Jocopia press( ጆኮፒያ)

Description
This is Jocopia press and media Communication official Telegram channel.

✅ informed well for all?


? For addition:- 0928716459
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 3 weeks ago

Last updated 3 days, 20 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 1 week ago

2 months ago
Landing of the airship Los Angeles …

Landing of the airship Los Angeles on the aircraft carrier Saratoga, USA, January 27, 1928.

3 months, 1 week ago
***?*** **ኤፍራታ YouTube Channel** ***?***

? ኤፍራታ YouTube Channel ?

በቅርብ ቀን አዝናኝ እንዲሁም አስተማሪ ፕሮግራም ወደ እናንተ ይዘን መጠናል። በነዚህም የፕሮግራም አማራጮች ትረካ ፣ ግጥም ፣ ቲክ ቶክ ላይ የተመረጡ ቪዲዮ ይቀርብበታል።

?አጠቃላይ መረጃዎች በቴሌግራም ቻናላችን የሚለቀቁ ሲሆን እናንተም በዚህ የሶሻል ሚዲያ አማራጭ መከታተል እንደምችሉ ለማሳወቅ እንወዳለን።

????????????

?የቴሌግራም አድራሻችን
@Ethiopia_Inclusiveness

3 months, 3 weeks ago
በጎፋ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ለመላው ኢትዩጵያዊ …

በጎፋ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ ለመላው ኢትዩጵያዊ መጽናናትን እንመኛለን ነብስ ይማር???

https://t.me/joco_pia_press

4 months, 3 weeks ago

በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ የታሪክና የጥበብ መፅሐፍት ??_??

የኛ የኢትዮጵያን ንብረት የሆኑት ነገር ግን በተለያዩ አጋጣሚ ወደ ዉጭ ሀገረ የተወሰዱ መፃህፍት እንዳሉ ይታመናል ከእነዚህም የተወሰኑትን እንመልከት፡፡
      ሀገራት  የመፃህፍት ብዛት
1-እንግሊዝ...2804  
2-ፈረንሳይ...854
3-ጀርመን ...511
4-እስራኤል...386
5-ቫቲካን...286
6-አሜሪካ ...401
7-ጣሊያን...108
8-ቤልጀም....71
9-ሲውዘረላንድ...38
10-ኦስትርያ..37
11-ሲዊዲን..12
12-ሆላንድ..4
13-ካናዳ....3
በአጠቃላይ  5515  መፃህፍት በለይ
፨ ከብዙ የአለማት ሀገራት በብዛት መፃሂፍቶቻችን የተወሰዱት እንግሊዝ ሲሆን 800 የብራና መፃሂፍቶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም መካከል የፍልስፍና ፣ የዜማ፣ የቅዱሳን ህይወት፣ ህክምና፣ የጥበብ......የመሳስሉት ይገኛሉ፡፡ የሚገርመው ነገር ማንም ሀበሻ ወደ ''The britsh libraray Ethiopic Geez book'' ከዚህ ሙዚየም ገብተው መጎብኘት አይችልም፡፡

#ጆኮፒያ_ፕሬስ በመዎዳጀት ይቀላቀሉን?*?*??**https://t.me/joco_pia_press

Telegram

Jocopia press( ጆኮፒያ)

This is Jocopia press and media Communication official Telegram channel. ***✅*** informed well for all***💎*** ***🌐*** For addition:- 0928716459

***በተለያዩ የዓለም ሀገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ የታሪክና የጥበብ መፅሐፍት*** ***??***\_***??***
4 months, 3 weeks ago
ይህ ሰው ተክለሀዋርያት ተክለማርያም ይሰኛሉ!!

ይህ ሰው ተክለሀዋርያት ተክለማርያም ይሰኛሉ!!
በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን ንጉሣዊውን የ1923 ሕገ-መንግስት ያረቀቁት(የጻፉት) እርሳቸው ናቸው!!

4 months, 3 weeks ago

ከሀገሩ ውጪ ላሉ ጭቁኖች የተፋለመው ኢትዮጵያዊው አፄ ካሌብ ***

5ኛው ክ/ዘመን ኢትዮጵያን ንጉሥ አፄ ካሌብ-_-_-_-_-_

በሚአስተዳድሩበት ዘመን በዓረብ አገራት የሚኖሩትን የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ አይሁዳውያኑ በፋርስ ድጋፍ አማካኝነት በመጨፍጨፍ፣ በማሰቃየትና በመጨቆን አላኖር አሏቸው።

በአሁን አጠራር የመን አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦችን ንጉሥ ፊንሐስ ክፋኛ መከራቸውን አበዛው ፤ በአንድ ቀን ብቻ 20,000 ክርስቲያኖችን እንዳስፈጀ ብዙዎች ፅፈዋል። በዚህ ጊዜም ቶማስ የተባለ ጳጳስ ከየመን አምልጦ ወደ አክሱም በመምጣት ለአክሱም ንጉሥ ካሌብ የተፈፀመውን ግፍ ሁላ አብራራ።

አፄ ካሌብም ሁኔታውን እንደሰማ ለዘመቻ ዝግጅት ጀመረ። ከዝግጅቱ በኋላም 72 ታላላቅ መርከቦችና 70,000 የሚሆኑ ሰራዊት ይዞ ጉዞ ጀመረ። በቦታው እንደደረሰም ውጊያው መርከብ ላይ እንዳሉ በጦር በቀስትና መርከቦቻቸው ተጠጋግተው በጨበጣ ለጥቂት ጊዜ ሲካሄድ ቆይቶ ፍልሚአው ወደየብስ ተቀይሮ በሁለቱም ወገን ብዙ ሰራዊት ካለቀ በኋላ ድሉ የአፄ ካሌብ ሆነና አይሁዳውያኑ ሲበታትኑ ንጉሥ ፊንሐስም ሸሸ።

ከዚያም አፄ ካሌብ ወደ የመን ከተማ ወደ ዛፋር ሔዶ የከተማውን ጠባቂዎች አሸንፎ ከተማውን ያዘ። አፄ ካሌብና ንጉሥ ፊንሐስም ፊት ለፊት ተገናኝተው በጨበጣ ፈረሶቻቸው ላይ ሆነው ሲዋጉ ካሌብ ፊንሐስን ወግቶ ከፈረሱ ላይ በመጣል ወደ ባህር ገፍትሮ ወርውሮ በመገድል ድል አረገው። ከዚህ በኋላ የሸሹትና የተደበቁት ክርስቲያኖች ወደየመንደራቸው ተመለሱ። የፈረሱትንና ያረጁትን ቤተክርስቲያኖች ራሳቸው አፄ ካሌብ እየቆፈሩ በማሰራት ጥቂት ጊዜ በየመን ተቀመጡ።

በየመን ህዝብ ፍላጎትም መሰረትም አርያት የተባለውን ሰው ንጉስ አርጎ ሾሞላቸው በየአመቱም ለአክሱም ቤተ መንግስት እንዲገብሩ ትዕዛዝ ሰጠ። በዚህም የየመን ህዝብ ከካሌብ ጀምሮ ለ100 ዓመታት በመገበር ቀጥለው የነበር ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ፋርሶች መጥተው የመንን በመቆጣጠር ቤተክርስቲያናትን አፍርሰው የጣኦት ቤተ መቅደሶችን ገነብተዋል።

ረሱለላሂ ነብዩ መሐመድ መጥተው ፋርሶችን አሸንፈው የጣኦት ቤተ መቅደስ በማስፈረስ መስጊድ እስካአስገነቡበት 630 ዓ.ም ፋርሶቹ በየመን ቆይተዋል። እንግዲህ አፄ ካሌብ የአክሱምን ስልጣኔ ከማሳደጋቸው ባለፈ ከሀገራቸው ውጪ ላሉ ጭቁኖች በመፋለም ነፃነትን ያጎናፅፋ መሪ በመሆናቸው በአረቦችና በቆስጠንጢኒያ የገነኑ ንጉሥ ናቸው።

ዛሬ ድረስ የሮም ቤተክርስቲያን ከሠማዕታቱ ጋር ቆጥራ በየዓመቱ የአፄ ካሌብን በዓል ኦክቶበር 27 ቀን ታከብራለች።

https://t.me/joco_pia_press
???
#Jocopia_press

ሸጋ ምሽት ተመኘን?

Telegram

Jocopia press( ጆኮፒያ)

This is Jocopia press and media Communication official Telegram channel. ***✅*** informed well for all***💎*** ***🌐*** For addition:- 0928716459

**ከሀገሩ ውጪ ላሉ ጭቁኖች የተፋለመው ኢትዮጵያዊው አፄ ካሌብ** ***
7 months ago
***ንግስት ፉራ ስመጥር የሲዳማ ንግስት የነበረች …

ንግስት ፉራ ስመጥር የሲዳማ ንግስት የነበረች ሲሆን ሴቶችን ሁሉ መልካም ባህሪን ያስተማረችና እስካሁንም ድረስ ተቀባይነት ያላት ሴት ነች***

ንግስቲቱ በጣም ብልህ ነበረች፡፡ በቅድሚያ ሴቶች ለወንዶች ሙሉ ለሙሉ ተገዢ እንዳይሆኑ፣ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ሴቶች ለወንዶች ሙሉ ለሙሉ ታዛዥ እንዳይሆኑ ትመክራቸው ነበር፡፡ ከዚያም በላይ ሴቶች አይን አፋር እንዲሆኑና ወንዶች እነርሱ ስለሚያስቡት ነገር ሁልጊዜም ግምታዊ እንጂ ግልፅ እንዳይሆን ታስተምራቸው ነበር፡፡ ሃፍረተ ገላቸውንም በአደባባይ እንዳያሳዩና ሰውነታቸውንም ከጉልበታቸው እስከ ወገባቸው ድረስ እንዲሸፍኑ ትነግራቸው ነበር፡፡ ወንዶች በውበት ስለሚማረኩ ሴቶች ራሳቸውን በደንብ እንዲጠብቁ ታስተምራቸው ነበር፡፡
ነገር ግን ንግስት ፉራ ለወንዶች በጣም መጥፎ ሴት ነበረች፡፡ የማይቻሉ ነገሮችን ሁሉ እንዲሰሩ ታዛቸው ነበር፡፡
“ወደ ወንዙ ሄደህ ውሃ በወንፊት አምጣ፡፡” እያለች ታዝ ነበር፡፡ ወይም በጣም ስስ ከሆነ ሳር ትልልቅ ገንዳዎችን እንዲሰሩ አለያም ከረጃጅም ፀጉሮቿ አንዱን ነቅላ ስድስት ቦታ እንዲሰነጥቁት በማዘዝ ወንዶችን ታሰቃያቸው ነበር፡፡
ከሁሉ በላይ ግን ራሰ በራና አጭር ወንዶችን አጥብቃ ትጠላ ነበር፡፡ ስለዚህ አጫጭር እንዲሁም ራሰ በራ ሰዎችን ሁሉ እንዲገደሉ ታዝ ነበር፡፡ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ አጫጭርና ራሰ በራ ሰዎች ሲገደሉ አንድ መላጣና አንድ ራሰ በራ ወንዶች ግን ከዚህ ችግር ተርፈው ነበር፡፡

✍️በአበበ ከበደ
?*** Jocopia press_(ጆኮፒያ)

ሠናይ እለተ ሰንበት?***

7 months ago
**ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም**

ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም

ከ 93 ዓመት በፊት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንግሥ በዓል ዋዜማ ፤ የታላቁ ንጉሠ ነገሥት የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ሐውልት በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ፤ ለበዓል የመጡት እንግዶች በተገኙበት ሥርዐት፣ የሐውልቱን መጋረጃ የመግለጥ ክብር ለብሪታንያ ንጉሥ ወኪል ለ(ዱክ ኦፍ ግሎስተር) ተሰጥቶ ሐውልቱ የተመረቀበት ዕለት ነበር።

የዳግማዊ አጤ ምኒልክ መታሰቢያ ሀውልት የቆመው/የተተከለው ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም ነበር፡፡

ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ የአባታቸውን የዳግማዊ አጤ ምኒልክን ስራና ውለታ ቀጣዩ ትውልድ ያስበውና ይዘክረው ዘንድ … ማስታወሻ የሚሆን የመታሰቢያ ሐውልት ለማሰራት አሰቡ፡፡

ሐውልቱንም በጀርመናዊው መሃንዲስ ሙሴ ሄንትል አማካኝነት አስጠንተው፤ ከጀርመን ተቀርፆ እንዲመጣ አዘዙ፡፡ ሀውልቱ የተመደበለት ቦታ ተደልድሎ ከተዘጋጀ በኋላ ገና ሳይተከል/ሳይቆም ንግሥቲቱ መጋቢት 22 ቀን 1922 ዓ.ም አረፉ፡፡

በመሆኑም የንግሥቲቱን እረፍት ተከትሎ ንጉሰ ነገሥት ለመሆን እየተዘጋጁ የነበሩት አልጋ ወራሽ ንጉሥ ተፈሪ መኮንን፣ ከዛሬ 93 ዓመታት በፊት (ጥቅምት 22 ቀን 1923 ዓ.ም) ሐውልቱ በታላቅ ክብረ በዓል እንዲተከል አደረጉ፡፡

በሐውልቱ ላይ አፄ ምኒልክ ካባ እንደለበሱ አንባር አጥልቀው በእጃቸው ጣምራ ጦር ይዘው በፈረሳቸው በ‹አባ ዳኘው› ላይ ተቀምጠው በግርማ ሞገስ ይታያሉ፡፡ የሐውልቱ ቁመት ከተፈጥሮ አካላዊ መጠን በላይ ሲሆን ‹አባ ዳኘው› ፊቱን ወደ ሰሜን መልሶ በኋላ እግሮቹ ቆሞ፣ የፊት እግሮቹን ወደላይ አንስቶ ይታያል፡፡ ፋሺስት ኢጣሊያ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በ 1929 ዓ.ም ወድቆ/ፈርሶ ነበር፡፡

#ጆኮፒያ

7 months ago
Jocopia press( ጆኮፒያ)
7 months ago
Jocopia press( ጆኮፒያ)
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 3 weeks ago

Last updated 3 days, 20 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 1 week ago