ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month ago
Last updated 1 month ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 2 days, 5 hours ago
🚩 ዘመኑ ቀርቧልና እንንቃ!
በዚህ ቪድዮ ላይ እንደምታዩት ይህ ሰው ያለ ምንም የወረቀት ገንዘብ፥ ያለ ምንም credit card, ያለ ምንም online transfer በቀኝ እጁ መዳፍ ብቻ ግብይት ሲፈጽም ይታያል። ያለ credit card እና ያለ online transfer በእጅ መዳፉ ብቻ እንደሚከፍል ቪድዮው ላይ ይናገራል
መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ ስለ መጨረሻው ዘመን እንዲህ ይላል 👇
"16፤ ታናናሾችና ታላላቆችም ባለ ጠጋዎችና ድሆችም ጌታዎችና ባሪያዎችም ሁሉ #በቀኝ_እጃቸው ወይም በግምባራቸው ምልክትን እንዲቀበሉ፥ 17፤ የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም #ሊገዛ_ወይም_ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል። ጥበብ በዚህ አለ" (የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ 13:16-17)
አስተውላችሁ ካያችሁ ሰውየው የከፈለው በቀኝ እጁ ነው። ይህ ማለት ይህ ቴክኖሎጂ ሀሰተኛው ክርስቶስ የሚጠቀምበት ቴክኖሎጂ ነው ወይም ደግሞ እርሱ ለሚጠቀምበት ቴክኖሎጂ መሰረት የሚጥል ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ነው። ነገሩ ወዴት እያመራ እንደሆነ ግልፅ ነው። ዘመኑን እናስተውል። የእግዚአብሔር ቃል የሚናገረው ነገር step by step ሲፈጸም በአይናችን እያየነው ነው!
እንንቃ!
አራት ዓይነት አፈጣጠር? በሚል ርዕስ የተጻፈውን ይህንን አዲስ ጽሑፍ ያንብቡ። የኢየሱስን ከድንግል መወለድ እንደ አራተኛ የሰው አፈጣጠር መንገድ ለሚቆጥሩት ሙስሊሞች የተሰጠ የማያዳግም ምላሽ ነው https://ewnetlehulu.net/four-creation/
በኤፌ 1:20-21 ክርስቶስ የበላያቸው እንደሆነ የተነገረላቸው ኃይላትና ጌትነት በሰማይ ያሉ መናፍስት ወይም መላእክት ሲሆኑ (ኤፌ 6:12 1ጴጥ 3:22 ይሁዳ 1:8-9) ከእነሱ የሚበልጥ እጅግ የሚበልጥ ስም እንዳለው ተገልጿል። በዕብ 1:4 ላይ የምንመለከተው ይህንን ነው። በሰማያት በግርማው ቀኝ ሲቀመጥ ከመላእክት እጅግ የሚበል ስምን መውረሱ ከአለቅነት፥ ከሥልጣን፥ ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይ በዚህ አለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም አለም ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያት በአብ ቀኝ መቀመጡ ነው። ይህ የዕብራውያን ጸሐፊ ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።
♦️ በኤፌ 1 እና በዕብ 1 መካከል ጠንካራ የመልእክት አንድነት አለ። በሁለቱም ስፍራ አብ ሁሉን ወራሽ እንዳደረገው ተነግሯል (ኤፌ 1:22/ዕብ 1:2) ትንሳኤው ተነግሯል (ኤፌ 1:20/ዕብ 1:3) በአብ ቀኝ መቀመጡ ተነግሯል (ኤፌ 1:21/ዕብ 1:3) ከመላእክት እጅግ የሚበልጥ ስም እንዳለው ተነግሯል (ኤፌ 1:20-21/ዕብ 1:4) ይህን አይነቱን አገላለጽ ከሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት ውጪ በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የማይመለከተው ሲሆን፥ የሁለቱም መልእክታት ጸሐፊ ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጸሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው
▶️ ይቀጥላል
በዕብ 1:3 ላይ በእግዚአብሔር የግርማው ቀኝ የተቀመጠው አለማት የተፈጠሩበት ልጁ መሆኑ እንደተገለጸ ሁሉ፥ በሮሜ መልእክትም ሞቶ፥ ከሙታን ተነስቶ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ልጁ ኢየሱስ መሆኑ በዚያው በሮሜ መልእከት ላይ በተደጋጋሚ ተገልጿል፦
"ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር #ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው" (ሮሜ 1:3-4)
" #በልጁ ወንጌል በመንፈሴ የማገለግለው እግዚአብሔር ምስክሬ ነውና፤ ምናልባት ብዙ ቆይቼ ወደ እናንተ አሁን እንድመጣ በእግዚአብሔር ፈቃድ መንገዴን እንዲያቀናልኝ እየለመንሁ ሁልጊዜ ስጸልይ ስለ እናንተ ሳላቋርጥ አሳስባለሁ" (ሮሜ 1:9-10)
"ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር #በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን" (ሮሜ 5:10)
✍️ ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንደተቀመጠ በተናገረበት በዚያው አውድም ያ በቀኙ የተቀመጠው ልጁ መሆኑን ሐዋርያው ገልጿል፦
"ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን እግዚአብሔር የገዛ #ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጎአልና" (ሮሜ 8:3-4)
" #ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና" (ሮሜ 8:29)
"ለገዛ #ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?" (ሮሜ 8:32)
✍️ በሮሜ 8 እና በዕብ 1 መካከል ያለው ይህ ከፍተኛ የሆነ የአስተምህሮ ቁርኝት ሁለቱም መልእክቶች በአንድ ጸሐፊ ለመጻፋቸው ማስረጃ ከመሆኑ ባሻገር የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውሰጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው
9) እጅግ የሚበልጥ ስም አለው
"ከመላእክት ይልቅ እጅግ #የሚበልጥ_ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ ይበልጣል" (ዕብ 1:4)
የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ በዕብ 1:3 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱ የክብሩ ነጸብራቅና የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑን፥ ሁሉንም በስልጣኑ ቃል እንደሚደግፍና ኃጢአታትንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ እንደተቀመጠ ከገለጸ በኋላ በዕብ 1:4 ላይ ከመላእክት እጅግ የሚበልጥ ስምን እንደወረሰ ይናገራል። በዚህ ስፍራ ስም የሚለው "position, status" ማለት ሲሆን ከእርገቱ በኋላ ወደ ቀድሞ ክብሩ መመለሱን የሚገልጽ ቃል ነው። ከስጋዌው የተነሳ ከመላእክት ጥቂት አንሶ የነበረው ክርስቶስ (ዕብ 2:9) በምድር ላይ ሲመላለስ እንደ አባቱ ባርያ ነበር፥ አላማውም ለማገልገል ነበር (ማቴ 20:28 ማር 10:45 ኢሳ 42:1) ነገር ግን ከትንሳኤው በኋላ አለም ሳይፈጠር ወደነበረው ክብር ተመሰለ (ዮሐ 17:5)
ለዚህም ነው በዕብ 1:4 ላይ በሰማያት ዘግርማው ቀኝ ከተቀመጠ በኋላ ከመላእክት የበለጠን ስም ወረሰ የሚለው። ከስጋዌው በፊት ወደነበረው position, status አርጎ መመለሱን እያመለከተ ነው። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ ከስም/position ሁሉ በላይ የሆነው ስም የእግዚአብሔር ስም ሲሆን (መዝ 148:13) ክርስቶስ ኢየሱስ ከመላእክት እንኳን እጅግ የሚበልጥ ስም እንዳለው መነገሩ በስጋ የመጣው አምላክ ለመሆኑ የማይታበል ማስረጃ ነው። ምድር ላይ የነበረውን የባርያ አገልገሎት ከፈጸመ በኋላ ዐርጎ የተመለሰው ወደዚህ ክብር መሆኑ መገለጹ ክርስቶስ ከስጋዌው በፊት በመለኮታዊ ክብር የነበረው እግዚአብሔር ለመሆኑ ተጨባጭ ማስረጃ ነው።
➢ በዕብ 1:3 ላይ የተባለው ይህ ነገር የልጁ የክርስቶስ ኢየሱስን ስጋዌና አምላክነት ከማሳየት ባሻገር፥ የመልእክቱ ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ሌላ ማሳያ ነው። ምክንያቱም ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ ስም ያለው መሆኑ በሐዋርያው ጳውሎስ መልእክት ላይ የተነገረ እውነት ነውና፦
"በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው #ከስምም_ሁሉ_በላይ_ያለውን_ስም_ሰጠው" (ፊል 2:9)
በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ኢየሱስ ከስም ሁሉ በላይ የሆነ ስም ከእግዚአብሔር አብ እንደተሰጠው እንመለከታለን። ይህ ማለት ክርስቶስ ኢየሱስ ምንም እንኳ በእግዚአብሔር መልክ/ባህርይ ሲኖር ሳለ የባርያን መልክ/ባህርይ ከያዘ በኋላ ለመስቀል ሞት እንኳ ሳይቀር ለአባቱ በመታዘዙ እግዚአብሔር ያለልክ ከፍ ከፍ አድርጎታል። ይህ ማለት ከስጋዌው በፊት ወደነበረው ክብሩ (ዮሐ 17:5) መልሶታል ማለት ነው። አለም ሳይፈጠር በፊት የነበረበት ክብር የመለኮት ክብር ሲሆን፥ ከትንሳኤው በኋላ በሰማያት በዙፋኑ በቀኙ በማስቀመጥ ወደዚያ ክብር መልሶታል። ያለ ልክ ከፍ አደረገው ማለት ይህ ነው።
በፊሊ 2:9 ላይ "ከፍ ከፍ" ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል "ὑψόω/ሂፕሲኦ" ሲሆን (Strong's G5312) ኢየሱስ በአብ ቀኝ ያለውን የመጨረሻውን ክቡርና ከፍተኛ የመንግስተ ሰማይ position ያመለክታል (ሐዋ 2:33 ሐዋ 5:31) ያም የእግዚአብሔር ዙፋን ነው (ራዕ 22:1) ስለዚህ ከስምም በላይ ስም ሰጠው ማለት ቀድሞ ወደነበረው የመጨረሻው ከፍተኛ position፥ አለም ሳይፈጠር ወደነበረው ክብሩ መለሰው ማለት ነው። ልዩነቱ አለም ሳይፈጠር የዚህ ክብር ባለቤት የሆነው በመለኮታዊው ባህርይው ብቻ ነበር። ከትንሳኤው በኋላ ግን የዚህ ክብር ባለቤት የሆነው ሰዋዊውም ባህርይ ኖሮት ነው። በዕብ 1:4 እና በፊሊ 2:9 መካከል ያለው የይዘት አንድነት የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።
♦️ በዕብራውያን 1 እና በፊልጵስዩስ 2 መካከል ሰፊ የሆነ የአስተምህሮ አንድነት ያለ ሲሆን ከሐዋርያው ጳውሎስ መልእክታት ውጪ በየትኛውም ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የምናገኘው አይነት አገላለጽ አይደለም። በሁለቱም ስፍራ ልጁ ክርስቶስ ኢየሱስ ከአብ ጋር በባህርይ አንድ እንደሆነ ተገልጿል (ፊሊ 2:6/ዕብ 1:3) ስለ ኃጢአታችን ተሰቅሎ መሞቱ ተገልጿል (ፊሊ 2:8/ዕብ 1:3) አርጎ ከስም ሁሉ በላይ ስም እንደተሰጠውም ተነግሯል (ፊሊ 2:9/ዕብ 1:4) ይህ በሁለቱ መካከል ያለው የማይታበል የሀሳብና የትምህርት አንድነት የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።
"ክርስቶስንም ከሙታን ሲያስነሣው ከአለቅነትና ከሥልጣንም ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይና በዚህ ዓለም ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ሊመጣ ባለው ዓለም ደግሞ #ከሚጠራው_ስም_ሁሉ_በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ #ሲያስቀምጠው በክርስቶስ ባደረገው ሥራ የብርታቱ ጉልበት ይታያል" (ኤፌ 1:20-21)
በዚሁ ስፍራም ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቶስ ከስም ሁሉ በላይ ስም እንዳለው ሲናገር እናነባለን። እግዚአብሔር አብ ልጁን ክርስቶስ ኢየሱስን ከሞት ካስነሳው በኋላ ከአለቅነት፥ ከሥልጣን፥ ከኃይልም ከጌትነትም ሁሉ በላይ በዚህ አለም ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም አለም ከሚጠራው ስም ሁሉ በላይ በሰማያዊ ስፍራ በቀኙ እንዳስቀመጠው ይናገራል። ማለትም ክርስቶስ ከትንሳኤው በኋላ ያለው position የመጨረሻው ከፍተኛ position ነው። እርሱም በሰማያት ያለው የእግዚአብሔር ቀኝ የሆነው የግርማው ዙፋን ነው። ከሁሉ በላይ የሆነው ስም የሚያመለክተው ይህንን ነው
? የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ (ክፍል 4)
ባለፉት ተከታታይ ክፍሎች የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ ጀምረን ነበር። ሙስሊሞች ሆኑ ሌሎች ከክርስትና ውጪ ያሉ አካላት የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ስለማይታወቅ መጽሐፉ የመጽሐፍ ቅዱስ አካል መሆን የለበትም፥ የእግዚአብሔርም ቃል ሊሆን አይችልም ብለው ሊሟገቱ ይሞክራሉ።
ነገር ግን ባለፉት ክፍሎች ለማሳየት እንደሞከርነው ይህ ፍጹም ስህተት የሆነ አመለካከት ነው። የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ከምሁራንና ከቤተክርስቲያን ታሪክ ብዙ ማስረጃዎችን ማምጣት ይቻላል። በተጨማሪም ከራሱ ከዕብራውያን መልእክት ጸሐፊው ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ማስረጃዎችንም ማቅረብ ይቻላል
▶️ እግዚአብሔር ቢፈቅድ በዚህም ክፍል ላይ ካለፉት ክፍሎች በመቀጠል የዕብራውያኑ ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያረጋግጡ ተጨማሪ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃዎችን ማቅረብ እንቀጥላለን፦
8) በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀምጧል
"እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ #በሰማያት_በግርማው_ቀኝ_ተቀመጠ" (ዕብ 1:3)
በዕብ 1:3 ላይ የዕብራውያኑ ጸሐፊ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአባቱ የክብሩ ነጸብራቅና የባህርይው ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑን፥ ሁሉንም በስልጣኑ ቃል እንደሚደግፍና ኃጢአታትንን በራሱ እንዳነጻ ከገለጸ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ መቀመጡን ይናገራል። ልጁ ጌታ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ በብሉይ ኪዳን ስለ መሲሁ የተነገረ ትንቢት ሲሆን (መዝ 110:1) ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ዐርጎ በአባቱ ቀኝ መቀመጡ (ዕብ 10:12-13) የዚህ የብሉይ ኪዳን ትንቢት ፍጻሜ ነው። ይህ ትንቢት በተነገረበት በመዝሙረ ዳዊት አስተምህሮ መሰረት እግዚአብሔር በሰማይ ያለ ሲሆን (መዝ 102:19 መዝ 2:4) ዙፋኑም ያለው በዚያው በሰማይ ነው (መዝ 103:19 መዝ 11:4) ስለዚህ መሲሁ በእግዚአብሔር ቀኝ ይቀመጣል ማለት እግዚአብሔር ወዳለበት ወደ ሰማይ ዐርጎ በዙፋኑ ላይ በቀኙ ይቀመጣል ማለት ነው። መሲሁ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ሰማያት አርጎ በአባቱ በእግዚአብሔር አብ ግርማ ቀኝ መቀመጡ ይህን ትንቢት ለመፈጸሙ የማይታበል ማረጋገጫ ነው።
በዕብ 1:3 ላይ ተገልጾ የምንመለከተው ይህ እውኑት ጌታ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን የተነገረውን ትንቢት እንደፈጸመ ከማሳየት ባሻገር፥ የመልእክቱ ጸሐፊ ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ ለመሆኑ ሌላ ማሳያ ነው። ምክንያቱም ልጁ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአብ ቀኝ መቀመጡ በሐዋርያው ጳውሎስ መልእክቶች ላይ የተነገረ እውነት ነውና፦
"እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፥ #ክርስቶስ_በእግዚአብሔር_ቀኝ_ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ" (ቆላ 3:1)
በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንደተቀመጠ ሲናገር እንመለከታለን። በበፊተኛው ምዕራፍ ላይ እንደ ሰው ስርዓት ላሉት ምድራዊ ነገሮች እንዳይገዙ ከነገራቸው በኋላ (ቆላ 2:22) በምዕራፍ 3 ላይ ማሰብ ያለባቸው ክርስቶስ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት ያለውን ነገር እንዲሹ ይመክራቸዋል። ክርስቶስ ኢየሱስ ያለው በላይ በሰማይ ስለሆነ እርሱ ባለበት በላይ ያለውን እንጂ በምድር ያለውን እንዳይደለም ይነግራቸዋል (ቆላ 3:2) ቆላ 3:2 ላይ "በላይ" ተብሎ የተተረጎመው የግሪክ ቃል በሌላው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ላይ ሰማይን ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል (ዮሐ 8:23) ስለዚህ ክርስቶስ የተቀመጠው በሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ ነው ማለት ነው።
በቆላ 3:1 ላይ ልክ እንደ ዕብ 1:3 ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንደተቀመጠ መገለጹ የሁለቱን ክፍሎች የሀሳብ አንድነት ከመጠቆም ባሻገር የሁለቱም መልእክታት ጸሐፊ አንድ ለመሆኑ ማሳያ ነው። በዕብ 1:3 ላይ በእግዚአብሔር አብ የግርማው ቀኝ የተቀመጠው አለማትን የፈጠረበት ልጁ መሆኑ እንደተገለጸ ሁሉ፥ በቆላ 3:1 ላይ በሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው ልጁ መሆኑ በዚያው በቆላሲስ መጽሐፍ ላይ ተገልጿል (ቆላ 1:13-14) ከዕብራውያን እና ከቆላሲስ መልእክታት እንደምንረዳው በሰማያት በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው የአለማት ፈጣሪ የሆነው የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው። ይህ የሁለቱን ክፍሎች የትምህርት አንድነት ከማሳየት ባሻገር የሁለቱም መልእክቶች ጸሐፊ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።
በዕብራውያን መልእክት እና በቆላሲስ መልእክት መካከል እጅግ በጣም የሚያስገርም ሰፊ የሆነ የትምህርት አንድነት አለ። በሁለቱም መልእክቶች ልጁ ኢየሱስ የአባቱ የእግዚአብሔር አብ ትክክለኛ ምሳሌ መሆኑ ተገልጿል (ቆላ 1:15/ዕብ 1:3) የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ እንደሆነ ተገልጿል (ቆላ 1:15-16/ዕብ 1:2) ፍጥረት ሁሉ በእርሱ እንደተጋጠመ ተገልጿል (ቆላ 1:17/ዕብ 1:3) ከሃጢአት መንጻት/የሃጢአት ስርየት በልጁ እንደተከናወነ ተገልጿል (ቆላ 1:13-14/ዕብ 1:3) በአብ ቀኝ መቀመጡም ተገልጿል (ቆላ 3:1/ዕብ 1:3) በሁለቱ መልእክቶች መካከል ያለው የይዘትና የአስተምህሮ ቁርኝት የሁለቱም መልእክታት ጸሐፊ ራሱ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለመሆኑ ጠንካራ ውስጠ-ጽሑፋዊ (inter-textual) ማስረጃ ነው።
"የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ #በእግዚአብሔር_ቀኝ_ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" (ሮሜ 8:34)
በዚህ ቦታ ላይም ሐዋርያው ጳውሎስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ እንዳለ ሲናገር እንመለከታለን። በዚህ ስፍራ ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ በዕብ 1:3 ላይ ያለውን ራሱ ሀሳብ ከነ ቅደም ተከተሉ እየደገመው ነው። በዕብ 1:3 ላይ ልጁ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ #በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ እንደተቀመጠ ይናገራል። ወደ ሰማያት አርጎ በአባቱ ግርማ ቀኝ የተቀመጠው ኃጠአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ ነው። በባለፈው ክፍል ለማየት እንደሞከርነው የክርስቶስ እኛን በራሱ ከኃጢአታችን ማንጻቱ በመስቀል ላይ ስለ እኛ በደል ተሰቅሎ መሞቱ ነው (ቲቶ 2:14 ኤፌ 1:7 ቆላ 1:13-14 ማቴ 20:28 1ዮሐ 4:10) ስለዚህ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ #በኋላ ማለት ስለ በደላችን ማስተሰርያ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ማለት ነው። እንደ ዕብ 1:3 ቅደም-ተከተል መሰረት ከዚያ በኋላ ነው በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠው
ይህን በዕብ 1:3 ላይ የምንመለከተውን ይህንን ቅደም-ተከተል በሮሜ 8:34 ላይ እንመለከተዋለን። በሮሜ 8:34 ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡን ሲገልጽ "..የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው.." በማለት በእግዚአብሔር ቀኝ ከመቀመጡ በፊት የሆኑትን ክስተቶች በዕብ 1:3 ላይ በምንመለከተው ቅደም-ተከተል መሰረት ያስቀምጠዋል። በሮሜ 8:34 ላይ የተጠቀሰው ሞትና ትንሳኤ በዕብ 1:3 ላይ በራሱ እኛን ከኃጢአታችን ማንጻቱ ነው። በሁለቱ ክፍሎች መካከል ያለው ይህ የሀሳብ፥ የአስተምህሮ እና የቅደም-ተከተል አንድነት የሁለቱም ክፍሎች ጸሐፊ ያው ራሱ ሐዋርያው ጳውሎስ መሆኑን የሚያሳይ ጠንካራ ውስጠ-ጽሑፋዊ (intertextual) ማስረጃ ነው።
? አሳዛኝ ዜና ?
ይህች በምስሉ ላይ የምትመለከቷት አንዲት ፍሬ የ7 አመት ሕጻን ልጅ እናቷ ስራ ላይ በነበረችበት ሰአት በአከራያቸው በአሰቃቂ ሁኔታ ተደፍራ ተገድላለች! ?
ወንጀለኛው ግለሰብ ይህችን ሕጻን ልጅ ወደ መጸዳጃ ቤት ስትሄድ ጠብቆ ካፈናት በኋላ እንዳትጮህ አፏ ውስጥ አሸዋ ከጨመረ በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ በማህጸኗ እና በመቀመጫዋ ደፍሯታል ?
ያደረሰባት ጉዳት እጅግ አስከፊ ከመሆኑ የተነሳ የጀርባ አጥንቷ እስኪታይ ድረስ ማህጸኗ ተጎድቷል። ወንጀለኛው ይህን ዘግናኝ ወንጀል ከፈጸመ በኋላ በሳፋ ውስጥ ያጠባት ሲሆን፥ ወድቃ የሞተች ለማስመሰል ገላዋን በምላጭ ተልትሎታል ?
በስተ መጨረሻም የፈጸመው እርኩስ ወንጀል እንዳይጋለጥበት አንቆ ገድሏት እንደ ተጣለ እቃ የቤቱ ደጃፍ ላይ ጥሏታል። በሃይል ከማንቁ የተነሳ የልጅቱ አስክሬን ሲገኝ አንገቷ ውስጥ ጣቶቹ የሰረጎደበት ምልክት ተገኝቷል ?
በአሁን ሰአት ላይ ወንጀለኛው ማረሚያ ቤት ውስጥ ቢገኝም የመንግስት አካላት በይግባኝ ሊያስፈቱት እንቅስቃሴ ጀምረዋል። የወንጀለኛውም ቤተሰቦች የልጅቱን እናት እያስፈራሯት በመሆኑ ሕዝብ ይፋረደኝ ብላ ሚድያ ላይ ወጥታለች ?
▶️ እግዚአብሔር አምላክ የተጎጂዋን ቤተሰቦች እንባ እንዲያብስና ወንጀለኛውንና ተባባሪዎቹን እንዲፈርድባቸው እንማጸነዋለን! በየትኛውም ነገር ከተጎጂዎቹ ጋር መቆም የምንችል ሰዎች አብረናቸው እንቁም! ?
♦️ እግዚአብሔር የሕጻን ሔቨንን ነፍስ በመንግሥተ-ሰማይ ያኑርልን!
በዚህ ስፍራ ላይ እስራኤላውያን ለሴዎን ንጉስ ከጉድጓድ ውሃ እንደማይጠጡ መልእክት እንደላኩለት እናነባለን። በዚህ ስፍራ ላይ አለመጠጣታቸው የተገለጸው በዘጽ 15:24 ላይ ያለው "נשתה/ናሽታህ" የሚለው ቃል ተጠቅሶ ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለውን ቃል እንደ prefix ገብቶ ነው። ስለዚህ እንደማይጠጡ ለማመልከት እንጠጣለን ከሚለው ቃል ፊት ለፊት ያ ቃል እንደ prefix ገብቷል። ይህ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ሲገባ ተቃራኒነትን፥ ያ ነገር አለመሆኑን እንደሚገልጽ የሚያረጋግጥ ሌላ ማስረጃ ነው።
♦️ በዕን 1:12 ላይ አለመሞታቸውን ለማመልከት ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "נמות/ናሙት" የሚለው ሲሆን ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለው ቃል እንደ prefix ገብቷል። ስለዚህ ቃሉ በትክክል "አንሞትም" ወይም "we will not die" ተብሎ ነው መተርጎም ያለበት። እንጂ በፍጹም "አትሞትም" ተብሎ አይተረጎምም።
ይህንንም ሀቅ ዕውቅ የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች አረጋግጠውታል፦
"12 Art thou not from everlasting, O LORD my God, mine Holy One? #we_shall_not_die. O LORD, thou hast ordained them for judgment; and, O mighty God, thou hast established them for correction." (Hab 1:12 KJV)
"Art not thou from everlasting, O Jehovah my God, my Holy One? #we_shall_not_die. O Jehovah, thou hast ordained him for judgment; and thou, O Rock, hast established him for correction" (Hab 1:12 ASV)
"Art thou not from everlasting, Jehovah my God, my Holy One? #We_shall_not_die. Jehovah, thou hast ordained him for judgment; and thou, O Rock, hast appointed him for correction" (Hab 1:12 DET)
"Wast thou not from the beginning, O Lord my God, my holy one, and #we_shall_not_die? Lord, thou hast appointed him for judgment: and made him strong for correction" (Hab 1:12 DRB)
"Art thou not from everlasting, O LORD my God, my Holy One? #We_shall_not_die. O LORD, thou hast ordained them for judgment; and O mighty God, thou hast established them for correction" (Hab 1:12 NWB)
"Aren`t you from everlasting, Yahweh my God, my Holy One? #We_will_not_die. Yahweh, you have appointed him for judgment. You, Rock, have established him to punish" (Hab 1:12 WEB)
"Art not Thou of old, O Jehovah, my God, my Holy One? #We_do_not_die, O Jehovah, For judgment Thou hast appointed it, And, O Rock, for reproof Thou hast founded it" (Hab 1:12 YLT)
▶️ ከኢንግሊዘኛ ትርጉሞች ባሻገር የአዲሱ መደበኛ ትርጉምም እንዲሁ "አንሞትም" በማለት ነው የተረጎመው፦
"እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን? የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ #እኛ_አንሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርዱ ሾመሃቸዋል፤ ዐለት ሆይ፤ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው" (ዕንባቆም 1:12 አ.መ.ት)
ስለዚህ የዕን 1:12 ትክክለኛ ትርጉም "አንሞትም" የሚለው እንጂ ለዕብራይስጥ እንግዳ የሆነው አብዱል የተረጎመበት መንገድና የሰጠው ትርጉም አይደለም።
♦️ አብዱሉ ዕን 1:12ን የተተረጎመበት መንገድ ትክክል የሚሆነው የዕብራይስጡ ቃል "תמות/ታሙት" የሚለው ቢሆን ኖሮ ነበር። "תמות/ታሙት" የሚለው አንድ ነጠላ አካልን የሚያመለክት ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ትሞታለህ" ማለት ነው። በዚሁ ቃል ተንተርሶ "አትሞትም" ማለት ካስፈለገ ደግሞ ከፊት ለፊቱ "לא/ሎ" የሚለው ቃል prefix ሆኖ ይገባል። ያኔ "አትሞትም" የሚል ትርጉም ይኖረዋል
ለምሳሌ፦
"እግዚአብሔርም። ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አትፍራ፤ #አትሞትም አለው" (መሳ 6:23)
ויאמר לו יהוה שלום לך אל־תירא #לא_תמות (Jud 6:23)
በዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሔር ጌዴኦንን እንደማይሞት ነግሮት ሲያረጋጋው እንመለከታለን። ጌዴኦን አንድ ነጠላ አካል ሲሆን እሱ እንደማይሞት ለማመልከት "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ገብቶ ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "תמות/ታሙት" የሚለው ቃል ነው። አብዱሉ ዕን 1:12 የተረጎመበት መንገድ ትክክል የሚሆነው ዕን 1:12 ልክ እንደዚህ ክፍል ይህን ቃል ቢጠቀም ነበር። ቅሉ ግን አልተጠቀመውም።
ሌላ ምሳሌ፦
"ንጉሡም ሳሚን። #አትሞትም አለው። ንጉሡም ማለለት" (2ሳሙ 19:23)
ויאמר המלך אל־שמעי #לא_תמות וישבע לו המלך (2Sam 19:23)
በዚህ ቦታ ላይ ንጉስ ዳዊት ሳሚን እንደማይሞት ሲነግረው እንመለከታለን። ሳሚ አንድ ነጠላ አካል ሲሆን እሱ እንደማይሞት ለማመልከት "לא/ሎ" የሚለው ቃል ከፊት ለፊቱ እንደ prefix ገብቶ ጥቅም ላይ የዋለው ቃል "תמות/ታሙት" የሚለው ቃል ነው። አብዱሉ ዕን 1:12 የተረጎመበት አተረጓጎም ትክክል የሚሆነው ዕን 1:12 ይህን ቃል ይህ ክፍል እንደተጠቀመው ቢጠቀመው ነበር። ነገር ግን አልተጠቀመውም።
ዕን 1:12 ላይ "תמות/ታሙት" የሚለው ይህ ቃል ከፊቱ "לא/ሎ" የሚለው prefix ኖሮ ጥቅም ላይ ቢውል ኖሮ ክፍሉ ልክ ከላይ እንዳየናቸው ሌሎች ክፍሎች "አትሞትም" ተብሎ ይተረጎም ነበር። ዕን 1:12 ግን በ"תמות/ታሙት" ፋንታ "נמות/ናሙት" የሚለውን ቃል ስለሆነ የሚጠቀመው ትክክለኛው ሰዋሰዋዊ አተረጓጎም "አንሞትም" የሚለው ነው።
? በዕን 1:12 ላይ "נמות/ናሙት" የሚለው የዕብራይስጥ ቃል በብሉይ ኪዳን ውስጥ አንድም ጊዜ የነጠላ አካልን ሞት ወይም አለመሞት አመልክቶ አያውቅም። ሁሌም ቢሆን ጥቅም ላይ የዋለው ከአንድ በላይ የሆኑ አካላትን መሞት ወይም አለመሞት ለማመልከት ነው። ለዚህም ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል
አብዱሉ ግን እሟገትበታለሁ ብሎ የተነሳውን ቋንቋ ስለማያውቅ እንዲህ አይነቱን የጀማሪ ስህተት ሰርቷል!
✍️ ተዋረድ ያለው አብዱል ዕብራይስጥ ይጠቅሳል!
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 month ago
Last updated 1 month ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 2 days, 5 hours ago