ጲያ ግጥም ✏️

Description
የተለያዩ ግጥሞች በፅሁፍና , በድምፅ
አጫጭር ታሪኮች

ለሀሳብ አስተያየት👉 @Hanipia
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

3 months ago

...ትዝታ

ትዝታ ገዳዩ ናፍቆትን ያብሳል
በጥላቻ መሀል ፍቅርን ይሰብካል
እንባን አሳብሶ በምናብ ይወስዳል
ትዝታ ከባዱ ቫይረስ ነው ይገላል

By
@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem

4 months ago

...ልመንህ ወይ
ላፈቅርህ ነዉ አተወኝም
ልመንህ ወይ አትከዳኝም
ገብሬልን ማርያምን በልና ማልልኝ
በልብህ ዙፋን ላይ ቃልኪዳን ግባልኝ
አልተውሽም ብለህ በላ በላኮ ማልልኝ
አምኜህ ልቀመጥ ቀልቤ ይረፍልኝ
ደግመህ እንደማተወኝ ልቤ ይወቅልኝ
በላ በላ በላኮ ማልልኝ

By

@Hanipia

@getem
@getem
@Hanipiagetem

6 months, 2 weeks ago

አጭር ዕድሜ

ዘላለም የምትመስል አጭር ዕድሜ
ዕለት ዕለት የምኖራት ደጋግሜ
የማትበቃ የእፍኝ ያህል
ለሰው ሲሏት የምትጎድል
ይችን አድር ባይ
ከወኔ አጉዳይ
ማን ነው የፈቀደ ከእኔ ሊያተያይ
ምስጢር ከሆነ አትናገሩት
መስማቴ አይቀርም.......
.!
አትንገር ብለው ለአንዱ ሲነግሩት።

አየሁ ነኝ

@tekle_ayehu

6 months, 2 weeks ago

ጊዜና የ'ኔቢጤ!

እየተቃቃርን
እየተገፋፋን
የጀመርነው ፍቅር
ደራሽ ወንዝ ቢሆን
የት ያደርሰን ነበር?
ወይ ወደ ሀዘን
ወይ ወደ ደስታ
ሁለት ምርጫ ቢኖረን ነው!
እያልኩ ሁሌ አቅማማለሁ
ሀዘን ምርጫን ሳስብ ደግሞ
እሰጋለሁ ?
ደስታን ብቻ ከአንቺ ጋር መጋራትን እሻለሁ
ደግሞ ደግሞ ይሕ ቅብጥና
በሐዘን መንገድ ሳያሰማራ

መልካሙን አይሰጥምና
እናዝግም ረጋ ብለን በጥሞና
ነይ....! ዝም ብለን እንጓዝ በሁለት ጎዳና
ለነፍስ ለስጋ አምሮት ሲባል
ሴትና ወንድ ዘር መተካት ጀምረዋል
ዓለም ማለት ይህች ናት
አንዴ ጥላ ከፌሽታ
ለእድሜ ልክ ጀባ የምትለን ስቃይ አሰናድታ
ከልባችን ሕንፃ ላይፈርስ ይፃፍ
የ'ቢጤ ናትና ጊዜ
እቆያለሁ አልቆይም እያሉ የሚያቅማሙባት ደጃፍ።

አየሁ ነኝ

@tekle_ayehu

6 months, 2 weeks ago

ምን እንልበስ

ነይ እንፅና በአንድ መንገድ
በሌለበት መሸዋወድ
እኔና አንቺን በሚያክለን
በፍቅር ሃሳብ ተደግፈን
በሚችለን ሰፊ ሜዳ
ነይ እንመር እንሰናዳ
የፀብ ሰአት ይታወቀን
እንዳለብን የእምነት እዳ
እየተራረምን የሄድንበቱ
የቱ ጋር ነው ስህተቱ
ፍቅር የጀመርን ሰሞን
እኔም ነበርኩ ወንድምሽ
አንቺም ተብለሻል እህቱ
እንዲህ ይዤሽ
እንዲህ ይዘሽኝ
በሕመምሽ ጎንሽ ሆኜ
በሕመሜም አስታመሽኝ
ለፍፃሜያችን ውበት ይጣል ዳስ
ከዚህ በኋላስ ምን እንልበስ
ለመኖር እስከምንመጥን ድረስ።

አየሁ ነኝ

@tekle_ayehu

6 months, 3 weeks ago

ሴትና ገላዋ

ቀልቤን እንዳልነሳሽው አስመስላለሁ
ልማዴ ቁጥብነት እንደሆነ በአኳኋኔ እገልፃለሁ

ከሴት የተለየው አማላይ ገላዋ
ወሮበላውን ልጅ አደረገው ጨዋ

አትፍረዱብኝ በፍቅር ሲሆን ነኝ ገራገር
ዝቅም ለማለት የማልቸገር

ውስጤን አጥንታ ለምትኮራብኝ
መለማመጥ ነው ትልቅ ጠላቴ ይሕን በሉልኝ

ሴትነት ይዟት ብትልም ፀጥ
ቀድማ ካልመጣች ስል
ለራሴ ማልኩ ልቤን ላልሰጥ

አፈር ለሚበላው ገላ ብዬ አልልሽም
ከሞቀበት መሄድ ይሻላል ብትይም
አመንሽም! አላምንሽም!
አካልሽን መሸጡ ንፅሕናሽን በልጦት አያውቅም

ለዛ ነው ሳይሽ የማዝነው
ለደስታዬ ግብአት ያደረኩሽ ቀን የምጨነቀው

ለሌላ ምኞት ከመነሳቴ
እንደ ተማረ ሆኜ እያለ ካለፈ ክፉ ስህተቴ

እዛው ነኝ አሁንም
እዛው ትላንትና
ከማይጠፉበት ቤት ሴቷና ገላዋ።

አየሁ ነኝ

@tekle_ayehu

8 months, 2 weeks ago

ሞት እና ሳቅ

አውቄ ነው አንዳንድ ጊዜ
ቀለድ መስሎኝ
በእውነት ቃል የማመረው
ዘና ሲያደርግ
የሚመቸው
በወዮታ የሚገለው
ከቀልድ ሁሉ የሚገርመው
በአሽሙር ድባቅ የሚገድለው
ከጠብ ይልቅ
ምቾት ያለው
ከማላውቀው
ከጥልቁ ውስጥ
በእሳት ንዳድ እንዳረፈው
እንደ ሳጥናኤል
ካለ መልዐክ
በእሱ ስራ እንደመሳቅ
ለእኔ በዓለም ከዚህ በላይ
ተዓምር የለም የሚያስደንቅ
ማሳቅ ማለት በዝረራ
ያለቀን ትግል ይመስላል
መሳቅ ደግሞ
በሞት ደጃፍ የሚዝናናን
ሰው ይመስላል
ከጭቅጭቅ ተራርቆ
በሰላም ዳስ ያለን
ስብስብ ያስቃኛል
ከቅኔ አድባር
ከወንዝ ዳር
በእረኞች ከመተረብ
ያሳምማል
የሞኝ ሀሳብ
እሱ ገብቶት ያላትን ቃል
ይቆጥረዋል
አዋቂ ያልነው እንደ ስድብ
ማሾመርን ማወቅ ሳይሆን
መኖር ያሻል
አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ ነኝ
አውቄ ነው የምጠይቀው
ባላሳቀኝ የምስቀው
ባልገረመኝ
መቃ አንገቴን የምነቀንቀው
አንዳንድ ጊዜ
በሞተ ሰው የምስቀው

መጥፎን ጊዜ የማዝናናው
ደስታን ደግሞ የማስጠላው
አቧራውን
ጥላሸቱን የምቀባባው

አውቄ ነው አንዳንድ ጊዜ
ቀልድ መስሎኝ የማሾፈው
በሞተ ሰው የምስቀው።

አየሁ ነኝ

ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት
?????
@tekle_ayehu

የቻናል ጥቆማ
????
@ayehu_melkam

8 months, 2 weeks ago

እርቅ ይሁን!

ከልብ ካዳመጥሽኝ ለአንቺ የሚሆን አንድ ሀሳብ አለኝ
ትቀበይው አትቀበይው እሱ ግድ አይሰጠኝ
ይልቅ አንዴ ስሚኝ
ትወጅኛለሽ ግን
ትዝ ካለሽ የጀማመርን ሰሞን
ልሙትልህ ስትይ
ምን በወጣሽ ብዬ ራሴን እንደገደልኩ
ዛሬ ኑሮ ይዞኝ ለዚህ ቃል ከቦዘንኩ
እኔ በሄድኩበት የፍቅር መንገዴ
አትመጪም በአንዴ
አታጫውችኝም ተውሰሽ ከቀልዴ
እንዲህ ብዬ ስልሽ አትቆጪ ቶሎ
ለጠላት አይከብድም ከእኛ
አንድነት ውስጥ መኖር ተቻችሎ
ልብስ የለበስሽ ዕለት
ውብ መሆንሽ ጎልቶ በታየኝ በዚህ ወቅት
አማረብሽ ማለት ታይቶኝ ከሆን ቀሎ
አፍሽ አይቆጣ
ልብሽ አያውቀውም ይሕን ቃል ወክሎ
ቢሞትም ይመርጣል አንገትሽ ተሰቅሎ
ነይ አብረን እንቁም ጠባብ ወንበር አምጪ
ምድር ትሁን ተያዥ
ቀድሞ የወደቀን
ሰማይ ይሁን አዉጋዥ
እውነት ስትጠፋ እንዲህ እያልን ነው
መወሰን ያቃታን
ከሰው አንድ ጠፋ ጠባችንን ሳይወድ
እርቅ ይሁን የሚለን
ቀኝ እጄ ያልነውም ሆኗል ባላንጣችን
ከልብ ለወደደ ሆድ ቁርጠት ምንም ነው
የአንጀት እውክታም የጉንፋን ያህል ነው
ለፍቅር መሰጠት
ለእውነት መሞትም አንድ ደዌ ናቸው
እንደ ጫካ እፅዋት
እንደማይነቅዝ እንጨት
ስለት ሰመረልኝ እንደምትል ባልቴት
እንኳን ሰው ይቅርና
አሪፉን ይወዳል የፈጣሪ ታቦት
እኔስ ምን ያንሰኛል
ከሰው ተመርጩ ባገኝ አንድ ሹመት
ንጉስ ነህ እያለ ተከታይ ሲደሰት
ንግስት ሆይ ብሎ አንቺን ባያካትት
የሞት ፍርድ ስፈርድ
አንዳች አልቆጭም
በየመንገድ ዳር አዋጅ አውጄ
ነፍሱን ባጠፋት
ዕርቅ ይሁን ስልሽ
ጥፋት ማጥፋቴን ስላወቅሽብኝ
በዚህ አይደለም
እርቅ ይሁን ያልኩሽ
ስህተቴን ሁሉ በመጥፎ ስለማታይው
እይታዎቼን በክህደት ሀሳብ ስላልቀየርሽው
ከግዛታችን ውብ ቆንጆ ሴቶች
አብረሽ ካየሽኝ
ስለምትመስይ እንዳላየሽኝ
ለዚህ ሁሉ ነው ከልቤ አልቅሼ እርቅ ይሁን ያልኩኝ።

አየሁ ነኝ

ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት
?????

@Hanipia
@tekle_ayehu

@ayehu_melkam

8 months, 3 weeks ago

ከልብ ወጪ ምን ሰብረሻል
ብዬ ስላት
እቃ አለች
ያስታውቃል አነጋገሯ ሌላ ገዝታ ተክታለች
ልቤንማ እንዴት ብላ
እንደቀድሞው ታደርጋለች። ?

አየሁ ነኝ

ለማንኛውም ሀሳብና አስተያየት
@Hanipia
@tekle_ayehu

8 months, 3 weeks ago

ሕማማቱን ብለን
ጥቂት ስግደት ሞከርን
ላባችን ጠብ አለ በዚህ ተሳለቅን
ፀሎቱ ረዘመ እያልን አጉረመረምን
የቀራንዮን ግፍ አላየንምና
በማሰብ ታግዘን ተማፅነናልና
እንኳን ከእግዜር አላልፍ አለ ምሕላችን ከደመና።?

አየሁ ነኝ

@Hanipia
@tekle_ayehu
@ayehu_melkam

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana