ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
ኤጀንሲው አንድ የወረዳ ጽ/ቤት አመራር እና አንድ ሰራተኛውን በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አደረገ
C R R S A: የካቲት 17/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በደረሰው የተገልጋይ ጥቆማ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ተስፋዬ አያለው እንዲሁም የነዋሪ መረጃ፣ ህትመት ስርጭት እና ቁጥጥር ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ እጅጉ በጋራ በመመሳጠር ላለተገባ ሰው አገልግሎትን በገንዘብ ለመሸጥ በ10ሺ ብር ተደራድረው የዲጂታል ምዝገባ በማከናወን ላይ ሳሉ በተደረገው ክትትል እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።
የተቋሙ የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ክፍል ከፖሊስ ጋር በመተባበር ላለፉት ሶስት የስራ ቀናት ክትትል ሲያደርግ በመቆየት ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ የካቲት 17 በጽ/ቤቱ ውስጥ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ተቋሙ በክትትሉ የተደራጁ የድምፅ ቅጂ እና ተጨማሪ ማስረጃዎችን ለፖሊስ አስረክቧል።
ውድ ነዋሪዎቻችን
ተቋማችን እራሱን ከህገ-ወጥነት ለመከላከል የስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና የስራ ክፍል የመረጃ አቅምን እያጠናከረ ያለና የዲጂታል አገልግሎቱም ኦዲት የሚደረግበት ስርዓት የዘረጋ በመሆኑ ይህንን ተቋማዊ ቆራጥ አቋም በመረዳት ከህገ-ወጥ ደላሎች እና አገልግሎትን በገንዘብ ከሚሸጡ እራሳችሁን እንድትጠብቁ እንዲሁም እራሳችሁም ተባባሪ ከመሆን እንድትቆጠቡ እያሳሰበ መሰል ሁኔታዎች በአገልግሎታችን ላይ ሲገጥማችሁ በ7533 የነፃ የስልክ መስመር ወይም ከታች ባለው የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ሊያገኙን ይችላሉ።
ሌብነትን በፅኑ እንታገላለን!
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
የፌስቡክ (facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (telegram): https://t.me/addisvaitalpress
በድጋሚ የወጣ ልዩ የቅጥር ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጃንሲ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የከተማዋን የሲቪል ምዝገባ እና ዲጂታላይዜሽንን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር የሚችል ስትራቴጂክ አማካሪ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።
የቅጥር ቦታ: የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት
የስራ ቦታ: የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጃንሲ ዋና መስርያ ቤት
ዝርዝር መረጃውን በመግባት ያግኙ
https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00333414
Special Vacancy Announcement (-Re)
The Civil Registration and Residency Service Agency (CRRSA), in collaboration with the Ethiopian National ID (NID) Program and with support from The World Bank, is seeking qualified Advisor to lead the Addis Ababa City Civil Registration and Digitalization efforts to the next level.
Project: NIDP
Duty Station : CRRSA HQ
For detailed information about the vacancy and application process, please visit the following link:
https://projects.worldbank.org/en/projects-operations/procurement-detail/OP00333414
ወርቃማው ሰኞ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በልዩ ሆኔታ ተከናወነ
የካቲት 17/2017ዓ.ም
አዲስ አበባ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ወርቃማው ሰኞ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፣ የስትራቴጂ እና ጠቅላላ ካውንስል አባላት እንዲሁም ሰራተኞች በተገኙበት ተከናውኗል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የኤጀንሲው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጅ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዕምሮ ካሳ ያለፉባቸውን የህይዎት ተሞክሮ እና የስራ ልምድ ያገኙትን እውቀት አካፍለዋል፡፡
ዕለቱን ልዩ ያደረገው በኤጀንሲው አዲስ ለተሾሙት የወሳኝ ኩነት እና የነዋሪነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ፣ እንዲሁም በምክትል ዋና ዳይሬክተር ማዕረግ የተቋሙ አማካሪ አቶ ጥጋቡ ሹመይ የኤጀንሲው አመራሮች እና ሰራተኞች የአንኳን ደስ አላችሁ እና የመልካም ምኞት ተመኝቷል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በመድረኩ ላይ በሰጡት የስራ መመሪያ አዲሶቹ ተሿሚዎች በተቋም ግንባታ የተፈጠሩና ከባለሙያ ጀምሮ የተሰጣቸውን ስራዎች በአግባቡ እየተወጡ የመጡ እንዲሁም የተቋም ሪፎርም ላይ አሻራቸውን ያስቀመጡ በመሆናቸው ለአመራርነት እንደበቁ በመጥቀስ ተቋሙ አሁን የደረሰበትን ስራ ወደ ፊት ማስቀጠል ከአዲሰቹ አመራሮች ከፍተኛ ኃላፊነት እንደሚጠበቅ አሳስበዋል፡፡
አዲሶቹ አመራሮችም በመድረኩ በመገኘት ከዋና ዳይሬክተሩ የስራ መመርያ ወስደዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፣ ጥቆማ ወይም ማብራርያ በተገልጋይ የስልክ መስመራችን 7533 ደውለው ያግኙን
ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et
የፌስቡክ (facebook): https://www.facebook.com/profile.php?id=100064083391686
ቴሌግራም (telegram): https://t.me/addisvaitalpress
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 3 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago