ማህተቤን አልበጥስም የተዋህዶ ድምፅ ✝💒

Description
""አንድነታችንን አንተው"" ዕብ መልዕክት 10:25
ይህ
✞✝ማህተቤን አልበጥስም የተዋህዶ ድምፅ ቻናል ነው ይቀላቀሉን
❓የምንለቃቸው ነገሮች❓
✞ወቅታዊ መረጃዎች
✞ ኦርቶዶክሳዊ ዜናዎች
፦የቅድስት ቤተክርስትያን ዶግማ እና ቀኖና የጠበቀ ቻነል ነው
®️ ማንኛውንም ጥቆማ አስተያየት
@mahteben_twahdobot ያድርሱን
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

3 days, 21 hours ago
እንኳን አደረሳችሁ

እንኳን አደረሳችሁ
" ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ሆይ፤ ለእርዳታ ፈጽመው ለሚፈጥኑት እግሮችህና ሰኰናህ ሰላም እላለሁ። ዑራኤል ሆይ፤ በስደት ወራት ለድንግል የምድረ ግብፅን መንገድ ያመለከትካት አንተ ነህ ሦስት ዓመት እያለቀሰችና እያዘነች በስደት ከቆየች በኋላ ተመልሳ ወደ ሀገሯ እንድትገባ የደስታ ምስራች ያበሠርካት አንተ ነህና።
ዑራኤል ሆይ፤ መዝናኛዋ በጽርሐ ጽዮን ለሆነና ነፍስን ከሲኦል የኵነኔ ፍርድ ለማውጣት የሲኦል ጐዳና መረገጫው ለሆነው ተረከዝህ ሰላም እላለሁ።
ዑራኤል ሆይ፤ ከፈጣሪህ ይቅርታን አስገኝተህ የኃጥኣንን ነፍስ የምትጐበኝ ነህና በዚያች የቁርጥ ፍርድ ቀን የሲኦልን ደጃፍ እንዳናይ።

ስለእመቤታችን ድንግል ማርያምና ስለልጅዋ ኢየሱስ ክርስቶስ በቃል ኪዳንህ እንማፀናለን። አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን የቅዱስ ዑራኤል አምላክ ሆይ፤ በክርስቶስ ክርስቶሳውያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆች እኛን አገልጋዮችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ለዘላለሙ አሜን። "

መልክአ ዑራኤል

4 days, 8 hours ago
እንኳን ለ ፂዮኗ ማርያም አመታዊ በአል …

እንኳን ለ ፂዮኗ ማርያም አመታዊ በአል አደረሳችሁ
እንኳን ደስ አላችሁ

እንኳን ለ ፪ኛ ዓመት አደረሰን አደረሳችሁ

ማህተቤን አልበጥስም የተዋህዶ ድምፅ እነሆ ሁለት አመት ሆነው እንኳን ደስ አላችሁ

ይህ ቻናል ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እናንተን ካለ እረፍት ሲያገለግል ቆይቷል
እውነተኛ መረጃ ሲያደርስ የቤተ ክርስትያን ድምፅ በመሆን ለምዕመኑ ደውል በመሆን ዘርፈ ብዙ ትሩፋቶችን ሲሰራ ቆይቶ እነሆ አሁን ዛሬ ፪ አመት ሆነን ከእናንተ ውድ ቤተሰቦቼ ጋር እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን አደረሳችሁ ከዚህ በላይ ለመስራት መረጃ ለማድረስ ድምፅ ለመሆን ተግቼ እሰራ ዘንድ አብሮነታችሁ አይለየኝ እውነተኛ መረጃ አድርሱን እንዘግባለን ድምፅ እንሆናለን ለዚህ ደርሻለሁ ክብሩን የድንግል ማርያም ልጅ ይውሰድ
እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን

4 days, 12 hours ago
ማህተቤን አልበጥስም የተዋህዶ ድምፅ ✝💒
1 week, 3 days ago

[📌 የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

📌 ሊቀ መዝሙራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
📌 ሊቀ መዝሙራን ይልማ ኃይሉ
📌 ዘማሪ አርቲስት ይገረም ደጀኔ
📌 ዘማሪ ገ/ዮሐንስን ገ/ፃዲቅ
📌 ቀሲስ ምንዴዬ ብርሀኑ
📌 ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ
📌 ዘማሪ ምርትነሽ ጥላሁን
📌 ዘማሪት አቦነሽ አድነው
እና የሌሎችንም ...........](https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk)

የዘማሪዎችው መዝሙሮችን ለማግኘት ከስር Join የሚለውን ንኩት 🔻🔻🔻
👇👇👇

https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk
https://t.me/+2ua4-eAbNTI1MTRk

1 week, 3 days ago

🌎አንዴ ብቻ ይንኩት አለማትን የፈጠረውን ጌታ በሕይወት ያመስግኑ ፣ ስትነኩት የሚወስዳችሁ ቦታ በጣም ይጠቅማቹሀል !
                 [👇👇👇

.            ✦              ‍ ‍ ‍ ‍                  ,    

.             .   ゚     .         🌑            .           .            

˚                     ゚     .               .      🌎 ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ‍ ,                * .                    .           ✦           ˚              *                      .  

.             .   ゚     .             .

,       .                               ☀️                                *         .           .             .                                                               ✦      ,         *   🚀        ,    ‍ ‍ ‍ ‍               .            .                                   ˚          ,                              .                 

*          ✦                                .                  .        .        .     🌑            .           .            

˚                     ゚     .               .](https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk)

1 week, 4 days ago

*🛑*የወሲብ ቪዲዮ የምታዩ ተጠንቀቁ፣ እነዚህን ጉዳቶች እወቁ! የወሲብ ቪዲዮ የመመልከት 31 አደገኛ ጉዳቶች!

ለሁሉም ክርስቲያን እንዲደርስ
👉#share እና #join ያድርጉ ያስደርጉ
👉**@enatachinmaryam

2 weeks, 2 days ago
አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ

አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ

እንኳን ለቅዱሱ አባታችን አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ ወርሃዊ የመታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን !!!

" የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።"
መዝ. ፴፬፥፲፭ /34፥15/

✝️ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ወሎ ውስጥ በሚገኝ ዳዎንት በሚባል አከባቢ እግዚአብሔርን ከሚፈሩና በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው ከሚኖሩ ወላጆች ተወለዱ

✝️ አዳም በ40 ቀኑ ወደ ገነት እንደገባ አባታችንም በተወለዱ በ40ኛ ቀናቸው ስርዓቱን ጠብቀው ተጠመቁ

✝️ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል እየጠበቃቸው በሞገስና በፀጋ አደጉ፤ የቤተክርስቲያን ስርዓትንም ተማሩ

✝️ ገና በወጣትነታቸውም የቤተክርስቲያን መጽሐፍትን አንብበው ቃሉን ከተረዱ በኋላ ዲቁናን ተቀበሉ

✝️ ይህንንም ዓለም ናቁ፤ ወደ ደብረ ሐይቅ ገዳምም በመሄድ የምንኩስናን ሕይወት ለመጀመር በአበምኔቱ ለሦስት ዓመት ተፈተኑ

✝️ በገዳምም የምንኩስናን ስርዓት ተምረው በጎንም እንጨት እየለቀሙ አባቶችን እያገዙ የምንኩስናን ሕይወት ጀመሩ

✝️ አባታችን አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በገዳም በበዓታቸው የሚተጉ፣ በጸሎት የጠነከሩ አባት ሆኑ

✝️ በዚያም ገዳም ብዙ ካገለገሉ በኋላ ወደ ተወለዱበት አከባቢ በመሄድ ቤተክርስቲያን አነጹ፣ በገዳማትም እየተዘዋወሩ የክርስቶስን ወንጌል እያስተማሩ ገዳማውያንን አበረቱ

✝️ የታመሙትን እየፈወሱ፣ በጸሎት እየተጉ በቅድስና የኖሩት አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ለብዙ መነኮሳት ምሳሌ፣ ለደቀ መዛሙርት አርአያ ሆነው ኖሩ

የአባታችን የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ በረከትና ምልጃ አይለን። ጸሎታቸው አይራቀን።

2 weeks, 3 days ago

የተከለከሉ ነገሮች

ክልክል ነው!
እንደዚህ ያለ መልዕክት የተሸከሙ ሰሌዳዎችን ብዙ ጊዜ አይተን ይሆናል። ማለፍ ክልክል ነው! መቆም ክልክል ነው!፣ ስልክ ማነጋገር ክልክል ነው!፣ ከተፈቀደላቸው ሰዎች በቀር ማለፍ ክልክል ነው!፣ ምግብ ከውጭ ይዞ መግባት ክልክል ነው!
እነዚህን የመሰሉ ማስታዎቂያዎች በጣም ብዙ ማንሣት ይቻላል። ደሞ ለክልከላ! ምን ቸግሮን! አንዳንዴ ደግሞ ከክልከላም አለፍ ብሎ ያስቀጣል! የሚልም ሊጨመርበት ይችል ይሆናል።
አዎ በእርግጥ ሁሉም ነገር ለሁላችንም የተፈቀደ ሊሆን አይችልም።

አንዳንድ ክልከላዎች ለራሳችን ጥቅም ተብለው የሚደረጉ ሲሆን ሰዎች ወይም ተቋማት ለራሳቸው ጥቅም ብለው የሚከለክሏቸው ጉዳዮችም ይኖራሉ። እኛም በተቻለን መጠን የተከለከልነውን ላለማድረግ ስንሞክር እንታያለን።

በእግዚአብሔር መጽሐፍም ውስጥ የተከለከለ ነገር አለ፤ እግዚአብሔርን ስለመጥቀም ሳይሆን ራሳችንን ስለመጥቀም ተብሎ የተቀመጠ ክልከላ ነው።
የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ መጥራት ክልክል ነው! እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠሩትን ከበደል አያነጻቸውምና ዘፀ. 20፥7
ገንዘብ ለማግኘት፣ ነገርህን ለማስረዳት ብለህ የእግዚአብሔርን ስም ልትጠራ አይገባህም። በስሙ መነገድ ይሆንብሃልና። ይልቁንም በጸሎት፣ በምስጋና እና በሥርዐተ አምልኮ ጊዜ ደግመህ ደጋግመህ ብትጠራው ስሙ ሕይወት ስለሆነ ነፍስህን ታድንበታለህ፤ ስሙ የሚቀድስ ስለሆነ ሀሳብህን ቅዱስ ያደርግልሃል።

ሐዋርያት ያጠመቁን በዚህ ስም እንደሆነ አስብ። ልጅነትን ያስገኘልህን መንግሥተ ሰማያትን ያወረሰህን ስም ያለ ቦታውና ያለጊዜው ልትጠራ አይገባህምና በልማድ ከምትጠራቸው ስሞች መካከል እንዳይሆንብህ ተጠንቀቅ።

ወንድምን መጥላት ክልክል ነው! ወንድሙን የሚጠላ ሰው በደል የሚፈጽመው በወንድሙ ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ነው። የእጅህ ሥራ ባልሆነ የሰው ልጅ ላይም ክፉ ነገርን ማድረግ የተፈቀደ አይደለም።
ዋጋው ውድ የሆነ ቤት፣ ልብስ፣ መኪና እንወድ አይደል? የሰውም እኮ ዋጋው ክርስቶስ ነው። ዓለም በመላው ለአንድ ሰው ዋጋ ሊሆን አይችልም። እንደዚያም ስለሆነ ነው አምላክ በሥጋ ተገልጦ ያዳነው። በዓለም ውስጥ ያለው ወርቅና ብር ተከማችቶ ሊገዛን ስላልቻለ በደሙ ገዛን። እጅግ ዋጋችን ትልቅ እንደሆነ ተመልከቱ! በዚህ መጠን ዋጋው ውድ የሆነ ምንም ነገር ስለማታገኙ በውድ ዋጋ ከተገዛ ቤት ውስጥ ከምታድሩ፣ በብዙ ዋጋ በተገዛ መኪና ከምትሽከረከሩ፣ ዋጋው ውድ በሆነ ልብስ ከምትሽቀረቀሩ በምድር ላይ ምንም ነገር ሊገዛው የማይችል ውድ ዋጋ ያለውን አንድ ሰው ብትወዱ እና ከእርሱም ጋር በፍቅር ብትኖሩ ይሻላችኋል።

በእግዚአብሔርም መጽሐፍ ሰውን መጥላት የተከለከለ በመሆኑ ያልተፈቀደልንን እያደረግን ለምን በግዚአብሔር ፊት ራሳችንን ለፍርድ እናዘጋጃለን?
ወንድምህ ተርቦ አይተህ ልታበላው እየተቻለህ አልፈህ መሄድ ክልክል ነው! አንተም ዘንድ ብዙ ረሀብ እንዳለ አስተውል። እንጀራ ብትጠግብም ሰላምና ፍቅርን ተርበሃል፤ አንተ ዘንድ ተርፎ ካለው እንጀራ ቆርሰህ የተራቡትን ብታጠግብለት እግዚአብሔር ደግሞ በርሱ ዘንድ ካለው ሰላምና ፍቅር ያጠግብሃል።

በባዶ መሬት ላይ ብትዘራ ሠላሳና ስሳ መቶም ያማረ ፍሬ ታገኛለህ፤ በባዶው የድሀ ሆድም ምጽዋትን ብት ዘራ ጽድቅን ታፈራልሃለች።
ዕራቁቱን የሆነ ሰው ብታገኝ ነገር ግን በሃይማኖቱ፣ በዘሩ፣ በቋንቋው እና በሌላም ምክንያት አንተን ስላልመሰለህ ሳታለብሰው ማለፍ አልተፈቀደልህም!

እግዚአብሔርን በፍርድ ቀን ለፀሐይና ለጨረቃ ካለበሳቸው የተሻለውን የብርሃን ልብስ ያለብስህ ዘንድ ዕራቁቱን ሆኖ ሳለ አይተህ ልታልፈው ስለማይገባ ነው።
ከፀሐይ ይልቅ የተሻለውን ብርሃን ለሚያለብሰን አምላክ እንኳን የተረፈንን የለበስነውንስ ገፈን ብናለብሰው የሚጎዳን ይመስላችኋል?
የምትሰጠው አንዳች ነገር በእጅህ ሳለ እንዳትሰጥ ልብህ ከወሰነ ልብህን ሰይጣን ምራቁን ተፍቶበታል ማለት ነውና ተጠንቀቅ።
ቅዱሳን ሐዋርያት የሚሰጡት እንኳን ባይኖራቸው “ወርቅና ብር የለኝም ያለኝ ግን እሰጥሀለሁ” ሥራ. 3፥6 ብለው እጃቸው ላይ ያለውን ተአምራት ሲያደርጉለት ሃይማኖቱን፣ ዘሩን፣ ቋንቋውን አልጠየቁትም።

እኛም የሐዋርያት ልጆች ስለሆንን እንደ ሐዋርያት ያለ ልብ ሊኖረን ይገባል።
ለባልንጀራህ መሰናክል መሆን ክልክል ነው! ጌታ በቅዱስ ወንጌል “በእኔም ከሚያምኑ ከታናናሾች አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቁ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር” ማቴ. 18፥6 ብሎ ያስተማረው ከሰው ልጆች አንዱን እንኳን ቢሆን ማሰናከል ትልቅ በደል ስለሆነ አይደለምን?
እግዚአብሔርን የበደለው አዳምና ሔዋን ቢሆኑም እርግማኑን የጀመረው በእባብ ነው ዘፍ. 3፥14 ለምን ይመስላችኋል?
የስህተት ምክንያት ስለሆነች አይደለምን?
በሰዎች ፊት መሰናክል መሆን ለእርግማን የቀረብን ያደርገናል።

ካህናትም ጽኑ ቀኖና ሰጥተው በንስሐ ባሕር እንዲወረውሩን ታዝዘዋል። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ጴጥሮስን “ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጅ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል” ማቴ. 16፥23 ብሎ የተቆጣው እንቅፋት ቢሆንበት ነው። ማሰናከያን በባልንጀራው ላይ የሚያመጣ ሰው ቢኖር “ሰይጣን” ተብሎ ሊጠራ የሚገባው መሆኑን ያሳያል። በአይሁድ ብዙ የነቀፋ እና የስድብ ቃላት ያልተቆጣው ክርስቶስ ምስጋና በሚመስሉ የጴጥሮስ ቃላት መቆጣቱ አያስገርማችሁም?

“ጌታ ሆይ አይሁንብህ ከቶ አይደርስብህም” ብሎ ለፍቅሩ ሳስቶ ቢናገር ነገሩን አልወደደለትም። በንግግሩ ውስጥ ማሰናከያ ቃላት ያሉ በመሆናቸው ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ዓላማ የሚያሰናክል ክፉ ንግግር ነበር። ስንቶችን በንግግራችን አሰናክለን ይሆን? ለስንቶቹስ ማሰናከያ ቃላትን ተናግረን ይሆን?

ንግግራችን እንደ ጴጥሮስ ሽባ ካላስፈታ ሥራ. 3፥6፣
እንደ ጳውሎስ ጋኔን ካልመታ ሥራ. 16፥18፣
እንደ ኤልሳዕ ችግር ካልፈታ 2ነገ. 4፥1፣ እንደ ኤልያስ ለተራቡት ተስፋን ካልሰጠ 1ነገ. 17፥14፣
ይልቁንም
እንደ አክዓብ መልዕክተኞች ለቅጣት አሳልፎ ከሰጠን 2ነገ. 1፥10፣ እንደ ዳዊት ካልተወደደልን 1ሳሙ. 18፥1፣
እንደ አባ አጋቶን ለፈተና አሳልፎ ከሰጠን
ባንናገርስ?
የተከለከሉ ነገሮችን እያደረግን የተፈቀደልንን ልናጣ አይገባንም።

ከተከለከልነው ይልቅ የተፈቀደልን ይበዛል፤ የተከለከልነውም ቢሆን የተፈቀደልን ነው። ዕፀ በለስን የተከለከልነው በሕይወት መኖር ስለተፈቀደልን ነው። ዕፀ በለስን በመጠበቅ እንጅ ዕፀ በለስን በመብላት ሕይወት እንደሌለ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ከለከለን።

ለተፈቀደልን ሕይወት ስንል የተከለከልነውን በለስ እንጠብቃለን።
ሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮን

2 weeks, 3 days ago

እንደሰይጣን ስልጣን አትውደድ
እንደሄዋን አትታለል
እንደቃኤል አትግደል
እንደደሊላ አታስመስል
እንደአጋግ ሆድ አትቅደድ
እንደአምኖን ሴት አትድፈር
እንደሄሮድስ ሕጻን አትግደል
እንደይሁዳ ገንዘብ አትውደድ

3 weeks, 2 days ago

💬 ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ከተነሳ በኋላ መጀመርያ የታየው ለማን ነው??

----------------------------------------------------

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago