ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ

Description
ዲያቆን ፍፁም ከበደ

ሀሳብ ካሎዎት @Fisumkeb

+ ግሩፕ ለመቀላቀል +

https://t.me/NablisNablis

+ facebook Link...

https://www.facebook.com/deaconezemarefitsume.kebede

TikTok
https://www.tiktok.com/@zdfitsumkebede1?_t=8pguEgtdsVq&_r=1
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

4 days, 18 hours ago
5 days, 8 hours ago

~ኅዳር 21~

እንኳን-ለቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ🙏🙏

~ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች ~።

በዚህች_ቀን:-
✞ ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

✞ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

✞ በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

✞ ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

✞ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

✞ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

✞ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

✞ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

1 week ago

ሰው ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን ?

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምዕራፍ ዐሥራ አምስት ላይ የተጠቀሰውን ትምህርት አስተምህሮ ከፈጸመ በኋላ ከገሊላ ወጥቶ በዮርዳኖስ ማዶ ወደሚሆን ወደ ምድረ ይሁዳ ደረሰ ። የተከሉትንም ሰዎች በዚያ ፈወሳቸው ።

ፈሪሳውያንም ሊፈትኑት "ሰው በሆነው ምክንያት ሁሉ ሚስቱን ሊፈታ ተፈቅዶለታልን ? ብለው ጠየቁት ። እርሱ ግን መልሶ "ፈጣሪ በመጀመርያ አዳምን ወንድ ሔዋንን ደግሞ ሴት አደረጋቸው ስለዚህ ነገር ሰው አቤቱንና ትቶ ሚስቱን ተከትሎ ይሄዳል ። ከሚስቱም ጋር ይተባበራል በግብር አንድ ይሆናል ። ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ ። አንድ አካል ማለትም እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ይሆናሉ ። ወንዶች ቢወለዱ ያንተ ናቸው ። ሴቶች ቢወለዱ ደግሞ የአንቺ ናቸው አይባባሉም ። የተወለዱት ልጆች መልካቸው እርሱን ቢመስሉ እኒህ የአንተ ናቸው አትለውም ። እርሱም የተወለዱት ልጆች እሷን ቢመስሉ እኒህ የአንቺ ናቸው አይላትም ። የሚለውን ከኦሪቱ አላነበባችሁምን ? ስለዚህ አንድ ሥጋ ናቸው እንጂ ወደፊት ሁለት አይደሉም ። በዚህ ዓለም ሳሉ በሕጋቸው ጸንተው ዐሥራት ፣ በኩራት ቀዳሚት አውጥተው እንግዳ ተቀብለው ይኖራሉ ። ወዲያውም መንግሰተ ሰማያት ወርሰው ይኖራሉ ።

እንደ መላእክት እንግዲህ እግዚአብሔር አንድ ያደረገውን ሰው አይለነው " አላቸው ።( ኪዳነ ጽድቅ ገጽ-148 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

1 week, 4 days ago

ጾመ ነብያት ነገ እሑድ ኅዳር 15 ይገባል ።

ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ:: እኛ ስለምን እንጾማለን? ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን? አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን? እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ? የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ? የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን:: ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው:: ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ::

(ዲያቆን ኄኖክ ኃይሌ )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

1 week, 5 days ago

እህታችን Sofia Shibabaw አንድ ኦርቶዶክሳዊ ወንድም መጽሐፍ ቅዱስ ታነባለህ ወይ ብላ ስትጠይቀው መዝሙረ ዳዊት ነው በየቀኑ የማነበው በማለቱ በእጅጉ ተገርማ የምትናገርበትን አንድ ውይይት ተመለከትሁ። በዚሁ ውይይት መዝሙረ ዳዊት የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ መሆኑን ጠቅሳ ዋናው አዲስ ኪዳን ነው ብላ የሰውዬውን ልማድ በመገረም ተችታ ታልፋለች። በርግጥ ንግግሯ ከመቆርቆር ይመስለኛል።

እህታችን ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን (በተለይም አዲስ ኪዳንን) ማንበብ እና መረዳት አለበት ማለቷ ትክክል እና የሚደገፍ ነው፤ ቤተ ክርስቲያንም በየቅዳሴው እና የማኅበር ጸሎቶቿ ሁሉ ዘወትር የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንዲነበቡ ሥርዓት ሠርታለች። ባይሆን እኛ ራሳችን እንደፈቀድን እንተርጉመው የሚለው ፕሮቴስታንታዊ መርሕ ብዙ ጣጣ ያለው ስለሆነ አንቀበለውም።

ነገር ግን ስለ መዝሙረ ዳዊት ያላትን አመለካከት ማስተካከል ያለባት ይመስለኛል። መዝሙረ ዳዊት ከጥንት ቤተ ክርስቲያን ጀምሮ ትልቅ ቦታ ያለው እና ለጸሎት እና ለትምህርት ትልቅ ቦታ የተሰጠው መጽሐፍ ነው። ጌታችንም ሐዋርያትም የጸለዩበት መጽሐፍ ነው። መዝሙረ ዳዊት ብሉይ እና አዲስ ኪዳንን አጠቃልሎ የያዘ ልዩ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ ንስሐን፣ ተአምኖን፣ ምሥጋናን፣ ልመናን፣ ትምህርትን፣ ተግሳጽን እና ሌሎች ዋና ዋና ጉዳዮችን የያዘ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጉዳዮችን ሁሉ አጠቃልሎ የያዘ መጽሐፍ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን በቀላሉ ማግኘት ወይም ቢገኝም ማንበብ በማይቻልበት ጊዜ መዝሙረ ዳዊትን ማንበብ እና ማሰላሰል (meditation) መጽሐፍ ቅዱስን ሁሉ እንደማንበብ የሚያገልገል ነው።
በዚህ ነገር የተሐድሶ መሪው ሉተርም ሳይቀር ይደግፈናል፦

"[The Psalter] might well be called a little Bible. In it is comprehended most beautifully and briefly everything that is in the entire Bible. It is really a fine enchiridion or handbook. In fact, I have a notion that the Holy Spirit wanted to take the trouble himself to compile a short Bible and book of examples of all Christendom or all saints, so that anyone who could not read the whole Bible would here have anyway almost an entire summary of it, comprised in one little book."
(Luther‘s Works 35:254).

(በረከት አዝመራው)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

2 weeks, 3 days ago
*****😍***** **ፊልም አፍቃሪ ከሆንክ ይሄ ቻናል …

*😍 *ፊልም አፍቃሪ ከሆንክ ይሄ ቻናል ላንተ ነው 😍**

ዶቃ ከለሊቱ 6 ሰአት አፍላ ፍቅር ዮአዳን ሊሊ ፍቅር እስከ መቃብሪ ኢንስፔክተር ኤርሚያስ የመሳሰሉትን ፊልም አዳዲስ ክፍል ለማግኘ👇*👇 *🔥 ለመመልከት👇**https://t.me/+EY6KSjZDHYBmYTM0

2 weeks, 4 days ago
  • ምጽዋት +

ምጽዋትን ለተቸገረ ወገኑ የሚሰጥ ሰው ለእግዚአብሔር መስጠቱ ነው ።

፦ ምጽዋት ለአምላክ የሚሰጥ ብድር ነው ።
፦ ምጽዋትን የሚመጸውት ለችግረኛ የሚራራ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል በስጦታውም መጠን እግዚአብሔር ይከፍለዋል( ምሳ19፥17 ሲራ 29፥1)

ምጽዋት ብልህ ሰዎች በእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስቀምጡት አደራ ነው ። ገንዘብ /ንብረትን/ በታመነ ሰው ዘንድ ማስቀመጥ /አደራ ማስጠበቅ / የተለመደ ነው። በፈለጉት ጊዜ የሚገኝ ስለሆነ ።

"ያላችሁን ሽጡ ሽጣችሁ ምጽዋት ስጡ የማያረጅ ከረጢት ለእናንተ አድርጉ የማያልቅ ድልብም በሰማይ ሌባ ከማይደርስበት ነቀዝ ፣ ብል ከማያበላሹበት ገንዘባችሁ ካለበት ልባችሁ በዚያ ይኖራል ። ሉቃ 12-32 ማቴ 6-19-21 እንዲል ማለት ነው ።

ምጽዋት ሰው ለሰው ያለው በጎ ፈቃድ የሚገለጥበት ክርስቲያናዊ የሥነ ምግባር ዘርፍ ነው ። በዚህ ዓለም ጥረት ከራሳቸው ተርፈው ለሌሎች ማካፈል ችግረኞችን መርዳት የሚቻላቸውን ብቻ ሳይሆን በመጠነኛ ኑሮ የሚተዳደሩ ደጋግ ሰዎች ያለንን ተመግበው ለሀብታችን ለዕውቀታችንና ጉልበታችን ሳስተን የምንኖር ከሆነ መንግሥተ ሰማያትን በምን እንወርሳለን ? ብለው ከሚበሉት ከሚጠጡት ከፍለው ይረዳሉ ይመጸውታሉ ። በኑሮአቸው በዝቅተኛነት የመስጠት ፈቃዳቸውን የልግስና ብልፅግናቸውን አያግደውም ። ከአቅማቸው የሚያልፍ እንኳ ቢሆን ጨክነው ያደርጉታል ። ፪ኛ ቆሮ ፰-፪ ።( ኪዳነ ጽድቅ ገጽ 96-97 )

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

3 weeks, 2 days ago

ማንም ተገርዞ ሳለ ተጠርቶ እንደሆነ ወደ አለመገረዝ አይመለስ ማንም ሳይገረዝ ተጠርቶ እንደ ሆነ አይገረዝ (1ኛ ቆሮንቶስ 7፥19-20) (ቁ.18) ፦ ሳይገረዝ አምኖ የተጠመቀ ክርስቲያን ሳይገረዝ መኖር ይችላል ። የአንድምታው ተርጓምያን ሐዋርያው ይህን አሳብ ያነሣበትን ምክንያት ሲገልጹ"ግዙር ቆላፍ አምነዋል ግዙር ቆላፍነትን ተመኝቶ ነበር ቆላፍም ግዙርነትን ተመኝቶ ነበር " ይላሉ ። ሐዋርያው ያለገረዘም ባለመገዘሩ ፣ የተገረዘም በመገዘሩ እንዲጸኑ ጽፎላቸዋል ።

መገረዝም ቢሆን አለመገዘርም ቢሆን ከንቱ ነው ። የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መጠበቅ ነው እንጂ(ቁ.19) ፦ ገላ 5፥6፣6፥15 ያነጻጽሩ ። ሰውን የሚያጸድቀው የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ነው እንጂ መገረዝ ወይም አለመገረዝ አያጸድቅም ።

እያንዳንዱ በተጠራበት መጠራት እንደዚሁ ይኑር(ቁ.20) ፦ ተገርዞ የተጠራ ተገርዞ ይኑር ። ሳይገረዝ የተጠራ ሳይገረዝ ይኑር ። ("የሐዋርያው የቅዱሰሰ ጻውሎስ መልእክታት ከሮሜ እስከ ገላትያ" መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ ዳምጤ ገጽ-237)

#ኦርቶዶክሳዊ_አእምሮ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago