AMU ግቢ ጉባኤ ቤተ-መፅሀፍት

Description
ይህ የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ main ካምፓስ ግቢ ጉባዔ የቤተ-መፃህፍት እና ጥያቄ ና መልስ እንዲሁም ወቅታዊ መረጃዎች የሚተላለፍበት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው

ማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት ካላቹ በዚህ @AMUgebigubae_bot ያድርሱን።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago

2 months, 2 weeks ago
**ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ …

ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ ።  _ መዝ 122፥1 _

ሰላም ተወዳጆች እንዴት ናችሁ
🎈🎈🎈ልዩ የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያው የክፍላት ምሽት🎈🎈🎈

⛪️ ቦታ ደ/ሎ/ቅ/ኪዳነ ምህረት ቤ/ክ
ምሸት: 12:00  (ሰዓት ይከበር)
👥 እህት ወንድሞቻችንን እንጋብዝ🥰

©️ ⚪️🔵 ሙያ እና ተራድኦ ክፍል⚪️🔵

2 months, 2 weeks ago
ውድ የአርባ ምንጭ ዋና ግቢ ጉባኤ …

ውድ የአርባ ምንጭ ዋና ግቢ ጉባኤ አባላት ተመርቃችሁ የወጣችሁ እና በትምህርት ላይ ያላችሁ መጻሕፍትን ከቤተ መጻሕፍት ወስዳችሁ ያልመለሳችሁ ወንድሞችና እህቶች ስማችሁ የተመዘገበ እንድሁም ያልተመዘገባችሁ በእምነት የወሰዳችሁት በእግዚአብሔር ስም እንድትመልሱ እናሳስባለን

⚠️ ማሳሰቢያ፦ አሁን ላይ ወደ ግቢ መምጣት ለማትችሉ ተመርቃችሁ የወጣችሁ አባለት መጽሐፉ አሁን ገቢያ ላይ ያለውን ዋጋ አይታችሁ እንድትልኩልን በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን።
በ1000285997357,,,,አብድ ጊዶ ,,,, ይላኩ

https://t.me/gebigubae_librarygroup

2 months, 2 weeks ago
2 months, 2 weeks ago
2 months, 3 weeks ago

+ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር +

☞ ተወዳጆች ሆይ ጊዜ ሳለልን ድኅነታችንን እንፈጽም፡፡ ጊዜ ሳለልን ለመብራታችን ዘይት የተባለ ምጽዋትን እንያዝ፡፡ ጊዜ ሳለልን መክሊታችንን ለማብዛት እንፍጨርጨር፡፡ በዚህ ዓለም ሳለን ይህን ለማከናወን ልል ዘሊል እና ሐኬተኞች ከኾንን በወዲያኛው ዓለም እልፍ ወትእልፊት ጊዜ ወዮ ብለን ብናለቅስ ብንጮህም እንኳን የሚረዳን የለምና፡፡ ያ ባለ አንድ መክሊት ሠራተኛ አንዲቷን መክሊት ሳይቀንስ ለጌታው ቢያስረክብም ከኩነኔ አላመለጠምና፡፡ አምስቱ ሰነፎች ደናግልም ጌታችንን ለምነውት ነበር፤ በሩን አንኳኩተው ነበር፡፡ ነገር ግን ልመናቸውም ማንኳኳታቸውም ከንቱ ነበር፥ ጥቅም አልባ ነበር፡፡

☞ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ዐውቀን በሀብታችንም፣ በትጋታችንም፣ ለወንድማችን በምናደርገው ማናቸውም ጠቃሚ ነገርም የዓቅማችንን ያህል እንጣር፡፡ መክሊት የተባለው የእያንዳንዱ ሰው በእጁ ያለውና ማድረግ የሚችለው ነገር ማለት ነውና፡፡ ለአንዱ ወንድሙን መጠበቅ ሊኾን ይችላል፥ ለአንዱ በገንዘቡ ደግ ነገር ማድረግ ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ማስተማር ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ደግሞ ይህን በመሰለ ሌላ ነገር ሊኾን ይችላልና ጊዜ ሳለልን በሞተ ሥጋም ሳንወሰድ መክሊታችንን እናብዛ፡፡ አንድ ሰውስ እንኳን መክሊቴ አንዲት ናት አይበል፡፡ የተሰጠችህ መክሊት አንዲት ብትኾንም አንተ ንቁ ከኾንህ ንዑድ ክቡር ከመባል አትከለከልምና፡፡ ምንም ያህል ድኻ ብትኾንም ከዚያች ኹለት ሳንቲም ከሰጠችው ሴት በላይ ድኻ ልትኾን አትችልምና የተሰጠቺኝ ትንሽ ናት አትበለኝ፡፡ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ዮሐንስ በላይ ያልተማርክ ልትኾን አትችልምና እኔኮ አልተማርኩም አትበለኝ፡፡ እነርሱ ምንም ያልተማሩ ቢኾኑም ባሳዩት ትጋት ርስት መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ተችሎዋቸዋልና እኔ አይቻለኝም አትበለኝ፡፡

☞ እግዚአብሔር አንደበትን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር እግርን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ብርታትን፣ አእምሮን፣ ማሰብን የለገሰን ለዚህ ነው፡፡ እነዚህን ኹሉ የሰጠን ለራሳችን እንድናተርፍባቸውና ለባልጀሮቻችንም እንድንጠቅምባቸው ነውና ኹለት ወይም አምስት መክሊት አልተሰጠኝም አትበለኝ፡፡'

ተርጓሚ፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

2 months, 3 weeks ago

🙏ሁላችሁንም ስለተሳተፋችሁ እግዚአብሔር ያክብርልን። የዛሬ ተሸላሚዎች

🥇 @Ar_Teamr10 (2 min 7 sec)
🥈 @Nigusebel9 (1 min 51 sec)
🥉 @Samuelawg9 (2 min 4 sec)

ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር @AMUgebigubae_bot በዚህ ላኩልን

ዛሬ መሳተፍ ያልቻላችሁ ጥያቄውን በማንኛውም ሰዓት መመለስ እና ራሳችሁን መፈተሽ ትችላላችሁ።
🔏የሚቀጥለው ሳምንት የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብራችን ጠቅላላ እውቀት ስለሚሆን የተለያዩ መፅሐፍትን እያነበባችሁ ቆዩን።
የሚቀጥለውን ሳምንት የጥያቄ እና መልስ መርሃ ግብር በአቅማቹ ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ @AMUgebigubae_bot  ወይም  +251963798300 ማናገር ትችላላችሁ ።

አስተያየት እና ጥያቄ ካላችሁ በ @AMUgebigubae_bot አድርሱን
የያዕቆብ ለሊት ይሁንላችሁ።

5 months, 3 weeks ago

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት

@AMUgebigubae_bot

ይቀላቀሉን⬇️
https://t.me/gebigubae_library

5 months, 3 weeks ago

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት

@AMUgebigubae_bot

ይቀላቀሉን⬇️
https://t.me/gebigubae_library

5 months, 3 weeks ago

?ሁላችሁንም ስለተሳተፋችሁ እግዚአብሔር ያክብርልን። የዛሬ ተሸላሚዎች

1-Edu
2-@tessfa_Ye21
3-@Ar_Teamr

23-@shime2121

ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር @AMUgebigubae_bot በዚህ ላኩልን

የዛሬውን ጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብር ስፖንሰር ያድርግልን ወንድማችን ወልደ ገብርኤል (@Justinfolleyy)እግዚአብሔር ያክብርልን ?

ዛሬ መሳተፍ ያልቻላችሁ ጥያቄውን በማንኛውም ሰዓት መመለስ እና ራሳችሁን መፈተሽ ትችላላችሁ።

5 months, 3 weeks ago

[  †  እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ [ ሕንጸታ ] በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። †  ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

?   †   በዓለ ሕንጸታ    †   ?

†  በዚህች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" [አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ] [ማቴ.፳፰፥፲፱] (28:19) ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::

የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና [ዮሐ.፮፥፶፮] (6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::

በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::

በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::

ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: [ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::]

ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::

በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::

ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::

እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል::

† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን::

?

[  † ሰኔ ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ ዕረፍቱ ]

[    † ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ ንጉሠ ኢትዮጵያ ]
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

" በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: " † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]

†              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
?                   ?                    ?

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 days, 23 hours ago

Last updated 4 days, 5 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 2 weeks, 2 days ago