Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute

Description
ዳሩል ሀዲስ
የዓረብኛ ቋንቋ እና የሸሪዓዊ ትምህርቶች ኢንስቲትዩት

✔ ኢስላማዊ ቤተ መፃህፍት
✔ የቁርአን ሂፍዝ ፕሮግራም
✔ የአረብኛ ቋንቋ እና ሸሪዓዊ ትምህርቶች

معهد دار الحديث لتعليم اللغة العربية والعلوم الشرعية
(أديس أبابا – تأسيس 1436 هے)

«من يرد الله به خيرا يفقهه في الدين»

👍ዳሩል ሀዲስ
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 weeks, 2 days ago

Last updated 3 weeks, 2 days ago

1 month, 3 weeks ago

📢ቅዳሜ ተጋብዛችኋል(ለሴቶች)🌙ልዩ የረመዳን ትምህርት🌙

📮በእለቱ የሚዳሰሱ ርእሶች ፦

❶  አላህን መፍራት (ተቅዋ)

❷ በዲን ላይ መፅናት (ኢስቲቃማ)

🗓ቀን ቅዳሜ መጋቢት 21 ፣2016

🕘ጠዋት ከ3:30-6:30

🕌 አድራሻ

☞ቤተል አደባባይ ከተቅዋ መስጂድ ፊት ለፊት ባለው መንገድ (ብሩክ ብረታ ብረት) ገባ ብሎ

መልእክቱን ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ እንሁን❗️

✔️ዳሩል ሀዲስ ቤተል ቅርንጫፍ
https://t.me/darulhadis18

1 month, 3 weeks ago

🌙የረመዷን ሙሃደራ ለሴቶች

"لعلكم تتقون "

በእለቱ የሚዳሰሱ ነጥቦች

💎የኢእቲካፍ ፣የለይልቱል ቀድር፣ የዘካተል ፊጥር፣ የኢድ እና የሸዋል ፆም ሽሪአዊ ድንጋጌዎችና ቱሩፋቶች

💎በመልካም ስራ ላይ መፅናት

እና ሌሎችም ቁም ነገሮች

🗓ቀን እሁድ መጋቢት 22  ፣2016

🕘ጠዋት ከ3:00-6:30

🕌 አድራሻ

☞ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ

⚠️ መልአክቱን ለእህቶች በማድረስ መልካም ስራን ያስመዝግቡ።

https://t.me/darulhadis18

1 month, 3 weeks ago

🌙 የጎዳና ኢፍጣር🌙

*🖌 በኢልያስ አሕመድ*

በቅድሚያ ይህን ፕሮግራም ለማሰናዳት በቅንነት የሚለፉ ግለሰቦችና ድርጅቶችን አላህ የኒያቸውን እንዲሰጣቸው እንለምናለን፤ ከዚህ በታች ያለው አጭር ፅሑፍ የልፋታቸው መሰረት የተስተካከለ እንዲሆን ታስቦ በተቆርቋሪነት የተከተበ ነው።
              ››››› ‹‹‹‹‹

በህብረት ማፍጠር ሁለት አይነት አፈፃፀሞች ሊኖሩት ይችላል፦

1ኛ/ ለማፍጠር መሰባሰቡን ዋና ኢላማ ሳያደርጉ በተወሰኑ አጋጣሚዎች በህብረት ማፍጠር ሲሆን ይህም እንደማይወገዝ ግልፅ ነው።
ለምሳሌ፦ ለሰላት ወደ መስጂድ የመጣውን ስብስብ ወይም ድሆችን በአንድ ቦታ ለማስፈጠር የሚኖረው መሰባብሰብ ተቃውሞ ሊነሳበት አይችልም። ዘመድና ጓደኛን ጠርቶ በጋራ ማፍጠርም እንደተራ ግብዣ ሊታይ ይችላል። ፆመኛን ማስፈጠርን አስመልክቶ የተወራውን ምንዳ ለማግኘት ከታሰበ ደግሞ እንደ እሳቤው የተወደደ ሊሆን ይችላል።

ብዙ ዑለማዎች የፈቀዱትም በዚህኛው ምድብ የሚካተተውን ነው።

2ኛው/ ለኢፍጣር መሰባሰቡ ራሱ እንደ ዋና ግብ ታልሞና ይህንንም በሚያሳብቁ ተግባራት ታጅቦ በስፋት የሚተገበር አፈፃፀም ሲሆን ይህ የቢድዓ መገለጫን ሊላበስ ይችላል።

በሀገራችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተለመደው የጎዳና ኢፍጣር ይህንን ይዘት እንደተላበሰ ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል፦

👉 እንደ በዓላት የሚጠበቅ ህዝባዊ ኩነት መሆኑ፣ (Grand Iftar 1, 2 እየተባለ ዘንድሮ 4ኛው ላይ ደርሰናል!)

👉 ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የበድር ዘመቻ የተካሄደበት የረመዳን 17ኛው እለት ለዚህ አመታዊ መሰባሰቢያ እንዲሆን በተደጋጋሚ መመረጡ፣

👉 ሰዎች በነቂስ ወጥተው እንዲታደሙ ሰፊ ጥሪ መደረጉ፣

👉 በታዳሚያን ብዛት ከሌሎች አገራት ጋር ፉክክር ውስጥ የተገባበት መሆኑ፣

እና ሌሎች አባሪ ሂደቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የነዚህ ሂደቶች ስብስብ ተግባሩን ራሱን የቻለ አዲስ የሙስሊሞች ይፋዊ ምልክት (ሺዓር) እያደረገው ነው።

📌 ታላቁ ኢማም #ኢብኑ_ተይሚያህ በዲን ውስጥ ስለሚጨመሩ የፈጠራ በዓላት በሚያብራሩበት አውድ ስለ በዓላት ምንነት ሲያስረዱ የሚከተለውን ይላሉ፦
«“ዒድ” (በዓል) በተለመደ መልኩ ለሚደጋገም ሁሉን አቀፍ መሰባሰብ የሚሰጥ ስያሜ ሲሆን በየአመቱ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታ (በውስን ቀናት) የሚመላለስ ነው።
በዓል የተወሰኑ ነገሮችን አቅፎ ይይዛል፤ ከነሱ መካከል፦
እንደ ዒድ አል-ፊጥር እና እንደ ጁሙዓ የሚመላለስ ቀን፣ (በቀኑ) መሰባሰብ፣ ይህን ተከትለው የሚመጡ አምልኳዊ ወይም ልማዳዊ ተግባራት ይገኛሉ።
በዓል በውስን ቦታ የተገደበ ሊሆን ይችላል፤ ያልተገደበም ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ (በነጠላ) ዒድ ሊሰኙ ይችላሉ....
“ዒድ” የሚለው ቃል ለእለቱና በውስጡ ላለው ተግባር ጥምረት የሚሰጥ ስም ሊሆን ይችላል፤ ይህም አብዛኛው (አጠቃቀሙ) ነው።»
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (1/496 – 497)]

📌 በሌላ ቦታም እንዲህ ብለዋል፦
«ከተደነገጉት መሰባሰቦች ውጪ ሳምንታት፣ ወራት፣ ወይም አመታት በተደጋገሙ ቁጥር የሚደጋገም  መሰባብሰብን በቋሚነት መያዝ ለአምስቱ ሰላቶች፣ ለጁሙዓ፣ ለሁለቱ ዒዶችና ለሐጅ ከመሰባብሰብ ጋር ይመሳሰላል፤ ፈጠራና አዲስ ተግባር ማለት ይህ ነው!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]

📌 አለፍ ብለውም እንዲህ ይላሉ፦
«ከነዚህ (ከተደነገጉት) መሰባሰቦች ባሻገር የሚለመድ ተጨማሪ መሰባሰብ ከተጀመረ አላህ ከደነገገውና ካፀደቀው ፈለግ ጋር የሚመሳሰል ይሆናል …. - ለብቻው የሆነ ግለሰብ ወይም ውስን ስብስቦች አንዳንዴ ከሚሰሩት በተለየ መልኩ!))
[“ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/144)]

ይህ ማብራሪያ ሰዎች በየውስን ጊዜ በታወቀ ቀጠሮ የሚፈፅሙት ህዝባዊ ስብስብ እንደ በዓል ባይታቀድ እንኳ በዓላዊ ይዘትን እንደሚላበስ ያሳያል።

አንድ ነገር በጥቅሉ የሚፈቀድ፣ ብሎም የሚደነገግ ከመሆኑ ጋር በአፈፃፀሙ ረገድ የሚኖሩ ተጓዳኝ ነገሮች ብይኑ እንዲቀየር ሊያደርጉ ይችላሉ።
📌 ታዋቂው ዓሊም #ኢብኑ_ደቂቅ_አል_ዒድ አንዳንድ ሸሪዓዊ አፈፃፀሞችን ለመተግበር በደካማ የሐዲሥ ዘገባ ላይ ስለመመርኮዝ የሚነሳውን ውዝግብ አስመልክቶ እንዲህ ይላሉ፦
«የ“መውዱዕ” (የተቀነባበረ የውሸት ሐዲሥ) ክልል ውስጥ ያልገባ ደዒፍ (ደካማ) ከሆነ በዲን ላይ አዲስ ይፋዊ ምልክት “ሺዓር” የሚፈጥር ከሆነ ይከለከላል፤ ካልሆነ ደግሞ ምልከታ የሚቸረው ይሆናል...» [“ኢሕካሙ’ል-አሕካም” (1/501)]

👉 አንድን ተግባር እንደ “ሺዓር” ከሚያስቆጥሩት የአፈፃፀም ሂደቶች መካከል ሰዎች ተጠራርተው የሚሰባሰቡበት ኩነት መሆኑ ነውበተለይ እንደ ዒድ ሰላት በጎዳና/በአደባባይ ላይ የሚተገበር ከሆነ!
ይህን የሚያብራራ አንድ ምሳሌ እንጥቀስ፦

ሰዎች በተሰባሰቡበት አጋጣሚ አንዳንዴ ዱዓ ማድረግ የሚቻል ከመሆኑ ጋር ይህን በህብረት ለመፈፀም መጠራራትን ብዙ የኢስላም ሊቃውንት አይደግፉም።
📌 #አል_ኢማም_አሕመድ እንዲህ ተብለው ተጠየቁ፦ «ሰዎች ተሰባስበው አላህን መለመናቸውና እጃቸውንም ማንሳታቸው ይጠላል?»
እርሳቸውም፦
«مَا أَكْرَهُهُ لِلْإِخْوَانِ إذَا لَمْ يَجْتَمِعُوا عَلَى عَمْدٍ إلَّا أَنْ يَكْثُرُوا»
= «ሆን ብለው ካልተሰባሰቡ ለ(ዲን) ወንድማማቾች አልጠላውም – ካልበዙ በስተቀር

📌 #አል_ኢማም_ኢስሓቅ ኢብኑ ራሀወይህ ሲጠየቁም ተመሳሳይ መልስ ሰጥተዋል።

«ካልበዙ በስተቀር» ሲሉ ልማድ በማድረግ እስካልተበራከቱ ድረስ ማለታቸው እንደሆነ ጠያቂው (ኢስሓቅ ኢብኑ መንሱር) ተናግረዋል!
[“መሳኢሉ’ል-ኢማሚ አሕመድ ወኢስሓቅ” (9/4879)፣ “ኢቅቲዷኡ’ሲራጢ’ል’ሙስተቂም” (2/140)]፣
አል-ኣዳብ አሽ-ሸርዒይ-ያህ” ሊ’ብኒ ሙፍሊሕ (2/103)]

👉 ስለሆነም ነገሩ ከዚህ በላይ ሳያድግ መግታቱ አስፈላጊ ነው።
ይህ ከዚህ በፊት የተስተዋሉ የአፈፃፀም ግድፈቶችን ከግምት ሳናስገባ የምንደርስበት መደምደሚያ ሲሆን፤ ያለ በቂ ምክንያት መንገድ መዘጋጋት፣ አግባብ ያልሆነ የወንድና የሴት መቀላቀል፣ የሴቶች ምስል በሚዲያ የሚሰራጭበት ቀረፃ፣ ሴቶች በምሽት መንገላታታቸው፣ በሙዚቃ መሳሪያ የታጀበ "ነሺዳ"፣ የምግብ ብክነት እና መሰል ጥፋቶች የሚታከሉበት ከሆነ ደግሞ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ይሆናል።

አዎን! ፕሮግራሙ ከዚህ በፊት ሞራላዊ ጥቅምን አስገኝቶ ሊሆን ይችላል፤  ነገር ግን በውስጡ ከላይ የጠቆምነውን አመዛኝ ጉዳት ማካተቱ ለመታቀብ በቂ እንደሆነ አስባለሁ።

አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው።

ረመዳን 15/1445
____
@ustazilyas

2 months, 3 weeks ago

📣ወቅታዊ ሙሃደራ ለሴቶች

"لعلكم تتقون "
ረመዳንን በእውቀት እንጹም!

በእለቱ የሚዳሰሱ ነጥቦች

🔆 የረመዳን ህግጋቶች

🔆የረመዳንና የጾም ቱሩፋት

እና ሌሎችም ቁም ነገሮች

🗓ቀን እሁድ የካቲት 24  ፣2016

🕘ጠዋት ከ3:00-6:30

🕌 አድራሻ

☞ከጦር ሀይሎች ከፍ ብሎ 18 ማዞሪያ አካባቢ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስኡድ

⚠️ሴቶች የረመዳንን ደረጃ አውቀው ከገፀ በረከቱ ይታደሉ ዘንድ መልአክቱን ያስተላልፉ።

https://t.me/darulhadis18

2 months, 3 weeks ago

ለሴቶች በቂ ቦታ ተዘጋጅቷል

2 months, 3 weeks ago

📃የረመዳንን መድረስ አስመልክቶ ታላቅ ምክር

ሸይኽ ሳሊሕ ኢብኑ ፈውዛን አል ፈውዛን አላህ ይጠብቃቸው ተጠየቁ:-

“የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ?”

ሸይኽ ሳሊሕ ፈውዛን:-

"አንድ ሙስሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዲያደርሰው እና አድርሶትም ፆሙ ላይ፣ ስግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘው አላህን መለመን አለበት። ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙስሊም ህይወት ዕድል ነው።

ረሱል ( ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ:-

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የፆመ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል።"

በሌላ ሃዲስ ደግሞ እንዲህ ብለዋል:

"ረመዳንን አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈው ወንጀሉ ይማርለታል"

ስለዚህ ይህ ወር ላይመለስ የሚችል ዕድል ነው። ሙስሊም የሆነ ሰው ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ ተስፋም ያደርጋል፣ በደስታ እና ነው የሚቀበለው፣ እድሉን በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነው ሚያሳልፈው።

ሌቱን በመቆም፣ ቀኑን በመፆም፣ ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማስታወስ ነው የሚያሳልፈው። ትልቅ ዕድል ነው።

ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ረመዳን ሲደርስ አዘናጊ ፕሮግራሞችን፣ ፊልሞችን፣ ዝባዝንኬዎችን፣ ውድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ። እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸው። ሸይጣን ነው ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸው። አንድ ሙስሊም የሆነ ሰው ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸው መጠንቀቅ አለበት።

ረመዳን የፍንጥዝያ፣የጨዋታ፣ የፊልም፣ የውድድር ወር አይደለም።"

አላህ የረመዳን ወር በሰላም አድርሰን፣ደርሶም ከሚጠቀሙበት አድርገን ያ ረ ብ ያ ረ ብ!

#ዝክረ_ረመዳን
_
📚ቅህን ለመገንዘብ📚

5 months ago

📢ልዩ ግብዣ ለዕውቀት ፈላጊ ሴቶች

በአላህ ፈቃድ ነገ እሁድ ታህሳስ 14/2016

"عشرون عائقا في طلب العلم "

▪️እውቀት ፍለጋ ላይ የሚያጋጥሙ 20 እንቅፋቶችን የሚያብራራ ትምህርት

🫧ትምህርቱ በአረብኛ በሸይኽ ኢብራሂም አልጋሚዲይ ይሰጣል

🫧ትርጉም በአማርኛ በኡስታዝ ሙሀመድ ሀሰን ማሜ

ሰአት :ጠዋት 5:00-6:15

ቦታ :18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

⚠️ለእህቶች መልእክቱን በማድረስ ጠቅመን እንጠቀም!

https://t.me/darulhadis18

5 months ago

📢إعلان

محاضرة لفضيلة الدكتور الشيخ إبراهيم بن رافع الغامدي - للنساء،

بعنوان
▫️"عشرون عائقا في طلب العلم "
▫️في مركز ابن مسعود الإسلامي
▫️الوقت: ٥ صباحا بتوقيت إثيوبيا

https://t.me/darulhadis18

5 months ago
6 months, 1 week ago

📢የማይቀርበት ልዩ ፕሮግራም ለሴቶች

➪በቤተሰብዎ፣ በግዜዎ፣በገንዘብዎ፣ በልጅዎ፣ በስራዎ በአጠቃላይ በህይወትዎ በረካን (ረድዔትን) አጥተዋል?

ዘመኑ "በረካ የመነመነበት ዘመን ነው!" የሚለው ስሞታ ዘውትር በጆሮዎ ያቃጭላል?

➪እነሆ! ለዚህ የዘመኑ ጠንቅ ለሆነው የበረካ መነፈግ መፍትሄ የሚሆን አስተማሪ ፕሮግራም ይዘን ቀርበናል።

በእለቱ
➤የበረካ ምንነት፣ በረካ ከየት ይገኛል ከማንስ ይፈለጋል? በረካን ያለ ቦታው መፈለግ ወደ ሺርክ የሚያዳርስ አደገኛ ወንጀል ነውን? የሚሉ ከበረካ ጋር የተቆራኙ ትክክለኛ ቁርኣናዊና ነብያዊ አስተምሮዎች ይዳሰሳሉ።

➤የበረካ አስፈላጊነት በህይወትዎ ምን ያህል ድርሻ እንዳለውም ይረዳሉ።

▪️ታዲያ ከፕሮግራሙ ይቀራሉ?  በፍፁም!

➤እሁድ ህዳር 9፣2016

➤ከጠዋቱ 3:00-:6:00

➤18 በሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

▪️የፕሮግራሙ ታዳሚ በመሆን፣ እህቶችንም በመጋበዝ የእውቀትና የምንዳ ተካፋይ ይሁኑ!

https://t.me/darulhadis18

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 6 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 weeks, 2 days ago

Last updated 3 weeks, 2 days ago