ጦብያ

Description
የ ቅኔ ማእድ?? join us?
@utorrr
@utorr12
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 months, 3 weeks ago

ሌላ አጭር ልቦለድ ይጀመርልን የምትሉ

3 months, 3 weeks ago
Remember never trust someone***☝️***

Remember never trust someone☝️

Join for more ??

@utorrr
@utorrr

3 months, 3 weeks ago
Join us

Join us

?@utorrr? ? @utorrr?

3 months, 3 weeks ago
3 months, 3 weeks ago

ከገጣሚዉ ጀርባ
.
.
.
ከገጣሚዉ ጀርባ አለች አንዲት እንስት፤
በምናቡ መስፈርት ነቅዕ ያላገኘባት፤
ፍፁም እንድትሆን አድምቆ የፃፋት፤
በህልሙ ሸምግሎ በህልሙ ያገባት።

አለች አንዲት እንስት....

ቆነጃጅቶችን ከእግሯ ስር ጥሎ፤
ከሰማይ የሚሰቅላት በኮከብ መስሎ፤
ሳቋ የሚያጠፋለት ሀዘኑን መንግሎ፤
እቅፏ የሚያስረሳዉ የአለምን ደበሎ።

አለች አንዲት እንስት........

ዉበቷን ለመግለፅ ቃላት ያጣላት፤
በተባ ብዕሩ ሠርክ የሚፅፍላት፤
የመኖሩ ትርጉም አለሙ ያረጋት፤
በልቡ አንግሶ የኔ ነሽ የሚላት።

አለች አንዲት እንስት..........

በመዉደዷ ንግር ተስፋን እየሰጠች፤
በእለተ ሰንበት ቀጥሯት ያረፈደች፤
እመጣለሁ ብላ ሳትመጣ የቀረች፤
የክት አስለብሳዉ እሷ ያልተገኘች።
አለች አንዲት እንስት........
.......................................................
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@topazionnn
@utorrr

3 months, 3 weeks ago
3 months, 3 weeks ago

ልጅ ማንን ይመስላል ቢሉት.......
(አጭር ዘውግ ሙሉ በሙሉ ፈጠራ በአርያም አስራት)

እግራን ፊት ለፊቷ ካለው የሶፋ ጠረጴዛ ላይ ሰቅላ ሶፉ ላይ ፈልሰስ ብላ ተቀምጣ ስልክ ትነካካለች። ድንገት ወደ ሳሎን ስገባ ያየሁትን ማመን አልቻልኩም እልህና ቁጣ ንዴትና ግዜያዊ ጥላቻ እያንገበገበኝ
"እህህህህህህ ምን እያረግሽ ነው ሳምሪ አሁን የወለወልኩት ጠረጴዛ ላይ እ እግርሽን" ስል ድምጼ ሻክሮ ወደ ለቅሶ አዘነበለ።
ለንግግሬ ቦታ ባለመስጠት በፌዝና በንቀት እያየችኝ
"ምን ያነጫንጭሻል እንደውም እኔ ነበርኩ እዬዬ ማለት የነበረብኝ ካንቺ ጠረጴዛ ቸኔ እግር አስር እጥፍ ይጸዳል "አለችኝ። ብስጭት ጭት ብዬ እየተነጫነጭኩ ወደ ጓዳ ተመልሼ ገባው።
እህቴ ሳምራዊት ትባላለች በ 5 አመት ብቻ ብትበልጠኝም በጠም ሞልቃቃ ለራሷ ያላት ግምት የተጋነነ ለሰው ቦታም ክብርም የለላት ብትሆንም እኔ ግን በጣም ነው ምወዳት ምትሰራውን ስር ስሯ እየሄድኩ ጠይቃታለው እሷም ሳትሰለች ትነግረኛለች።

አንድ ቀን እንደለመደችው ተሽሞንሙና ተሽቆጥቁጣ በጨለማ መሀል የምታበራ እንቁ መስላ ለረጅም ግዜ እራሷን በመስታወት አንዴ ስትጣቀስ ደግሞ ፈገግ ስትል ከዛ ደግሞ ኋላዋን ገልመጥ ስታረግ አረማመዷን ስትፈትሽ ወደ 20 ደቂቃ ሚሆን ፈጅታ እንደ ሀር ወገቧ ላይ የተንጎማለለውን ጸጉራን በእጇቿ ነስነስ እያረገች ፊልም ላይ እንደሚራመዱት አይነት አረማመድ እየተራመደች ወጣች። ድርጊቷ ስላስገረመኝ ተከትያት ወጣው።ትንሽ እንደሄደች በአንድ ጀማ የተሰበሰቡ ዱርዬዎች በለከፋ ያጣድፋት ገቡ እሷም በልሰማ ሙድ ጀነን ቆፍጠን ቆንጠር እያለች አልፋቸው ሄደች።እስክትመለስ ሰአቱ አመት ነው የሆነብኝ።

ገና መታ አረፍ ከማለቷ። እሩጬ መጥቼ አጠገቧ ከሰፈርኩ ቡሀላ ሳምሪ የቅድሞቹ ልጆች ምን እያሉሽ ነበር? ስል ጠየኳት።እሷም ጀነን ኮራ ብላ ሞዘዝ ባለ አነጋገር
"አ  ም  ሮ ብ ሻል ነው ያሉኝ" አለችኝ ቃሉን እየጎተተች እኔም ባለማመን የታቸኛው ለንቦጬን ዘርግቼው" እረ ባክሽ ታዲያ አንቺ ለምንድ ነው የተናደድሽው እንደዛ ከሆነ? "ስል ጠየኳት በሰአቱ ሁኔታዋ የንዴት መስሎኝ ስለነበር"
እሷም ከጣሪያ በላይ እየሳቀች
"መች ተናደድኩ ኮራ ቆፍጠን እያልኩባቸው እንጂ ለለከፈሽ ሁሉ ግግ ማስጣት እራስን ማስናቅ ነው። "ስትለኝ ይባስ ግራ ገባኝ።
"አልገባኝም ለምንድ ነው እራስ ማስናቅ ሚሆነው?ስል ጠየኳት እሷም በታከት ድምፅ እሱን ስታድጊ ት"ደርሺ በታለሽ  አሁን ግን I am so tired so i need rest "ብላኝ ወደ መኝታዋ ገባች። ብዙ ግዜ እንዲ ምታረገው ስልክ ለብቻዋ ማውራት ስትፈልግ እንዳትረብሹኝ አይነት መልእክት ስለሆነ እኔም ተከትያት አለሄድም ብቻ ግራ በተጋብ ስሜት ውስጥ ሆኜ መኝታ ክፍሏ ድረስ በአይን ሸኘዋት። በሌላ ግዜ እንዲሁ ተሽሞንሙና ወታ ዝም ብለው ካሳለፏት በስጨት በስጨትጨት እያለች ጉዳዩዋን ፈጽማ ትመጣና በድጋመሚ እራሷን በመስታወት እያየች
"እንደ ማኩረፍ እየቃጣት ቆይ ግን ቤቲ ዛሬ አላማረብኝም ብላ ትጠይቀኛለች እኔም ቀልጠፍ ብዬ
"እረ ሳምሪ አምሮብሻል አንቺ እኮ ሁሌም ቆንጆ ነሽ ግን ምን ተፈጠረ?"ስል አሞግሼ በጥያቄ ንግግሬን አሳርጋለው። እሷም በንግግሬ ፊቷ በርቶ አይ" ዛሬ ዝም አሉኝ ብዬ ነው "ትለኛለች።
"እነማን"ስል ጠይቃታለው
"እነ ሰሚ ናቸዋ ቁጭ ብለው ዲንቃይ ማሞቃቸው ካልቀረ ምናል ለኛም ቢያራግፉ? "
"እህ ባለፎ ተናደሽ አልነበር?"ስል ያልገባኝን ጥያቄ ድጋሚ ለመጠየቅ እድል ስላገኘው ስል ብሎኝ ጠየኳት።
"አልተናደድኩም አልኩሽ እኮ ታዲያ እነሱ ካለከፉን እንዳማረብን በምን አንወቅ አሁን ምንም ብልሽ አይገባሽም ተይው በቃ "ብላኝ ትሄዳለች።
እኔም አሁን ልክ እንደሷ ለመሆን እየጣርኩ ነው ከቤት ከመውጣቴ በፊት 1-2 ሰአት ተሽሞንሙኜ ቆንጠር ቆንጠር እያልኩ እሄዳለው ልዩነታችን እኔ ስለከፍ ከት ብዬ ስቅና የሀከፋኝን ቁሜ አዉርቼ ቤስት ፍሬንድ አርጌአቸው አልፋለው።ዝም ያሉኝ ቀንም እኔ እራሴ ጠረቼ እ ዛሬ እንዴት ነኝ ብዬ ለክፌአቸው አስተያየት ተቀብዬ አልፉለው።(ከኮረጁ አይቀር እንዲ ነው??)
ሌላው ከእህቴ በሀሪ መሀል ይገርመኝ የነበረው ስልክ አወራሯ ነበር።ወንድ እና ሴት ስታወራ የድምጽ ቃናዋ አኳኋና ይለያያል።ሴት ስትሆን ድምጿን ከፍ አድርጋ
"ሄለው "
"እ/አቤት እንዴት ነሽ ጠፋሽ ኡኡቴ አልቀረብሽም ምናም...." እያለች ከጣሪያ በላይ ትስቃለች።
ወንድ ሲሆን
ሞልቀቅ ቀዝቀዝ ባለ አነጋገር
"ሄሎ ወዬ በሰላም ነው የጠፋኸው እኔማ ከአንተ ናፍቆት ውጪ ምን እሆናለው ትልና ቁጥብና ማራኪ ሳቅ ትስቃለች በዚ ሁኔታዋ ከሩቅ ሆኜ ደዋዩ ወንድ ይሁን ሴት እለያለው።
እኔም ከማን አንሼ ብዬ መጀመሪያ አከባቢ እንደሷ አወራ ነበር ነገር ግን ሳወራ 2 ችግሮች ይገጥሙኛል።እነሱም
1)በመሀል እረሳውና አነጋገሬ ተቀይሮ ኖርማል ከጓደኞቼ ጋ እንደማወራው ይሆናል
2)አውርቼ አውርቼ ስጨርስ ምን፣ ምን አልሽ፣ድምጽሽ ምን ሆኖ ነው፣እረ ኔቶርክ ይሁን ድምጽሽ ይቆራረጣል"ይሉኛል(የጀማሪ ሰልጣኝ ነገር ተሟዘዝኩ ብዬ ለካ ስደነዝዝ ነው ምውለዉ ምን ባሉኝ ቁጥርም ስናዘዝ?። ከሁን አሁን ግን ምርርርር ብሎኝ ትቼዋለው ሆሆሆሆ ጎመን በጤና እሷን መሰልኩ ብዬ እራሴን ለምን ልጣ)
እናም ኢሄን ያዩ የሰፈር ሰዎች
ልጅ ማንን ይመስላል ቢሉት አሳዳጊውን አሉ ድሮስ ማንን እያየሽ አድገሽ ማንን ትመስይ።እያሉ ሲያሽሟጥጥቡኝ ሁሉን እርግፍ አርጌ ትቼ እራሴን እየሆንኩ ነው።? ተመስገን እሷም ወደ ዩኒቨርስቲ ሂዳ አሁን አስኮራጅ ስለለ ሳልወድ በግዴ ወደ መስመሬ ገብቻለው።?

✍️አርያም አስራት

Join for more ??

@utorrr
@utorrr

3 months, 3 weeks ago

ፀጉረ ልውጡ
ክፍል አስራ ዘጠኝ


...የዋሻው ሰዎች ደማቸውን ለመበቀል እንደመጡ ተሰማኝ የዋይታና የደስታ
በሚመስል ጩኸት ወደ ጎሳው መንደር ተቃረቡ በግራ እና በቀኝ ቀጥ ባለ
ረድፍ እሳት የያዙ ሰዎች ይታያሉ መሀል ላይ ከወገብ በላይ እርቃናቸውን የሆኑ
እዘለሉ እየተንከባለሉ ወደ መንደሩ መቅረብ ጀመሩ ከጎሳው አባል አንዱ
ድምፁን ከፍ አርጎ በማላስተውለው ቋንቋ ተናገረ አንደኛው ከሱ ተቀብሎ
አስተላለፈ ሙሉ ጎሳው የተፈጠረውን ሰማ ሁሉም ከመኝታው ተነሳ
ሚመጣውንም ለመቀበል ተሰናዳ በድንገት የጎሳው መሪ ጣቱን ወደኔ ቀስሮ
የሆነ ነገር አለ ሶስት ሰዎች ጦራቸው ቀስረው እንድነሳ አዘዙኝ እኔም ተነሳሁ
ከጎሳው መንደር መውጫ ወደ ሚታየው ድንበር ጠቆሙኝ የዋሻው ሰዎች
እየተቃረቡ ነው ኮቴያቸው እንደ ብዙ ፈረስ ነው ሳቃቸው እንደ ስሪያ ጅብ ነው
ከነሱ ያተረፉኝ የጫካው ሰዎች አሳልፈው ሰጡኝ በድንገት የዋሻዎቹ ሰዎች
ኮቴም ሆነ ዋይታና እልልታ ፀጥ ረጭ አለ የጎሳው አባላት አፈገፈጉ እኔ በሁለቱ
ቤተሰቦች መሀል ነኝ ፀጥታው ደቂቃዎችን አስቆጠረ ከየት መጣ ሳልለው
የአንድ ሰው ጭንቅላት እግሬ ስር ወደቀ በድንጋጤ መሬት ወደኩ አሁንም
ጫካው ፀጥ እንዳለ ነው ፍርሀቴ ለመግለፅ በሚያዳግት ሁኔታ ጨምሮብኛል
ሰውነቴ ይቀጠቀጣል ጥርሴ ከጥርሴ ይጋጫል እጅና እግሬ ተሳስሯል
አንደበቴ ተለጉሟል በድንገት ብርታቴ ከዳኝ ትንፋሽ አጠረኝ ለፀሎትም አቅም
አጣሁ በመሬቱ ላይ በደረቴ እየተሳብኩ የተወረወረውን ጭንቅላት ተመለከትኩ
ጫካው ውስጥ ከዋሻው ሰዎች ያዳነኝ ነበር የማየው ነገር ራሴን አሳተኝ
ለማየት እየፈለኩ አይኔ መግለጥ አቃተኝ ልቤ እጅግ ደከመ ራሴን
ሳትኩኝ....ለምን ያህል ደቂቃ እንደሆነ ባላውቅም ራሴን ግን አላውቅም ነበር
ከሞት ያልተናነሰ ነበር እስትንፋሴ የአይኔ ቆብ እንደ አንዳች ከብዶ አልገለጥ
አለኝ እንደምንም ገለጥኩት ከፊት ለፊቴ የተኛ ሰው አለ ማንነቱን ግን
አለየሁትም ከአንገቱ በታች የሌላ ሰው አንገት አለ በጣም ደነገጥኩኝ የሞት
ሞቴን ተነስቼ ተቀመጥኩ ሁለቱም አንገቶች ቀሪ አካል አልነበራቸውም
እንደገና ሌላ ጭንቅላት አየው ዙሪያዬን በሙሉ የጎሳው አባላት ጭንቅላት
ከቦኛል ቀሪ አካላቸውና የዋሻው ቤተሰቦች አሁንም የሉም ደረቴ እንደተወጋ
ነገር ደም ይፈሰው ነበር ከቋንጃዬም አካባቢ ቁስለት ይሰማኛል በጭንቅላቶቹ
ላይ እየተረማመድኩ ራሴን ለማዳን እርምጃ ጀመርኩ ግን አልቻልኩም
አንገቴን ያላየሁት ስለት በጆሮ ግንዴ አካባቢ ቆረጠኝ ጮውኩኝ ህመሙ ሀያል
ነበር ጭንቅላቴን አዞረኝ የማየውን ማስተዋል አልቻልኩም አይኔን ጋረደኝ
ለሰከንዶች አይኔን ጨፍኜ እንደገና በደም ተጨማልቄ ዳዴ በማይባል እርምጃ
መጓዝ ጀመርኩ ከጢቂት እርምጃዎች በሗላ የግራ እግሬን ውስጠኛ ክፍል
አሁንም ያላየሁት ስለት ወጋኝ ተዘረርኩ የነበርኩበት ስፍራ ትንሽ ከፍታ
ስለነበረው ቁልቁል ተንከባለልኩ ከአንገቴ የእግሬ ህመም ከበደኝ ደሙ
በሀይል ይፈስ ነበር ያለማቋረጥ ያረኩት ጫማ ሰላም እስኪነሳኝ ድረስ እግሬ
አበጠ በዚ ጊዜ ነበር የዋሻው ሰዎች እልልታና ጩኸት የቀለጠው ከየት መጡ
ሳልል ዙሪያዬን ከበቡኝ ንግስቲቷ ነጩን ፈረስ ተሳፍራ በእጇ ሰው ሚመስል
አሸንጉሊት እና ደም የተነከረ ትልቅ መርፌ ይዛለች ከፈረሱ ወርዳ ወደኔ
አመራች በእጇ ትዕዛዝ ፀጥ እንዲሉ ነገረቻቸው ምንም ቃል ሳትናገር በግራ
አቅጣጫ ጀምራ ሰባቴ ዞረችኝ ልቤ እየከዳኝ ሄደ አይን አይኔን እያየች በመርፌ
አሸንጉሊቱን ስትወጋው አልቻልኩም ደጋግማ በምሬትና በእልህ ወጋች
ወጋጋችው ሙሉ ገላዬ በቁስል ተሞላ የምድሩ አፈር በደሜ ጨቀየ ሁለት
እጆቼን እንደ መስቀል ቅርፅ አርጌ ላልነሳ ተዘረርኩ በጀርባዬ ተንጋልዬ በሞት
ጣር ውስጥ ሆኜ ንግስቲቱ ምታረገውን ለማየት አይኔን ገለጥኩ መርፌውን
በአሸንጉሊቱ አንገት አቅጣጫ አድርጋ ልትወጋው ስትል አሸንጉሊቱ ነፍስ
እንዳለው ፍጡር እየተንቀሳቀሰ ይሸውዳት ጀመር ወዲያው ወደ መሬት
ወረወረችው የንግስቲቷን ተግባር በጥሞና ሲመለከቱ የነበሩት ቤተሰቦች
በድንጋጤ እየጮሁ ከላዬ ላይ ገለል አሉ ፈረሱ ወደ ዘንዶነት ወዲያው ተቀየረ
መንታ ምላሱን እያርመሰመሰ አይኖቹን አይኔ ላይ ተክሎ ጭራውን እያወራጫ
አፉን ከፍቶ በፍጥነት ወደኔ መጣ...ይቀጥላል

Join for more ??

@utorrr
@utorrr

3 months, 3 weeks ago

ፀጉረ ልውጡ *** ክፍል 18


....ነጩ ፈረስ ከበላዬ ቆሞ ቁልቁል ይመለከተኛል አይኑ ከአይኔ ተጋጥሞ
ሳለ....ከመቅፅበት ወደ ጥቁር አስፈሪ ዘንዶ ተቀየረ ከጭራው ተጠቅልሎ ቀጥ
ብሎ ቆሞ አፉን ከፍቶ ቁልቁል ወደኔ መምዘግዘግ ጀመረ...ፈርቼ መሞቴን
ተውኩትና ጫካ ውስጥ ከዛፍ ላይ ተሰብሮ በወደቀ እንጨት ከዘንዶው ጋር
ትግል ልጀምር ወሰንኩ...እንጨቱን ፍለጋ ጫካ ውስጥ ስርመሰመስ የዛፍ ስር
ጠልፎኝ ከቅጠል ርጋፊ መሀል ወደኩኝ....የቅጠሉ ርግፊ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ
መላ አካሌን ጋርዶታል....ዘንዶው በመጣሁበት አቅጣጫ ተከተለኝ ነገር ግን
ሊያገኘኝ አልቻለም በንዴት ያወጣው እጅግ ሰቅጣጭና ቀጭን ድምፅ
አሸበረኝ በጣም ፈራሁ እርቄ እንዳልሄድኩ የተረዳ ይመስለኛል እዛው
ይጥመለመላል ይርመሰመሳል እየደጋገመም ይጮሀል ምሽቱ ይብስ አስፈሪ
ሆነብኝ....አይኔን የጋረዱትን ቅጠሎች ዞር አድርጌ አጮልቄ ስመለከት ሰማዩ
ጎህ እየቀደደ ነው....በድንገት የሰዎች ድምፅ ጆሮዬ ገባ ንግስቷና የዋሻው
ሰዎች ነበሩ...ከሰዓታት በሗላ ፈረሱ ወደ ቀድሞው ይመለሳል በቀንም
ከዋሻው ቅጥር ግቢ ውጪ መውጣት እንደማይችል ታውቃላቹ ስለዚህ
ሰይፋቹን ይዛችሁ ጫካውን አብጠርጥራቹ አስሱት በገኛችሁበት ግደሉት
በያዛችሁት ብልቃጥ ደሙን በእጃችሁ ደሞ ልቡን አምጡልኝ የቀረውን
ብሉት
አለች ንግስቲቷ መሞት እንዳለብኝ ወስና.... ነገር ግን የኔ እስትንፋስ
ሰማይና ምድርን ባበጀው የዘልአለም አምላክ እጅ ላይ ነው
....ዘንዶው ወደ
ፈረስነቱ ተመለሰ መሰል የሚያሽካካ የፈረስ ድምፅ ሰማሁ ....ወደኔ አቅጣጫ
ኮቴዎች ተበራከቱ ቅጠሎቹን መግለጥ ጀመሩ ልቤ ምቴ እጅግ አየለ
ትንፋሼም ቁርጥ ቁርጥ ማለት ጀመረ ወበቀኝ ላብ ጠመቀኝ....እሱ ጋር
ከምትምሰ ዛፍ ላይ ፈልገው
አለ አንዱ የዋሻው ሰው ቅጠሉን ሲገልጥ
የነበረውም ትዕዛዙን ተቀብሎ ከኔ ገለል አለ....ትንሽ ተነፈስኩ ሰዎቹ እኔን
ፍለጋ ወደ ጫካው ውስጥ ዘልቀው ገቡ በዚ ሰዓት ከነበርኩበት ስፍራ
ለመውጣት ተነሳው ነገር ግን እግሬ በወጥመድ ተይዞ ነበር ከያዘኝ ነገር
እግሬን ለማላቀቅ ለመበጠስ ስሞክር ገመዱን ስወጥረው የቤተክርስቲያን
ቃጭል የመሰለ ድምፅ ሰማሁ ከደውሉ በሗላ እንደ ተኩላ የሚጮህ ድምፅ
ተሰማኝ ከወገባቸው በታች ብቻ ቅጠል ያገለደሙ ብዛት ያላቸው ጦርና ቀስት
የያዙ ሰዎች መጡ እጅግ ፈራሁ....አንዱ ችግር ሄደ ስል ሌላ ችግር...አጠገቤ
ከደረሱ በሗላ በማላውቀው ቋንቋ ይለፍፉ ጀመር በድንገት አንዱ አጎንብሶ
እግሬ ላይ ያለውን እስራት ፈታልኝ እጁንም ዘርግቶ አነሳኝ ፈራቻም
አግራሞትም በአንድነት ነገሱብኝ.....
....የዋሻው ሰዎች እዚ ያለውን ጫጫታ ሰምተው ነው መሰል እየተጣደፉ
መጡ እኔም እጄን ይዞ ካነሳኝ ሰው ጀርባ ተሸሸግሁ በዚ ጊዜ ነበር
እንደወገናቸው ቆጥረውኝ ከዋሻው ሰዎች ጋር ሰይፍ የተማዘዙት...ሁሉንም
የዋሻ ሰዎች ገደሏቸው እኔንም ይዘውኝ ወደ ግዛተታቸው ወሰዱኝ የማየውንና
የተፈጠረውን ማመን አልቻልኩም...እስራኤልን ከግብፃውያን የታደገው ያ
የእግዜር እጅ ዛሬ ለኔም ተዘርግቶ ነበር....ሞቅ ባለ አቀባበል ተቀበሉኝ
ጠቦትም አርደው አጠገቡኝ ከመሀላቸው አማርኛ ቋንቋን የሚናገር ሰው ነበርና
ብዙ ነገሬን ነገርኩት አእሱም ስለ ጎሳው ነገረኝ እኔም ከቀረበልኝ መብል
እየጎረስኩ ፅዋም እየተጎነጨው አዳመጥኩት...እንዲህ ሰሲል ነበር
ያወጋኝ....የዚህ ጎሳ መሰረት ከሚንኖሩበት ደን ውስጥ ያለ የሰላም መንፈስ
ነበር አንድ ሰው ከመንደሩ ሰዎች የተነሳበትን ተቃውሞና መገለል ሽሽት ወደዚ
ቦታ መጣ እዚም ስፍራ ላይ ለስጋው ሚሆን ነገር ብዙ ነበር ይህ ለአንድ ቀን
ነፍሱን ለማትረፍ ብሎ እዚህ ከትሞ ቀረ የሚያውቃቸውንም ሰዎች አመጣ
ተዋለዱ ተባዙም እናም እዚ ደርሰናል ከየትኛውም ገጎሳ ገጋር ተነካክተን
አናውቅም ነገር ግን ዛሬ ደመም ተፋሰናል ምላሹ መምን እንደሚሆን አእንጃ
የዚህ አካባቢ ተታላቁ መንፈስን አስቀይመናል ለአንድ አንተ ስንል ብዘዙ ነፍስ
አደገጋ ላይ ጣልን* አለኝ በማዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ እኔም ይህ ነገር እጅግ
አሳሰበኝ ግን ምንም አላልኩም ሰዓቱም መሸ ሁሉም ወደ መኘኛ
መመምራታቸውን ሰስጠብቅ ነገር ግን ከፊሉ ነበር ወደ መኝተታ የሄደወው
ከፊሉ ጎሳውን ለመጠበቅ ነቅቶ ተዘጋጅቷል ጊዜው ተጉዞ እኩለ ለሊት ደረሰ
እንቅልፍ መምንም ሊይዘኝ አልቻለም.....በድንገት ጮክ ያለ የሚየያሽካካ
የፈረስ ድምፅ ተሰማ.....ይቀጥላል

Join for more ??

@utorrr
@utorrr

3 months, 4 weeks ago
*‹‹እኔ እዘጋዋለሁ፣ ቤቴን እንዳመሉ፤

*‹‹እኔ እዘጋዋለሁ፣ ቤቴን እንዳመሉ፤
ሰዎች ከጠየቁ፣ ከፍቶት ሄደ በሉ፤››

ደበበ ሰይፉ*

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana