ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
በአፋር ክልል፣ ሳጋንቶ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየወጡ ነው
በአፋር ክልል፣ ዱለሳ ወረዳ በተከሰት የመሬት መንቀጥቀጥ ሳቢያ በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየተፈጠሩ ይገኛሉ።
በወረዳው በሳጋንቶ ቀበሌ የደረሰውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ በስፍራው በአካል በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ የኢቢሲ ሪፖርተር በቀበሌው በበርካታ ሥፍራዎች ላይ ፍል ውሃዎች እየወጡ መሆኑን መታዘቡን ገልጿል።
ሊመረቅ 4 ቀን ቀረው‼️
''ተመስገን'' የተሰኘው የዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ቁጥር 2 የዝማሬ አልበም የፊታችን እሁድ ታኅሣሥ 27 ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ ይመረቃል::
በፍላሽ የተዘጋጀውን የዝማሬውን አልበም ገዝተው 16ቱን መዝሙራት ለመስማት ቀዳሚ ይሁኑ:: መዝሙራቱ በሁሉም የCD Distribution አማራጮችና (spotify, itunes…) በተለያዩ መተግበሪያዎች ይገኛሉ::
በመላው ዓለም ለማከፋፍል
በ+251941518851/ +1 469 733 0150 ይደውሉ ወይም [email protected] ይጻፉልን::
ተመስገን ተመስገን
ለምስጋና ስላሰባሰብከን
እግዚአብሔር ተመስገን
በህክምና የታገዘ ሞት እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ
በኢትዮጵያ በህክምና የታገዘ ሞት፣ የወንድ የዘር ፈሳሽ ልገሳ እና የሰውነት አካል መለገስ እንዲጀመር የሚፈቅደው ህግ ጸደቀ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና አገልግሎት እና አስተዳድር ረቂቅ አዋጅን አጽድቋል።
አዋጁ ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ተጀምረው የማያውቁ እና አዳዲስ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችሉ የጤና አገልግሎቶች እንዲጀመሩ የሚያደርግ ነው።
ለአብነትም መዳን በማይችል እና በስቃይ ውስጥ ያሉ ታማሚዎች በሀኪሞች እርዳታ እንዲሞቱ የሚፈቅደው፣ የሰውነት አካልን ያለ ክፍያ መለገስ፣ የወንድ የዘር ፍሬ እንዲለገስ እና ሌሎችም አዳዲስ የህክምና አገልግሎቶችን ይፈቅዳል ተብሏል።
ምክር ቤቱ ላለፉት ወራት የተለያዩ ውይይቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።
የዋልያዎች ቁጥር እየቀነሰ ነው ተባለ
ሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ እንዲመሰረት ዋናው መሰረት የነበረው ዋልያ ቁጥሩ እየቀነሰ መምጣቱን የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ አስታውቋል፡፡
የፓርኩ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ማሩ ቢያርግልኝ እንዳሉት፤ በሰሜኑ የተከሰተው ጦርነት የቱሪስት ፍሰቱ ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ እንደነበር እና ለዋልያዎቹ መቀነስ ምክንያትም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ዋልያዎችን ለመጠበቅ ሲባል እንደ ሳር፣ ደን እና ውሀ የመሳሰሉ ነገሮች ስለሚጠበቁ ዋልያዎች ከቀነሱ እና ከጠፉ የአካባቢው ማህበረሰብ ተጎጂ እንደሚሆንም ተናግረዋል፡፡
ዋልያ በአለም በኢትዮጰያ ሰሜን ተራሮች ብቻ የሚገኝ የዱር እንስሳ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
የዋልያዎች ቁጥር እንዳይጠፋ እና ወደነበረበት ለመመለስ፤ የሚገኙበት አካባቢ ላይ ከፍተኛ ክትትል የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
ሀላፊው ቀደም ካሉት ግዜያት አሁን በፓርኩ የተሻለ የቱሪዝም ፍሰት መኖሩን አንስተዋል፡፡
ያለንበት ወቅት የፈረንጆች ዘመን መለወጫ ስለሆነ በቀጣይ ሁለት ሳምንታት በርከት ያሉ ቱሪስቶች ፓርኩን ይጎበኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል፡፡
ኢትዮ ኤፍኤም
ናሳ ለፀሐይ ቅርብ በሆነ ርቀት መንኮራኩር ማሳለፍ ቻለ
የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ፓርከር ሶላር ፕሮብ ለፀሐይ ቅርብ በሆነ ርቀት መንኮራኩር ለማሳለፍ ያደረገው ጥረት መሳካቱን አስታውቋል፡፡
ናሳ መንኮራኩሩ ከጸሃይ በቅርብ ካለፈ በኋላ "ደህንነቱ የተጠበቀ" መሆኑን እና የተሳካ ተልዕኮ ማድረጉን ገልጿል፡፡
በጸሃይ ጎን በሚያልፍበት ወቅት ከምድር ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ያልነበረው መንኮራኩሩ ትናንት ከእኩለ ሌሊት በፊት ከናሳ ጋር ግንኙነት ማድረጉ ተጠቁሟል፡፡
የተልዕኮው መሳካት የፀሐይ ንፋስ አመጣጥን እንዲሁም በፀሐይ ወደ ምድር በሚለቀቁ ቅንጣቶች ላይ ሳይንስቶች የተሻለ መረዳት እንዲኖራቸው ያደርጋል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የጠፈር መንኮራኩሩ በሰዓት 430 ሺህ ሜትር የሚጓዝ ሲሆን፤ ከፍተኛ ሙቀትን እና ጨረሮችን መቋቋም አንዲችል ተደርጎ መሰራቱም ተገልጿል፡፡
ዩክሬን ለሩሲያ ሲዋጋ የነበረ ሰሜን ኮሪያዊ ወታደር ማረከች
የዩክሬን ጦር ለሩሲያ ወግኖ ሲዋጋ የነበረ የቆሰለ ወታደር ለመጀመሪያ ጊዜ መማረኩን የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት አስታወቀ።
ወታደሩ ሰሜን ኮሪያ የሩሲያን ጦር ለመደገፍ ወታደሯቿን አሰማርታለች ከተባለበት ታህሳስ ወር ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ የተማረከ ነው ተብሏል።
የቆሰለውን ወታደር የሚያሳይ ፎቶ በቴሌግራም ከተጋራ በኋላ ነው የደቡብ ኮሪያ ደህንንት ማረጋገጫውን የሰጠው።
ሰሜን ኮሪያ ሩሲያን ለማገዝ ከ10 ሺህ በላይ ወታደሮች ማሰማራቷን የዩክሬን እና የደቡብ ኮሪያ ባለስልጣናት ገልጸዋል።
ሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ወታደሮቹ መሰማራታቸውን አላረጋገጡም እንዲሁም አልካዱም።
ነገር ግን መንግሥታዊ የዜና ወኪል ኬሲኤንኤ በቅርቡ ባሰራጨው የሰሜን ኮሪያ መግለጫ አገሪቱ ከሩሲያ ጋር ያላት አጋርነት "የአሜሪካ እና የምዕራቡ ዓለም ያሰቡትን ተጽእኖ እያደናቀፈው ነው" ብሏል።
ከ3 ሺህ በላይ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በከርስክ ግዛት ሲዋጉ እንደሞቱ ወይም እንደቆሰሉ የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሰኞ ዕለት ገልጸው ነበር።
ሩሲያ የተጣለባትን ማዕቀብ ለማምለጥ ቢትኮይንን እየተጠቀመች ነው ተባለ።
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ግዛቶች መላኳን ተከትሎ ምዕራባዊያን ሀገራት በሞስኮ ላይ ከ12 ሺህ በላይ ማዕቀቦችን ጥለዋል።
ይህን ተከትሎ ሩሲያ ከዚህ በፊት የነበሯትን የንግድ ልውውጦች እንደልብ ማድረግ አልቻለችም።
ይህን ለማምለጥም እንደ ቢትኮይን ያሉ የምናባዊ መገበያያ መንገዶችን እየተጠቀመች እንደሆነ የሩሲያ ፋይናንስ ሚንስትር ተናግረዋል።
ሚንስትሩ አንቶን ሲሉአኖቭ ለሩሲያ 24 በሰጡት ቃለ መጠይቅ፤ ሩሲያ ከዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር የቢትኮይን ግብይት እንዲያደርጉ ፈቅዳለች ብለዋል።
ሩሲያ በተለይም ዋነኛ የንግድ አጋር ከሆኑት ቻይና እና ቱርክ ጋር የቢትኮይን ግብይት እያደረጉ እንደሆነም ሚንስትሩ ጠቅሰዋል።
የቢትኮይን ልማት እየተካሄደባቸው ካሉ የዓለማችን ሀገራት መካከል ሩሲያ ቀዳሚዋ ስትሆን፤ ይህ ግብይት ማዕቀቦችን መቋቋም እንድትችል አስችሏታል ተብሏል።
የአሜሪካ ባለስልጣናት በደማስቆ
ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ከሶሪያ መሪዎች ጋር ለመነጋገር በደማስቆ እንደሚገኙ ተነገረ፡፡
የፕሬዝደንት ጆ ባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን በሀያት ታህሪር አል ሻም (ኤችቲኤስ) ከሚመሩት የሶሪያ ባለስልጣናት ጋር ለመመከር በዛሬው እለት ደማስቆ መሆናቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አስታውቋል።
የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ዋነኛ ዲፕሎማት ባርባራ ሊፍ፣ የሆስቴጅ ጉዳይ ፕሬዝደንታዊ ተወካይ ሮገር ካርስቴንስ፣ በቅርቡ የሶሪያን ጉዳይ እንዲከታተሉ የተሾሙት ከፍተኛ አማካሪ ዳኒኤል ሩቢንስተን ሶሪያን ለረጅም ጊዜ የመራው በሽር አላሳድ በተቃዋሚ ታጣቂዎች ከስልጣን ከተገረሰሰ በኋላ ደማስቆን የጎበኙ የመጀመሪያዎቹ ዲፕሎማቶች ሆነዋል።
ይህ ጉብኝት የተካሄደው ምዕራባውያን ሀገራት ቀስ በቀስ በራቸውን እየከፈቱ እና በቡድኑ ላይ የተጣለውን የሽብርተኝነት ፍረጃ ስለማንሳት ወይም ስላለማንሳት እየተወያዩ ባለበት ወቅት ነው።
የአሜሪካ የሉእካን ቡደን ጉብኝት ቡድኑ በቅርቡ ከፈረንሳይ እና እንግሊዝ ጋር ግንኙነት ማድረጉን ተከትሎ የመጣ ነው ተብሏል።
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana