ን ዑ ስ - ኗ ሪ ?

Description
ኑረታችንን እንጋራ፣ cheers ? !






ስናወጋ በ @yfelgalubot ቢሆንስ ግን?
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 2 weeks ago

Last updated 1 month, 1 week ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 week, 2 days ago

11 months, 3 weeks ago
ወዳጄ! እኔ ሌላን አልመስልም። ላንተ ስኬት …

ወዳጄ! እኔ ሌላን አልመስልም። ላንተ ስኬት ብለህ ያሰመርከው ግድ አይሰጠኝ ይሆንና የኔ ጥረት 'ለዚህች ነገር' ያስብልህ ይሆናል። አንተን እንድመስል ቢፈለግ ኖሮ አንተን ሁለቴ ይፈጥርህ አልነበር?! እኔ ለምድር ሌላ ቅመም ነኝ፤ አንተም እንደዛው! የማልፈው ፈተና የምደርስበት ሰማይ እንደሚለየው ሁሉ የማበረክተውም ይለያልና መንገድህን ለብቻህ ተጓዝ። ስለ'ኔ መቆም ና መንቀራፈፍ ግድ አይስጥህ። የኑረቴ ፀፀት ለኔው ይትረፍ። አንተን ባልመሰልን ላይ ሁሉ አትፍረድ። መፍረድ የፍፁም ሐቅ ነውና!

@my_jas

1 year, 1 month ago
የአላህ ሰላምታ የሚሻ ማን ነው?

የአላህ ሰላምታ የሚሻ ማን ነው?

የአሏህ ሰላምታ ፣ ሐያታችንን በበረካ የሚያስውብልን የጀሊል ስጦታ ነው።
« በኔ ላይ አንድ ሰለዋትን ያወረደ አሏህ በእርሱ ላይ አስር ሰላምታን ያወርድበታል። »

اللهُمَّ صَلِّ على مُحَمَّدٍ عَبْدِكَ ونَبِيِّكَ ورَسُولِكَ النَبِيِّ الأُمِّيِّ?

#ሸጋ_ጁምዓ

@My_Jas

1 year, 1 month ago
`በነዛ በጎደልንባቸው ቀናት፣ ከጎናችን እንዲቆም የከጀልነው …

በነዛ በጎደልንባቸው ቀናት፣ ከጎናችን እንዲቆም የከጀልነው ሁሉ ሲርቅ መሸሻም መጠጊያ አሏህ መሆኑን እንረዳለን። ከነነውራችን እጃችንን ዘርግተን ባዶ የማይመልስ አሏህ``! ስንፈግግ ተደስቶ ስንቸገር የማይሸሸን መሸሻ `አሏህ``!

#هو?`

@my_Jas

1 year, 1 month ago
ኹሉም ለኸይር ነው። የምንሔደው የእሾህ መንገድ …

ኹሉም ለኸይር ነው። የምንሔደው የእሾህ መንገድ መቋጫው ገደል ቢመስልም ለኸይር ነው። ኑሕ አለይሒ ሰላም መርከብ ሲሰራ መጀመሪያው ልፋት እንደነበረው ሁሉ። የማይሽር ለሚመስል ሕመማችን ፣ የማይሳካ ለሚመስል ጭንቃችን መታገሳችንም ለኸይር ነው። ዘከሪያ አለይሒ ሰላም እስከእድሜው ጫፍ ትእግስትን እንደታገሰው። ሰበብ በማድረስ ብቻ የማይመቻቹ ክዋኔዎቻችንን ከውኖ በቀሪው ተአምር መጠበቅም ለኸይር ነው። ከፊርአውንና ጭፍሮቹ ሲሸሽ ተከፍሎ ሊቆም የሚሳነው ባህር አጠገብ ነብዩሏህ ሙሳ እንደገሰገሰው።

በሁሉም ውድቀት መሳይ ጭንቅ ውስጥ አሏህ ያሰበልን ኸይር (ቢገለፅም ቢደበቅ) አልለና አብሽሩ!

ሰባህ አል ኸይር?
@my_jas

1 year, 2 months ago
°|

°|
ገፀ ሰማይ ላይ . . .
ኮከብ ተዘርቶ ብርሀን ሲታጨድ
ልቤን አድርጋት የፍቅር አፀድ ፡
እንደ ጨረቃ. . .
በፅልሙ መሀል ሙት ነፍሴ ትንቃ ፡
:
ይሄም ያልፋል . . .
ይገፈፋል እንዳልነበር
ይዘከራል እንደ "ነበር" !
ብለህ በላት
ሲያጥራት ተስፋ ፡
ልቤን ያዛት ፡
ከእዝነት እቅፍ እንዳ'ጠፋ ።

ሲገፈፍ ፅልሙ ስትርቅ ጨረቃ
ፀሀይ ስትፈግግ ከውኑን አድምቃ ፡
ትፈንድቅ ሩሄ. . .
ይልቀቃት አዚም ድካም ህመሙ ፡
ባ'ንተ አይደለም ወይ
ፅልመት ተረትቶ ብርሀን የሞላው አለሙ!
:
•[ አብዱ ሩሚ ]•

@ktebiban_meder

1 year, 2 months ago
`ሰላምሽን ታጫለሽ፥ ልክነትሽን በሰዎች ጭብጨባ መመዘን …

ሰላምሽን ታጫለሽ፥ ልክነትሽን በሰዎች ጭብጨባ መመዘን ስትጀምሪ። የ"ትችያለሽ" ድምፅን የመስጠት መብትሽን ስታጋሪ... በቃ አንቺው በቂ ነሽ። የሌላው ሆይሆይታ ባለሽ ነገር ላይ ኢምንት አይጨምርም፤ የሱ አለመኖር አያጎድልብሽም። ያለፍሽውን፣ የደረስሽበት ለመድረስ የደረሰብሽን የምታውቂው አንቺ እያለሽ መቋጫሽን አይተው ለሚፈርዱ የነፃነት ገመድሽን አሳልፈሽ አትስጪ... እባክሽን! ይኼን ሁሉ የገበርሽለት አላማሽ ዘንድ ደርሰሽ ማየት የምንፈልግ አእላፍ ነንና በርትተሽ ገስግሺ!

@My_Jas

1 year, 3 months ago
እኔም የምድነው

እኔም የምድነው
አንተም የምትሽረው ባንድ ፍቅር ብቻ!

@My_Jas

1 year, 3 months ago

ለምን ከምናለቅስበት ነገር በላይ ማፅናኛው ሳግ እንደሚያስተናንቀን ብዙም አይገባኝም።አይዞን መባል ያማል እንዴ? አይ በቃ ተይው ለዚ ደሞ ስንባል በሆነ ጎን አለመቻላችን ያጎድለናል እንዴ?

እንጃ ብቻ ሰዎች ባያፅናኑኝ እመርጣለሁ የት አለ የማልለው እምባ ሲፈልቅ ሲያጥለቀልቀኝ ለባሰ ሀዘን ሲገፋኝ ይታወቀኛልና አታፅናኑኝ ብል አልባለግኩም አይደል..! አይ በቃ የገባኝ ከነ ሀዘኔ ከነ ውድቀቶቼ ና ጠባሳዎቼ ተውኝና ልመለስ እስከዛ እርሱኝ ማለት ያምረኛል። እንጃ ብቻ

1 year, 3 months ago

ኢላሂ!
ሠራዊትህ አይሸነፍም።
ቃልህ አይታጠፍም።
ኃይልህ አይገታም።
ለዲን እና የነብይህ ቅርስ ለሆነችው ቅድስት መሬታቸው የሚታገሉ ወንድሞቻችንን አግዛቸው። ለቁስለኞቻቸው ፈውስን ስጥ። ለሰማእታቶቻቸው ምህረትን ለግስ። ለታጋዮቻቸው ሁሉ ድል አጎናፅፍ። አሚን!

1 year, 4 months ago

አንዳንዴ ከመንገዴ መሐል ቆሜ .... የወረደብኝን ኹሉ የምሸከምበት አቅም ሳይኖረኝ ለመቀበል መታጨቴን ሳስብ እንደሌላሰው ሆኜ ለራሴው ከንፈር እመጣለሁ፣ ሳላስበው አይኔ በእርጥበት ይረሰርሳል። ያቺ ትንሽ የምታሳሳ ልጅ በቅፅበታት ውስጥ ሐላፊነቶች የተደራረቡባት፣ ራሷን ዘንግታ ለሌላው የምትኖር ነዝናዛ ሴትን የወለደችው መች ነው እስክል ድረስ... ብቻ ሁሉም ነገር ፍትህ አለው ብለን እናድበስብስ እንጂ...

አልሐምዱሊላህ

@my_Jas

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 2 weeks ago

Last updated 1 month, 1 week ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 week, 2 days ago