ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
‹‹አዎ አባዬ ያንተው ልጅ ነኝ…ዘላለም ካአንተ መለየት አልችልም…እማዬ እኔ ልጅሽ ነኝ››ሶስቱም አንድ ላይ አርስ በርስ ተቃቅፈው ለበርካታ ደቂቃ ተላቀሱ ..በመከራ ነበር አካባቢውን የለቀቁት…ሁሉም የቤተክርስቲያኑ በራፍ ላይ ተሰብስበው እየጠበቋቸው ነበር….ግን በፊት ከነበሩት በተጨማሪ የበፀሎት እናትና አባት ልዩ አይነት ባስ መኪና አጠገብ ቆመው በራፍ ላይ ሲጠብቋቸው ነበር..ይሄ ደግሞ እነአቶ ለሜቻን ብቻ ሳይሆን በፀሎትንም ጭምር ነበር ያስደነቃት…እርስ በርስ ተቀራርበው ሰላምታ ከተለዋወጡ በኃላ ሁሉም በመኪና ውስጥ እንዲገቡ ተደረገ…በመኪና ውስጥ ጠቅላላ 25 የሚሆኑ ሰዎች ገቡ…ሹፌሩ መኪናውን ወደእነ አቶ ለሜቻ ቤት አቅጣጫ መንዳት ጀመረ…ቤታቸው ለመድረስ ግማሽ ኪሎ ሜትር ያህል ሲቀረው ግን ወደግራ ተጠመዘዘና አንድ ግቢው ውስጥ ገባ..ሁሉም ግራ ተጋባ….አቶ ኃይለልኡል መኪናው እንደቆመ በራፈ ከመከፈቱ በፊት ከተቀመጡበት ተነሱና መናገር ጀመሩ‹‹ ..ይቅርታ የማታውቁኝ ካላችሁ ኃይለልኡል እባላለሁ…የበፀሎት አባት ነኝ…በዛሬው ቀን በደም የተጣመሩ ሁለት ቤተሰቦች እዚህ ይገኛሉ ..የእኛና የአቶ ለሜቻ ቤተሰብ፡፡ይሄ ሁለት ቤተሰብ የተሳሰረው ዛሬ አብራን በሌለችው በበሬዱና አጠገባችን ባለችው በፀሎት ነው፡፡የእኔ ልጅ ዛሬ በህይወት ያለችው ከበሬዱ በተሰጣት ልብ ነው፡፡እዚህ እነአቶ ለሜቻ ቤት ለሟች ልጃቸው የሙት አመት መታሰቢያ ሲከበር በእኛ ቤት ግን ለልጃችን ንቅለ-ተከላ ተደርጎላት ዳግም የመኖር እድል ስላገኘች ድል ያለ የምስጋና ድግስ እናዘጋጅ ነበር ..ዘንድሮ ግን በፀሎት ውሳኔ እንደዛ ማድረግ አልቻልንም…እዚህ ግቢ አንድ ላይ መታሰቢያውንም ምስጋናውንም አብረን እንድናከብር ወስነናል..አሁን ሁላችንም ወርደን የተዘጋጀውን ዝግጅት እንታደም፡፡››የሚል ንግግር ካሰሙ በኃላ በራፉ ተከፈተ …
ዛሬ እየሆነ ያለው ነገር በጠቅላላ ምንም ያልገባቸው አቶ ለሜቻና ወ.ሮ እልፍነሽ አቶ ኃይለልኡልንና ባለቤታቸውን ተከትለው ከባስ ወረዱ፡፡ይሄንን ሰፈራ የሚገኘው በገዛ ቀበሌያቸውና በሰፈራቸው ስለሆነ በደንብ ያውቁታል፡፡ግቢው ንብረትነቱ የቀበሌው ሲሆን ባለ5 ሺ ካሬ ግዙፍ ጊቢ ነው…ከመኪና ወርደው ሲመለከቱ ግቢው በሰዎች ታጭቆል ፡፡ ሰዎቹ ደግሞ አብዛኛው ጎዳና ተዳዳሪዎች፤የኔ ቢጤዎች የደከሙና የተጎዱ አቅመ ደካሞች…..ለአይን እንኳን ተቆጥሮ የማያልቅ የእንጀራ ክምር ..በበርሜል የተደረደረ ልዩ ልዩ የወጥ አይነት…ራቅ ብሎ ደግሞ በተንጠልጣይ ብረት ላይ የተደረደረ ጥሬ ስጋ እንደተራራ የተቆለለ የታሸገ ውሀ……
በሌላ ጎን ከአዳራሹ ፊት ለፊት ግዙፍ ፖስተር ይታያል…በፖስተሩ ላይ በቀኝ የበሬዱ ፎቶ በስተግራ ደግሞ የበፀሎት ፎቶ መሀከል ላይ የበሬዱ በፀሎት የምገባ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ይላል፡፡ብዛት ያላቸው ጋዜጠኛች ከወዲህ ወዲያ እየተዘዋወሩ ፎቶ ያነሳሉ ኢንተርቪው ያደርጋሉ፡፡
ማታ በሁለት ሰዓት ዜና ላይ በኢትዮጴያ ቴሌቭዝን የቀረበው ዜና የሚከተለው ነበር….
‹‹የታዋቂ የቢዝነስ ማን አቶ ሃይለልኡል ብቸኛ ልጅ ከጠፋችበት መገኘቷ ታወቀ…በፀሎት ከሶስት አመት በፊት ልቧ መስራት አቁሞ የነበረ ሲሆን በዛን ወቅት የመኪና አደጋ ደርሶባት አብራት ለህክምና ወደ ታይላንድ የሄደችው በሬዱ ለሜቻ ህይወቷ በማለፉ አባትዬው በሰጡት ፍቃድ መሰረት ልቧን ለበፀሎት በመለገሷ የልብ ንቅለ-ተከላ ሊደረግላትና ድና ወደሀገር ልትመለስ ችላለች…ባለፈው ወር የጠፋችው በፀሎት ኃይለልኡል የተገኘችው በእነዚሁ በአቃቂ ክፍለከተማ በሚኖሩት ልብ በለገሰቻት ልጅ ቤተሰቦች ቤት መሆኑ በጣም አነጋጋሪና አስደማሚ ታሪክ ሆነዋል፡፡
በዛሬው እለት የበሬዱ የሶስተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ የነበረ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ባለፉት ሁለት አመት እንደተደረገው በአቶ ኃይለልኡል ቤት የምስጋና ድግስ ሲደገስ የቆየ ቢሆንም..ዛሬ ግን ይሄ ቀርቶ አቶ ኃይለልኡልና ቤተሰባቸው በቤታቸው የደገሱትን ድግስ ሙሉ በሙሉ ሰርዘው በሞች በሬዱ ለሜቻ የትውልድ አካባቢ ለስሟ መታሰቢነት እንዲሆን ከዛሬ ጀምሮ በአካባቢው አቅም የሌላቸውና ችግረኞችን በቀን ሁለት ጊዜ የሚመግብ በሬዱ በፀሎት ምገባ ተቋምን ከፍተው ያስመረቁና በቦታውም ከ500 በላይ ሰዎችን በመመገብ ማስጀመራቸውን ማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህም የሞች አባት የሆኑት አቶ ለሜቻ ስለሁኔታው ሲናገሩ‹‹በእውነት ልጄ ዛሬ ሞትን ድል ነስታ እንደተነሳች ነው የምቆጥረው..ልጄ በህይወት እያለች ለተቸገረ ሁሉ የምታዝን የዋህ ነበረች..አሁንም ከሞተች በኃላ ይሄው በስሟ ብዙዎች ጠግበው እንዲያድሩ ምክንያት ስለሆነች ኮርቼለሁ….ይሄንን እውን ያደረጉትን አቶ ኃይለልኡል እና ባለቤታቸውን አመሰግናለሁ….የእነሱ ልጅ የሆነችው በፀሎት ለእኔም ልጄ ነች….ከአሁን በኃላ በሬዱ ሞተች ብዬ አላዝንም…. ስትናፍቀኝ በፀሎትን አቅፌ አፅናናለሁ…ደግሞ እዚህ ስፍራ መጥቼ በስሟ ሰዎች ምግብ ቀምሰው ሲያድሩ ተመልክቼ ረካለው››በመላት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል…የሚል ነበር፡፡
ከድግሱ በኃላ አቶ ኃይለልኡልና ወ.ሮ ስንዱ ወደቤታቸው ሲሄዱ በፀሎት ግን ለሊሴን ተከትላ ወደእነሱ ቤት ነበር የሄደችው…በማግስቱ ግን ቤተሰቡ በአጠቃላይ ተሰብስበው ወደቦሌ ሄዱ ፡፡ሲደርሱ ሰለሞንም ነበር….ይህ ዝግጅትና ግንኙነት ለሁለቱም ቤተሰብ ልክ እንደቅልቅል ነው፡፡በዚህ ደግሞ ቁጥር አንድ የፈነጠዘችው በፀሎት ነች፡፡የእሷን ደስታና ፈንጠዝያ ሲከታተል የነበረው ሰለሞን ‹‹እሺ ይህቺን ልጅ ለማግባት ልጃችሁን ስጡኝ ብዬ ሽማግሌ ምልከው ለየትኛው ቤተሰብ ነው፡፡ብሎ እራሱን ጠየቀና ፈገግ አለ፡፡‹‹ግድ የለም እሷ ትስማማ እንጂ እኔስ ሁለት የሽማግሌ ቡድን ማቋቋም አያቅተኝም፡፡›› ሲል ለራሱ መልስ ሰጠ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ፊራኦልም ከሰለሞን ጎን ተቀምጦ ፊት ለፊቱ በፀሎትን እየተመለከተ በውስጡ ‹‹እሺ አሁን የእህቴን ልብ ተሸክማ እህቴ ስለሆነች ልደሰት ወይስ. ፍቅሬን ተቀብላ ፍቅረኛዬ መሆን ስለማትችል ልከፋ?››በውስጡ የሚያመነዥገው ጥያቄ ነበር፡፡‹‹ፍቅሯ በዚሁ ቀጥሎ ከባሰብኝ ምንድነው የማደርገው?››በጣም ተጨነቀ፡፡
ተፈፀመ
ለቆይታችን አመሰግናለው…በሌላ ስራ እስክንገናኝ ደህና ሁኑልኝ!!
…..በጣም ነው የምወድህ……››አለችው
‹‹እኔም እህቴ በጣም ወድሻለው…አሁን እራት እየቀረበ ነው መሰለኝ ወደቤት እንግባ…››
‹‹እሺ እንግባ››ተባባሉና ተያይዘው ወደቤት በመግባት ከቀረው ቤተሰቡ ጋር ተቀላቀሉ፡፡
//
አቶ ለሜቻና ቤተሰባቸው በአጠቃላይ ሙሉ ትኩረቱ የበሬዱ የሶስተኛ አመት የሙት አመት መታሰቢያ ላይ ነው፡፡ይሄ ባለፈው ሁለት አመት በተመሳሳይ የመታሰቢያ ድግስ የተደገሰ ቢሆንም የዘንድሮ ግን በተለየ ሁኔታ ትኩረት ተሰጥቶታል ፡፡የዚህም ምክንያት በቤተሰቡ ውስጥ ተአምራዊ በሆነ መንገድ በፀሎት የምትባል ልጅ ስለተጨመረችና ከዛም ተያይዞ ከሞላ ጎደል የቤተሰቡ የገንዘብ ችግር ስለተሻሻለ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው ከፍ ባለ ሁኔታ ለመደገስና በሟቾ ስም በርከት ያሉ ችግረኞችን በማብላት ነፍስ ይማር በማሰኘት የተወሰነ የመንፈስ እረካታና የአእምሮ መረጋጋት ለማግኘት ጠንክረው በጥሩ ሞራል እየደገሱ ነው፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታ አቶ ኃይለልኡል ቤት በአይነቱ ለየት ያለ ድብልልቅ ያለ ድግስ እየተደገሰ ነው፡፡የእነሱ ምክንያት ደግሞ ሚያዚያ 20 ቀን የልጃቸው በፀሎት የልብ ንቅለተከላ ያደረገችበትና ሁለተኛ የመኖር እድል ያገኘችበት ስለሆነ ያንን ቀን በፌሽታና በምስጋና የማሳለፍ አላማ ያለው ነው፡፡ይሄንን ድግስ ያለፉትን ሁለት አመታት አድርገውታል፡፡ የዘንድሮው ግን በአይነትም ሆነ በመጠን ከፍ ያለ ነው፡፡ይሄም ዘንድሮ ሁኔታዎች የተለዩ
ስለሆኑ ነው፡፡ከቤታቸውም ከፊታቸውም የተሰወረችው የልጃቸው በፀሎት ከወር በኃላ ወደቤቷ ምትመለስበት ቀን ይሆናል የሚል ጉጉት ስላላቸው ልጃቸውን እጥፍ ድርብ በሆነ ፌሽታ ለመቀበል ያደረጉት ነው፡፡ከዚህም በተጨማሪ ሌላ የተለየ ምክንያት አላቸው ፡፡ባልና ሚስቶቹ ለአመታት ከገቡበት አስጠሊታ ግንኙነት እና የእርስ በርስ ጥላቻ ተገላግለው. ቀሪ ህይወታቸውን በመከባበር እና በፍቅር ለማሳለፍ ወስነውና ተስማምተው ቀሪ እንደአዲስ ለመጀመር የወሰኑበት ወቅት ስለሆነ ለእነሱም እንደ ዳግማዊ ሰርግ ነው…ለዛ ነው የተለየና እንከን አልባ ድግስ እንዲሆን እየጣሩ ያሉት…ያው እንደተለመደው የድግሱን ቅንጅት በሀላፊነት የወሰዱት ፕሮፌሽናል ባለሞያዎች ናቸው፡፡
የጭንቁ ቀን ደርሶል ፡፡አቶ ለሜቻና ወይዘሮ እልፌ ከሌሎች ጎረቤቶች ጋር በለሊት ነው ወደ ቤተክርስቲያን ሄደው ቅዳሴ የገቡት…በጸሎትን ጨምሮ ሌሎቹ ልጆች ግን ወደ ቤተክርስቲያን የሚወሰደውን ምግብና መጠጥ ሲያዘጋጁ ከቆዩ በኃላ አንድ ሰዓት ተኩል ሲል ዳቦ፤ እንጃራና ጠላውን በፒካፕ መኪና እስጭነው ቤተክርስቲያን በመውሰድ ለቄሶቹ የተዘጋጀውን ወደሰንበቴ ቤት አስገብተው ሌላውን ውጭ አስቀምጠው ቅዳሴው እስኪገባደድ መጠበቅ ጀመሩ ፡፡ልክ ቅዳሴው ተጠናቆ ሁሉም እንደወጣ አቶ ለሜቻና ወይዘሮ እልፌ ከቄሶቹ ጋር ወደሰንበቴ ቤት ቄሶቹንና ሌሎች ምዕመናንን ለማሰተናገድ ሲገቡ፡፡ በፀሎትና እና ለሊሴ ደግሞ ከሌሎች የሰፈር ወጣቶች ጋር በመሆን ቤተክርስቲያኑ የውጭ አጥር ጋር ተኮልኩለው ለሚገኙ የእኔ ቢጤዎችና፤ ምፅዋት ጠያቂዎች አንድ እንጀራ በወጥ ፤አንድ ጉማጅ ዳቦና አንድ ሀይ ላንድ ጠላ ለእያንዳንዱ እያደሉና ነፍስ ይማር እያስባሉ ካጠናቀቁ በኃላ ዕቃቸውን ሰብስበው እነአቶ ለሜቻ ከሰንበቴ ቤት እስኪወጡ መጠበቅ ጀመሩ…ሁሉ ነገር ከተጠናቀቀ በኃላ ቤተሰቡ ወደቤታቸው ከመመለሳቸው በፊት ቀጥታ ተያይዘው ወደበሬዱ መቃብር ነው የሄዱት፡፡የእሷ ምስል ያለበት ጥቁር ቲሸርት የለበሱት አስራ ምናምን ሰዎች የሀውልቱን ዙሪያ ገባ ከበው በዝምታ ሲፀልዩና አንዳንዱም ሲያነባ ከቀዩ በኃላ ሁሉም ቀስ በቀስ ስፍራውን እየለቀቁ ሄዱ…በመጨረሻ የቀሩት በፀሎት አቶ ለሜቻና ወ.ሮ እልፍነሽ ነበሩ፡፡
በፀሎት ይሄንን የልጅቷን ሀውልት ስታይ በጣም ትልቅ የሆነ ሀዘን ነው የተሰማት…‹‹በእሷ ምትክ..እኔ ነበርኩ እዚህ ስፍራ ከዚህ ሀውልት ስር መተኛት የሚገባኝ››ብላ ስታስበው እራሱ ዝግንን አላት…ልክ እንደሁል ጊዜውም የሌላን ሰው ህይወት ሰርቃ እየኖረች እንዳለች አይነት ስሜት ነው እተሰማት ያለው….የሚቀፍ አይነት ስሜት…›
አቶ ለሜቻ በዝምታ ሲያስተውሏት ስለቆዩ ያመማት መሰላቸው…‹‹ለማታውቃት ልጅ ይሄን ያህል ሀዘን ከየት የመጣ ነው?››በውስጣቸው ያብሰሰሉት ሀሳብ ነበር፡፡ በዝምታ ወደእሷ መጥተው ትከሻዋን በመያዝ…‹‹ልጄ በቃ እንሂድ ይበቃል››ሲሏት ከገባችበት ጥልቅ የመደንዘዝ ስሜት ባነነችና ቀና ብላ አየቻቸው…ትከሻዋን አቅፈው በፍቅር እየተመለከቷት ነው፡፡በሶስት ሜትር ርቀት ፈንጠር ብለው ወ.ሮ እልፍነሽ እያነቡ ይታዬታል…የአቶ ለሜቻን እጅ ያዘችና ‹‹አባዬ ና..››ብላ ወስዳ ከባለቤታቸው ጎን አቆመቻቸውና…ሁለቱም እግር ስር ድፍት ብላ አንድ አንድ እግራቸውን በመያዝ…‹‹አባዬ እማዬ እኔን ይቅር በሉኝ….በበሬዱ ይዣችኃለው ይቅር በሉኝ….ይቅር ካላላችሁኝ መኖር አልችልም….የእውነቴን ነው የምላችሁ ይቅርታችሁን ካላገኘው ሞታለው፡፡››ስትል ሁለቱም በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ…ምንም እየገባቸው አይደለም….‹‹ምን አጥፍታ ነው…?ምንስ ብታጠፋ ይቅርታ መጠየቂያው ቦታና ጊዜው ትክክል ነው?፡፡››በውስጣቸው የተፈጠረ ጥያቄ ነበር…ሁለቱም ግራና ቀኝ ትከሻዋን ይዘዘው ቀና ሊያደርጎት ሞከሩ ..ግን እልቻሉም፡፡
‹‹ይቅርታ ካላደረጋችሁልኝ አልነሳም››
‹‹ምን አጥፍተሸ ነው? ምንም አልገባንም እኮ››አቶ ለሜቻ ጠየቋት፡፡
‹‹አጭበርብሬችኃለው ..ዋሽቼያችኃለው..እኔ እናንተ ጋር የመጣሁት ከእንጀራ አባቴ ጠፍቼ አይደለም….››
‹‹እና ምን ሆነሽ ነው?፡፡››ወ.ሮ እልፍነሽ ጠየቁ፡፡
‹‹እኔ ማለት …የልጃችሁን ልብ በውስጤ ተሸክሜ የምዞር..በእሷ ምክንያት እየተነፈስኩ ያለው ልጅ ነኝ…..፡፡››
ሁለቱም የሚሰሙትን ለማመን አልቻሉም ..አቶ ለሜቻ ቀስ ብለው ትከሻዋን ይዘው አስነሷት…ፊቷን የተሻፋፈነችበትን ሻርፕ ቀስ ብለው ከላዮ ገፈፉና ጣሉት.. ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ ፊቷን ተመለከቱት‹‹አዎ እራሷ ነች››ትከሻዋን ያዙና ደረታቸው ላይ ለጠፏት…ግንባሯን፤ ጉንጮን፤ ፀጉሯን እየደጋገሙ ሳሟት‹‹….ልጄ አዎ አውቄው ነበር..አንቺ ወደቤቴ ያለምክንያት እንዳልመጣሽ ታውቆኝ ነበር….ከዛሬ ነገ ጥላኝ ትሄዳለች በሚል ስጋት ስሳቀቅ ነበር..አሁን ግን የራሴው ልጅ ነሽ የትም አትሄጂም..አዎ የራሴው ልጅ ነሽ››ተንሰፈሰፉላት….ፍፁም ያልጠበቀችውን ምላሽ ነው ያገኘችው፡፡
የመጨረሻ ክፍል
ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሀያስምንት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ድክምክም ብሎታል፡፡ግን ደግሞ አልጋው ላይ ተኝቷ በሀሳብ እየተንገላታ ነው፡፡ ሰለሞን በሁለት በኩል ስለት ባለው ሰይፍ የሚጫወት ህፃን አይነት ሰው እንደሆነ እየተሰማው ነው፡፡ሞያውን በተመለከተ ለሶስት አመት በከፍተኛ የፕሮፌሽናል ደረጃ በምድረ-አሜሪካ ሲሰራ አንድም ጊዜ እንደዚህ አይነት ክፍተት ተከስቶበት አያውቅም..በዛም በራሱ ሲመካና ሲኮራ ኖሮ ነበር፡፡አሁን ግን ወደሀገሩ ተመልሶ ባጋጠሙት የመጀመሪያ ደንበኞቹ ከፍተኛ የሚባል ሽንቁር ተከስቶበታል፡፡አንድ ባለሞያ የሞያውን ስነምግባር አክብሮ ስራውን መስራት የሚገደደው ለደንበኞች ደህንነትንና ጥቅም ሲባል ብቻ አይደለም…ለራሱ ለሞያው ክብርና ተቀባይነትም እያንዳንዱ ባለሞያ የስራ-አፈፃፀም ሁኔታ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡በሙስናና በጥቅማጥቅም የሚታለሉ ዳኞችና አቃቢ-ህጎች በሞሉበት ሀገር ፍርድቤት ሊከበርና ሊታመን አይችልም፡፡ሌላውም ሞያ እንደዛው ነው፡፡ ይህን ስራ ከጀመረ ያጋጠመችው ትልቋ ደንበኛው በፀሎት ነች፡፡እርግጥ ቀጥታ ደንበኛው እሷ ሳትሆን ወላጆቾ ናቸው፡፡ከእነሱ ጋር እየሰራ ያለውን ስራ የሞያው ስነምግባር በሚፈቅደው መንገድ ጥርትና ጥልል አድርጎ እየሰራ ነው፡፡ቢሆንም ቀጥታ ቀጣሪው ልጃቸው በፀሎት ነች፡፡እሷ ፍላጎቱን ተረድታ አፈቅርሀለው ብትለው እንኳን ፍቅሯ እሱ ለወላጆቾ በሚያደርገው የሞያ ድጋፍ ተፅዕኖ ስር የወደቀ ወይንም በይሉኝታ ስሜት የተቀነበበ ሊሆን ይችላል…ይሄንን ማንም በእርግጠኝነት ማወቅ አይችልም…በዚህም ምክንያት ከእሷ ጋር ደግሞ ያለው ግንኙነት እየሄደ ያለበት መንገድ ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል፡፡ከሞያ ስነምግባር ውጭም እንደሆነ ያምናል፡፡ይሄ ጉዳይ ነው በጣም እያስጨነቀው ያለው፡፡ ከበፀሎት ጋር የፍቅር ስሜት በተሰማበት ቅፅበት ሁለት ምርጫ ነበረው፡፡አንድም በእሷ ቀጣሪነት ወላጆቾን ለማከም የተዋዋለውን የስራ ውል አፍርሶ ነፃ መውጣትና.. ከልሆነም ልቡን ገስፆ እና ፍቅሩን በውስጡ አክስሞ ስራው ላይ ብቻ አትኩሮ መቀጠል፡፡ቢያንስ ስራውን በተዋዋለው መሰረት ሙሉ በሙሉ አጠናቆ እስኪጨርስ ድረስ እንደዛ ነበር ማድረግ ያለበት፡፡ግን ይሄው ሁለቱንም ማድረግ አልቻለም፡፡ ‹‹ግን እኮ ይሄ በስራ አለም ቆይታዬ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈፀምኩት የሞያ ስነምግባር ጥሰት ነው››ሲል እራሱን ለማፅናናት ሞከረ…..፡፡ንግግሩ ግን እራሱንም ሊያሳምነው አልቻለም፡፡ ‹‹ስህተት የመጀመሪያም ሆነ የመጨረሻ ያው ስህተት ነው››የገዛ አእምሮ መልሶ የነገረው ነበር፡፡ ‹‹አሁን ወደኃላ መመለስ አልችልም…ይሄንን ጉዳይ ከዳር ላድርስና ..ከእሷ ጋር ያለኝ የፍቅር ግንኙነት የሚደርስበትን ከፍታ አይቼ ውጤታማ የሚሆን ከሆነ ምን አልባት ሞያውን በክብር ብለቅና ወደሌላ ዘርፍ ብሸጋገር እንኳን ያዋጣኛል››ሲል ለጊዜው የታየውን መፍትሄ አስቀመጠ…የገዛ አእምሮው ግን ወዲያው ነበር አፍራሽ የሆነ ሀሳብ የሰጠው‹‹ሰውዬ ምን ነካህ..?ይሄንን ሞያ ለቀህ…ነጋዴም ብትሆን …ወይም ደራሲ… ሁሉም ሞያ አይነቱ እና ተጋላጭነቱ በመጠኑ ይለያይ እንደሆን እንጂ የራሱ ህጋዊም ሆኑ ሞራላዊ የስነምግባር ገደቦች አሉበት…በተለይ ፍቅርን በተመለከተ ሁሉም ሞያ ይፈተናል…አስተማሪ ብትሆን ተማሪህ ላይ አይንህን መጣል የለብህም…ማናጀር ሆነህ ፀሀፊህን መጎነታተል ስህተት ነው፡፡ሞያህን ሳይሆን አመለካከትህን ነው መቀየር ያለብህ… ራስህን አታሞኝ፡፡››አለው…. ለጊዜው በዚህ ጉዳይ ላይ ከዚህ በላይ ማሰብ አልፈለገም….ጉዳዩን ለጊዜ አሳልፎ ሰጠና ብድርብሱን ተከናንቦ እራሱን ለእንቅልፉን አሳልፎ ሰጠ ....ወዲያው ነበር ያሸለበው…የሚገርመው ደግሞ አይኖቹ በተከደኑ ከሁለት ደቂቃ በኃላ ነበር በፀሎት ነጭ ቬሎ ለብሳ ጭንቅላቷ ላይ የሚያብረቀርቅ የወርቅ አክሊል አጥልቃ ግራና ቀኝ ጎኗ ላይ የበቀሉ ውብ ክንፏቾን እያማታች ከሰማዩ ላይ ሰንጥቃ መጥታ እቅፉ ውስጥ ስትገባ በህልሙ ያየው፡፡
///
በፀሎትና ለሊሴ ከወንጪ ከተመለሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡መሽተዋል…አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ነው…በፀሎት እና ፊራኦል ግቢው ውስጥ ካለ ግዙፍ የመንጎ ዛፍ ስር ጎን ለጎን ቁጭ ብለው እያወሩ ነው፡፡
‹‹እንዴት ነበር ወንጪ?››
‹‹ውይ ሲዊዘርላድ በለው፡፡››
‹‹እኔ ወንጪን እንጂ ሲዊዘርላንድን አላውቃትም፡፡››
‹‹አኔ ደግሞ አውቃታለዋ ለዛ ነው ያነፃፀርኩልህ..ደግሞ ዘመዶቻችን እንዴት ደግና ቀሽት መሰሉህ?፡፡››
‹‹የእኔም ዘመዶች እኮ ናቸው አውቃቸዋለው››
‹‹አይ ቢሆንም ..አንተ ምንአልባት ከልጅነትህ ጀምሮ ስለምታውቃቸው …ብዙም ጣእም ላይሰጥህ ይችላል..ማለት ሁለም ሰው እንደእነሱ አይነት ዘመድ ያለው ስለሚመስልህ ተራ ነገር አድርገህ ልትቆጥረው ትችላለህ….እንደእኔ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደዛ አይነት ዘመድ ሲኖርህ ግን በቃ ..ከአሁኑ እንዴት እንደናፈቁኝ ብታውቅ››
‹‹ገና በሁለት ቀን››
‹‹አዎ በሁለት ቀን››
‹‹አሁን ከእኛ ስትለይና ወደቤትሽ ስትሄጂ እንናፍቅሻለን ..?ማለት እኔ ናፍቅሻለሁ?››ለቀናት በውስጡ ሲያብሰለስለው የነበረውን ጥያቄ ጠየቃት፡፡
‹‹ምን ማለት ነው….?ወደየትኛው ቤቴ ነው የምሄደው?››
‹‹ወደቦሌው ቤትሽ››
‹‹ምን….ለሊሴ ነገረችህ››
‹‹እሷ ታውቃለች እንዴ?››
‹‹እሷ ካልነገረችሽ ታዲያ ማን ነገረህ?››
‹‹እራሴ ነኝ የደሰረስኩበት ..ወደ ወንጪ ከመሄዳችሁ በፊት ነው ያወቅኩት››
‹‹እኮ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?››
‹‹ያው እንዳልኩሽ የእህቴን ልብ ከተቀበልሽ በኃላ በሩቅ ሆኜ ለረጅም ጊዜ ስከታተልሽ ነበር..ስለዚህ በደንብ አውቅሻለው…እዚህ ቤት ከመጣሽ ከሳምንት በኃላ ጀምሮ ከፍተኛ ጥርጣሬ አድሮብኝ ነበር..ከዛ ምን አደረኩ አንድ ቀን ስትተኚ ሻርፕሽን ሙሉ በሙሉ ከፊትሽ ላይ ገፍፌ ተመለከትኩሽ…እና ኦርጅናለዋ በፀሎት መሆንሽን አረጋገጥኩ፡፡
‹‹ትገርማለህ..ከዛ ፀጥ አልክ?››
‹‹ምን ላድርግ…ምንም ማለትና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወቅኩም ነበር፡፡››
‹‹አሁንስ አወቅክ?››
‹‹አይ….አንቺ ንገርኝ እስኪ …ምን ልታደርጊ ነው…?እስከመቼ ነው ከወላጆችሽ ምትደበቂው?››
‹‹ወላጆቼን በቀደም አግኝቼቸዋለው..እዚህ መሆኔን ያውቃሉ››ብላ ያልጠበቀውን ዜና ነገረችው፡፡
‹‹ጥሩ..እሺ እነአባዬን እንዴት ልታደርጊ ነው….?እንደዋሸሻቸው ሲያውቅ በጣም ነው የሚያዝኑብሽ…በአንቺ ብቻ ሳይሆን እኛም አውቀን ከነሱ ደብቀን ዝም በማለታችን ምን እንደሚወጥን አላውቅም? በጣም ጨንቆኛል›ብሎ እውነተኛ ስሜቱን ነገራት፡፡
‹‹ይቅርታ ፊራኦል..እንደዚህ አይነት ነገር ውስጥ ስላስገባዋችሁ በጣም አዝናልው…ግን በዚህ ሁለት ሶስት ቀን ውስጥ እፈተዋለው…ማለት እናንተ ቀድማችሁ እንደምታውቁ ሳላሳውቅ እፈተዋለው››
‹‹እስኪ እናያለን…››
‹‹እኔ የእህትህን ልብ የተሸክምኩ በፀሎት መሆኔን እርግጠኛ ስትሆን ምን ተሰማህ?››
‹‹ግማሽ ሀዘን ግማሽ ደስታ››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ለረጂም ጊዜ ላናግርሽና ቀርቤ ላወራሽ የምመኝሽ የእህቴን ከፊል አካል የተሸከምሽው በፀሎት የገዛ ቤቴ መጥተሸ ከእኔ ጋር አንድ መአድ እየቆረሽ መሆንሽን ሳውቅ ፍጽም ድስታ ነው የተሰማኝ…በሌላ ጎኑ ደግሞ ያችኛዋን በፀሎት አፍቅሬት ስለነበር….ሌላ በፀሎት እንዳልሆንሽ ሳውቅ ቅር ብሎኛል››
‹‹ከመቀመጫዋ ተነሳችና እላዩ ላይ ተጠምጥማ ጉንጩን እየሳመችው‹‹….የእኔ ወንድም
‹‹እሱማ ምን ጥርጥር አለው….ግን እንደው ትረዳዋለች ወይ የሚለው ጥርጣሬ አድሮብኝ ነው..እሷን ለማታለል ለማስመሰል ያደረግነው መስሎ እንዳይሰማት››ወ.ሮ ስንዱ ጥርጣሬያቸውን አሰሙ፡፡
‹‹እሷ የምታውቀንን ያህል እኛ እኮ ልጃችንን አናውቃትም …..››ሃይለልኡል የሚስታቸው ሀዘንና ጥርጣሬ ውደውስጣቸው እንዳይገባ እየታገሉ መለሱ፡፡
‹‹እሱስ እውነትህን ነው….የልጃችን ትልቅ ውለታ አለብን››
‹‹አዎ .አሁን ልጃችን በጣም በስላለች…ምን አስቤለው መሰለሽ….ካምፓኒው ውስጥ የሆነ ቦታ ይዛ ስራ መጀመር አለባት…እኔ በቅርቡ ጡረታ ወጥቼ ከአንቺ ጋር አለምን እየዞርኩ ዘና
ማለት ነው የምፈልገው…ከአሁን በኃላ በተጨናነቀው የቢዝነስ አለም ውስጥ ቀሪ ህይወቴን ማባከን አልፍልግም››
‹‹እና ስራውን ሙሉ በሙሉ እንድትረከብህ ነው የምትፈልገው?፡፡››
‹‹አዎ ከእኔ ጋር ሆና አንድ ሁለት አመት ከሰራች በቃ ከእኔ በተሻለ ውጤታማ እንደምትሆን እርግጠኛ ነኝ..እይ እስኪ እኔና አንቺን ወደስምምነት ለማምጣት የተጠቀመችበት የረቀቀ ውጤታማ ዘዴ….እንዴት እንዳቀናጀችው…ያን የመሰለ ባለሞያ እንዴት እንደመለመለች
…በእውነት ይህቺ የእኛ ልጅ ነች ብዬ እስክደነቅ ድረስ ነው ያስደመመችኝ፡፡››በንግግራቸው ኩራታቸውን ሲግልፁ ፊታቸውም በደስታ እያበራ ነበር፡፡
…በሶስተኛው ቀን
ሰለሞንና በፀሎት ቢያንስ በቀን አንድና ሁለት ጊዜ እየተደዋወሉ ለረጅም ሰዓት ማውራትና የተለያዩ ርዕሶች እያነሱ መወያየት ልምድ አድርገውታል..ይሄ ደግሞ እርስ በርስ የበለጠ እንዲተዋወቁና በደንበኝነት መልክ ሳይሆን ልክ እንደአንድ የልብ ጓደኛ ወጣ ባለ ርዕሶች ላይም ረጅም ሰዓት ማውራት ጀምረዋል፡፡፡ይሄ ጉዳይ ለሁለቱም በጣም ተመችቷቸዋል፡፡አሁንም ተደዋውለው እያወሩ ነው፡፡
በፀሎት‹‹አንድ ሰው እንዳፈቀረን እንዴት ማወቅ እንችላለን…?ለምሳሌ እኔ አንድ አብሮኝ ያለ ወንድ የእውነት እንደሚያፈቅረኝና በምን ማረጋገጥ እችላለው፡፡››ስትል ያስደነቀውን ጥያቄ ጠየቀችው፡፡
‹‹ሴት ልጅ ካለገመች በስተቀር አንድ ወንድ እንደሚያፈቅራትና እንደማያፈቅራት በቀላሉ መለየት ትችላለች…አንዳንድ ጊዜ ግን ምን ይሆናል ?እሷ በጣም ካፈቀረችው እሱ እንደማያፈቅራት ብታውቅ እንኳን ሽንፈትን ላለመቀበል ብላ እንደሚያፈቅራት እራሷን ለማሳመን ትጣጣራለች..የዛን ጊዜ የምታያቸውን ምልክቶች ሁሉ በተቃራኒው ተርጉማ ለመረዳት ትሞክራለች››
‹‹እና ምልክቶቹ ምን ምን ናቸው?››
‹‹ለምሳሌ ድምፅሽን ለመስማት ብቻ ይጠራሻል።ስትስቂ ስቆ ስታለቅሺም ያለቅሳል። ከመተኛቱ በፊት በመጨረሻዋ ደቂቃና ከእንቅልፍ በነቃ በመጀመሪያው ደቂቃ ስለአንቺ ነው የሚያስበው።ያለምክንያት ሊያቅፍሽ እና ከሰውነቱ ሊለጥፍሽ ይፈልጋል።አንቺን ከነማንነትሽ ለመቀበል ፍቃደኛ ሆኖ ይገኛል።አንቺን በሌላ ለመቀየር ፍፅም ፍቃደኛ አይደለም።ስህተት ሲሰራ አንቺ እንዲያስተካክል ከመጠየቅሽ በፊት ቀድሞ ለማስተካከል ጥረት ሲያደርግ ታገኚዋለሽ፤ሁል ጊዜ ሊረዳሽ ጥረት ያደርጋል።እንቅልፍ አሸልቦሽ ሊመለከትሽ ነቅቶ ይጠብቃል።ግንባርሽን በስስት ይስማል።መክሳትሽም ሆነ ክብደት መጨመርሽ ከውበትሽ አንፃር ብዙም አያስጨንቀውም፡፡በጓደኞቹ መካከል እጆችሽን ይይዛል።ወይም አቅፎ ጉያው ይሸጉጥሻል።ወዘተ…እንግዲህ እኚንና መሰል ምልክቶችን በማየትና በማመዛዘን አንድ ሰው አፍቅሮሽ ይሁን ወይስ አይሁን መለየት ትችያለሽ››
‹‹እሺ ወሲብስ ምንድነው..?በፍቅር ውስጥ ያለው ድርሻስ?››
‹‹ወሲብን የፍቅር ተጣማሪሽ ጋር ያለሽን ግንኙነት ለማጠንከር እና ለማዋሀድ እንደ ሲሚንቶ የሚያገለግል ተፈጥሯዊ ቅመም ነው፡፡ወሲብ በአግባቡ ከተጠቀምሽበት ፍቅርን በማሳደግና በማጎልበት ትልቅ የሆነ ድርሻ አለው፡፡አይደለም ወሲብ መተሻሸትና መሳሳም እራሱ የፍቅር ግለትን ጠብቆ ለማስቀጠል ትልቅ ጥቅም አለው፡፡››
‹‹እና ከፍቅረኛሽ ጋር ተሳሳሚ እያልከኝ ነው››
‹‹ፍቅረኛው ካለ አዎ በደንብ..ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሚስቶች በጋብቻ ውስጥ ከከራረሙ በኃላ ለመሳሳም ያላቸው ፍላጎትና ትኩረት በጣም ይቀንሳል ወይም እስከወዲያኛው ይጠፋል።ላጤዎች ደግሞ ብዙውን ጊዜ በዚህ ረገድ ትኩስና ያልተገደበ ፍላጎት ይኖራቸዋል፡፡ይሄ ግን አግባብ አይደለም ።ባልዬው ድንገት ውጭ ሌላ ላጤ ሴት ቢያጋጥመው ከኤክስፐርት ጋር ነው የሚላተመው...ልዩነቱ ሰፊ ስለሚሆንበት ይከብደዋል።ቶሎ ስህተቱን ለማረም እንዳይችል ይፈተናል።››
‹‹እኔ ግን ሳገባ እንደዛ አላደርግም…ለባሌ በጣም የምመቸው ይመስለኛል›››
‹‹እያስጎመዠሺኝ ነው››
‹‹ምን ያስጎመዠሀል ..አንተን አላገባ?››
‹‹ምን ይታወቃል….ካፈቀርሺኝ ለምን አታገቢኝም?››
‹‹ሳላውቅህ እንዴት ላፈቅርህ እችላለው?››
‹‹ከዚህ በላይ እንዴት ታውቂኛለሽ..ለወራት ድምፄን በስልክ ስትሰሚ ነበር…በቀደም ደግሞ በአካል አይተሸኛል…ምነው አላምርም እንዴ?››
‹‹አረ ቆንጆ ነህ…ግን ቁንጅና ብቻ በቂ አይደለም››
‹‹እስኪ እናያለን››
‹‹ለማንኛውም ለባልሽ መዋብ የምትጀምሪው ከእርቃን ገላሽ ጀምሮ መሆን አለበት...ፓንትሽንና ጡት ማሲያዛሽን የሚያየው ባልሽ ነው።...ለእነሱ ትኩረት መስጠት መቻል በባልሽ እና በአንቺ የፍቅር ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ይፈጥራል።ከላይ ያሉ ልብሶችሽን፣ ፀጉርሽን ፣ጌጣ ጌጦችሽን ለሁሉም ሰው በጋራ የምታደርጊያቸው መዋቢያዎች ናቸው።የውስጥ ልብሶችሽ ጥራት ግን የባልሽ ስሜት ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚኖራቸው ግንዛቤ ሊኖርሽ ይገባል፡፡››
‹‹ገባኝ››
‹‹አይ ስለአንቺ እኮ አይደለም ያወራውት አጠቃላይ ስለፍቅር እና ፍቅረኛሞች ለማውራት ፈልጌ ነው…ባልሽ በአጋጣሚ የሚያገኛቸው እንግዳ ሴቶች ድንገት ፊቱ ልብሳቸውን የማውለቅ እድል ካገኙ እመኚኝ የውስጥ ልብሶቻቸው ብቻ አይደሉም ውብና አማላይ የሚሆነው.. ለሊቱንም ውብና አማላይ እና ያልተለመደ አይነት ያደርጉለታል።አንቺ ሚስቱ ነሽና ብዙ ኃላፊነትና የህይወት ውጣ ውረዶች ስላለብሽ የአመቱን ቀናቶች ሁሉ ውብና አማላይ ልታደርጊለት አትቺይም ግን በሳምንት አንድ ቀን ካልሆነም በወር አንድ ቀን መቼም ሊረሳው የማይችል እንደዛ አይነት ውብ ለሊቶችን በገፀ-በረከትነት ልታቀርቢለት ይገባል።የዛኔ ከውጭ፣በአጋጣሚ የሚፈቱኑትን በልበ ሙሉነት ሊያልፋቸው አቅም ይኖረዋል።››
‹‹ይገርማል …ምንም ሳልከፍልህ በነፃ የቅድመ ጋብቻ ስልጠና እየሰጠኸኝ ነው፡፡››
‹‹ያው ማወቅሽ ዞሮ ዞሮ ጥቅሙ ለእኔው ነው ብዬ ነው››
‹‹እንዴት ማለት?››
‹‹ነገርኩሽ እኮ…ምን አልባት እድለኛው ባልተቤትሽ እኔው ልሆን እችላለሁ››
-ጥቂት ክፍሎች ቀሩት…ሰኞ ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5
ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-ሀያአራት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ለሊሴና በፀሎት በእቅዳቸው መሰረት በአንቦ በኩል አድርገው ወንጪ በመድረስ የለሊሴ አጎት ቤት ከደረሱ ሁለት ቀን ሆኗቸዋል፡፡በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ በአካባቢው ያሉ የአቶ ለሜቻ ዘመደች ጋር እየዞሩ ሰላም ማለት እና መጋበዙ እራሱ ማደረስ አልቻሉም…እሷ ብዙ የሀብታም ድግሶችና ፓሪዎችን እንጂ እንዲህ አይነት በየሳር ጎጆውና በየደሳሳ የቆርቆሮ ቤቶች እየዞሩ በግዳጅ መጋበዝ በህይወቷ አይታው የማታውቅ ትዕይንት ስለሆነ በጣም አስገራሚና ትንግርታዊ ነው የሆነባት..በየሄደችበት የሚቀርብላት እርጎ፤ ለወተት…የማር ወለላ…አንጮቴ……ጨጨብሳና ገንፎ..ሁሉም ውብ ነበር፡፡በዚህም የተነሳ ወደፓርኩ
ለመሄድና ለመጎብኘት ጊዜ አላገኘችም..ቢሆንም በአካባቢው ቢያንስ የሚመጡትን 15 ቀን ስላምታሳለፍ ሁሉንም ነገር ለማድረግ በቂ ጊዜ እንዳላት ስላወቀች ብዙም አልተጨናነቀችም፡፡
ሰለሞንም የበፀሎትን ወላጆች ይዞ ወደወንጪ እያመራ ነው፡፡በመጀመሪያ እቅዱ ወደላንጋኖ ወይም ሰደሬ ይዞቸው ሊሄድ እንጂ ወንጪ የሚባል ስፍራ ፈፅሞ በአእምሮው አልነበረም..ግን በፀሎት ወደወንጪ እንደሄደች ስትነግረው ግን ወደያው ሀሰቡን ቀየረና ለእነአቶ ኃይለልኡል ሀሳብን ነገራቸው፡፡እነሱ የትም ሆነ የትም ለቦታም ብዙም ግድ ሳልልነበራቸው ወዲያው ነበር ሀሳቡን የተቀበሉት፡፡ከዛ ወዲያው ቻርተር አውሮፕላን ተከራይተው ወንጬ ኢኮቱሪዝም ፓርክ እንግዳ ሆነው ተከሰቱ፡፡ጉዞ ተገባዶ ከቻርተር አውሮፕላኑ እንደወረዱ እነሱን ባሉበት ትቶ ቀጥታ ወደኢንትራንስ ጌት ነው የሄደው
…ስለጠቅላላ የጉብኝቱ ፓኬጅ ማብራሪያ ጠየቀና ሁለት መኝታ ክፍል ተከራየ፡፡ የኤሌክትሪክ መኪና ተከራይቶ እቃቸውን በመጫን ቀጥታ ወደተከራየበት ሎጅ ይዞቸው ሄደ…
ሰለሞን ወላጆቾን ወደወንጪ ይዞ መምጣቱን ለበፀሎት አልነገራትም፡፡እሷ የምታውቀው ወደላናጋኖ እንደሚሄዱና ሲደርስና ሲመቸው እንደሚደውልላት ነው፡፡
ወንጪ ከአዲስ አበባ በ135 ሜትር ርቀት ላይ በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ክልል በአንቦ እና በወሊሶ ከተሞች መካከል የሚገኝ ድንቅ ስፍራ ነው ፡፡ወንጪ ሀይቅ ከባህር ወለል በላይ 3000ሜትር ከፍታ ላይ ሲገኝ 75 ሜትር ገደማ ጥልቀት ያለው ንፁህ እና ጥርት ያለ ሀይቅ ነው፡፡ሀይቁ ከ3000 ዓመት በፊት በተከሰተ እሳተ ጎመራ የተፈጠረ እንደሆነ ይነገራል፡፡በአካባቢው የሚነገሩ አፈታሪኮች እንደሚያስረዱት በወቅቱ እንደሶደም አይነት ተንቀልቃይ እሳተ ጎመራ ተነስቶ የአካባቢውን ፍጥረት ለረጅም ጊዜ እየበላ ከቆየ በኃላ ድንገት በቦታው አርባ አራት ምንጮች ተፈጥረው የሚንቀለቀለውን ውሀ ካጠፋት በኃላ በእሳተ ጎመራው አማካይነት የተፈጠረውን ረባዳ አካባቢ መሙላት ይጀምራል….ውሀው ግን ሞልቶ በመሀከል ትንሽ ደሴት በውሀ ሳትዋጥ ደረቅ መሬት ሆና ትቀራለች…ከዛ ያንን የታዘብ የአካባቢው ኑዋሪዎች ያቺ መሬት በውሀው ሳትሸፈን የቀረችው የተቀደሰች ስፋራ ስለሆነች ከአሁን በኃላ ቦታዋና እንደማመስገኛና ከፈጣሪ ጋር መገናኛ የተለየች ስፍራ አድርገን እንገለገልባታለን ብለው ይስማማሉ…በአሁኑ ወቅት በቦታው ላይ ቤተክርስቲያን ታንፆበታል፡፡
የውንጪ ኢኮቱሪዝም መዝናኛ..መንገዶቹ ጠባብ ስለሆኑና የመኪና መተረማመስ የአካባቢውን ተፈጥሮ እንዲያበላሽው ስለማይፈለግ .ማንኛውም ጎብኚ በራሱ መኪና ወደውስጥ ዘልቆ መግባት አይችልም…ግን ወደሎጆችም ሆነ ወደመዝናኛ ፓርኮች ወይንም ደግሞ ወደገበሬዎች መኖሪያ ቤት ለመሄድ የፈለገ ሰው የተለያዩ አይነት ቀላል የትራንስፖርት አማራጭ ተዘጋጅቶ ይጠብቀዋል..ለምሳሌ…የፈረስ ትራንስፖርት ..ሳይክል
…ኤሌክትሪክ መኪና ካልሆነም ደግሞ በጠባበቹ የአስፓልት መንገድ ግራ ቀኝ ያለውን ውብ ተፈጥሮና የፓርክ ክፍሎችን በመጎብኘት በእግሩ ወክ እያረገ ስጋውን ማዝናናት ነፍሱንም ማስፈንጠዝ ይችላል፡፡
አጠቃላይ የወንጪ የመንገድ ልማት 70 ኪሎ ሜትር አካባቢ ሲሆን ተራራውን የሚዞር 10 ኪሎ ሜትር የአስፓልት መንገድ … ወደ ዲንዲ ሚሄድ ሀይ ወይ …ማራቶን ራጮች እንዲለማመዱበት ታስቦ የተሰራ የሩጫ ትራክ ሁሉም ውብ ነው፡፡በተለይ ተራራውን በሚዞረው መንገድ ላይ ሁለት ሶስት ሆነው ሳይክል እየነዱ ወይም ፈረስ እየጋለቡ ዙሪያ ገባውን መጎብኘት ገነት ደርሶ እንደመመለስ አይነት አስካሪ ስሜት ውስጥ ይከታል፡፡
አንድ ጎብኚ ሎጆቹን የመከራየት አቅም ማይኖረው ከሆነ እዛው ከሪስፕሽን በፓርኩ ግንባታ ምክንያት ከቦታቸው የተነሱ ገበሬዎች በመንግስት በካሳ መልክ የተሰራላቸው ዘመናዊ ቤቶች ውስጥ ከክፍሎቹ የተወሰኑትን ለቱሪስት እያከራዩ ገቢ እንዲያገኙ ታስቦ የተሰራላቸው ስለሆነ ቀጥታ እዛው ሬስፕሽን ቡክ ያደረገ ሰው የየትኛው የገበሬ ቤት እንደሚያድር ይነገረውና ቀጥታ እዛ ሄዶ በተመጣጣኝ ዋጋ ማደሪያ ያገኛል፡፡
ወንጪ ውበትን ለመግለፅ እግዜያብሄር እንደምሳሌነት ለማሳያ የፈጠራት ስፍራ ትምስላለች…ውበቷ ሀይቆ ብቻ አይደለም…ዙሪያዋን የከበቡት አረንጋዴ ልብስ የለበሱት ሰንሰለታማ ወጣ ገባ ተራሮች ፣አየሩ ሁሉ ነገር ጠቅላላ ውብ ነው፡፡አሁን ደግሞ ቦታውን የቱሪስት መነኸሪያ ለማድረግ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች ይበልጥ ወደፍፁምነት ያስጠጋው ነው፡፡ደረጃቸውን የጠበቁ ሙሉ ተራራውን የሚሽከረከሩ የአስፓልት መንገዶች በእያንዳንዱ ኮርነር ላይ የታነፁ የተላያዩ ታሪክ እንዲሸከሙ ተደርገው በጥንቃቄና በጥበብ እንዲታነፁ የተደረጉ ህንፃዎች፤ ሎጆች፤ ካፌዎች ፤ፈንጠርጠር ብላው ከሩቅ የሚታዩ የገበሬ ቤቶች እርሻዎች …ሁሉ ነገር አይን ሞልቶ የሚፈስ የመንፈስ ትፍስህት ነው፡፡በወንጪ ኢኮቱሪዝም ፤የባንክ አገልግሎት፤ የአካባቢው ልጆች ተደራጅተው የሚሰጡት የሬስቶራንት አገልግሎት ፤የተለያዩ የባህል እቃዎች የሚሸጡበት ሱቆች..ካፍቴሪያ …አነስተኛና ትላልቅ
አዳራሾች…አንፊትያትሮች ሁሉም በአቅሙ ልክ አገልግሎት እንዲያገኝ ተደርጎ የተዘጋጀ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ይገኛሉ ፡፡
ወንጪ ኢኮቱሪዝም ባህልና ተፈጥሮን ማእከል አድርጎ የተገነባ ነው፡፡የወንጪ አካባቢ ስድስት ወር አካባቢ ዝናብ የሚዘንብባት ለምለምና እርጥብ ቦታ ነው፡፡እነሰለሞን የተከራዩት ክፍል የእሱ ባለአንድ አልጋ ሲሆን የባልና ሚስቶቹ ግን ሁለት አልጋ በአንድ ክፍል ያለበት ለቀቅ ያለ ዘመናዊና ባህላዊ እቃዎች በስምምነት ተሰባጥረው ያሳመሩት… ለሀይቁም ሆነ የአካባቢውን ተፈጥሮ ለማየትና ለማድነቅ ውብ እይታ ያለው በአንቦ ድንጋይ ተጠርቦ የተሰራ…በአሻራ ወይም በካርድ የሚከፈት ውብ ክፍል ነው፡፡ መኝታ ክፍሉ ዘመናዊ ማሞቂያ የተገጠመለት ስለሆነ ምቹ በሆነ የአየር ሁኔታ ውስጥ ተቀምጠው ወይም ተኝተው በተከፈተው መስኮት ቁልቁል ሀይቁን ሲመለከቱ ልብን ጥፍት ያደርጋል፡፡
ምሽት ነው…አራት ሰዓት አካባቢ..አቶ ኃይለ ልኡልና ባለቤታቸው ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ክፍላቸው በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ቁልቁል የጨረቃዋ ብርሀን ወንጪ ሀይቅ ላይ ስታርፍ እና ከሀይቁ ጀርባው ያለውን ውብ ሰንሰለታማ ተራራ እያዩ ያወራሉ
‹‹ሃይሌ..ልጃችን ግን አሁን ወደአዲስአባ እንደተመለስን የምትመጣ ይመስልሀል?››
‹‹አታስቢ….ትመጣለች….››
‹‹እንደማስበው አሁን እሷ እንድንሆንላት የምትፈልገውን አይነት ወላጆች የሆን ይመስለኛል…፡፡››
ለሊሴ ግቢው ውስጥ ይዛው ገባችና መጀመሪያ ከአባቷ ጋር ከዛ ከወንድሞ ጋር አስተዋወቀችውና ይዛው ወደ ሌላ ክፍል ውስጥ ይዛው ገባች…ክፍሉ አዲስ የተሰራ መሆኑን ያስታውቃል….ጥግ ላይ በስርአት የተነጠፈ አንድ አልጋ ..ከዛ ሁለት ወንበር እና አነስተኛ ጠረጴዛ ይታያል..ጠረጴዛ ላይ ሁለት ነጭ ሻማ ተለኩሶ እየበራ ነው…የቤቱ ወለል ሙሉ በሙሉ ቄጤማ ተጎዝጉዞ አውዳአመት መስሏል…አልጋው ጠርዝ ላይ አንድ ወጣት ተቀምጣለች …ከዛ ውጭ ቤቱ ባዶ ነው፡፡
በፀሎት‹‹ግባ ዝለቅ…. ››የሚል ድምጽ ስትሰማ ካቀረቀረችበት ቀና አለችና ግባ እየተባለ ያለው ሰው ላይ አፈጠጠች…ጠይም ነው…ባለደማቅ ጥቁር ፀጉር…ቆንጆ ወንዳወንድ
ነው…ልክ እንደባንክ ቤት ስራአስኪያጅ ሽክ ብሎ ሰማያዊ ሱፍ ለብሶል..ሰማያዊ ሱፍ በነጭ ሸሚዝ…ከረባት አላሰረም….በቅፅበት ውስጥ ነው ሙሉ ቁመናው ውስጧ ስምጥ ብሎ የገባው፡፡ስሯ ደርሶ ሲቆም ከተቀመጠችበት ተነሳች…..‹‹ተዋወቂው ሀለቃዬ ነው….እሷ ደግሞ እህቴ ነች››
‹‹ሰለሞን እባላለሁ››ብሎ እጁን በትህትና ዘረጋላት፡፡
በደመነፍስ እጇን ዘረጋችለት..ጨበጣትና እየወዘወዛት ስሟን እስክትነግረው ይጠብቅ ጀመር…..ምን ብላ ትንገረው….ለእሷ በዛሬው ቀን ይሄ ሰው ያለችበት ቦታ ድረስ መጥቶ እጇን መጨበጥ የማታሰብ ነገር ነው….፡፡
‹‹ስምሽን ንገሪው እንጂ …?.›››
‹‹ስሜን የማን የእኔ..ማለቴ..››ተርበተበተች፡፡
‹‹ተዋትና ተቀመጥ ልጄ…..››እጇን ለቀቀና ወደመቀመጫው ሄዶ ተቀመጠ… ፡፡ ለሊሴ‹‹ተጫወቱ መጣው..››ብላ ወደ ዋናው ቤት ሄደች፡፡
‹‹ምነው ስምሽ ያስጠላል እንዴ?››ሲሌ ጠየቃት፡፡
‹‹እኔ እንጃ….ሰናይት እባላለሁ››
‹‹እና ሰናይት የሚለውን ስም ለመናገር ነው የተናነቀሽ?››
‹‹አይ …ሱፍ ለባሽ ክፍላችን ሰተት ብሎ ይገባል ብዬ ስላልጠበቅኩ ነው፡፡››
‹‹ቱታ ለብሼ መምጣት ነበረብኝ…?››
‹‹ለካ እንዲህ ነገረኛ ና አሽሟጣጭ ሰው ነው እንዴ? ››ስትል በውስጧ አሰበች…ዝም አለችው….. ወዲያው ለሊሴ እና እናቷ እንጀራና ወጡን ይዘው መጡ…እዛው የእጅ ውሀ አስታጠቡትና የሚበላ ቀረበለት…እንጀራውን ሲነሳ ደቦና ቆሎ ቀረበለት..ለእሱ ተብሎ የተገዛ ቢራ ተከፈተለት…..
‹‹እንዴ ቢራ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ ምጠጣው…?››
‹‹ለጊዜው አዎ…አባዬ ትንሽ ቆይቶ መጥቶ ይቀላቀልሀል….እንግዶች ስለመጡ እማዬን ባግዛት ቅር ይልሀል..አልቆይም፡፡ ››
‹‹ሂጂ ችግር የለውም ..እህትሽ ታጫውተኛለች›› ለሊሴ‹‹ጥሩ ..በቃ መጣሁ››ብላ ወጣች
ሰለሞን ወደ በፀሎት ዞረና ‹‹አሁን ብቻችንን ቀርተናል….››አላት፡፡ ደንግጣ‹‹ ማለት?››
‹‹አትደንግጪ ሰኒ…ምን አስደነገጠሸ?››
‹‹አይ እሱማ ምን ያስደነግጠኛል…?አልደነገጥኩም…››እውነቱን ለመናገር ከመደንገጥም አልፋ ሰውነቷ በላብ እየተዘፈቀ ነው፡፡
‹‹አህቴ ስለአንተ ብዙ ነገር ነግራኛለች….››
‹‹እህትሽ ብቻ… እኔስ ብዙ ነገር ነግሬሽ የለ እንዴ?››
‹‹መቼ ..?የት ተገናኝተን….?››
መልስ ይመልስልኛል ብላ ስትጠብቅ ስልኩን አወጣና እያየችው ደወለ…ኪሷ ያለው ስልክ ተንጣረረ…አወጣችና አየችው…ምን እንደምትል እንዴት እደምታደርግ ግራ ገብቶት
አፍጥጣ እስክሪኑን እያየች ባለችበት ሰዓት ለሊሴ ከውጭ ገባች….ሰለሞን ስልኩን ዘጋው..የሚያንጣርረው የበፀሎት ስልክም ተቋረጠ…፡፡
‹‹በፀሎት ሀለቃዬን እንዳታስደብሪው››
‹‹አረ …የምን መደበር አመጣሽብኝ….እህትሽ ካንቺ በላይ ተጫዋች አይደለች እንዴ?››
‹‹እንግዲያው ጥሩ ..ቢራውን ጨምሪለት››ብለ ተመልሳ ወጥታ ሄደች፡፡
‹‹እሺ ጨምርለታለው››
መሄዷን ከረጋገጠች በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀና ብላ በትኩረት አየችው‹‹ምነው ቆንጆ ነኝ?››
‹‹በጣጣጣ…..ም››
‹‹አንቺም ልክ እንደጠበኩሽ ነሽ…ግን እንዳትታወቂ ነው የተሸፋፈንሽው….››
ቀስ ብላ ሻርፕን ከፊቷ አነሳችና አሳየችው…..ደነገጠ….ወዲያው በፍጥነት መልሳ አሰረችው፡፡
‹‹ምን ተፈጥሮ ነው?››
‹‹የጠፋው ቀን በሞተር ነበር ከቤት የወጣሁት..እና ይዚህን ጊቢ አጥር ጥሼ ከበሩ ጋር ተላትሜ ነው የቆምኩት….እግሬ ሁሉ ተሰብሮ ነበር…አሁን ግን ድኛለሁ››
‹‹ይሄንን እንዴት እስከዛሬ ሳትነግሪኝ?››
‹‹ለምን ነግርሀለው..?ምን እንድታደርግልኝ?››
‹‹ምን ባላደርግልሽስ….እኔ ላንቺ አንደዚህ ነኝ?››
‹‹እንዴት ነህ?››
‹‹ትናት ማታ እንደዛ ዳባሪ ስሜት ላይ ሆኜ ለማን ደወልኩ ?ላንቺ አይደል?››
‹‹በነገራችን ላይ በጣም ስታሳስበኝ ነበር…ለሊቱን ሙሉ ስላአንተ እየተጨነኩነው ያሳለፍኩት…..እንደማይህ ግን እንደማንኛውም ወንድ ወዲያው ማገገምና ወደተመደ እንቅስቃሴ መግባት ችልሀል፡፡››
‹‹ምን ጠብቀሽ ነበር…?ዛሬም አልጋዬ ላይ ተኮራምቼ እንዳለቅስ?››
‹‹አዎ.. እኛ ሴቶች ብንሆን እንደዛ ነው የምናደርገው››
‹‹ይሁን…አሁን እንደተመለስኩ እንዳልሺኝ አደርጋለው….በነገራችን ላይ ይሄንን የመቁሰልሽን ዜና ወላጆችሽ ቢሰሙ በቃ ቁም ስቅሌና ነበር የሚያሳዩኝ…››
‹‹ቆይ እንዴት እኔ መሆኔን አወቅክ…..ማለት እንዳየሁህ እኮ ስሜን ቀይሬ የነገርኩህ ማንነቴን የምትለይበት ምንም መንገድ እንደሌለ እርግጣኛ ሆኜ ነበር፡፡››
‹‹እንግዲህ ይሄን ያህል ነው የማውቅሽ….››
‹‹በጣም ነው ያስገረምከኝ››
‹‹ያው ሰውን ማስገረሙን ካንቺው ነው የኮረጅኩት››
‹‹እሺ..በመሀከላችን ስላለው ነገር ለሊሴ ምንም ማወቅ የለባትም››
‹‹እንዴ በመሀከላችን የሆነ ነገር አለ እንዴ?››
‹‹አትቀልድ››
‹‹እሺ እንዳልሽ››
‹‹በነገራችን ላይ ከለሊሴ ጋር ከነገ ወዲያ ወደወንጪ ልንሄድ ነው…የጋሼ ዘመዶች እዛ አሉ….እንዝናናለን፡፡››
‹‹ደስ ይላል..ያው እኔም ከተውሻቸው ወላጆችሽ ጋር የሆነ ቦታ ሄጄ ዘና እላለው…ሳስበው አንቺ እዚህ ስለተመቸሽ አነሱን ለእኔ ብትሰጪኝ ደስ ይለኛል፡፡;;
‹‹ውሰዳቸው››
‹‹ተይ በኃላ..እንደድሮ እንዳይመስሉሽ…ፍቅር ሲያገረሽ አደገኛ መሆኑን ያየሁት በእነሱ ነው…ጎረምሳ በያቸው››
ለሊሴ አባቷን አስከትላ መምጣቷን ጫወታቸውን እንዲያቆርጡ አደረጋቸው፡፡
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu
TikTok-https://www.tiktok.com/@zerihungemechu67
ፌስቡክ- https://www.facebook.com/zerihun.gemechu.5
ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራስምንት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ሰለሞንና በፀሎት በስልክ እያወሩ ነው፡፡
‹‹ለመሆኑ የት ነው ያለሽው?››ሲል ጠየቃት
‹‹ምነው ጠየቅከኝ?››
‹‹አይ ..እንዲሁ ደህንነትሽ አሳስቦኝ ነው….ምን አልባት የማይመች ቦታ ካለሽ ልረዳሽ እችላለው፡፡››
‹‹ምነው ወደቤትህ ወስደህ ደብቀህ ልታኖረኝ አሰብክ››
‹‹ምነው ..ችግር አለው.?.የእውነት የማይመች ቦታ ካለሽ ንገሪኝ››
‹‹አሁን ካለሁበት ቦታ የተሻለ ሊመቸኝ የሚችለው ምን አልባት ገነት ነው….እሱንም ደግሞ ስላላየሁት እርግጠኛ አይደለሁም››
‹‹እንዴ…ከእናትና አባትሽም ቤት የተሻለ ቦታ ነኝ ነው የምትይኝ…ይሄንን ማመን አልችልም፡ ››
‹‹ነገርኩህ እኮ…››
‹‹‹እ ..ገባኝ››
‹‹ምኑ ነው የገባህ?››
‹‹ከእናትና አባት ቤት በበለጠ የሚመች ቦታ የፍቅረኛ ቤት ነው››
‹‹በጣም ተሳስተሀል..አዲስ ቤተሰብ አግኝቼለሁ…አራት ናቸው..ሽማግሌ አባትና እናት፣አንድ ዋንድ ሴትና ወንድ ልጅ አላቸው..ሀለት ክፍል ሰርቢስ ውስጥ ነው የሚኖሩት፣ኑሮቸው ከእጅ ወደአፍ ነው… ፍቅራቸው ግን ሞልቶ የፈሰሰ ነው….ለዘላለም ልጃቸው አድርገው ተቀብለውኛል…ከአሁን ወዲህ ባለው ህይወቴ ሙሉ አነሱ ወላጆቼ እና ቤተሰቦቼ እንደሆኑ እንዲቀጥሉ ምንም ነገር አደርጋለው››
‹‹የሚገርም ነው….እናትና አባትሽ ይሄንን ንግግርሽን ቢሰሙ ልባቸው የሚሰበር ይመስለኛል፡፡››
‹‹እንግዲህ ምንም ማድረግ አልችልም…በእነሱ ስህተት ነው ከቤት የወጣሁትና እነሱን ያገኘሁት…አሁን አግኝቼ በደንብ አጣጥሜቸዋለው…እና ወደቤት ብመለስ እንኳን ወላጆቼን ከእነሱ ጋር ነው ማነፃፅራቸው…እና ለእነሱ ቀላል የሚሆንላቸው አይመስለኝም››
‹‹….ለመሆኑ ማንነትሽን ያውቃሉ?›
‹‹አይ አያውቁም.. እኔ ለእነሱ እናቷ የሞተችባት እና የእንጀራ አባቷ ሰክሮ በለሊት ሊደፍራት ሲል አምልጣ የወጣች ሚስኪን ሴት ነኝ››
‹‹ይሄንን ታሪክ አንቺ ነሽ የፈጠርሽው?››
‹‹አዎ…..››
‹‹የምትገርሚ ልጅ ነሽ ..እኔጋም መጥተሸ ተመሳሳይ ታሪክ ብትነግሪኝ አምኜ ልረዳሽ መሞከሬ አይቀርም ነበር››
‹‹የእነሱ እኮ መርዳት አይደለም….እናትና አባት መሆን ነው…..እንደልጃቸው መቀበል››
‹‹ የእውነት አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እኔ እራሱ ለመተዋወቅ ጓጓሁ› ›
‹‹መጓጓትህ ትክክል ነህ››
‹‹ነገሮች ከተስተካከሉ በኃላ ታስዋውቂኛለሽ ብዬ ገምታለው››
‹‹መጀመሪያ እስኪ እኛ ለመተዋወቅ ያብቃን››
‹‹እንዴ እኛኮ በደንብ ተዋወቅን፣ለአመታት የማውቅሽ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ››
‹‹እሱስ እውነትህን ነው..ያው አካል ለአካል አልተገናኘንም ብዬ ነው፡፡››
‹‹ባክሽ የስልኬ ጋላሪ ባንቺ ፎቶዎ ተጨናንቆል ››ብሎ ያልጠበቀችውን አስደንጋጭ ነገር ነገራት፡፡
‹‹እንዴ በምን ምክንያት?››
‹‹እንዴ ..ደንበኛዬ አይደለሽ?››
‹‹እና የሁሉንም ደንበኞችህን ፎቶ ትሰበስባለህ ማለት ነው?››
‹‹ቆንጆ እና የተለየ የሆኑትን ..አዎ››
‹‹በቻይንኛ ቆንጆ ነሽ እያልከኝ ነው፡፡››
‹‹እ..ምነው አይደለሽም እንዴ?››
‹‹እኔ እንጃ ….ለማንኛውም ደስ የሚል ስሜት እንዲሰማኝ አድርገሀል…እና እኔስ የአንተን ፎቶ የማግኘት መብት ያለኝ አይመስልህም?››
‹‹አይ..አዲሶቹን ቤተሰቦችሽን እንድምታስተዋውቂኝ ቃል ካልገባሽ የምታገኚ አይመስለኝም››
‹‹አዲሶቹን ቤተሰቦቼን….እኔ እንጃ ..ስለምሰስታቸው የማደርገው አይመስለኝም››
‹‹‹ትገርሚያለሽ…፣ዋናዎቹን ቤተሰቦችሽን እኮ ተቆጣጥሬቸዋለው…..ለማንኛውም ይህን የመሰለ ቤተሰብ ስላገኘሽ ደስ ብሎኛል….ይሄውልሽ በህይወት ውስጥ ሶስት አይነት ሰዎች አሉ፡፡ቅጠል የሆኑ ሰዎች… ቅርንጫፍ የሆኑ ሰዎችእና… ስር የሆኑ ሰዎች።ቅጠል የሆኑ ሰዎች ወቅትንና ሁኔታዎችን ጠብቀው ወደ ህይወትሽ የሚገብ ናቸው።ደካሞች ስለሆኑ በእነሱ ተፅዕኖ ስር ፈፅሞ እንዳትወድቂ። ከአንቺ የሚፈልጉትን የሆነ ነገር ስላለ ነው ወደህይወትሽ የሚመጡት... የመከራ ንፍስ በህይወት ዙሪያ ሲነፍስ መርገፍ ይጀምራሉ።እነዚህ ሰዎች አንቺን ማፍቀር የሚቀጥሉት በዙሪያሽ ያሉ ነገሮች ጥሩ እስከሆኑ ጊዜ ብቻ ነው።ንፋስ እንደመታው የወየበ ቅጠል ከላይሽ ላይ ተዘንጥለው ይረግፋሉ። ቅርንጫፍ ሰዎች ደግሞ በአንፃራዊነት ጠንካሮች ናቸው ግን ልትጠነቀቂያቸው ይገባል።ህይወት ጨከን ስትል መገንጠላቸው አይቀርም። ምክንያቱም ጠንከር ያለ የህይወት ጫና የመሸከም አቅም የላቸውም።ነገሮች ጨለምለም ሲሉ እና ተስፋም የሌላቸው ሲመስሉ ጥለውሽ ዞር ለማለት አያመነቱም። ሌሎቹ ልክ እንደአንቺ አዲሶቹ ቤተሰቦች ስር የሆኑ ሰዎች ናቸው። እነዚህ በህይወትሽ በጣም አስፈላጊ ሰዎች ናቸው።ለመታየት ብለው የሚሰሩት ስራ የለም።በመከራሽም በደስታሽም ጊዜ አብረውሽ ናቸው።አስከሞት የታመኑሽ ናቸው።ሲያፈቅሩሽ በነፃ ምንም መልስ ካንቺ ሳይጠብቁ ነው፣እንደዚህ አይነት አንድ ወይም ሁለት ሰው ከጎንሽ ማግኘት የህይወት ዘመን ሽልማት ነው፡፡
‹‹ጥሩ አድርገህ ገልጸኸዋል፡፡እነሱ ብቻ ሳይሆኑ፣አንተም ለእኔ ስር ነህ…በቃ ቸው…ነገ እንደዋወላለን፡፡››
‹‹ቸው …..ደህና ሆኚ››ብሎ ስልኩን ከዘጋ በኃላ …ባለበት ቆሞ ትካዜ ውስጥ ገባ..ይህቺን ልጅ በተመለከተ የተለየ አይነት ኬሚስትሪ በሰውነቱ እየተረጨ ነው….ነገሮች ወዴት እያመሩ ነው?››ሲል እራሱን ጠየቀ፡፡
በማግስቱ……
በፀሎት ከሞላ ጎደል ጤንነቷ እየተመለሰ ነው…አረ እንደውም ድናለች ማለት ይቻላል..የእግሯ ስብራት ሙሉ በሙሉ ተጠግኖ በደንብ መራመድ ችላለች..የፊቷ ቁስለትም ሙሉ በሙሉ ጠጓል..አሁን ብቸኛ ችግሯ ፊቷ ላይ ተሸነታትሮ የሚገኘው ጠባሳ ብቻ ነው….እንግዲህ ግማሽ ፊቷን ባደረሰው በተበታተነው ጠባሳ ውስጥ ምን ያህሉ እንድሚጠፋና ከበፊት ቆዳዋ በቦታው እንደሚመለስ ምን ያህሉ ደግሞ እንዳዛው እንደሚቀር ምንም የምታውቀው ነገር የለም…ያንን ለማወቅ በርከት ያሉ ተጨማሪ የማገገሚያ ቀኖች ያስፈልጋታል…ከዛ በኃላ የቆዳ ስፔሻሊስቶች ጋር ሔዳ ሰርጀሪ መሰራትም የግድ ያስፈልጋት ይሆናል….ለጊዜው ያ እያሳሰባት አይደለም…‹‹እሱን ጊዜው ሲደርስና ሁሉ ነገር ተስተካክሎ ወደቤት ከተመለስኩ በኃላ አስብበታለው››ብላ ወስናለች….አሁን ከጎኗ አቶ ለሜቻ ቁጭ ብለው እያጫወቷት ነው፡፡
‹‹ለልጆቾህ ያለህ ፍቅር ያስገርመኛል››
‹‹አይ ልጄ ሁሉም ወላጆች እኮ ልጆቻቸውን አብዝተው ይወዳሉ…››በትህትና መለሱላት፡፡
‹‹እሱን ማለቴ አይደለም..የእናንተ የተለየ ነው…አይኖችህ ከልጆቾህ ላይ አይነቀሉም….ሙሉ ትኩረትህ ልጆቾህ ላይ ነው..ስለእለት ውሏቸው ታውቃለህ….ጥዋትና ማታ አብረሀቸው ባንድ መሶብ ቀርበህ ሁለቱንም እያጎረስክ ነው የምትበላው፣ብዙ ብዙ ነገር…››
‹‹ልጄ ወድጄ አይደለም እኮ…. እንደምትይው እኔ አባትሽ በብዛት ተትረፍርፎ ያለኝ ፍቅር ነው…ገንዘብ ኖሮኝ ይሄን ስሩ ብዬ መቋቋሚያ..ወይም መነገጃ ጥሪት አልሰጣቸው….ሁል ጊዜ ታዲያ ይሄንን ነገር በምንድነው የማካክሰው ብዬ ሳስብ አንድ የማገኘው መልስ…ጊዜዬንና ፍቅሬን ሳልሰስት መስጠት ነው..አዎ ቢያንስ በዛ ነው ልክሳቸው የምችለው፡››
‹‹ግን እንሱ ምን ያህል እድለኞች መሆናቸውን ያውቃሉ?››
‹‹እስከአሁን ወደእኔ መጥተው የሚያናግሩኝ ከሁለት አንዱ ማለቴ ባልዬው ወይም ሚስትዬው ናቸው….የእናንተ ግን ልጃችሁ ነች ያናገረችኝም የቀጠረችኝም፡፡››
‹‹አዎ እሱስ ትክክል ነህ››
‹‹ስለዚህ አሁን ስራችንን ስንጀምር እሷን እያሰብን መሆን አለበት ፡፡በፍቅር የታነፀ ትዳር ውስጥ ያላደጉ ልጆች በመጨረሻ በስነ-ልቦናም ሆነ አካላዊ በሽታ እንደማያጣቸው የተረጋገጠ ነው። ልጅ ስናሳድግ ጥሩ ልብስ ፣ጥሩምግብና ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት እንዲያገኙ መጣር ብቻ ሳይሆን የተሞላ ፍቅርም እየመገብን ማሳደግ እንዳለበት እንደወላጅ ግንዛቤው ሊኖረን ይገባል።የመፈቀር እና የመፈለግ ስሜት ማጣት በከፍተኛ ሁኔታ የልጆችን በራስ የመተማመን ችሎታን ከመሸርሸሩም በላይ ለአእምሮ ውጥረትና ድብርትም እንዲዳረጉ ያደርጋቸዋል።ለልጆች በፍቅርና በእንክብካቤ ማደረግ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር ብቻ ሳይሆን ጤነኛም ሆኖ ለመኖር በጣም አስፈላጊ ነገር ነው።በወላጆቹ የሚወደድ እና ወላጆቹም የሚወድት ልጆች በጣም ደስተኛ ናቸው።በፍቅር ውስጥ መኖር ጤነኛ ሆኖ ለመኖር እና የበሽታ የመከላከል አቅማችንን ለመጨመር እንደሚያግዝ በሳይንስ የተረጋገጠ ነው።ስለዚህ ልጆቻችን በፍቅር ታንፀው የመፈለግና የመወደድ ስነልቦና ኖሮቸው ማደግ አለባቸው፡፡ለዚህም ወላጆች ሁሉ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው፡፡፡ እንደውም እናንተ እድለኛ ናችሁ፡
‹‹እድለኛ ናችሁ ስትል?››
‹‹እንዴ በፀሎት እኮ በጣም የምትገርም ብስልና በቀላሉ የማትሰበር ልጅ ነች፣አብዛኞቹ በእሷ እድሜ ያሉ ልጆች በእንደዚህ አይነት ችግሮች ውስጥ ሲያልፉ ከፍተኛ ድብርት ውስጥ ይገቡና ለተለያዩ ሱሶች ይጋለጣሉ ..ከዛም አልፈው በህይወት ተስፋ መቁረጥ ውስጥ ይገቡና እራሳቸውን ወደማጥፋት ይሄዳሉ….በፀሎት ግን ያደረገችው ከውጥረቱ ራሷን ዞር አድርጋ እናንተን ለመርዳትና ወደመስመር ለመመለስ መጣር ላይ ነው ያተኮረችው››
‹‹አዎ እውነትህን ነው …በልጄ ታላቅ ኩራት ተሰምቶኛል….ምንም ጭረት ሳይነካት ወደቤቷ እንድትመለስ ማድረግ ያለብኝን አደርጋለሁ..ማለት ሁለታችንም ማድረግ ያለብንን እናደርጋለን አይደል ስንዱ?››
‹‹አዎ ትክክል ነህ…ለዛም አይደል እዚህ የተገኘነው››
‹‹እንግዲያው ጀመርን …ከአሁን በኃላ የምናወራውና የምንናገረው ሁሉ እየተቀዳ ነው.››.ብሎ አይፓዱን አስተካክሎ ተጫነውና ቦታውን ይዞ ተቀመጠ…››
ለሶስት ሰዓት ቀጠለ…..በመጀመሪያ ወ.ሮ ስንዱ አቶ ኃይለመለኮት ላይ ያላቸውን ቅሬታ እስከአሁን በደሉኝ የሚሉትን ነገር እንዲያወሩና አቶ ኃይለመለኮት ደግሞ ለደቂቃ እንኳን ሳያቆርጡ እንዲሰሙ አደረገ…በቀጣዩ ሰዓት ደግሞ አቶ ኃይለልኡል በተራቸው ሚስታቸው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በዝርዝር እንዲናገሩ አደረገ……..ቀጣዩን አንድ ሰዓት ደግሞ እራሱ ሰሎሞን ጥያቄ እየጠየቃቸው ሁለቱም ተራ በተራ እዲመልሱ ተደረገና የጥዋቱ ክፍለጊዜ አለቀና ሶስቱም ተያይዘው ወደሳሎን ሄዱ ..ምሳው በስርአት ተዘጋጅቶ ስለጠበቃችው ሶስቱንም ጠረጴዛውን ከበው ፀጥታ በተጫነው ና እርስ በርስ በተፈራራ በሚመስል ሁኔታ ምሳቸው ተበልጦቶ አለቀ..ብና ተፈልቶ ስለነበረ በረንዳ ላይ ቁጭ ብለው ንፋስ እየተቀበሉ ጠጡ
‹‹አሁን ለአንድ ሰዓት ያህል መኝታ ክፍላችሁ ገብታችሁ አረፍ በሉ….ሰዓት ሲደርስ እኔ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው››
እሺ ብለው ሁለቱም ከመቀመጫቸው ተነሱ..ሰለሞን ከኃላ ተከተላቸው….››መኝታ ቤታቸው እንደደረሱ ሊከፍቱ ሲታገሉ‹‹ይቅርታ ሳልነግራችሁ መኝታ ቤታችሁ ተቀይሮል..ተከተሉኝ››ብሎ ቀደማቸው፡፡
‹‹የማ…? የእኔም ነው የተቀየረው?››
‹‹አዎ ወ.ሮ ስንዱ….ሁለታችሁም ተከተሉኝ..››
ግራ በማገባት ሁለቱም በዝምታ ከኃላው ተከተሉት …የኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ካለው በራፍ ሲደርስ ቆመና ከፈተው….‹‹ግቡ ››
‹‹ማ እኔ ነኝ እሷ?››
‹‹ሁለታችሁም››
እርስ በርስ ተያዩ…ቀጥሎ በጋራ እሱ ላይ አፈጠጡበት…አንድ ክፍል ውስጥ አብረው ከተኙ አስር አመት አልፏቸዋል..አሁን በአንዴ እንዴት….?ጉዳዩ ሁለቱንም እኩል ነው ያስበረጋጋቸው፡፡
ጫን ባለ የአዛዥነት ቃና‹‹እባካችሁ ግቡ››አላቸው
ምርጫ ስላልነበራቸው አቶ ኃይለልኡል ቀድመው ገቡ…ወ.ሮ ስንዱ ተከተሏቸው….ሁለቱም ጎን ለጎን ቆመው ክፍሉን ዙሪያ ጋባ ቃኙት …ሻንጣቸው ሆነ ጠቅላላ እቃቸው በየቦታው ተቀምጦል…ሁለት አልጋ ማዶ ለማዶ ግድግዳ ተጠግቶ ይታያል…፡፡
ያው ..ሁለት አልጋ አለ …ተነጋገሩና አንዳንደ አንድ ተካፈሉ …በቃ መልካም እረፍት..ሰዓቱ ሲደርስ መጥቼ ቀሰቅሳችኃላው››አለና ከክፍሉ ወጥቶ በራፉን መልሶ ዘግቶላቸው ወደገዛ ክፍሉ ሄደ፡፡
///
የሁለት ሰዓት የረፍት ጊዜ ከሰጣቸው በኃላ በጥዋቱ ጊዜ ባለው ፕሮግራም የቀረጸውን ወደኮምፒተሩ ገለበጠና ይዞ ወደእነሱ ክፍል አመራ…በስሱ ቆረቆረ…ወዲያውን ነበር የተከፈተለት፡፡
‹‹መጣህ ..?እየጠበቅንህ ነበር››
‹‹አዎ መጥቻለው››
‹‹ስንዱ ተነሽ..እንሂድ››አቶ ኃይለልኡል ተናገሩ፡፡
‹‹አይ ቆይ መሄድ አያስፈልግም ….እዚሁ እናድረግው››
‹‹ይሻላል ..እሺ ግባ..››ብለው በራፉን ለቀቁለትና ወደውስጥ በመመለስ አልጋቸው ጠርዝ ላይ ተቀመጡ ፡፡ወ.ሮ ስንዱም የራሳቸው አልጋ ላይ እንደተቀመጡ ነው፡፡
ወንበር ሳባና ከሁለቱ መካከል ተቀመጠና ኮምፒተሩን ጠረጳዛ ላይ አስቀመጠው፡፡
‹‹ይሄውላችሁ በትዳር ውስጥ ችግር መፈጠርና አለመስማማት የእናንተ ብቻ ሳይሆን የሚሊዬን ጥንዶች ችግር ነው..እመኑኝ ያልተስማማንበት ነገር ይህ ነው ያ ነው ብላችሁ ቀኑን ሙሉ ስትዘረዘሩ ብትውሉ የእናንተ ከሌላው ትዳር ውስጥ ከተፈጠረው ችግር የተለየ ሊሆን ይችላል እንጂ የባሰ ግን አይደለም፡፡ስሙኝ አብዛኛውን ጊዜ በትዳር ውስጥ ችግር ሲከሰት በትዳር ውስጥ ችግር የፈጠረውን ነገር ከማየት ይልቅ እራሱ ትዳርን እንደችግር የመውሰድ አዝማሚያ ይታያል።ያ ደግሞ ከትዳራቸው ውስጥ ሾልኮ ስለመውጣት
ስለመፋታት እንዲያስብ ያደርጋቸዋል።እንደሀሳባቸው ትዳራቸውን ፈተው የተሻለ ወዳሉት ወደሌላ ትዳር መሸጋገር ቢችሉም ችግሩም አብሯቸው ነው ወደአዲሱ ትዳራቸው የሚሸጋገረው።
መፍትሄው ትዳሩን እንደችግር ወስዶ ያልሆነ ድምዳሜ ላይ ከመድረስ ይልቅ ትዳሩ ውስጥ የተከሰቱ ችግሮች ምን ምን ናቸው ብለው በመለየት እነሱን ለማስወገድ መጣር እና በዛ ሂደት የጋብቻውን ህልውና ማስቀጠል ይበጃል።ምክንያቱም የመኪናህ ጓማ ቢያልቅ ጎማውን ትቀይራለህ እንጂ መኪናዋን ሙሉ በሙሉ አታስወግድም።አይደለም ጎማ ሞተሩ ቢነክስ እንኳን ሞተር አስወርደህ ከእንደገና ተፈቶና ተበታትኖ ችግሩ ተለይቶ ከተወገደ በኃላ መልሶ ይገጣጠምና መኪናው እንደነበረ ይቀጥላል... ጋብቻም እንደዛ ነው የሚደረገው።እና አሁን እያደረግን ያለነው በመሀከላችሁ ያለውን ችግር የመቃቃራችሁን መንሴ መለየት ነው፡፡አሁን በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ ሁለታችሁም የተናገራችሁትን እዚህ ኮምፒተር ላይ ከፍትላችኃላው በጋራ አብራችሁ ታዩታላችሁ…ይሄ መልሳችሁ የተናገራችሁትን እንድታዳምጡና የትኛው ትክክል ነው..የትኛው ንግግራችሁ ተጋኗል የሚለውን መልሳችሁ እንድታስበቡበት ይረዳችኃላ…በቃ አሁን ቀጥታ ወደማዳመጡ እንግባ ››አለና ኮምፒተሩን ከፈተና ለ.ወሮ ስንዱ አቀበላት…አቶ ኃይለልኡል ያለምንም ንግግር ከተቀመጠበት የራሱ አልጋ ተነሳና ሄዶ ወ.ሮ ስንዱ አልጋ ላይ ከጎኗቸው ተቀመጠና በኮምፒተር የሚታየውን የራሳቸውን ንግግር ለማደመጥ ዝግጁ ሆነ…ሰለሞን በፀጥታ ከተቀመጠበት ተነሳና ክፍልን ለቆ በራፍን ዘጋላቸውና ወጥቶ ሄደ…
ይቀጥላል
youtube-https://www.youtube.com/@ethio2023
ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራ ሰባት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
ይዘውት የሄዱት ቦታ ከቢሾፍቱ ከተማ በባቦጋያ ሀይቅ አካባቢ ከከተማው ወጣ ብሎ የሚገኝ ቪላ ነው፡፡ይህ ቪላ ቤተሰቡ ከውጥረት ረገብ ለማለት ሲፈልግ የሚገለገልበት ስፋራ ነው፡፡ለአለፉት አንድ አመት ከግማሽ ማንም ዝር ብሎበት አያውቅም ነበር፡፡ሰለሞን ስፍራውን ሲያይ ከውበትም ሆነ ከፀጥታ አንፃር ሲታይ ሙሉ በሙሉ እሱ እንደሚፈልገው አይነት ሆኖ ነው ያገኘው፡፡አንድ ሺ ካሬ ሜትር በላይ የሚሆን ቅፅር ግቢ ነው፡፡መሀከል ላይ ግዙፍና ባለግርማ ሞገስ ጥንታዊ ግን ደግሞ ጥሩ ይዞታ ላይ ያለ ግዙፍ ቪላ ቤት አለበት…ግቢው ውስጥ እድሜ ጠገብ ግዙፍ ባለግርማ ሞገስ የባህር ዛፍና የጥድ ዛፎች ስብስባ ላይ እንደተቀመጠ ታዳሚ እዚህም አዛም ዙሪያውን ተሰራጭተው ይታያሉ…ገና ግቢውስጥ ገብተው እንዳቆሙ የቤት ጠባቂዎች በልና ሚስቶች በፍጥነት መጥታው መኪናዋ አጠገቡ ቆሙ፡፡መኪናዋን ሲነዳ የነበረው እራሱ ሰሎሞን ስለነበረ….ሞተሩን
አጠፋና ቀድሞ ወረደ…አቶ ኃይለመለኮትን ወ.ሮ ስንዱም ወረዱና ከጠባቂዎቹ ጋር ሰላምታ መለዋወጥ ጀመሩ…ከዛ ቀጥታ ወደ ቤት ነው የገቡት….ቀድመው ደውለው ስለነበር..እቤቱ ምሉ በሙሉ ፀድቶና የእነሱም መኝታ ክፍል ተዘጋጅቶ ነበር የጠበቃቸው….
ታፈሰ ‹‹ጋሼ ባዘዙኝ መሰረት ሶስት ክፍል ለመኝታ አዘጋጅቼያለው…ይሄው እርሶ እዚህ ግቡ….እትዬ ደግሞ ቀጥሎ ያለው …ወንድም አንተ ደግሞ የፊት ለፊተኛው ክፍል…..ድንገት ስለሆነብን ሁሉንም ነገር ማዘጋጀት አልቻልንም….የጎደለውን ንገሩኝና ከተማ ወጣ ብዬ ገዝቼ አሟላላሁ››
አቶ ሃይለመለኮት ወደሰለሞን እያመለከቱ‹‹ተፈሰ…ይሄውልህ እዚህ 15 ቀን ነው የምንቆየው….በዚህ 15 ቀናት ውስጥ የእኛም ሆነ የአንተ ሀለቃ እሱ ነው….ምንም ነገር ቢያዝህ እሱ ያለውን ነው የምታደርገው…እኛም እንደዛው››ሲሉ መመሪያ አስተላለፉ፡፡
ታፈሰ…የአቶ ኃይለልዕልን ንግግር ከበፊት ቆፍጣና ባህሪያቸው ጋር አልሄድ ስላለው ..ግራ በመጋባት አፍጥጦ ያያቸው ጀመር…እሱ እንደሚየውቀው እኚ ግዙፍ አዛውንት ለሰው ምንም ሊሰጡ ይችላሉ የአዛዥነት ቦታቸውን ግን ፈፅሞ ሸርፈው እንኳን ለሌላ ሰው ይሰጣሉ ብሎ ማመን ይከብደዋል፡፡
‹‹ታፈሰ ..ሰምተኸኛል…የሁሉ ነገር አዛዣችን እሱ ነው››ደገሙለት፡፡
‹‹አዎ ..ገባኝ ጌታዬ…እንዳሉት ይደረጋል››
‹‹አሁን ሁላችንም ወደክፍላችን እንግባና ትንሽ አረፍ እንበል ..አይደል?››ወ.ሮ ስንዱ የሰለሞንን አይኖች በልምምጥ እያዩ ጠየቁ፡፡
ቆይ አንዴ ክፍላችሁን ልይ ብሎ..ለአቶ ኃይለልኡል የተመደበውን ከፍቶ አየው፡፡ቀጥሎ የወ.ሮ ስዱን ከፈተና አየው፡፡‹‹ጥሩ በቃ ግቡና እረፉ››
ሁለቱም ገቡና የየራሳቸውን ክፍል ዘጉ
‹‹አንተም ወደክፍልህ ግባ ጌታዬ..እኔ ደግሞ እቃችሁን ከመኪና ላውርድ››
‹‹ቆይ አብሬህ ልምጣ››ብሎ ተከተለው፡፡የታፈሰ ባለቤት ለእንግዶቹ ምግብ እያበሰለች ስለነበር ታፈሰ እቃዎቹን ማለት ይዘው የመጡትን አስቤዛ እና ሻንጣዎች ሲያወርድና ወደቤት ሲያስገባ ሰሎሞን አገዘው፡፡እንደጨረሱ፡፡‹‹ተለቅ ያለ ክፍል የለም?››ሲል ጠየቀው፡፡
‹‹ምን አይነት ክፍል…ማለቴ ለምን የሚሆን?››
‹‹ለመኝታ ቤት የሚሆን ..ሁለት አልጋ የሚያዘረጋ››
‹‹ቆይ ..ኮሪደሩ መጨረሻ ላይ ያለው ክፍል ሰፋ ይላል››
‹‹ማየት እችላለሁ?››
‹‹አዎ ይቻላል….››ብሎ ይዞት ሄደና ከፈተለት…ሰለሞን ወደውስጥ ዘልቆ ሳይገባ በራፉ ላይ በመቆም አንገቱን ወደውስጥ አስግጎ ተመለከተው….አቦራ የጠጣና ለብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቢሆንም የሚፈልገው አይነት ክፍል ነው፡፡››
‹‹ታፈሰ ይሄንን ክፍል በአስቸኳይ ልታስፀዳልኝ ትችላለህ….?››
‹‹እችላለሁ..አፀዳዋለው››
‹‹አይ ብቻህን ይከብድሀል..ሰው ቅጠርና በፍጥነት ወለሉም ግድግዳውም ይፅዳ….ውስጥ ያሉት እቃዎችም ወደሌላ ክፍል ይዘዋወሩ››
‹‹እሺ››
ተሰናብቶት ንፁህ አየር ሊቀበልና እግረመመንገዱን አካባቢውን ለመቃኘት ወጥቶ ሄደ፡፡
///
በማግስቱ ጥዋት 3 ሰዓት ላይ ሁለቱንም የማይጣጣሙ ባለትዳሮችን አንድ ክፍል ጎን ለጎን እንዲቀመጡ አደረገና እሱ ከፊት ለፊታቸው ተቀመጠ..ጉሮሮውን አፀዳዳና የመግቢያ ንግግሩን ጀመረ
‹‹በሰዎች መካከል ለተለያየ አለማ ተብለው የሚደረጉ የእርስ በርስ ጉድኝቶችና ቁርኝቶች አሉ፡፡ከነዛ መካከል ግን በጣም ውስብስቡ የጠበቀውና የጠለቀው ግንኙነት በአንድ ወንድ እና ሴት መካከል የሚፈጠር የጋብቻ ጉድኝት ነው፡፡በጋብቻ ውስጥ የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ሁሉ ጊዜ ቀላል የተባለ መንገድ አይገኝም….አንዱ ጋብቻ ውስጥ የሚፈጠረው ችግር ከሌላው ጋብቻ ችግር በአይነትም በይዘትም ፍፁም የተለየ በመሆን ችግሩን ለማስተካከል የሚወሰደውም እርምጃ የዛኑ ያህል የተለያ ነው፡፡በዛ ላይ ሁሉም ችግሮች እዲፈቱ በጥንዶቹ መካከል ስክነት፣ ትዕግስትን፣ጥረትን እና እራስ መግዛትን
ይጠይቃል፡፡አሁን ልብ በሉ ፣ጥረታችን በመካለላችሁ ያላውን ግጭትና ጭቅጭቅ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይደልም..አይ እንደዛማ አይሆንም እናንተ ሰው ናቸው፣ሁለት ሰዎች ደግሞ በአንድ ጣሪያ ስር አብረው እስከኖሩ ድረስ በሆነ ነገር መነጋገራቸውና በነገሩ ላይ የተለያየ ተቃራኒ ሃሳብ ማንፀባረቃቸው አይቀርም…ስለዚህ መነጋገርና መጨቃጨቃችሁ ኖርማል ነው…አሁን ምንድነው ምናደርገው በማንኛውም ጉዳይ ላይ አለመግባባት ተከስቶ ስትነጋገሩ በምን መልኩ ነው ኮምንኬት የምታደርጉት..?ነገሩን ማስረዳትና ማሳመን ላይ ነው ትኩረታችሁ ወይስ ያንን ምክንያት አድርጎ በስድብና በዘለፋ ማጥቃትና ልብ መስበር…አያችሁ ትልቁ ችግር መጋጨታችን ሳይሆን በያንዳንዱ ግጭታችን አንዳችን ለሌላቸውን የልብ ቁስለትና የነፍስ ህመም መስጠታችን ነው፡፡ማጥፋት ያለብን እርስ በርስ መወጋጋቱን ነው…አንዳችን ሌላችን ላይ በምንም አይነት ሰበብ የሚያቆስል ጦር አስበን አይደለም አምልጦን እንኳን መወርወር የለብንም፡፡
እርስ በርስ ከፍ ባለ ቃላት በተነጋገራችሁ ቁጥር ደግሞ እየተጣላችሁ መሆኑን አታስቡት..መጣላት ቃሉ እራሱ አሉታዊ ነው፡፡እየተጣላችሁ ሳይሆን በጋለ ስሜት እየተነጋገራችሁ ነው፡፡በቃ እንዲህ ነው ማሰብ ያለባችሁ፡፡እንደዛ ካሰባችሁ ቀጥታ ችግሩ በጋለ ስሜት መነጋገራች ብቻ ስለሆነ ስሜታችሁን በማረጋጋት ነገሩን ትፈታላችሁ፡፡እየተጣላን ነው ብላችሁ ካሰባችሁ ግን ገና ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው ወይም ሽማግሌ ልትፈልጉ ነው፡፡ልብ በሉ ጮክ ብሎ መናጋገር ሁል ጊዜ መጣላት አይደለም ..አዎ አብዛኛውን ጊዜ በጋለ ስሜት መነጋገር ነው፡፡ሌላው በምንም አይነት ሁኔታ ንግግራችሁ ሰው ፊት አይሁን፡፡የምንወደው ሰው ላይ ያለንን ቅሬታ ብቻውን በሆነበት ጊዜ ነው መናገር ያለብን…እንደዛ ሲሆን ነው ውጤታማና ጥፈቱን ለማረም ፍቃደኛ የሚሆነው…ወቀሳው..ሰው ፊት ሲሆን ግን ሰውዬው የበለጠ በእኛ ቅሬታ እንዲያድርበት መንገድ ያመቻቻል፡፡
‹‹እንግዲ ሁላተችሁም እንደምታውቁት አሁን ለእኛ እዚህ መገኘት ዋናዋ ምክንያት በፀሎት ነች፡፡እኔ በስራ በተለይ ከሀገር ውጭ በነበርኩበት ጊዜ በጣም ብዙ ባለትዳሮችን አማክሬያለሁ ትዳራችውም መካከል ያለውን ችግር በመተጋገዝ ለመፍታት ችያለሁ....በብዙዎችም ረክቼለው..ከብዙ ቤተሰቦች ጋርም እቤተሰብ ለመሆን ችያለው….ግን እመኑኝ እንዲህ እንደእናነተ የተለየ ጉዳይ ገጥሞኝ አያውቅም››
‹‹የተለየ ስትል?››
ጉዞ በፀሎት(አቃቂ እና ቦሌ)
ደራሲ-ዘሪሁን ገመቹ ዋቤ
ምዕራፍ-አስራሁለት
(ያለፈው ምዕራፍ ያመለጣችሁ ወደሚከተለው የቴልግራም ቻናል ጎራ በማለት ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ቴሌግራም -https://t.me/zerihunGemechu)
//
አቶ ለሜቻ ተንሰቅስቀው እያለቀሱ ነው..፡፡የቤቱ ሰው ሁሉ በድንጋጤ ተሸብሯል…፡፡በፀሎት የምትገባበት ጠፍቷት አብራቸው እንባዋን እያረገፈች ነው፡፡፡ልጃቸው ፊራኦል ላጠፋው ጥፋት አባትዬው ይቅር እንዲሉት በጉልበቱ ተንበርክኮ እየለመናቸው ነው፡፡
‹‹ልጄ ይቅር የምልህ..እያንዳንዱን የገዘኸውን ዕቃ ወይ በየገዛበት መልሰህ ካልሆነም ለሌላ በመሸጥ ገንዘቡን አንድም ሳታጎድል ለልጅቷ ስትመልስ ነው፡፡››
‹‹እሺ አባዬ እንዳልክ አደርጋለው፡፡››
‹‹እኮ ተነስና አድርግ››
‹‹አሁን እኮ መሽቷል….ነገ በጥዋት ተነስቼ እንዳልከው አደርጋለው››
‹‹እስከዛው ላይህ አልፈልግም፣ወይ ቤቱን ለቀህ ውጣ ወይ እኔ ልልቀቅልህ››
‹‹አረ አባዬ… አንተ ምን በወጣህ እኔ ወጣለሁ….››ብሎ ከተቀመጠበት ሲነሳ በፀሎት ከተቀመጠችበት ሆና ጣልቃ ገባች…ጋሼ የሆነው ነገር ሁሉ የእኔ ሀሳብ ነው….ቆርቆሮውም..ሲሚንቶውም ሁሉም የተገዛው በእኔ ሀሳብ ነው፡፡በወቅቱ እሱ እንደማይሆን ነገሮኝ ተቃውሞኝ ነበር..እኔ ነኝ ያስገደድኩት…ስለዚህ ወቀሳውም ቅጣቱም የሚገባው ለእኔ ነው…ለሊሴ ታክሲ ልትጠሪልኝ ትችያለሽ?››
ጥያቄዋ ሁሉንም ሰው አስደነገጠ፡፡
‹‹እንዴ ታክሲ ምን ሊያደርግልሽ?››ለሊሴ ጠየቀች፡፡
‹‹የጋሼን ቅጣት ተግባራዊ ለማድረግ ነዋ…ሆቴል ድረስ የሚወስደኝ ታክሲ ጥሪልኝ…ከቤት መባረር ያለብኝ እኔ ነኝ››
‹‹ተይ እንጂ ልጄ..ለምን ጡር ውስጥ ታስገቢኛለሽ?››አቶ ለሜቻ ለዘብ ብለው ተናገሩ
‹‹ጋሼ ..ይሄ ምንም ጡር አይደለም…ይሄንን እቃ ያስገዛሁት ለራሴ ስል ነው….ያው እንደምታዩት በዚህ አያያዜ ለመዳን ሁለትና ሶስት ወር ይፈጅብኛል ..ከዳንኩ በኃላም ቶሎ የምሄድበት ቦታ ስለሌለኝ ከእናንተ ጋር ቢያንስ ስድስት ወር ኖራለው..ስድስት ወር ሙሉ ደግሞ እንዲህ የለሊሴን መኝታ አስለቅቄ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መኖር ከባድ ስለሆነ ነው
ሀሳብን ያመጣሁት..እኔ እንደውም ቤቱን ተረባርበን በአንድ ወር ውስጥ አልቆ እኔ ከእነለሊሴ ጋር እኖርበታለው ብዬ ነው››ስትል አብራራች፡፡
‹‹ልጄ ቢሆንም አግባብ አይለም..በእኛ ላይ ይሄን ሁሉ ብር መከስከስ እኛም አሜን ብለን መቀበል ነውር ነው…ሰውን ተይው …እግዚያብሄሩስ ምን ይለናል?››
‹‹አሁን ልጅህ ለሊሴ ብር አግኝታ እንዲህ ብታደርግ ይሄን ያህል ትበሳጭባታለህ?›› ዝም አሉ
‹‹ገባኝ አትበሳጭባትም….እኔንም እንደልጅህ አድርገህ ከምር ብትቀበለኝ ኖሮ ይሄን ያህል ቅር አትሰኝም ነበር..በቃ ለሊሴ ደውለሽ ታክሲውን ጥሪልኝ››
ለሊሴ ፈራ ተባ እለች… ስልኳን ከተቀመጠበት አነሳችና ለመደወል ስትዘጋጅ ጋሽ ለሜቻ‹‹ልጄ ስልኩን አስቀምጪው..እስኪ ሁላችሁም ተቀመጡና እንረጋጋ…››
‹‹አዎ ልጆች ሁላችሁም ተቀምጡ….ለሊሴ እስኪ ሲኒውን አቀራርቢና ብና እናፍላ››እናትዬው ውጥረቱ ረገብ ስላለ ተደስተው የተናገሩት ነበር፡፡
////
በማግስቱ
‹‹…አየሩ በጥላቻ ጥላሼት ጠቁሯል፡፡ከፍቅር ዕጦት በሚመጣ የፍራቻ ግንብ ተከልያለው….በንዴቴ አጥር ስር ተሸሽጌ እየተንቀጠቀጥኩ ነው፡፡ይበርደኛል..አዎ በጠራራ ፀሀይ ይበርደኛል…ይርበኛል..እየበላው ሁሉ ይረበኛል….፡፡ጉሮሮዬ በጥማት ተሰነጣጥቆል….ግን ከዛ ከጥማቴ የሚፈውሰኝ ውሀም ሆነ ምድራዊ ወይን የለም፡፡››በፀሎት ነች የምታወራው…ፊራኦል ግን ምንም አልገባውም
‹‹አንዳንዴ እንደፈላስፋ ነው የምታወሪው?››
‹‹እንደእኔ ህይወትህን ሙሉ በብቸኝነት በራፍ ዘግተህ ለብዙ ሰዓታት በትካዜና በቁዘማ የምታሳልፍ ከሆነ ወደፈላስፋነት መቀየርህ የግድ ነው፡፡ከሞት ደጃፍ ደርሶ..በቃ አበቃልኝ ብሎ ተስፋ ከቆረጠ በኃላ ወደህይወት ተመልሶ ሁለተኛ እድል የተሰጠው እደእኔ አይነት ሰው ነገሮችን በተለየ መልክ ባያይ ነው የሚገርመው፡፡›››
‹‹አልገባኝም የሞት አፋፍ ላይ መድረስ ስትይ?››
ደነገጠች..አንደበቷን አንሸራቷት ሚስጥር ልታወጣ በመድረሶ እራሷን ወቀሰችና‹‹ማለቴ በዛ ለሊት በሞተሬ ከእዚህ በራፍ ጋር ስለ መጋጨቴ እያወራው ነው…የሞትኩ ማስሎኝ ነበር እኮ››
‹‹እ..እሱ እንኳን እውነትሽን ነው….ግን አሁን ፊትሽ ቁስሉ ደርቆል እኮ …ለምን ቀንና ለሊት በሻርፕ ትሸፍኚዋለሽ…››
‹‹እርግጥ እንዳልከው ድኗል ግን ጠባሳው ያስጠላል..እንዲህ ሆኜ ሰው እንዲያየኝ አልፈልግም ..በተለይ ወንዶች ››
ፈገግ አለ….‹‹ዝም ብለሽ እያካበድሽው ነው እንጂ እርግጠኛ ነኝ ከነጠባሳሽ በጣም ቆንጆ ልጅ ነሽ…እንደውም እንዲሁ አቋምሽን ሳየው የት እንደሆነ የማውቃት አርቲስት ወይም ሞዴል ነገር እየመሰልሽኝ ደነግጣለው፡፡››
‹‹አየህ አንደውም ለዚህ ነው ፊቴን ዘወትር በሻርፕ ምጆብነው››
‹‹አልገባኝም››
‹‹ሙሉ በሙሉ ገልጬልህ ፊቴን በደንብ ካየኸው የትኛዋ ሞዴል ወይ አርቲስት እንደሆንኩ ወዲያው ስለምትለየኝ፣እንደዛ እንዳይሆን ስለፈለኩ ነው››
‹‹ትቀልጂያለሽ አይደል?››
‹‹ምን ላድርግ ብለህ ነው….በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ያለ እንደእኔ አይነት ሰው ባይቀልድ ነው የሚገርመው››
‹‹እስኪ እርእሱን እንቀይር ፣ሌላው ስለአንቺ የሚገርመኝ እስከአሁን ሞባይል ይዘሽ አለማየቴ ነው››
‹‹የለኝም…..ማለቴ ከቤቴ ስወጣ ይዤ መውጣት አልቻልኩም፡፡››
‹‹ታዲያ ልግዛልሽ…ማለቴ በራስሽው ብር የምትፈልጊውን አይነት ስልክ ልገዛልሽ እችላለሁ፡፡››
ፈገግ አለችና‹‹በራስህ ብር ብትገዛልኝ አይሻልም?››
‹‹ደስ ይለኝ ነበር..ግን አቅሜ ላንቺ የሚመጥን ስልክ ለመግዛት በቂ አይመስለኝም…››
‹‹የእኔ አቅም ምን ያህል ነው..?በምንስ ሚዛን ለካሀው…?ለማንኛውም ለጊዜው አያስፈልገኝም…ስፈልግ ግን ነግርሀለው፡፡››
‹‹ይገርማል… በአንቺ እድሜ ያለች ሴት ስልክ አያስፈልገኝም ስትል አጃኢብ ነው፡፡››
‹‹ምኑ ይገርማል..?ለጊዜው ማንም ጋር ለመደወል እቅድ የለኝም..››
‹‹ሶሻል ሚዲያስ….እንዴት ያስችልሻል፡፡››
‹‹ዕድሜዬን ሙሉ ስልክና ላፕቶፕ ላይ አረ አንቺ ልጅ አይንሽ ይጠፋል እየተባልኩ እስክሪን ላይ አፍጥቼ ነው የኖርኩት…ሶሻል ሚዲያ ከጨለማ ሀሳቦቼ እና ከድብርቶቼ መሸሺጊያ እና መደበቂያ ዋሻዬ ነበር…አሁን ግን ችግሮቼን ፊት ለፊት መጋፈጥ ነው የምፈልገው
….እስከአሁን ከኖሩኩት ህይወት በተቃራኒ ነው መኖር የምፈልገው፡፡ይልቅ ከቻልክ ነገ መፅሀፎች ገዝተህልኝ ትመጣለህ፡፡››
‹‹እሺ ምን ምን መፅሀፍ እንደምትፈልጊ ትንግሪኝና ገዝቼልሽ መጣለው፡፡››
‹‹ጥሩ አሁን ደግሞ ምርጥ አንድ ሙዚቃ ብትጋብዘኝ በጣም ደስተኛ እሆናለው…››
‹‹ጥሩ …አለና ከአጠገቡ ያለውን ክራር አንስቶ ክሮቹን በእጁ እያጠበቀ እና እያላላ ቅኝቱን አስተካከለና‹‹ምን አይነት ዘፈን ይሁንልሽ?››ሲል ጠየቃት፡፡
‹‹መቼስ በዚህ ውድቅት ለሊት ስለሀገር ዝፈንልኝ አልልህም…የፍቅር ዘፈን ይሁንልኝ፡፡›› እንደማሰብ አለና ክራሩን መገዝገዝ ጀመረ ..አፏን ከፍታ ነበር የምታዳምጠው…
የነገን ማወቅ ፈለኩኝ … መጪውን አሁን ናፈቅኩኝ.. የፍቅር ምርጫዬ አንቺ ነሽ…ልቤንም መንፈሴን የገዛሽ ወሰንኩኝ ልረታ አስቤ፣አካሌን መንፈሴን ሰብስቤ
በፍቅር ህይወቴን ላኖረው..ላልመኝ ፍፁም ሌላ ሰው የፍቅርን ትርጉም ገልፀሸ አስተማርሺኝ
ካንቺ ደስታ ፣እኔን እያስቀደምሺልኝ ፍቅር ለካ ለራስ …ማለት እንዳልሆነ ስታደርጊው አይቶ… ልቤ በቃ አመነ ከነገርሽ…. ባህሪሽ ማርኮኛል…
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana