ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ሼሁ ቁርአን ላይ በተፃፈው መሠረት እውነቱን ነው የተናገረው
ቁርአን ከ20 በሚበልጡ አንቀፆቹ በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ ተዋጉ ነው የሚለው
አላህ ከምእመናን ነፍሶቻቸውንና #ገንዘቦቻቸውን_ገነት_ለእነሱ_ብቻ ያላቸው በመሆን ገዛቸው ሱራ 9:111
በቁርአን ሶላትና ግዴታ ምፅዋት ጂዚያ ወይም ግብር እኩል አብሮ ነው የሚሄዱት ሶላት ሚሰግድ ከሆነ ዘካት ግዴታ ምፅዋት መክፈል አለበት
እስልምናን የማይቀበል ሶላት የማይሰግድ ከሆነ ደግሞ ጂዚያ ግብር መክፈል አለበት
ከሀዲዎች ወይም ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች በተገኙበት ቦታ ሁሉ መገደል አለባቸው ነገር ግን ገንዘብ ከከፈሉ ተውዋቸው ነው የሚለው ሱራ 9:5 😁
ከኡስታዝ ዮሱፍ
tiktok.com/@ekklesia90
ተቀላቀሉን ቤተሰብ
ሙስሊሞች የገሀነብ ናቸው 😢
በመጀመሪያ እስልምና ክርስትናን በመቃወም የተነሳ ነው ከዚ በፊትም የሰይጣን ትምህርት እንደሆነ በእስልምናው አስተምህሮ ውስጥ አይተናል መልሼ ፎርዋርድም አረግላችኃለሁ
ዛሬ ግን ምናየው እስልምና መጨረሻው ሲኦል እሳት እንደሆነ ነው
እስልምናው ከዚህ አለም በኃላ ወዳኛው አለም ላይ ቅርቢቱ ይለዋል ቁርአኑ የቅርቢቱ ሕይወት እሄን አለም ከዚ አለም በኃላ ያለውን ማግባት መጋባት የለም ሚለውን ጥሶ ወንድ ከሴትጋ ግንኙነት ያረጋል የወይን ጠጅም ይጠጣል ሚል እምነት አለው በቪዲኦም ማቅረብ ይቻላል የማይካድ እውነታ ስለሆነ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ
መጽሀፍ ቅዱስ ለአውሬው ሚሰግዱትን አማኝ ያልሆኑትን በመጨረሻ ቅጣት አላቸው እርሱም በእሳት በሲኦል መቀጣል ነው የንስሐ እድሜአቸውን ስላልተጠቀሙ እና በእሳት መቃጠሉን ባይብል ምን ይለዋል የወይን ጠጅ ይጠጣሉ ከሞት በኃላ ስላለው ፍርዱን አማኝ ያልሆኑትን የወይን ጠጅ ይጠጣሉ ይላል እሄም የወይን ጠጅ በእሳት መቃጠልና የእግዚአብሔር ቁጣ መሆኑን ሚገልጽ ነው እሄው
ራእይ 14
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹⁰ እርሱ ደግሞ በቍጣው ጽዋ ሳይቀላቅል ከተዘጋጀው ከእግዚአብሔር ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል፥ በቅዱሳንም መላእክትና በበጉ ፊት በእሳትና በዲን ይሳቀያል።
ይህ የወይን ጠጅ ቅጣትና በእሳት ዲን መቃጠል ነው። እንዳየነው
የእስልምናው ደሞ አማኞቾ በገነት የወይን ጠጅ ይጠጣሉ ይላል
ከሚመነጭ ወይን ጠጅ በያዘ ብርጭቆ በእነርሱ ላይ ይዞርባቸዋል፡፡ የተሰላፊዎቹ ምዕራፍ 45 ላይ
ስለዚህ ምን ይመስላችኃል የወይን ጠጅ ይጠጣሉ ቁጣውን በእሳት ዲን እየተቃጠሉ ሚለውን የባይብል ሀሳብን
እስልምናው አማኞች መስሊሞች የወይን ጠጅ ይጠጣሉ ማለቱ የእሳት ዲኑን እንደሆነ አያመላክትም መጽሐፍ ቅዱስ የወይን ጠጅ ቁጣውን ይጠጣሉ የእሳት ዲንም ይቃጠላሉ ብሎ ያነሳውን ቁርአን ደሞ አማኞቼ የወይን ጠጅ ይጠጣሉ ማለቱ አላህ የገሀነብ መሆኑን እና እናንተንም ይዟችሁ ለማስገባት እንደሆነስ አያመላክትምን
ለሙስሊማኑ እሄን ቻሌጅ ከእራሳችሁ ጋር ተሟገቱ አስተውሉ ራዕይ መጽሀፍ ደሞ ትንቢቱ ሚለው ተፈጻሚ መሆኑን አትርሱ ከዛሬ 2000 አመት በፊት ስለ 666 ተናግሮና ተንብዮ በዚህ ዘመን በኛም ሰይጣን ምልክቱን 666 ብሎ በአይኖቻችን ያየነውን የሰማነውን አስቀድሞ የተናገረ ትልቅ መጽሀፍ ነው
እና በጀነት የወይን ጠጅ እሳትና ዲን የፈጣሪ ቁጣ ነው
አላህ ደሞ የወይን ጠጅ አለ እያለ ነው ስለዚህ አላህ የሲኦል የገሀነብ ሆኖ ጀነት በሚል ማታለያ ገሀነብ ሊያስገባችሁ መሆኑን ትንሽስ አልተገለጠላችሁም ቻሌጁን ተቀላቀሉ ሙስሊሞች የሕይወት ጉዳይ ነው ለምቶዷቸው ሙስሊሞች ሼር አርጉላቸው መጽሀፉ ባታምኑበትም ቃሉ ተፈጻሚ እውነታ መሆኑንም ከግምት አስገቡ በጀነት የወይን ጠጅ የለም
እግዚአብሔር በአንድም በሌላ ይናገራል አስተውሉ 🙏
ምሳሌ፡- “ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው” አለ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ምሪት ይሰጣል፡፡ ውሳኔን ያጠራል፡፡ የምንኖርበት ሕይወት ውሳኔን የሚጠይቅ ነው፡፡ አስተማማኝ ውሳኔ እንደወሰንን ለማወቅ በጉዳዩ መጸለይና የልባችንን ሰላም ማዳመጥ የእግዚአብሔር ሰዎችን (አገልጋዮችን) ምክር መጠየቅ አስፈላጊ ሲሆን የመጀመሪያው ግን ቃሉ ይደግፈኛል ወይ ማለት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ሲል ሦስት ነገሮችን እንደሚገልጽ በመጠቆም ብቻ የፈጸምን ሲሆን እነዚህን ሦስት ነገሮች ቀጥሎ እንዘረዝራለን፡፡
1. አካላዊ ቃልይህ በግሪኩ ሎጎስ /Logos/ የሚለው ሲሆን እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ዮሐንስ በወንጌሉ፡- “በመጀመሪያ ቃል ነበረ÷ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ÷ ቃልም እግዚአብሔር ነበር” (ዮሐ. 1፥1) የሚለው “በመጀመሪያ ሎጎስ ነበረ” ማለቱ ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ አካላዊ ቃል (ሎጎስ) ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ሎጎስ የሚለው ቃል አይገኝም፡፡ ለምን? ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ ገና በሥጋ አልተገለጠምና ነው፡፡ በአዲስ ኪዳን ግን “ቃልም ሥጋ ሆነ” ስለሚል ሎጎስ ተግባራዊ ሆኗል (ዮሐ. 1፥14)፡፡ ሌሎች ቃሎች ረቂቅ፣ ዝርው (ብትን) ናቸው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን መለኮታዊ አካል ያለው ስለሆነ አካላዊ ቃል ተብሏል፡፡ ይህ ብቻም አይደለም፣ ቃል የልብ መልእክተኛ ነው፣ ሥልጣንና አዛዥነትም ይገልጣል፡፡ እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ መልእክተኛ ሆኖ ወደ ዓለም መጥቷል፡፡ ሥልጣንና አዛዥነትም አለውና የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል፡፡
ታላቁ የዜማ አዋቂ መሪጌታ ፀሐይ ብርሃኑ፡- “ሎጎስ በጥንት የአረማውያንና የአይሁዳውያን ሥነ ጽሑፍ የታወቀ ነው፡፡ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ500 ዓመት የነበረው ሒራክሊቱስ የተባለው ፈላስፋ “ሎጎስ እግዚአብሔርን በመግለጥ ዓለምን የሚገዛና የሚያሳውቅ የበላይ ምክንያት በማለት ጽፎ ነበር፡፡ ከእርሱም በኋላ በይበልጥ ለሌሎች ያስተዋወቁት ስቶይክስ የተባሉ ከ335-263 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩ ፈላስፎች ናቸው፡፡ እነዚህ ፈላስፎች በአቴንስ ትምህርት ቤት አቋቁመው ስለ ሎጎስ ያስተምሩ ነበር፡፡ የዚህ ጽንሰ ሐሳብ ትርጉም ግሪክኛ በሚናገሩ አይሁዳውያን ዘንድ ይበልጥ እየተስፋፋ መሄዱ ጥበብ(Wisdom)ከሚለው ጋር የትርጉም ዝምድናን አገኘ፡፡ በእስክንድሪያ ከ30 ዓመተ ዓለም እስከ 50 ዓ.ም የነበረው ፋይሎ የተባለ አይሁዳዊ ፈላስፋ ግሪክኛ መጽሐፍ ቅዱስን በማዛመድ ሎጎስ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለም አንድ ያደረገ መለኮታዊ ኃይል ነው በማለት ይገልጻል፡፡ የፋይሎን መጻሕፍት ያነበቡ ግሪክኛ ተናጋሪ አይሁድም እግዚአብሔር ራሱን ለዓለም ይገልጥ የነበረው በቃል አማካይነት ነው፡፡ ያህዌ ለአብርሃም፣ ለአጋር፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ፣ ለሙሴ በቊጥቋጦ ራሱን የገለጠላቸው በቃል አማካይነት ነው… በማለት ይተርካሉ፡፡ ስለዚህ ወንጌላዊው ዮሐንስ በግሪክኛ ወንጌሉን ሲጽፍ አይሁዳውያንና አረማውያን በለመዱት “ሎጎስ” የሚለውን ቃል በመጥቀስ፡- “ለአባቶችና ለነቢያት ሥጋን ከመልበሱ በፊት የተገለጠው የያህዌ ቃል ዛሬ በሥጋ የተገለጠው ክርስቶስ እንጂ ሌላ አይደለም በማለት በመጀመሪያው ምዕራፍና ቊጥር ይገልጻል፡፡” ብለዋል /ቃለ ምዕዳን 1 ፡ 1993 ዓ.ም ቦስተን/፡፡ አዎ መጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሲል በመጀመሪያ የሚገልጸው አካላዊ ቃል የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ነው፡፡
2. የተጻፈው ቃል (መጽሐፍ ቅዱስ)በግሪኩ ግራፌ /Graphe/ የሚለው ነው (ዮሐ. 5፥39-40)፡፡ በጥንት ዘመን እግዚአብሔር ቃሉን በሕልም፣ በራእይ፣ በሜዳ ይሰጥ ነበር፡፡ አሁን ግን በተጻፈው ቃሉ በኩል ይናገረናል፡፡ ብዙዎች በክርስትናቸው ለማደግ ተአምር ይፈልጋሉ፡፡ ነገር ግን በክርስትና ለማደግ ከቃሉ የበለጠ ተአምር የለም (1ጴጥ. 2፥1)፡፡ ነቢዩ፡- “በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጽኑ” (መዝ. 32(33፥6) ይላል፡፡ ታዲያ ሰማይን ያፀና ቃል የእኛን ሕይወት ማቆም እንዴት ይሳነዋል?
3. መገለጥበግሪኩ ሪህማ (Rhema) የሚለው ነው፡፡ ለአንድ ሰው ለተለየ ጉዳይ የሚነገር የእግዚአብሔር ድምፅ ወይም የመንፈስ ቅዱስ መልእክት ነው፡፡ ይህ ወቅታዊ መገለጥ በዕብራይስጥ ዳቫር /Davar/ ይሉታል፡፡ በግሪኩ ግን ሪማ-ሬማ ይለዋል፡፡ ይህ ድምፅ ተአምራዊ ስለሆነ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም አጋንንትም ተአምራት ያደርጋሉና፡፡ ይህ ወቅታዊ መገለጥ እግዚአብሔር ሲሰጠን የምንቀበለው እንጂ አንቴናችንን ገትረን የምንጠባበቀው አይደለም፡፡ ይህን ወቅታዊ መገለጥ እንደ ዶክትሪን ይዘው ቤተ ክርስቲያን የሚመሠርቱ፣ በሐሰተኛ ተስፋ ሕዝብን የሚያስቱ ወገኖች ብዙ ናቸው፡፡
መቼም እግዚአብሔር ሲናገር አትናገር አንልም፡፡ ነገር ግን ድምፁን መለየት ግድ ይላል (ዮሐ. 10፥4)፡፡ ይህንን ወቅታዊ መገለጥ ለመቀበል፡- አንደኛ፡- የመጣው መገለጥ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ይስማማል ወይ? ማለት ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም መገለጡ የመንፈስ ቅዱስ ከሆነ መንፈስ ቅዱስ የሚናገረው በቃሉ ነው (ዮሐ. 14፥26)፡፡ እግዚአብሔር፣ ከእግዚአብሔር ቃል ውጪ አይናገርምና መገለጡ የቃሉ ድጋፍ አለው ወይ? ብሎ መመርመር ይገባል፡፡
ሁለተኛ፡- ተቀባዩ ወገን መገለጡን ከተጻፈው ቃል በላይ ያከብራል ወይ? ማለት ያስፈልጋል፡፡ እንድናውቀው የተፈቀደልን የመጨረሻው ነጥብ በቅዱስ ቃሉ ሠፍሯል፡፡ የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ፡- “ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና ጐዳና ለአባቶቻችን ለነቢያት ተናግሮ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን” (ዕብ. 1፥1-2) ብሏል፡፡ ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ የመጨረሻው መልእክተኛ በመሆኑ በእርሱ ከተነገረው የሚበልጥ የሚመስል መልእክት ማንም ይዞ ቢመጣ ከእግዚአብሔር የተላከ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ሲል
የቃሉ ምሳሌዎች“መጽሐፍ ቅዱስ የሚተረጎመው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው” ይባላል፡፡ የእግዚአብሔር ቃልም ስለ እግዚአብሔር ቃል ይናገራል፡፡ ከዚህም ውስጥ ለቃሉ የተሰጡ ምሳሌዎችን እናያለን፡-
– የወንዝ ዳር፡- ያለመልማልና (መዝ. 1፥2-3)፤
– የማር ወለላ፡- ያጣፍጣልና (መዝ.118(119) ፥103፤ሕዝ. 3፥2-3)፤
– ጥሩ ውኃ፡- ያረካልና (መዝ.22(23)፥2)
– መዶሻ፡- ያደቃልና (ኤር.23፥29)
– እሳት፡ ያጠራልና (ኤር.23፥29)
– ብርሃን፡- ያሳውቃልና (መዝ.118(119፥105)፤
– እንጀራ፡- ያኖራልና (ማቴ. 4፥4፤ ዘዳ. 8፥3)፤
– ራጅ፡- ውስጥን ያሳያልና (ዕብ. 4፥12)
– ዘር፡- ያፈራልና (ሉቃ. 8፥4-15)፤
– ወተት፡- ያሳድጋልና (1ኛ ጴጥ. 2፥1) ፤
– ሰይፍ፡- ትጥቅ ነውና (ኤፌ. 6፥17) …፡፡
የእግዚአብሔር ቃል በብዙ ምሳሌዎች የተገለጠ መሆኑን አይተናል፡፡ ከምሳሌዎቹ ውስጥ አንዱን እንደገና ብናይ፡-
የእግር መብራት፡- “ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው” (መዝ. 118(119)፥105)፡፡ በመካከለኛው ምሥራቅ ከቀኑ ሐሩር የተነሣ በሌሊት መጓዝ የተለመደ ነው፡፡ ከጨለማውም ጋር ሽፍቶችና ዘራፊዎች አሳሳቢዎች ስለሆኑ በኅብረት መጓዝ የተለመደ ነው፡፡ ጨለማው ጥልቅ መልክአ ምድሩም ገደላማ በመሆኑ የሚረግጡትን በትክክል ለማየት ይቸገራሉ፡፡ ሜዳ የረገጡ መስሎአቸው ገደል ሊገቡ ይችላሉ፡፡ የሚረግጡትን እርምጃ በትክክል ለማየት እግራቸው ላይ መብራት አስረው ይሄዱ ነበር፡፡ ይህ የሚረግጡትን በትክክል ያሳያል፡፡ ነቢዩ በዚህ
በዐይነ ሥጋ የማይታይና የማይመረመር፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል፣ የሰው ህሊና አስሶ የማይደርስበት፣ ሁሉን የፈጠረ፣ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው፣ ለዘላለም የሚኖር አምላክ መኖሩን እናምናለን፡፡ እርሱም በአካል፣ በስም፣ በግብር ሦስት፤ በባሕርይ፣ በመለኮት፣ በሕልውና፣ በፈቃድ አንድ ነው፡፡ ከዚህም ባሻገር በመስጠት በመንሳት፣ በመፍጠር በማሳለፍ፣ በመግዛትና በአኗኗር አንድ ነው፡፡
“ሥላሴ” የሚለው ቃል “ሠለሰ” ሦስት አደረገ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ቅድስት ሥላሴ ስንል ለሥላሴ ቅድስት ብለን እንቀጽላለን፡፡ ቅድስት ሥላሴ ማለት ልዩ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ይህም ሦስት ሲሆኑ አንድ፣ አንድ ሲሆን ሦስት ስለሚሆኑ ልዩ ሦስትነት ተብሏል፡፡ ሥላሴ የሚለውን ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ያለና የሚኖረውን አምላክ ለመግለጽ የተጠቀመው የአንጾኪያው ቴዎፍሎስ በ169ዓ.ም ነው፡፡ኋላም በኒቅያ ጉባዔ 318ቱ ሊቃውንት አጽንተውታል፡፡ እነዚህ ሊቃውንት በቅዱሳት መጻሕፍት የተመሰከረውን የእግዚአብሔርን ፍጹም አንድነትና ልዩ ሦስትነት ለእኛ በሚረዳ ቋንቋ ገለጡት እንጂ አዲስ ትምህርት አላመጡም፡፡ ይልቁንም ነገረ ሥላሴን ሳይረዱ በሥላሴ መካከል የክብርና የተቀድሞ ልዩነት ያለ አስመስለው በክህደት ትምህርት የተነሱ መናፍቃንን ክህደት ለማስረዳት፣ የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያንን የቀናች ሃይማኖት ለመግለጥ ምሥጢረ ሥላሴን አብራርተው አስተምረዋል፡፡
ምስጢረ ሥላሴ (Mystery of the Trinity) ማለት የአንድነት የሦስትነት ምስጢር ማለት ነው፡፡ ምሥጢር መባሉም በእምነት የተገለጠ፣ ያለ እምነትም የማይመረመር ስለሆነ ነው፡፡ ይኸውም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ሲሆኑ በባሕርይ በሕልውና፣ በመለኮት ደግሞ አንድ ናቸው፡፡ እንደዚህ ባለ ድንቅ ነገር አንድ ሲሆኑ ሦስት፣ ሦስት ሲሆኑ አንድ ይባላሉና፣ ይህም ልዩ ሦስትነት ረቂቅ እና በሰው አእምሮ የማይመረመር ስለሆነ ምስጢር ይባላል፡፡ ስለዚህም በአንድ አምላክ፣ በሦስቱ አካላት እናምናለን፡፡
የክርስትና ዶግማ (መሠረተ እምነት) በምስጢረ ሥላሴ ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ምስጢረ ሥላሴ የእምነታችን ዋነኛው ምሰሶ ነው፡፡ በመዳን ትምህርት ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው ምስጢረ ሥላሴ ነው፡፡ ለመዳናችንም መሠረት ነው፡፡ ክርስቲያኖች ሁላችን የተጠመቅነው በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ነው (ማቴ 28፡19)፡፡ የሥራችን ሁሉ መጀመሪያም አድርገን በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ስንልም በሥላሴ ማመናችንን እየመሰከርን ነው፡፡ በሥራችን መጨረሻም “ምስጋና ይሁን አንድ አምላክ ለሚሆን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን” ብለን ሥራችንን በሥላሴ ስም ጀምረን በሥላሴ ስም እንፈጽማለን፡፡ሆኖም ግን ምስጢረ ሥላሴ ለሰው አእምሮ እጅግ የረቀቀ ስለሆነ የሰው አእምሮ ሊያውቅ የሚችለው እግዚአብሔር በገለጠለት መጠን ብቻ ነው፡፡
አበው ሥለ ሥላሴ እንዲህ አሉ
“እግዚአብሔር አንድ ነው፤ የማትከፈል የማትፋለስ መንግስትም አንዲት ናት፤ ከሥላሴ ምንም ምን ፍጡር ደኃራዊ የለም፤ በእነርሱ ዘንድ አንዱ ለአንዱ መገዛት የለም፡፡ አብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፣ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ ሥሉስ ቅዱስ በዘመኑ በቀኑ ሁሉ በግብርም በስምም ሳይለወጥ ሳይፋለስ ጸንቶ ያለ ነው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘሠለስቱ ምዕት ምዕራፍ 19፡5-6)
“ወንድሞቻችን እኛስ እንዲህ እናምናለን፤ ያልተወለደ እግዚአብሔር አብ በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ የተወለደ እግዚአብሔር ወልድ ዋሕድ ኢየሱስ ክርስቶስም በተለየ አካሉ አንድ ነው፤ በወደደው የሚያድር የአብ የወልድ እስትንፋስ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በተለየ አካሉ አንድ ነው እንላለን፡፡…አብ አምላክ ነው፤ ወልድም አምላክ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም አምላክ ነው፡፡ ግን ሦስት አማልክት አይባሉም አንድ አምላክ እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ምዕራፍ 25፡2-4)
“ከሦስቱ ፍጡር የለም ፍጡራን አይደሉምና፡፡ ከዕውቀት ከሃይማኖት የተለዩ መናፍቃን ከቅድስት ሥላሴ መለኮት መከፈልን በአካላት መጠቅለልን ሊያመጡ አይድፈሩ ሦስት አማልክት ብለን አንሰግድም አንድ አምላክ ብለን እንሰግዳለን እንጂ፡፡ በስም ሦስት ናቸው እንላለን፤ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ አንድ ባህርይ አንድ ሥልጣን ናቸው፤ በአንድ መለኮት በባህርይ አንድነት የጸኑ ሦስት አካላት ሲሆኑ ከሦስቱ አንዱ የሚበልጥ አንዱ የሚያንስ አይደለም፤ በማይመረመር በአንድ ክብር የተካከሉ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ምዕራፍ 60፡6-7)
“ወልድ ሳይኖር አብ ከአዝማን በዘመን ፈጽሞ አልነበረም፤ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ በዘመን አልነበረም፤ ሳይለወጡ ሳይለዋወጡ በገጽ በመልክ ፍጹማን በሚሆኑ በሦስት አካላት ጥንት ሳይኖራቸው በዘመን ሁሉ የነበሩ፤ ፍጻሜ ሳይኖራቸው የሚኖሩ ናቸው እንጂ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቴዎፍሎስ ምዕራፍ 68፡5)
“አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በአካል ሦስት በባህርይ አንድ ነው ብሎ ማመን ይህ ነው፤ የማይመረመር በቅድምና የነበረ አብ በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤…የማይመረመር በቅድምና ነበረ ወልድም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤….የማይመረመር በቅድምና የነበረ መንፈስ ቅዱስም በገጹ በአካሉ ፍጹም ነው፤ ሐዋርያት ያስተማሩዋት ቅድስት ቤተክርስቲያን የተቀበለቻቸው ቅዱሳት መጻሕፍት እንደተናገሩ፡፡” (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ቄርሎስ ምዕራፍ 70፡14-17)
“እኛ ግን በሥላሴ ዘንድ በማዕረግ ማነሥና መብለጥ የለም በመለኮት አንድ ወገን ናቸው እንላለን” (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ተግሳጽ ዘሰባልዮስ)
የቁርአን ተቃርኖዎች
ሙስሊም ወገኖች ከክርስቲያኖች ጋር ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ሲወያዩ ብዙ ጊዜ ግጭቶች ናቸው የሚሏቸውን ነጥቦች በማንሳት መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል እንዳልሆነ ለማስረዳት ይሞክራሉ፡፡ ነገርግን ይህ አይነቱ አካሄድ አንዳችን የሌላችንን ኃይማኖት ለመረዳት እና ፍሬያማ የሆነ ውይይት ለማድረግ ተመራጭ መንገድ አይደለም፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስንና የቁርአንን እውነተኛነት ለመመርመር ከዚህ ይልቅ ጠንካራ እና ጠቃሚ የሆኑ መንገዶች አሉ፡፡ ለምሳሌ የተፈፀሙ ትንቢቶች፤ የቀዳማውያን ጽሑፎች ኃቀኝነት፤ የመልዕክቶቻቸው ወጥነት፤ ስለ ደህንነት መንገድ የሚያስተምሩ ትምህርት፤ ስለ እግዚአብሔር ማንነትና ባህርያት የሚሰጡት ገለፃ ወዘተ. ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ አንድ ሰው ቅዱሳት መጽሐፍትን ማጥናት ያለበት ትክክለኛ መልዕክታቸውን ከመረዳት አንፃር እንጂ ተቃርኖዎችን ከመፈለግ አንፃር መሆን እንደማይገባው አጥብቀን እናምናለን፡፡ እኛ ቁርአንን እንደ እግዚአብሔር ቃል የማንቀበለው በዋናነት በዚህ ገጽ እና በሌሎች ገጾች ላይ በተዘረዘሩ ተቃርኖዎች ምክንያት አይደለም፡፡ ነገር ግን በእስልምና ላይ ከነዚህ የተሻሉ ጠንካራና መሰረታዊ የሆኑ ጥያቄዎች አሉን፡፡ በእኛና በሙስሊሞች መካከል የሚደረጉ ውይይቶችም በነዚህ ርእሶች ዙርያ እንዲያጠነጥኑ እንፈልጋለን፡፡
እነዚህን ተቃርኖዎች ለአንባቢዎች ስናቀርብ ዓላማችን ሙስሊሞች መጽሐፍ ቅዱስን የሚመረምሩበትን ተመሳሳይ መንገድ ቁርአንን ለመመርመር ቢጠቀሙ ይህ አካሄድ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ቁርአንን ውድቅ እንደሚያደርግ እንዲረዱ እና ሁለቱንም መጽሐፍት በተመሳሳይ ሚዛን መመዘን እንዲጀምሩ ለመርዳት ነው፡፡
በሎጥ ዘመን የነበሩት ህዝቦች ለሎጥ የመለሱለት መልስ የትኛውን ነው?
27:55-56 “«እናንተ ከሴቶች አልፋችሁ ወንዶችን ለመከጀል ትመጣላችሁን በእውነቱ እናንተ የምትሳሳቱ ሕዝቦች ናቸሁ፡፡» የሕዝቦቹም መልስ የሉጥን ቤተሰቦች «ከከተማችሁ አውጡ፡፡እነርሱ የሚጥራሩ ሰዎች ናቸውና» ማለት እንጅ ሌላ አልነበረም፡፡”
29:29 “እናንተ በእርግጥ ወንዶችን ትመጣላችሁን? መንገድን ትቆርጣላችሁን? በሸንጓችሁም የሚነወርን ነገር ትሠራላችሁን?(አላቸው)፤ የሕዝቦቹም መልስ ከውነተኞቹ እንደ ኾንክ የአላህን ቅጣት አምጣብን ማለት እንጂ ሌላ አልነበረም።”
26:165-167 “«ከዓለማት ሰዎች ወንዶችን ትመጣላችሁን? «ከሚስቶቻችሁም ጌታችሁ ለናንተ የፈጠረላችሁን ትተዋላችሁን በእውነቱ እናንተ ወሰን አላፊዎች ሕዝቦች ናችሁ፡፡» (እነርሱም) አሉ «ሉጥ ሆይ! ባትከለከል በእርግጥ (ከአገር) ከሚወጡት ትኾናለህ፡፡»”
የነዚህ ሶስቱ ጥቅሶች አውድ ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን ተመለሱ የተባሉት መልሶች ግን በጣም የተራራቁና እርስ በርሳቸው የማይስማሙ ናቸው፡፡ የመጀመርያው ጥቅስ ሰዎቹ የተናገሩት እንዲህ ብቻ ነው ሲል ሁለተኛው ጥቅስ ደግሞ ከመጀመርያው መልስ የተለየ ነገር እንደ ተናገሩና ከዝያ ውጪ ሌላ ምንም ነገር እንዳልተናገሩ ይነግረናል፡፡ ሶስተኛውንም ጥቅስ ስንመለከት ከሁለቱ የተለየ ንግግር ያቀርብልናል፡፡ ታድያ የትኛውን እንቀበል?
አላህ በመጥፎ ስራ ያዛል ወይንስ አያዝም?
ያዛል- 17:16 “ከተማንም ለማጥፋት በፈለግን ጊዜ፣ ባለጸጋዎችዋን እናዛለን፤ በውስጧም ያምጣሉ፤ በርሷም ላይ ቃሉ (ቅጣቱ) ይፈጸምባታል፤ ማጥፋትንም እናጠፋታለን።”
አያዝም- 7:28 “መጥፎንም ስራ በሰሩ ጊዜ፦ በርሷላይ አባቶቻችንን አገኘን፣ አላህም በርሷ አዞናል ይላሉ፤ አላህ በመጥፎ ነገር አያዝም፤ በአላህ ላይ የማታውቁትን ትናገራላችሁን? በላቸው።”
አመጽ መጥፎ ስራ እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ የመጀመርያው ጥቅስ ጥፋት የተወሰነባት ከተማ ቅጣቱ እንዲፈጸምባት በውስጧ ያሉ ባለጠጎች እንዲያምጹ አላህ እንደሚያዛቸው ሲናገር ሁለተኛው ጥቅስ ግን አላህ በመጥፎ ስራ እንደማያዝ ይናገራል፡፡
ዓድ በተባለችው ከተማ ላይ የቅጣት ነፋስ ለስንት ቀን ነው የነፈሰው?
ከአንድ ቀን በላይ- 69:6-7 “ዓድማ በኀይል በምትንሻሻ ብርቱ ነፋስ ተጠፉ። ተከታታይ በሆኑ ሰባት ሌሊቶችና ስምንት መዓልቶች ዉስጥ በነሱ ላይ ለቀቃት ሕዝቹንም በዉስጧ የተጣሉ ሆነዉ ልክ ክፍት የሆኑ የዘንባባ ግንዶች መስለው ታያቸዋለህ።”
41:15-16 “ዓድም በምድር ላይ ያለ አግባብ ኮሩ፤ ከኛ ይበልጥ በኀይል ብርቱማ ነው? አሉም፤ ያ የፈጠራቸው አላህ እርሱ በኀይል ከነርሱ ይበልጥ የበረታ መሆኑን አያዩምን? በታምራታችንም ይክዱነበሩ። በቅርቢቱ ሕይወት የውርደትን ቅጣት ልናቀምሳቸውም፣ በነሱ ላይ የሚንሻሻን ብርቱ ነፋስ፣ መናጢዎች በሆኑ ቀናት ውስጥ ላክንባቸው፤ የመጨረሻይቱም (ዓለም) ስቃይ በጣም አዋራጅ ነው፤ እነርሱም አይረዱም።”
ለአንድ ቀን- 54:18-19 “ዓድ አስተባበለች ቅጣቴና ማስጠንቀቂያዎቼም እንዴት ነበሩ! እኛ በነርሱ ላይ ዘወትር መናጢ በኾነ ቀን በኀይል የምትንሻሻ ነፋስን ላክንባቸው::” “For We sent against them a furious wind, on a Day of bitter ill-luck”
በመጀመርያዎቹ ጥቅሶች መሰረት በከተማዋ ውስጥ በሚኖሩ ህዝቦች ላይ የአላህ ቅጣት የሆነችው ነፋስ የተላከችው ከአንድ ቀን በላይ ለሆነ ጊዜ እንደሆነ ሲናገር በሁለተኛው ጥቅስ መሰረት ግን ለአንድ ቀን (“ቀን” የሚለው ነጠላ መሆኑን ልብ ይሏል) እንደሆነ እናያለን፡፡ ታድያ የትኛው ነው ትክክል?
አንዱ የሌላውን ኃጢዓት ይሸከማል ወይንስ አይሸከምም?
አይሸከምም- 35:18 “ኀጢአትን ተሸካሚም (ነፍስ)፣ የሌላዋን ሸክም አትሸከምም፤ የተከበደችም (ነፍስ) ወደ ሸክሟ ብትጠራ (ተጠሪው) የቅርብ ዝምድና ባለቤት ቢሆንም እንኳ ከርሷ አንዳችን የሚሸከምላት አታገኝም። የምታስጠነቅቀው፣ እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሦላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፤ የተጥራራም ሰው፣ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው፤ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው።”
53:37-42 “በዚያም (የታዘዘውን) በፈጸመው በኢብራሂም ጽሁፎች ውስጥ ባለው አልተነገረምን?) (እርሱም ኃጢአት) ተሸካሚ ነፍስ የሌላይቱን ነፍስ ኃጢአት አትሸከምም። ለሰውም ሁሉ የሠራው እንጅ ሌላ የለውም። ሥራውም ሁሉ ወደፊት ይታያል። ከዚያም ሙሉውን ምንዳ ይመነዳዋል። መጨረሻውም ወደ ጌታህ ብቻ ነው፡፡”
ይሸከማል- 16:24-25 “ለነርሱም ጌታችሁ (በሙሐመድ ላይ) ምንን አወረደ? በተባሉ ጊዜ (እርሱ) የመጀመሪያዎቹ ሕዝቦች ተረቶች ነው ይላሉ። ይህንንም የሚሉት) በትንሣኤ ቀን ኃጢአቶቻቸውን በሙሉ ከነዚያም ያለ ዕውቀት ኾነው ከሚያጠሟቸው ሰዎች ኃጢአቶች ከፊሉን ሊሸከሙ ነው፤ ንቁ የሚሸከሙት ኀጢአት ምንኛ ከፋ”
ይቀጥላል
የእስልምና አስተምህሮ በክርስትና እይታዎች ሰላም ውድ የቻናል ቤተሰቦቼ እንደምን ሰነበታችሁ ከእግዚአብሔር አባታችን ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ዛሬ በአንዲት ርዕስ ተከስቻለሁ በጥሞና ተከታተሉኝ
በሙስሊሞች እምነት መሠረት ቁርኣን ከሰማይ የወረደ መገለጥ ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ ሐሰን ታጁ እንዲህ ይላሉ፡-
ቁርኣን በመላኢካው ጅብሪል አማካይነት ለነቢዩ ሙሐመድ ከአላህ የተወረደ መለኮታዊ መጽሐፍ መሆኑን ደግሞ ደጋግሞ ያውጃል፡፡
ለዚህ ማስረጃ ይሆናቸው ዘንድ ሱራ 11፡1፣ 27፡6፣ 17፡105፣ 26፡52 ላይ የሚገኙትን ጥቅሶች ከጠቀሱ በኋላ ተከታዩን ስሞታ ያቀርባሉ፡-
… የክርስቲያን ሚሽነሪዎችና ለእስልምና የመረረ ጥላቻ የቋጠሩ ምእራባዊ አጥኚዎች (ኦሪየንታሊስትስ) ‹‹ወንዝ የማያሻግሩ›› መናኛ ሰበቦችን እየፈጠሩ ቁርኣን መለኮታዊ መሆኑን ላለመቀበል ሲያንገራግሩ ይታያሉ፡፡ … የቁርኣንን መለኮታዊነት መቀበል ማለት የእምነታቸውን ግብአተ መሬት መቀበል ማለት ነው፡፡ … ባጭሩ የክርስትናን ሐሰትነት በይፋ ማወጅ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ መቼም ቢሆን የነቢዩ ሙሐመድን (ሰዐወ) ነብይነት፣ የቁርኣንን መለኮታዊነት አይቀበሉም፡፡
አንድ መጽሐፍ ከሰማይ የመጣ መገለጥ መሆኑን ስለተናገረ ብቻ አንቀበለውም፡፡ ከንግግር ያለፈ በማስረጃ የተደገፈ ማረጋገጫ ያስፈልገዋል፡፡ አቶ ሐሰንና መሰሎቻቸው የቁርኣንን መለኮታዊነት የሚያሳይ አሳማኝ ማስረጃ ማቅረብ ስለማይችሉ “መጽሐፋችንን ያልተቀበሉት ጥላቻ ስላለባቸው ነው” በማለት ሌላውን ወገን መውቀስና ማማረር ልማዳቸው ነው፡፡
እኛ ክርስቲያኖች ቁርኣንን እንደ ፈጣሪ ቃል የማንቀበልበት አብይ ምክንያት ከፈጣሪ ዘንድ ስለመሆኑ ማስረጃ ስለሌለው ነው፡፡ ቁርኣንን ለመቀበል የሚያበቃ ሰበብ ስለሌለ ላለመቀበል ምንም ሰበብ መስጠት አያስፈልገንም፡፡ ለመቀበል የሚያስችል ምክንያት አለመኖሩ በራሱ በቂ ምክንያት ነው፡፡ ነገር ግን ቁርኣን የፈጣሪ ቃል አለመሆኑንና የሰው እጅ ሥራ መሆኑን የሚያረጋግጡ ብዙ ውጪያዊና ውስጣዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል፡፡ ከውጪያዊ ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ በአሰባሰቡ ዙርያ የነበሩት አጠራጣሪ ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ከውስጣዊ ማስረጃዎች መካከል ደግሞ ምንጮቹ ይጠቀሳሉ፡፡
አድምጡት ትማሩበታላችሁ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana