ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 5 days, 23 hours ago
Last updated 1 day, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 5 days ago
ሩሲያ ዶንባስ የተሰኘ ሮኬት ወደ አለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ አመጠቀች
ሩሲያ ትናንት አርብ ዶንባስ የተሰኘ ሮኬት ወደ አለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ አስወንጭፋለች ፡፡
ስያሜው በዩክሬን ዶንባስ ግዛት ውስጥ ለሚገኙ ተገንጣይ ሪፐብሊካኖች (የዶኔትስክ እና የሉሃንስክ ህዝባዊ ሪፐብሊኮች) ክብር ለመስጠት በማሰብ የተሰጠ ነው፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት 100 ቀናትን አስቆጥሯል፡፡
እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2014 ለሚከናወነው የምስጋናና እውቅና አሰጣጥአሰጣጥ ፕሮግራም ዝግ የሚሆኑ መንገዶች!!
በህግ ማስከበር ፣ በህልውና እና በህብረ ብሄራዊ አንድነት ዘመቻዎች ወቅት ጀግንነት ለፈፀሙና የላቀ የስራ ውጤት ላስመዘገቡ የፖሊስ አመራርና አባላት የምስጋናና የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም "በመስዋዕትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል” በሚል መሪ ቃል እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በመስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል።
በመሆኑም ስነ-ሥርዓቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት :-
?ከቦሌ አየር መንገድ በሚሊኒየም አዳራሽ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር (ኦሎፒያ አደባባይ)
? ከመገናኛ ፣በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኔዓለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ በላይና በታች
? ከአራት ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ገብርኤል መሳለሚያ አካባቢ
?ከቸርችል ጎዳና በሃራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፖስታ ቤት
? ከተክለ ሀይማኖት በሜትሮሎጂ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ሜትሮሎጂ መስሪያ ቤት አካባቢ
?ከተክለ ሀይማኖት ፣ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ወደ ኢሚግሬሽን የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ የኋላ በር
? ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ለከባድ መኪና አጎና አካባቢ ለቀላል መኪና የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር
?ከጦር ኃይሎች ፣ ልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ሜክሲኮ አደባባይ
?ከሜክሲኮ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ለገሃር መብራት
?ከሰንጋ ተራ በቴሌ ባር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች በድሉ ህንፃ አካባቢ
?ከንግድ ማተሚያ ቤት በውስጥ ለውስጥ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦርማ ጋራዥ አካባቢ
?ከሸራተን ወደ አምባሳደር ለሚመጡ ፍል ውሃ አካባቢ
?ከካዛንቺስ ወደ ፍል ውሃ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል አካባቢ
ቅዳሜ ለዕሁድ አጥቢያ ከለሊቱ 10፡30 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆናቸውን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት መሰረት አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
በ49 ቢልዮን ብር ወጪ አዲስ ቤተመንግስት ሊገነባ ነው። ‼️****
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በ49 ቢልዮን ብር ወጪ አዲስ ቤተመንግስት አዲስ አበባ ውስጥ ሊያስገነባ እንደሆነ ተሰምቷል። የካ ተራራ ላይ በ503 ሔክታር መሬት ላይ የሚገነባው ቤተመንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ከህዳሴው ግድብ ቀጥሎ ትልቁ ፕሮጀክት ይሆናል ተብሏል።
ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለፕሮጀክቱ ሲባል እንደሚነሱ ጠቅሶ ምትክ ቦታ ይሰጣቸዋል ብሏል።
ይህ "ጫካ ፕሮጀክት" የተባለውን ፕሮጀክት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በከፊል እንደሚደግፍ ጋዜጣው ዘግቦ ለዚህ የሚሆን የ20ኪሜ የመንገድ ግንባታ ከሰሞኑ እንደተጀመረ አስነብቧል።
(ኢትዮኒዉስ ፍለሽ)
@bbc_amharic1
Update❗️
የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ተባለ❗️
የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።
የቢሮ ኃላፊው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የህንፃ ስታንዳርድና የውጭ ማስታወቂያ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህን መነሻ አድርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አዲስ ከተማ ግራጫ ቀለም ልትቀባ ነው በሚል በስፋት ሲዘዋወር የታየው መረጃ የተሳሳተ ነው ብለዋል፡፡
እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ አመልክተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም ከህ ቀደም ‹‹ከተማችን ቡራቡሬ ሆና ባለቤት አልባ መስላለች›› ማለታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊው፤ ይህን ችግር ማንኛውም የመዲናዋ ነዋሪም ሊታዘብ ይችላል። የከተማ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል።
ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያውና የከተ ማዋ ቀለም ሁኔታ የሚመራበት ስታንዳርድ ዝግጅት ተደረገ እንጂ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ጠቁመዋል።
© ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
@bbc_amharic1
የብ/ጀነራል ተፈራ ማሞ ክስ ምንድነው❓
ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ዛሬ በቀረቡበት ፍርድ ቤት ግንቦት 8 በአዲስ አበባ ከተያዙ በኋላ ዓይናቸው በጨርቅ ተሸፍኖ ወዳልታወቀ ምድር ቤት ተወስደው ለሁለት ቀናት ማደራቸውን ተናግረዋል።
ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ከሩብ ሲሆን ጀነራሉ ነጠላ ጫማ አድርገው ጠቆር ያለ የስፖርት ሱሪና ሸሚዝ አድርገው ነው አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት፣ የመሰላቸትና የድካም ስሜት ይታይባቸዋል።
ጀነራሉ ለፍርድ ቤቱ እንዳስረዱት በጦር ሜዳ በጥይት የተመቱባቸው የሰውነት ክፍሎቻቸው ከነርቫቸው ጋር በመገናኘት እየታመሙ በመሆኑ ለህክምና ቅድመ ሁኔታ ለማመቻቸት ወደ አዲስ አበባ መሄዳቸውን አመልክተው ሆኖም ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ ም ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ እዛው አዲስ አበባ ዮሴፍ ከሚባል አካባቢ በማያውቋቸው አካላት ግን ደግሞ የደህንነት ሰዎች ብለው ባሰቧቸው ሰዎች ተይዘው ዓይናቸው በጨርቅ ተሸፍኖ ወደ አልታወቀ ምድር ቤት ተወስደው ለሁለት ቀናት ማደራቸውን ተናግረዋል።
ከዚያም በሄሊኮፕተር አሁንም አይናቸው በጨርቅ ተሸፍኖ ወደ ማያውቁት ቦታ ከተወሰዱ በኋላ አይናቸው ሲገለጥ ራሳቸው በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው 9ነኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዳገኙ ተናግረዋል። አቃቤ ህግ ያልተጠናቀቁ ሥራዎች ስላሉኝ የ14 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ለመጠርጠራቸው ምክንያት የሆኑና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለመናድ ለተለያዩ ሚዲያዎች የሰጧቸውን የቪዲዮ ምስሎች ለመሰብሰብ፣ ሌሎች ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች ስለሚቀሩ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት የሚመጡ ማስረጃዎች ስለሚቀሩ፣ ሁለት ስልኮቻቸውን ለመርመር የተጠየቀው ቀን ይሰጥኝ ስል ተከራክሯል፡፡
የጀነራሉ ጠበቃ በበኩላቸው ቪዲዮዎቹን በቀላሉ ከኢንተርኔት ማውረድ ይቻላል፣ ሌሎች የተባሉ ተጠርጣሪዎችም በስም ባለመጠቀሳቸው፣ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ግለሰቡን ወደ ባሕር ዳር ሲልክ ያሉትን ማስረጃዎች ጨምሮ ልኳል፣ ተንቀሳቃሽ ስልኮችም ግለሰቡን በቁጥጥር ባደረጉ ሰዎች እጅ በመሆናቸው ያለፉት 5 ቀናት ምርመራውን ለማድረግ በቂ ጊዜ ስለነበር ደንበኛዬ የዋስ መብታቸው ተጠብቆ ከእስር ይፈቱ ሲል ጠይቋል፡፡
ፍርድ ቤቱ የግራቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ የተጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ቀሩ የተባሉትን የምርመራ ስራዎች ለማከናወን ተገቢ ሆኖ ባለማግኘቱ በ10 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዷል፡፡
በዚሁም መሰረት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ እስከዛው ድርስ አሁን ባሉበት የፖሊስ ጣቢያ እንዲቆዩ ብሏል፡፡ ጀነራል ተፈራ ማሞም አሁን ባሉበት ቢቆዩ እንደሚመርጡ ለፍርድ ቤቱ አመልክተዋል፡፡ በመሆኑም ጀነራሉ ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ ም ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የሚቅረቡ ይሆናል።
ጀነራሉ ወደ ፍርድ ቤት በመጡ ጊዜ በርካታ የፀጥታ ኃይል አካባቢውን በከፍተኛ ሁኔታ ሲጠብቅ ነበር፡፡
© የጀርመን ድምፅ
@bbc_amharic1
ኢትዮ ቴሌኮም 5ጂ አገልግሎቱን ግንቦት አንድ ያስመቃል❗****
ኢትዮ ቴሌኮም በዓለማችን የመጨረሻውን የሞባይል ኔትዎርክ 5ተኛ ትውልድ (5ጂ) አገልግሎቱን ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ያስመርቃል፡፡
© Capital
@bbc_amharic1
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 5 days, 23 hours ago
Last updated 1 day, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 5 days ago