ ይመስላቸዋል፡ ትዳርን ለመመስረት በሚያስፈልገው ቁመና ላይ እንደሆንክ/ሽ ይሰማቸው እንደሆነ በግልጽ ጠይቃቸውና ስሜታቸውን በነጻነት እንዲያጸባርቁ ጠይቋቸው፡፡
?የራስህንም ጥንካሬና ድክመት ከግምት ውስጥ አስገባ፡
??♂️ባል ብሆን ለሚስቴ ምን ልሰጣት እችላለሁ፡ በምን ምክንያትስ ላስከፋትና ላልመቻት እችላለሁ፡ ብሎ ከራስ ጋር ማውራት ደግ ነው፡
??እህትም እንዲሁ እውን ሚስት ለመሆን ዝግጅቱ (ውጫዊውም ውስጣዊውም) ዝግጅት አለኝ ብለሽ እራስሽን በታማኝ ሚዛን ላይ አስቀምጠሸ እይው፡
?ይህን ሁሉ ውጣውረድ ለምን አመጣህ ልባል እንደምችል እገምታለሁ፡ መልሴ
??የሰው ልጅ በሕይወቱ ከሚወስናቸው ትላልቅ ውሳኔዎች መካከል የትዳር አጋሩን መምረጥ ነው፡፡ የህይወቱ አጋር፣ የልጆቹ እናት/አባት የሚመርጥበት ሂደት ከባዱ እና ትልቁ የውሳኔ አጋጣሚ ነው፡፡ ምክንያቱም ረጅሙ የህይወት ክፍል በዚህ ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ የዚህን ውሳኔ ውጤት ተከትሎ መደሰት ወይ ተቃራኒ ሊገጥመው ይችላል፡፡ ስለሆነም ተቻኩሎ ከመወሰኑ በፊት ከራሱ ጋር ጊዜ ወስዶ ማሰብ፣ ከአዋቂዎች ጋር መምከር አለበት ጌታውንም ጠለቅ ብሎ መለመን አለበት (ኢስቲኻራ ማድረግ አለበት)
አንዳንዴ የፊልምና የድራማው ዓለም ምርጫውን ቀለል አድርጎ የሚያቀርብበት አጋጣሚ አለ አንዴ በጓደኝነት ሌላ ጊዜ በድንገት፣ የአይን ፍቅር፣ በአድናቆትና ተያያዥ አጋጣሚዎች ወጣቶች ፍቅር ይዟቸው በዚያው እንደተጋቡ ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡ በዚህም ወጣቶችን ሳያውቁም ሆነ አውቀው በዚሁ አቅጣጫ እንዲፈሱ ለማድረግ ስራን ይሰራሉ፡፡
አድናቆት ብቻውን አይበቃም ጣፋጭ የፍቅር ቃላትን መለዋወጥ ብቻውን ለዚህ ከባድ ውሳኔ በቂ ግብአት አይደለም ምክንያቱም ሕይወት በስሜት ትስስር ብቻ የምትፈስ ወንዝ አይደለችምና፡፡ አላህም እንዲህ ይላል “ጌታችን ሆይ በዚህ ዓለም በቀጣይም ዓለም በጎ ነገርን ለግሰን……” ሰይዲና አሊይ “ፊዱኒያ ሀሰነተን” ማለት መልካም ሚስት ማለት ነው ብለው ተርጉመውታል በአኼራ ደግሞ ሁረልአይን ነው ብለዋል “ወቂና አዛበናር” ከመጥፎ ሚስት ነው ብለዋል፡፡
መልካም ተጣማሪ ማግኘት በዱንያ ላይ ሰላምና ደስታ ሲያጎናፅፍ መጥፎ ምርጫ ደግሞ ውጥንቅጥ መከራና ድካምን ይዞብህ መምጣቱ አይቀርም፡፡ አላህ ይጠብቀንና
መልካም ሚስትና ሙዕሚን የሆኑ ልጆች ቀጣዩ ዓለምም ከእትና አባት ጋር የሚሰበሰቡ መሆኑን አላህ ነግሮናል፡፡
ادْخُلُوا الْجَنَّةَ أَنتُمْ وَأَزْوَاجُكُمْ تُحْبَرُونَ
«ገነትን ግቡ እናንተም ሚስቶቻችሁም ትደሰታላችሁ ትከበሩም አላችሁ» (ይባላሉ)፡፡[ሱረቱል ዙህረፍ ፡70]
وَٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ وَٱتَّبَعَتۡهُمۡ ذُرِّيَّتُهُم بِإِيمَٰنٍ أَلۡحَقۡنَا بِهِمۡ ذُرِّيَّتَهُمۡ وَمَآ أَلَتۡنَٰهُم
مِّنۡ عَمَلِهِم مِّن شَيۡءٖۚ كُلُّ ٱمۡرِيِٕۭ بِمَا كَسَبَ رَهِينٞ
እነዚያም ያመኑትና ዝርያቸውም በእምነት የተከተለቻቸው ዝርያቸውን በእነርሱ እናስጠጋለን፡፡ ከሥራቸውም ምንም አናጎድልባቸውም፡፡ ሰው ሁሉ በሠራው ሥራ ተያዢ ነው፡፡[ሱረቱል ጡር ፡ 21]
?ስለሆነም ተጣማሪን ለመምረጥ መረጋጋት፣ ማስተዋል መመካከርና ኢስቲኻራ የሚያስፈልገው ትልቅ አጀንዳ ነው፡፡ የስሜት ግፊት በዚህ ውሳኔ ላይ ተቀባይነት የለውም ወይም ከዚህ በታች የምንዘረዝራቸውን መስፈርቶች ከግምት ሳይከቱ ልቤ ወዷታል ማለት ዋጋ የለውም፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፡፡ “ለዚህ ፍሬያችሁ የምታኖሩበትን ስፍራ በጥንቃቄ ምረጡ እኩዮችን አጋቡ ለሴቶቹም እኩዮቻቸውን አጋቡዋቸው“ ኡስማን ኢቢልአስ የሚባል ሰሃባ ልጆቹን፣እንዲህ ይላቸው ነበር፡፡ ጋብቻ አድራጊ ሰው እንደ ገበሬ ነው ገበሬ ደግሞ ቡቃያውን የት እንደሚተክለው ያስተውላል፡ መጥፎ ዝርያ ጥሩ ፍሬ የሚሰጥበት እድል በጣም ጠባብ ነው፡፡”
??ወደ ዝርዝር መስፈርቶች ከመግባታችን በፊት የሚከተሉት ጥቂት ነጥች ማስታወሻ ተደርገው ይወሰዱልኝ፡እየተዘረዘሩ ካሉት ነጥቦች መካከል የኔ ሚስት ወይም ባል የትኛውን ነው አሟልታ/አሟልቶ ያገባሁት እያልን መብሰልሰል ዋጋ የለውም፡ ባይሆን፡-
1ኛ. አላህ የሰጠንን ወደን መቀበል፡- አንተ ገይብን (የሩቅ) ማወቅ ቢሰጥህ ኑሮ አሁን ያለውን ነበር የምትመርጠው፡፡
2ኛ. ለባለቤትህ/ሽ በርህራሔና በመልካም ዘዴ አስተምራት/ሪው፣ ስታነብ ለምሳሌ አንዱን ጉዳይ ግልፅ ድክመት ሆኖ ሊታይህ ይችላል ያንኑ ጉዳይ (ምሳሌ ንፅሕና ቢሆን) ከዱዓው ጎን ለጎን ብታስተምራት በዘዴ ልትቀየር/ ሊቀየር ትችላለች/ይችላል፡፡
3ኛ. እውቀትና ተሞክሮ የሚገኝባቸው የእውቀት መድረኮች ላይ ለመገኘት ሞክሩ፡ ይህ ስፍራ የአላህ ራህመት የሚወርድበት ቦታ ነው፡፡ ከሰማዩ ጀነት በፊት የምድር ላይ የጀነት ጨፌም ነው፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ተጣማሪዎቻችንን ከመምረጣችን በፊት ከግምት ከተን ማሳብ ያሉብንን ነጥቦች በዝርዝር እናያለን፡ ሀሳቦቹ የመጨረሻና ያለቀላቸው ናቸው ብዬ አላስብም፡ ሰው የራሱ ብዙ ፍላጎቶች ሊኖሩት ይችላል፡ በተጨማሪም የተወሳሰበ መስፈርት በመደርደርም ጋብቻን ማወሳሰብም ተገቢ አይደለም፡ ግና የህይወት አጋርንም መምረጥ ትልቅ ቁም ነገር መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለበትም፡፡
ይቀጥላል…
በኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሚንበር ቲቪ ዘወትር ማክሰኞ
ምሽት 2:30-3፡30
??♂️??በእርግጥ አብሮ በመቆየትና በሒደት ግን የመቀራረብ እድላቸው እየጨመረ ይመጣል አንዱ ሌላውን መረዳትና መግባባቱ እያደገ ሲሄድ የልዩነት ነጥቦች ደግሞ እየጠበቡና እያነሱ ይሔዳሉ፡፡ የትዳር ተጣማሪን ባለበት ሁኔታ ተቀብሎ ለመኖር እራስን ማዘጋጀት ብልህነት ነው፡፡ የሚመሰረተው ቤት ከአደጋ ለመከላከል እጅግ ስለሚረዳው::
??♂️??አንዳንድ ጥናቶች ባልና ሚስት ረዘም ላለ ጊዜ አብረው ከመኖራቸው የተነሳ ብዙ ነገራቸው እየተመሣሠለ ሄዶ በመጨረሻም አካሔዳቸውና ቁመናቸው ጭምር እንደሚመሣሰል ይገልፃሉ፡፡
•“ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳሉ” ማለትም ይኸው ነው፡፡
??♂️??ስለባልና ሚስት ልዩነት ወደፊት በተለያዩ ርእሰጉዳዮቻችን እየተመላለስን ግንዛቤ ለመፍጠር የቻልነውን ያህል ስለምንሞክር ለጊዜው እዚህ ላይ እናቁም።
በኡስታዝ አብዱልገፋር ሸሪፍ
ሚንበር ቲቪ ዘወትር ማክሰኞ
ምሽት 2:30-3:30
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana