Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

Description
ዲያቆን ፍፁም ከበደ

ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb

facebook Link...
https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month, 1 week ago
  • ምልጃ ለምን ያሰፈልጋል +

  • ክፍል ሦስት (3) +

ለመኾኑ ምልጃ ለምን አስፈለገ ? እግዚአብሔር ያለ ሦስተኛ ወገን ሲነግሩት ስለማይሰማ ነውን ? ወይስ የእግዚአብሔር ፍርድ በጠበቃው ችሎት የሚለወጥ ስለኾነ ? ምልጃስ በማጭበርበር ሰነድ በመለወጥ ኃጥኡን ጻድቅ ማድረግ ነውን ? ታድያ ምንድን ነው ምልጃ ? ሰዎች እኛ እግዚአብሔር በቀጥታ ማነጋገር እንችላለን እርሱ ይሰማናል ፤ ስለዚህ ሦስተኛ ወገን አያስፈልግም ይላሉ። በውኑ ምልጃ የሚሹት ወገኖች እግዚአብሔር አይሰማንም ብለው ይኾንን ወይስ ስለ ሌላ ?

ሀ. ድኅነት ሥርዓት ስላለው ?
ለ.የእግዚአብሔርን የምሕረት ብዛት እንድናደንቅ?
ሐ.የእግዚአብሔርን ባለሟሎች ለይተን እንድናቅ ?
መ.ስለ ትሕትና ?

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

1 month, 1 week ago

🎵 የስልክ ጥሪ 🎵

  • የንስሐ ዝማሬ +

  • የጴጥሮስን እንባ +

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

1 month, 1 week ago

🎵 የስልክ ጥሪ 🎵

  • የንስሐ ዝማሬ +

  • በምጓዝበት ተጓዥ +

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

1 month, 2 weeks ago

#በልብህ ብታምን ትድናለህ

"ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚአብሔር ከሙታን ለይቶ እንደ አስነሣው በልብህ ብታምን ትድናለህ ። በልቡ የሚያምን ይጸድቃልና በአፍ የሚመሰክር ይድናል " ሮሜ 10፥9-10 ። ምን ማለት ? በውኑ መናፍቃን እንደሚሉት ኢየሱስ ጌታ ነው ብቻ በልን የጽድቅን ሥራ ሳትሰራ ትድናለህ ማለት ነውን ? ሌላው በጣም ትኩረት ልንሰጠው የሚገባው ጉዳይ በልቡ የሚያምን ይድናል ማለቱ ምን እንደ ኾነ ማወቅ ነው ።

#ሲብራራ ፦ ኢየሱስ ጌታ እንደ ኾነ በአፍህ ብትመሰክር ማለት "ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ እንደ ኾነ በልብህ ብታምን አንድም የባሕርይ ገዥነቱን ብትቀበል አንድም አብን ጌታ ፈጣሪ ገዢ ጠባቂ አንደምትል ሁሉ እኩል በኾነ መልኩ ወልድንም ብትል ፤ ብለህ ብታምን " ማለት ነው ። በመጽሐፍ ቅዱስ ሰው ኹሉ አብን እንደሚያከብር ወልድንም ያክብር ዘንድ ፍርድን ኹሉ ለወልድም ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው እንኳን አይፈርድም ይላልና ሐዋ 5፥19-25 ።
ይህ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌል ቀጥሎ እንዲህ የሚል ንባብ አለው ፦ አብ ሙታንን እንደሚያነሳ ሕይወትንም እንደሚሰጥ እንዲሁ ወልድ ደግሞ ለሚወዳቸው ሕይወትን ይሰጣል። ይላል። በመኾኑም ይህን ማመን መመስከር ግድ መኾኑን ልብ ማለት ያስፈልጋል ። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ከልብ አምኖ በአንደበትም መመስከር ተገቢ መኾኑን የሚያስረዳ ነው ። ይህ ከልብ አምነው የሚያቀርቡት ምስክርነት ለሰማዕትነትም ሊያበቃ ይችላል። ብዙ ቅዱሳን ሰማዕታት በአላውያን ነገሥታት ፈት ምንም ሳይፈሩ ስለ ክርስቶስ ጌትነት አምላክነት መስክረው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀብለዋልና ። ( ትምህረተ ጽድቅ ገጽ-285፥286

#ይቀጥላል ...

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ

1 month, 2 weeks ago

#ቅድስት

ሁለተኛው እሁድ ቅድስት በመባል ሲታወቅ ይኽም ጌታ ስለ ዕለተ ሰንበት ቅድስና በምኩራብ ያስተምራቸው ነበርና ይህን ግልጽ አድርጎ የሚያስረዳ ነው ። ምክንያቱም አይሁድ በሰንበት ያደርጉት የነበረው ሥርዓት ለሰንበት ያላቸው አክብሮት ፈሩን የለቀቀ ስለነበር የሰንበትን ምስጢር በግልጽ ያስቀመጠበት ነው ። ለሰንበት ጌታዋ የሰው ልጅ መሆኑንም አስረድቶታል ። ማቴ 12፥8

1 month, 2 weeks ago

🔴አዲስ የንስሐ ዝማሬ "የመዳን ቀን ዛሬ" በዘማሪ ዲ/ን አክሊሉ

🤴ናታኒም ቲዩብ🤴 SUBSCRIBE በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ ናታኒም ማለት የእግዚአብሔር ቤት ጠራጊ ታናሽ አገልጋይ ማለት ነውና። 👇🏽👇🏽👇🏽
https://youtu.be/i6uvg2vDmvQ

YouTube

"የመዳን ቀን ዛሬ አዲስ የንስሃ ዝማሬ" በዘማሪ ዲ/ን አክሊሉ ሽመልስ Subscrbers🔔 Like👍 sher⤵️ በማድረግ ናታኒም ቲዩብ ቤተሰብ ይሁኑ!!

1 month, 2 weeks ago
[#ለገዳማዊ](?q=%23%E1%88%88%E1%8C%88%E1%8B%B3%E1%88%9B%E1%8B%8A) ሕይወት ለምንኩስና ለብሕትውና ጀመሪውና መሪው …

#ለገዳማዊ ሕይወት ለምንኩስና ለብሕትውና ጀመሪውና መሪው ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ራሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ።ይኸው እንደ ተጠመቀ ወዲያውኑ ሳይውል ሳያድር ወደ ምድረ በዳ ሄዶ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ምንም ነገር ሳይቀምስ ከማንም ጋር ሳይገናኝ በተባሕትዎ ቆይቷል ። በዚህም ለባሕታውያን ብሕትውናን ባርኮ ቀድሶ ሰጥቷል። እንዲሁም በድንግልና በመኖር ለደናግልና ለመነኮሳት አብነት መምህር ሆኗል ። ማቴ 4፥1-2

#ከክርስቶስ ዕርገት በኋላ በስምንት ሽህ ማኅበረ ክርስቶስ (ማኅበረ እስጢፍኖስም ይባላሉ) ነበሩ ። እነዚህ ያላቸውን ነገር ሁሉ እያመጡ ከሐዋርያት እግር ስር እየጣሉ "ይህ የአንተ ነው ፣ ይህ የእኔ ነው " ሳይሉ በአንድነት ለጸሎትና ለትምህርተ ወንጌል ጽሙዳን ሆነው ይኖሩ ነበር ። ይህ ያላቸውን ሁሉ ትተው ከሐዋርያት አንድነት ገብተው መኖራቸው በመንኖ ጥሪት በአንድነት ለሚኖሩ ገዳማውያን አብነት እና መሠረት ነበር ። የሐዋ 4፥32-37 (ፍኖተ ቅዱሳን ዲያቆን ያረጋል አጋዝ ገጽ-241)

1 month, 2 weeks ago
[#በቅድመ](?q=%23%E1%89%A0%E1%89%85%E1%8B%B5%E1%88%98) ውሳኔ አይፈረድብንም

#በቅድመ ውሳኔ አይፈረድብንም

"#ሰማዕቱ ጀስቲኖስ" እያንዳንዱ በዓለም የሚከናወነው ክንውን በእግዚአብሔር ቅድመ ውሳኔ ምክንያት ነው የሚሉትን ሰዎች ሲገሥጽ "አንዱ ሰው መልካም አንዱ ደግሞ ክፍ እንዲሆን አሰቀድሞ በእግዚአብሔር የተወሰነ ከሆነ መልካም እንዲሆን የተወሰነለት መልካምነቱ በራሱ ሥራ ሳይሆን በተወሰነለት ውሳኔ መሰረት ነውና ስለመልካምነቱ ምሥጋና አይገባውም ። ክፍም ክፍ የሆነው ክፍ እንዲሆን አሰቀድሞ ስለተወሰነበት እንጂ በራሱ ሥራ ክፍ ስላልሆነ ወቀሳ አይቀርብበትም ። የሰው ልጆችም ኃጢአትን የማስወገድና ጽድቅን የመምረጥ ኃይልና ችሎታ ባይኖራቸው ኖሮ በሚሠሩት ማንኛውም ሥራ አይጠየቁም ነበር ። በማለት እግዚአብሔ በነጻፍቃዳችን ተጠቅመን በምንሰራው ስራ እንጂ በእርሱ ቅድመ ውሳኔ በማንም ላይ እንደማይፈርድ ማንንም ቀድሞ ለበጎ እንጂ ለክፍ አንደማይወስን አስተምሯል ።

1 month, 2 weeks ago

#ፀጉሬን ባስረዝም ችግር አለው ?

ቅዱስ ጳውሎስ ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥ ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና ። ( 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥14-15) በማለት ፀጉርን ማሳደግ ለወንድ ነውር መኾኑን ነግሮናል ። ከዚህ በተጨማሪ ሠለስቱ ምዕትም በፍትሐ ነገሥት "ኢታስተርኢ ለእርስተከ በአፍአ" ይህ ማለት ፀጉርን ስበህ እስክታየው ድረስ አታሳድገው ።

እነዚህ ሥርዓቶች የሚያስገነዝቡን ወንዶች ፀጉራቸውን ማስረዘም እንደሌለባቸው ነው ። እንዲያውም ሊቁ ቅዱስ አምብሮስ "ለወንድ ሴትን መምሰል ተገቢ አለመኾኑን ይገልጻል ። ወንዶች ጠጉራቸውን ማስረዝ የለባቸው የሚለው ሕግ ለሁላችንም የተሰራ ሐዋርያዊ ሥርዓት ስለ ኾነ ክርስቲያን እስከሆን ድረስ ልንተገብረው ግድ አለብን ። (መጽሕተ ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው ገጽ-120)

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ የቴሌግራም #መንፈሳዊ ቻናል  #ይከታተሉን

1 month, 2 weeks ago

#ቤተክርስቲያን ለአንድ ክርስቲያን የነፍስ ምግብ ቤቱ ናት ሥጋ ወደሙን ይቀበልባታል ፣ ሐኪም ቤቱ ናት ከኃጣአት በሽታ ይታከምባታል ፣ ማረፊያው ናት ይጽናናባታል እንዲሁም ኤምባሲው ናት የሰማዩን የይለፍ ማኅተም ያስመታባታል ።

ቅድስት ቤተክርስቲያን የሰማይ ደጅ ናት ። 🙏

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas