Dive into the Ultimate Free Library: Your One-Stop Hub for Entertainment!

Esubalew Abera N.

Description
contact ፡ @esubalewabera
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago

6 days, 8 hours ago
***⭕️*** የመጻሕፍት ወግ | አፍሮጋዳ

⭕️ የመጻሕፍት ወግ | አፍሮጋዳ

“አፍሮጋዳ” የሌሊሳ ግርማ የወግ ስብስብ ድርሳን ነው። በይዘቱም ባሕላዊ፣ ኪነ ጥበባዊ፣ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ጸሐፊው ከዚህ ሥራው በፊት “የነፋስ ሕልም” የተሰኘ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ አሳትሟል። በኋላም “መሬት - አየር - ሰማይ”፣ “የሰከረ እውነታ”፣ “እስቲ ሙዚቃ”፣ “ነጸብራቅ” እና “ይመስላል ዘላለም” የሚሉ የወግና የአጫጭር ልብ ወለድ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።

📌 “የመጻሕፍት ወግ” ቆይታውን በሌሊሳ ግርማ “አፍሮጋዳ” ድርሳን ላይ አድርጓል።

የቪዲዮው አድራሻ👇

⭕️ https://youtu.be/MwBTJPMY0dc?si=pFSDz409J3U1ZjQN

1 week, 1 day ago
Esubalew Abera N.
1 week, 1 day ago

*°°°የደሳሳ ጎጆዬን የተቆለፈ በር ከፍቼ ስገባ ቤቴ ውስጥ አንድ እንግዳ ሰው እየጠበቀኝ ነበር። ያልጠበቅኩት ክስተት ስለነበር ልቤ ተናወጸብኝ። ሰውዬው ዓይን የሚያጥበረብር ፀኣዳ ሸማ ለብሷል።

“ጌታው ማን ነህ?” አልኩት።

ቃል ሊያወጣ አልወደደም። እራሱ ላይ የሾህ አክሊል አለ። የተቸነከሩ የእጆቹንና የእግሮቹን ቀዳዳ፣ እንዲሁም የጎኑን ቁስል በዝምታ አሳየኝ።

በተዘጋው ደጄ የገባው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደኾነ ተረዳሁ። ወዲያው አቅም አልባ ኾንኩ። ጉልበቴ ከድቶኝ እግሩ ሥር ተደፋኹ። ከዓይኔ እንደ ዥረት ዕንባዬ ፈሰሰ። እያንዳንዱ ሕዋሳቴ ሲሰንፉ ተሰማኝ። እዚህች ቅጽበት ላይ ሁሉ ነገር ቢያበቃ ተመኘሁ። ከመቃብር መከተት፣ ትኩስ አፈር መልበስ ናፈቀኝ። ይህን ያህል እንደ ደከመኝ፣ ይህን ያህል እንደ ታከተኝ፣ ይህን ያህል ማረፍ እንደ ፈለግኩኝ አላወቅኩም ነበር።

“ልጄ ሆይ ምን ትፈልጋለህ? ምን ልቸርህ?” ሲል ጠየቀኝ። ቃሉ ውስጥ የለመኑትን እንደማይነሣ የሚያስረግጥ ኃይል ነበር።

“ጌታ ሆይ እባክህ ሞትን ስጠኝ!” ብዬ ከልቤ ተማጸንኩት።

እርሱም ለአፍታ በዝምታ ተውጦ ቆየ። ይህች ዝምታው የዘለዓለም ያህል ረዥም ነበረች። ቃሉን ተደፍቼ በትዕግሥት ጠበቅኩ። በመጨረሻም እንደ ተሸነፈ ኹሉ “በእኔ ዘንድ ሕይወት እንጂ ሞት የለም” ብሎ መለሰለኝ።

photographer : Betty_tamrat_*

1 week, 4 days ago
Esubalew Abera N.
1 week, 4 days ago
***☝️***

☝️

1 week, 4 days ago

*ስለ “ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?” | “ከአመጿ ጀርባ” ደራሲ ኤደን ሀብታሙ

— መግቢያ —

ይሄ ዓመት የበርካታ ምርጥ መጻሕፍት ትሩፋት ይመስለኛል። ባለፉት ጥቂት ወራት ከታተሙት ውስጥ በተለያየ ቀናት (በአጉል መንገብገብ ይመስለኛል) ጀምሬ የወደድኳቸው፣ ያልጨረስኳቸውም አሉበት —በምስሉ ላይ ታገኙታላችሁ። የእሱባለው አበራ ንጉሤ ሁለተኛ ሥራው የሆነው  “ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?” በጣም ወድጄ ከጨረስኳቸው ውስጥ አንዱ ነው። እንደ አንድ ተራ አንባቢ የተሰማኝን ባካፍል ወደድኩ።

— ማሕሌታዊ —

ደራሲው፣ “ማሕሌታዊ” ብሎ ከቀየሰው አዲስ የአጻጻፍ ስልት ሥራውን እና ስልቱን ያስተዋወቀበት ምርጥ መጽሐፍ ነው። በበኩሌ ስልቱ አዲስ ይሁን ከዚህ በፊት የተሞከረ ሌላ ጉዳይ ቢሆንም.... እንደዜማ እየተንቆረቆረ የሚወርድ፣ ለመሰልቸት ቦታ የማይሰጥ ምርጥ “ልብ–ገብ” አካሄድ (ስልት) ነው።  

የወደድኳቸው ነጥቦች፦

— ቋንቋው —

ቋንቋው የሚቆረጠም የሚመስል፣ ክሽን ያለ፣ ሰከን ብሎም ሆነ ተግለብልቦ ለሚያነብ አንባቢ፣ ለዛ እና ውበቱን እንደጠበቀ የሚንቆረቆር ሥራ ነው። የቋንቋው ሀብት እና ከሌሎች ሥነ ቃሎች ጋር ያሰናሰለበት መንገድ ለሥራው የበሰለ እና ብዙ ሀብት ያቀፈ እንዲሆን አስችሎታል።

— ዳራ —

ትውፊታዊ፣ ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ዳራዎችን ከአሁን ሁነቶች እና ልቦለዳዊ ፈጠራዎች ጋር አቆላልፎ እና አሳምሮ ማቅረቡ ሥራውን ከልቦለድ አወቃቀር ከፍ ባለ ፍልስፍና “እንዲኳል” አድርጎለታል።

— ቅርጹ እና አወቃቀሩ —

አዲስ ዓይነት፣ ውስን በሆኑ ገጸ ባህርያት እና መቼት ላይ አጠንጥኖ ነገር ግን በርካታ ሀሳባዊ፣ ቁሳዊ፣ ሰዋዊ እና መለኮታዊ ጉዳዮችን እራሱ በቀየሰው መንገድ እያሰገረ ይወስደናል። ልክ መንገዱን እንደምናውቅ ሁሉ አምነን እንከተለዋለን። (ለነገሩ ያለፍነውን፣ አሁን ያለንበት ወይም ከፊታችን ያለውን ኑሯችንን ስለሚያሳየን ዝምድናው ቅርባችን ነው።)

— ጭብጥ —

የጭብጡ አስኳል እና የደራሲው ታማኝነት እና ድፍረት፣ የታሪኩ ጭብጥ ጠጣር እና የየቀን ነባራዊ ህይወታችንን በጥልቀት የሚመረምር ቢሆንም ያረፈበትን የጨለምተኛ ጥላ፣ ፍጹም ሳይፈራ እንዲያውም በጥልቀትና በዝርዝር ያሳየናል። ጦርነት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ምሬት፣ መታከት፣ ጭንቀት፣ መነጠል፣ ብቸኛነት፣ ፍርሀት፣ ሞት፣ ልሽቀት፣ ነውጥ... ያለምንም ማንገራገር እና መቀባባት ለዛ ባለው ቋንቋ አሳምሮ ማቅረቡ፣ ደራሲው ሊያስተላልፍ ለፈለገው ጭብጥና መንገድ ምን ያህል ታማኝ እና ደፋር እንደሆነ ያሳየናል።

— ዲዛይኑ እና አርትዖት —

እያንዳንዱ ውስጡ ያሉ የምዕራፍ ክፍሎች እና አወቃቀራቸው፣ ሙዚቃዊ ምልክቶች፣ የታሪክ አንጓዎች እና አርትዖቱ ልቅም ተደርጎ እንደተሠራ ያስታውቃል።

— ቢሆን ብዬ የተመኘሁት / ምኞቴ —

ትንሽ ተስፋ፣ ትንሽ ብርሀን፣ ትንሽ.... የአዲስ ህይወት ህልም... ቢኖር አንባቢ በእውነታውም፣ በፈጠራውም ዓለም ደጋግሞ ከመጭለም አውጥቶ ... ትንሽ ተስፋ ይሰጥ ነበር ብዬ ተመኝቻለሁ።

— ጉዳዬን ስጠቀልል — 

በበኩሌ “ፀሓይ ከጭለማዬ ምን አለሽ?” ን በጣም ወድጄዋለሁ። ካላነበባችሁት አያምልጣችሁ። ምስጋናዬ ለእሱባለው አበራ ንጉሤ🙏🙏🙏!*

2 weeks, 5 days ago

*ለመኖርህ በህይወት መገኘት ብቻ ዋስትና አይሆንም። በሌሎች ኃይልን የተጎናጸፉ ባለጡንቻዎች ለመኖርህ ማረጋገጫ ካልሰጡህ በስተቀር። ድንገት አንድ ጠዋት የጦር መሣሪያ ጥይት በቤትህ ጣሪያ አናት ላይ ሲርከፈከፍ ትነቃለህ። ገና ህይወትን በመጀመሪያህ ሰዓት ይመጣና “ለዓላማዬ ተማገድልኝ” የሚል ጉልበተኛ ደጅህን ይቆረቁራል፣ እጣፈንታህን ይወስንልሃል።

የዘመኔን ወጣት ምስቅልቅል ሥነ ልቡናው ፣ ፍርሃቱ፣ ተስፋ ቢስነቱ፣ የዛለ መንፈሱን ይወክላል። ህይወት ይሏት ፍዳ ተጭናበት አሳሩን ይበላል። ተራኪው በዚህኛው ክፍል የገፈቱ ቀማሽ ነው። ታድያ ይህ የማይሽር ጠባሳ ከትውልድ ትውልድ እየተሸጋገረ ገና ከእናታቸው ማህፀን ብቅ እንኳን ላላሉት ለመጻዒ ትውልዶች እጣፈንታቸው ዛሬ እየተሠራላቸው እንዳልሆነ ማን ደፍሮ መናገር ይችላል?

— የ “ያ ትውልድ” —

ከተማዋ ትታመሳለች። ብዙ ነገሮች መናድ ይጀምራሉ። ሀገሬው ሰማዩን ሲያርስ ንጉሡን ሲከስስ ይውላል። ወጣቱ ያነገባትን ተስፋ ይዞ በስሜት እየተመራ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የለኮሳት እሳት መልሳ ራሱን ትበላዋለች።
“አብዮት ልጆቿን በላች” የተባለለት የ60ዎቹ ትውልድ ገፅታ ልብ ይሏል።

— ጥላ (shadow) ሲገፈፍ —

አንድ ግለሰብ ለመካድ ወይም ለመጨቆን የሚሞክረውን ንቃተ ህሊና የሌለውን፣ የተጨቆነ እና ብዙውን ጊዜ የማይፈለጉትን የእራስ ገጽታዎችን ይወክላል። የግል ጥላው ልንገነዘበው ወይም መጋፈጥ የማንፈልገውን የራሳችንን ማንነቶች ያቀፈ ነው።

ለምሳሌ፦

ተቀባይነት የሌላቸው ግፊቶች፣ ምኞቶች ወይም በማኅበራዊ ደረጃ የማይፈለጉ ባሕርያት ወዘተረፈ..

ዩንግ እንደሚለን እነዚህ ማንነቶች ባልተቀበልናቸውና በካድናቸው ቁጥር በእኛ ላይ ኃይል እያገኙ እና ከቁጥጥራችን እየወጡ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን እስከመፈጸም ሊያደርሰን ይችላል። ስለዚህ ጥላን ማቀናጀት የጁንግ የግለሰባዊነት ፅንሰ-ሀሳብ አስፈላጊ አካል ነው - የግል እድገት እና ራስን የማወቅ ሂደት። ጥላውን በመቀበል እና በማዋሓድ ግለሰቦች የበለጠ ሙሉ፣ ትክክለኛ እና በሥነ-ልቡና የተዋሓዱ እንዲሆኑ ያስችላል —ይለናል።

ማኅበረሰብ የተዋቀረበት ጠንካራ መሠረት መፈረካከስ ሲጀምር፦ ግለሰብ በደህና ጊዜ ሸሽጎ ያኖራት ነውሩ የሚፈራው እና የሚገዛለት ነገር ሲያጣ ከጓዷ ወጥቶ አደባባይ ላይ ርቃኑን ይቆማል። እንግዳ ማንነቶች ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ። ሥርአት አልበኝነት፣ ስግብግብነት፣ ሌብነት፣ ጭካኔን የመሳሰሉ የሰው ልጅ አውሬያዊ ባሕሪዎች ጥርሳቸው አግጥጠው መታየት ይጀምራሉ። ይህም ማኅበረሰባዊ መልክ ሲይዝ እኛን ይመስላል። መጽሐፏ ቆም ብለን እራሳችንን እንድናይ ትጋብዘናለች።

— የሰፈሩ የተከበረ አድባር —

ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ትልቅ ቦታ የሚሰጠው እና ማንነቱን የመሠረተበት አንድ አይነኬ፣ አይመረመሬ አድባር አለው። በወለፈንዴነት የምንመላለስባትን ህይወት ትርጉም የምትለብሰው በዚህ አድባር በኩል ነው። ይኽን አድባር የወከሉት ካህኑ የተራኪው የማደጎ አባት ናቸው። የቅድስና ምሳሌ እርሳቸው ናቸው።

እርሳቸው የሰፈሩ አድባር፤ የማይናዱ የሚመስሉ የማኅበረሰብ ዕሴት፤ እልፎች የተመረኮዙት ተሰባሪ የማይመስል ምርኩዝ ናቸው። በጊዜ ጉልበተኝነት ከዕለታት በአንዱ ቀን የዚህ አድባር መገለጫ እንደቅርፊት ከላዩ ላይ እየተገፈፈ ድራሹ ይጠፋል። የተጠለሉበት ቤት ምሰሶው የጊዜ ፈርጣማ ክንድ ሲያርፍበት ይዘምማል። ከዕለታት በሌላኛው ቀን ደግሞ የጊዜ አውሎ ነፋስ ጣሪያውን ገንጥሎ መጠለያ አልባ ቤተኛ ያደርገናል። በመጨረሻም ማገሩ ይወድቃል። ያ ባለግርማ በምልአት የቆመ የሚመስለው ዋርካ ዳግመኛ እንዳንጠለልበት ሆኖ ይፈርሳል። ድንገት በዙሪያችን ባዶነት ያረባል።

— የመጨረሻው መጀመሪያ ነጥብ —

ይሄ መጽሐፍ ከፈጠራ ልቦለድነት ከፍ ያለ ኮርኳሪ፣ መተከዣ የሚሆኑ ጥልቅ ሀሳቦችን ይዳስሳል። ሥነ ጽሑፋዊ ውበቱ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ አይደለም። ሁሉም ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ነው። ይህን ውብ ድርሳን ለሰጠንን ለእሱባለው አበራ ንጉሤ እጅ ነስተናል።🙏*

2 weeks, 5 days ago

*ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?
— ዳሰሳ | Yodit Amanuel —

“ቀለም በቀንድ (በብልቃጥ) ሳለ ጨለማ ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን ብርሃን ነው። ቀለም በቀንድ ሳለ ድዳ ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን መላሰኛ ነው። ቀለም በቀንድ ሳለ ጭምት ነው፤ በተጻፈ ጊዜ ግን እንደሰከረነው። ሁሉንም ይለፈልፋል።”

—ከዘነብ ኢትዮጵያዊ፣ መጽሐፈ ጨዋታ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ—

ከመጽሐፏ ማለፊያ እግረ መንገዳችንን ጨልፈን
እነሆ በረከት...

ደራሲው ከዚህ በፊት ያልተሞከረ አዲስ “ማሕሌታይ” የተባለ የድርሰት አጻጻፍ ስልት እንደጻፈው በመጽሐፉ ማሳረጊያ ላይ ይነግረናል። ይህ መጽሐፍ በኢትዮጲያዊው የዜማ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሦስት የዜማ ስልቶች ባሕርይ በግዕዝ፣ ወመቋሚያ፣ ዕዝል ወጸናጽል፣ አራራይ ወከበሮ በተወከሉ ሦስት ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን በዋናነት ጦርነት፣ ቀቢፀ ተስፋ፣ ፀፀት፣ ህላዌ፣ ነፃ ፍቃድ በጥልቀት ይዳስሳል።

በመጀመሪያው ማለትም በ “ግዕዝ ወመቋሚያ” በተወከለው ክፍል ደራሲው የግዕዝን ዜማዊ ባሕርይ በመመሰል በዚህኛው ክፍል ጠንካራና ጠጣር ፍልስፍናዎችን ትዝብቶችን በሦስተኛ ተራኪ መደብ፣ ሁሉን አወቅ (omniscient) አንጻር ይተርክልናል።

በ“ሰማይ አይታረስ፣ ንጉሥ አይከሰስ” ሁሉም ነገር ቀዝቃዛ ይመስላል። በስሜት ተካልበው ከደጃቸው ያኖሩት ባዕድ፣ ከመጡበት መንገድ የሚነፍሰው ንፋስ ከቀልብ ያልተረገጠ ዳናቸውን እያጠፋ መነሻ ቢስ አድርጓቸዋል። ከትላንት ሲያሻግሯቸው የነበሩ ድልድዮችን አፈራርሰው ዳግም በትውስታ እንዳይመለሱባቸው ሆነዋል።

ትዝታቸው ደብዛው ጠፍቶ ድንገት ከየትም እንደመጡ፣ ግር በተሰኙ ሕዝቦች የተመላች ከተማ፣ ማንም በማንአለብኝነት ህመምና ጉስቁልናውን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ባላየ ባልሰማ የሚተላለፍባት በውል ያልተቃኘን የዘመን መልክ በዚህ ባልታወቀው ሦስተኛ መደብ ተራኪ ከየጓዳው መጋረጃውን እየገለጠ ትዝብቱን ያስቃኘናል።

ዐበይት ከሆኑት የፍልስፍና ዘርፎች ዲበአካላዊ (metaphysical) የሆኑ ጥያቄዎችን እያነሣ ሲብሰለሰል እናገኘዋለን። ለምሳሌ፦ በገፅ 31 ላይ እንዲህ ይላል፦

“ይህ ዓለም ፈጣሪና መጋቢ አለውን? ወይስ የሰው ልጅ የመለኮት ሥራ ሳይሆን ከአጽናፈ ዓለሙ ጋር ወደ መኾን የመጣ የዐቢይ ፍንዳታ ክስተት ውጤት ነው? አምላክ የሰውን ልጅ ፈጠረ ወይስ የሰው ልጅ አምላክን?”

...በማለት የሰው ልጅ የህላዌን ወለፈንድነት (Absurdity) ለማምለጥ የሸሸገባት ድንኳኑን ህልው መሆን፣ አለመሆኗን ተያያዥ ኈልቆ መሳፍርት ጥያቄዎችን እያነሣ የሰውን ልጅ መሠረተ ምሥጢር ለመፍታት ሲበረብር ይታያል።

— ነፃ ፍቃድ / free will —

በነፃ ፍቃድ (Free will) እና በተወስኗዊነት (determinism) ፅንሰ ሀሳብ በፍልስፍና፣ በሥነ መለኮት እና በሥነ ልቡና ውስብስብና አከራካሪ ሲሆን። በፍልስፍናው ዘርፍ ዲበአካላዊ (metaphysics) ላይ የተመሠረተው ነገረ ህላዌ (existentialism) ሥር የሚዳሰስ እሳቤ ነው።

በነጻ ፍቃድ ላይ በርካታ ቁልፍ አመለካከቶች አሉ።

— ነፃ ፈቃድ —

የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ በውጫዊ ሁኔታዎች ወይም አስቀድሞ የተወሰነ የክስተቶች ሰንሰለት ሳይወሰን በነፃነት ምርጫ እና ውሳኔ የማድረግ ፍቃድ አለው የሚለው አመለካከት።

— ተወስኖአዊነትት / Determinism —

የሰዎች ድርጊቶች እና ምርጫዎች ጨምሮ ሁሉም ክስተቶች የሚወሰኑት በቀደሙት ክስተቶች እና በተፈጥሮ ሕግጋት ነው የሚለው አመለካከት ነው። ምርጫችን ከቁጥጥራችን ውጪ የሆኑ ነገሮች ውጤት ተደርጎ ስለሚወሰድ የነጻ ምርጫን እና የሞራል ኃላፊነትን ይፈታተናል። ሌላኛው፦

— ተኳሃኝነት / compatibilism —

ነፃ ምርጫን እና ተወስኖአዊነትን ለማስታረቅ የሚሞክር የመካከለኛ ደረጃ እይታ። ታዲያ በ“ፀሓይ ከጨለማዬ ምን አለሽ?” መጽሐፍ ላይ ከተነሡት አያሌ ጭብጦች ውስጥ ነፃ ፍቃድ አንደኛው ነው። በመጽሐፉ በገፅ 41) እንዲህ ሲል ይጠይቃል፦

“በምልዕተ ዓለሙ ውስጥ የሰው ልጆችን ዕድል ፈንታ የሚወስን ኃይል አለ? የተጻፈው ይፈጸም ዘንድ ግድ አይደለምን? ወይስ ነገረ ፍርቱና እና የአርባ ቀን ዕድልም ያረጀ ያፈጀ የአቅመቢሶች ተረት ነው?”

...ይቀጥልናም፦

“በነፃ ፍቃድ መኖር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ የመሸከም ነገር በሰው ልጅ እጅ ላይ ብቻ እንዲወድቅ ይኾናል። ኃላፊነትን በመውሰድ ውስጥ ተጠያቂነት ይከተላል። ቀናው ሲፀድቅ፣ ስሁቱ ደግሞ በሥጋውም በነፍሱም ይኮነናል። ነገር ግን በደግም፣ በክፉም ከሞት በኋላ እስከዘላለም የሚፀና ፍርድ ለመቀበል የአንድ ሰው እድሜና ህይወት በቂ ነው?”

...ብሎ በገፅ 41 ነፃ ፍቃድ፣ “እጣፈንታና የዕለት እንጀራ” ብሎ በሰየማት ንዑስ ርእስ ሥር መብሰልሰሉን ይቀጥላል።

ሁለተኛው ክፍል በ“ዕዝል ወጸናጽል” ይወከላል። በዚህ ክፍል ተራኪው ከሦስተኛ መደብ ወደ አንደኛ መደብ ተራኪነት ሽግግር ያደርጋል።

— ሽግግር / transcend —

ይህ የተራኪውን የሰብዕና ሽግግር በአንድ ግለሰብ አንፅሮተ ዓለም ምልከታ ከመነሻ ተነሥቶ ወደ ምንምነት የሚሸጋገርበትን መሥመር ተከትሎ የተራኪውን በልጅነት ያለውን የህላዌ አረዳድ (ከነገሮች ሁሉ መለኪያነት ማዕከላዊነት) ተነሥቶ ቀስ በቀስ እየተገፈተረ ከጨዋታው ሜዳ እስከወጣበት የወጣትነት ጊዜው ያደረገውን የህይወት አረዳድ ሽግግር አስፍሮል።

በህይወት ዘመናቸው በቅድስና ተመላለሱ ስለሚላቸው የተራኪው ስለ ካህኑ የማደጎ አባቱ እንዲህ ሲል ይመሰክራል፦

“ጠባያቸውና ምግባራቸው ጠንካራ ነው። ከዓለም ፍቃድ ራሳቸውን አግልለዋል። የንጽህናን ዝናር ታጥቀዋል።” (ገፅ 55)

...ሆኖም ህይወት መልኳን እየቀየረች ጀንበር እያዘቀዘቀች ስትመጣ ቀስ በቀስ እምነቱ መፈረካከስ፣ ተስፋውም መሟጠጥ ቢጀምርም በዚህ ክፍል ጭላንጭል ብርሃን ማየት የተሳነው አይመስልም።

— ቀቢፀ ተስፋ —

በመጽሐፉ የሚዳሰስው ሌላኛው ጭብጥ ቀቢፀ ተስፋ ነው። በህይወት መድከም እና ስለወደፊት ምስል ከሳች አንዳችም ነገር ማጣት ተስፋ ቢስነት ነው። የሁላችንም የልብ ጓዳ ቢበረበር ቢያንስ ለአንድ ጊዜ በዚህ ዓይነት ስሜት ውስጥ አልፈናል።

— ኢምንትነት —

በውጪው ዓለም ያለውን ትርምስ ሽሽት ወደ ውስጥ የሚደረግ ጉዞ እና በውስጣዊ ዓለም ከተንሰራፋው ጥልቅ እና አስፈሪ ጨለማ ጋር መፋጠጥ፣ በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ተራኪው ከመታዘብ እና ከመብሰክሰክ ያለፈ እዚህ ግባ የሚባል እንኳን ተሳትፎ እንደሌለው ሲረዳ የማይቀረውን የህይወት ስንክሳር ይጋፈጣል።

ተራኪያችን በስተመጨረሻም የሰው ልጆች እድል ፈንታቸው በእጃቸው ላይ እንዳልሆነች ከእነርሱ ቁጥጥር ውጪ መሆኑንና ሌሎች በእነርሱ ላይ አቅም እንዳላቸው ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦

'“በድንገት ከእንስሳ በታች እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ሊያደርጉኝ የሚችሉ ሰዎች ደጃፌን በየትኛውም ቅፅበት ቢያንኳኩ ላስቆማቸው አልችልም። ኢምንት ነኝ።'” (ገፅ 109)

በመጨረሻም በ “አራራይ ወከበሮ” የተወከለው የመጽሐፉ ሦስተኛ ክፍል ህልው በመሆናችን የማይቀርልን የህይወት ድለቃ ህማም ሲቃኝ፦

— ጦርነት —

ዛሬ እያለፍንበት ያለውን የህይወት ምስቅልቀል በትክክልም የዚህኛውን ዘመን ትውልድ ወካይ ተደርጎ የተገለጸው አንደኛ መደብ ተራኪ የጦርነትን አሰቃቂነት ይነግረናል። በዚህ ውስጥ እልፍ የተረሣ እና ችላ የተባሉ የግለሰብ ህይወቶች ሰሚ የሌላቸውን የጣር ድምፆችን ያወጣሉ።*

3 weeks, 3 days ago

*በ “Midnight children” እና “The Satanic Verses” በተሰኙ፣ በቢኾን ዓለም (magical realism) ቀለም በተነከሩ፣ ዝነኛና አነጋጋሪ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎቹ ይታወቃል። በተለይም “The Satanic Verses” መታተም ታላቅ ቁጣን የቀሰቀሰ ነበር። ከዚህ መጽሐፉ ጋር ተያይዞ ያገኙት እንዲገድሉት በኢራኑ መንፈሣዊና የፖለቲካ መሪ አያቶላህ ሆሚኒ የሞት አዋጅ ተነግሮበታል። በዚህም ምክንያት ሕይወቱ ከሰዎች የመረረ ጥላቻ፣ አስፈሪ የግድያ ዛቻ፣ ማስፈራሪያና ጥቃት ያረበበበት ነው።

በቅርብ እ.ኤ.አ በ2020 በአንድ መድረክ ተጋብዞ ቃለ ምዕዳን በሚሰጥበት ወቅት በድንገት ሊገድለው በሞከረ አንድ ወጣት በጩቤ ተወግቶ አንድ ዓይኑን አጥቷል። በእጁ ላይም ጉዳት ደርሶበታል። ይህ ሰው — “Salman Rushdie” ነው። ከዚህ ጉዳት ሲያገግም እንዲሁ ባዶ እጁን አልወጣም። ይልቁንም ከሰሞኑን ባልተጠበቀ መልኩ በሞት ግድያ ሙከራው ማግስት የተሰማውን የግል ጽሞና የሚተርክ “Knife” የሚል ድርሳን ወደ አንባቢያኑ ይዞ ብቅ አለ።

ይህን መጽሐፍ “Knife” ወይም “ጩቤ” ሲል ለምን እንደሰየመው በመጽሐፉ መግቢያ ላይ እንዲህ ሲል ይገልጻል — በግሌ የሳበኝም ይኸው ነው።

“If I had unexpectedly been caught in an unwanted knife fight, Maybe this was a knife I could use to fight back.”

"ባልጠበቅኩትና ባልፈለግኩት የጩቤ ጸብ ውስጥ ራሴን ባገኘው ኖሮ፣ ምናልባትም ይህ [መጽሐፍ] መልሼ ለመዋጋት የምጠቀምበት ጩቤ ይኾን ነበር።”*

2 months, 3 weeks ago

ሰላም እንዴት ናችሁ? 😊

በድጋሜ በአዲስ የከቨር ሙዚቃና የቪዲዮ ክሊፕ ተመልሼያለሁ። በእኔ አረዳድ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከተሠሩ የሙዚቃ አልበሞች መካከል በጌቴ አንለይና በኤልያስ መልካ ጥምረት የተሠራው “መልክሽ አይበልጥሽም” አልበም ዘመን አይሽሬ የሚባል ተሻጋሪ የሙዚቃ አበርክቶ ነው ብዬ አምናለሁ። በሙዚቃ ግጥም፣ በዜማ፣ በሙዚቃ አጨዋወትና በቅንብር የሰመረ ሥራ ነው። ከዚህ ተወዳጅ አልበም ላይ ለእናንተ “ወይ ብሬ” የተሰኘውንና የብሉስ ቃና ያለውን ተወዳጅ ሙዚቃ ዳግም ለመጫወትና አዲስ የሙዚቃ ቪዲዮም ልሠራለት ሞክሬያለሁ። እንድታደምጡት፣ እንድትመለከቱት እጋብዛለሁ🌻

https://youtu.be/6jn7JrSCj18?si=XAH8du443bNtf717

YouTube

ወይ ብሬ | Wey Birr'e | ጌቴ አንለይ | Gete Anilye | | ቤቴል | Bethel Getu

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 4 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 5 days ago

Last updated 2 weeks, 5 days ago