የስነ-ፅሑፍ አፍቃሪያን ማህበር 2

Description
መፅሐፍ

መጣጥፍ

መፅሔት

ልቦለድ
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

1 month, 2 weeks ago
በምድራችን ላይ የመጀመሪያው ፖለቲከኛ ሙሴ ነው …

በምድራችን ላይ የመጀመሪያው ፖለቲከኛ ሙሴ ነው ። ሙሴ የእስራኤልን ሕዝብ ከ ግብፅ ባርነት ነፃ ለማውጣት የተጠቀመው መሳርያ ተስፋ ነበር። ማር እና ወተት ወደምታፈልቀው ምድር ነው የምወስዳችሁ ብሎ ሕዝቡን አማለለ። ሕዝቡም ማርና ወተት የምታፈልቅ ድንቅ ምድርን በምናቡ ማሰብ ጀመረ። ከሚፈልቀው ወተት ጠጥቶ እና ከሚፈልቀው ማር በልቶ ሲጠግብ በዓይነ ህሊናው እዬታዬው ሙሴን ለመከተል ቆርጦ ተነሳ።

ከግብፅ ባርነት ነፃ ወጥተው ወደ ተባለው ምድር ሲገቡ እንኳንስ ማርና ወተት ሊያፈልቅ ይቅርና ባዶ በረሀ ነበር። ግብፅ ሳሉ ምንም እንኳን በረሀ ቢሆንም የዓባይ ወንዝን እየገደቡ ጠግበው በልተው ያድሩ ነበር። በእርግጥ የግብፅ ባሮች እንደመሆናቸው ከግብፅ እኩል አይታዩም። ቢሆንም ግን ከግብፅ ወጥተው የራሳቸውን ሐገር ስለመመስረት ከማሰብ ይልቅ ሪቮልሽን አካሂደው አይሁዳዊያኑ ከግብፃውያኑ እኩል የሚታዩበትን ስርዓት ለመፍጠር ነበር መንቀሳቀስ የነበረባቸው።

ሙሴ አይሁዳዊያኑን ማርና ወተት ወደምታፈልቀው ምድር ሊያስገባቸው ቃል ገብቶላቸው ሲያበቃ በረሀ ላይ ሲተዋቸው ሕዝቡ ውስጥ ውስጡን ማጉረምረም ጀምሮ ነበር ። ከዚህስ ግብፅ ትሻለን አልነበር እንዴ? እያሉ። "

አቢ የሰጠሁትን ማብራሪያ ከምንም ሳይቆጥር ብርጭቆው ላይ የቀረችውን ጭላጭ ወደ አፉ ልኮ ሶስተኛ ቢራውን ወደ ብርጭቆው ማንደቅደቅ ጀመረ።

https://www.ethiobookreview.com/book/yeabi-sigat-yeabtsega-ambaw

1 month, 2 weeks ago
በአገራችን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጉዳዩን የበለጠ …

በአገራችን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታ ጉዳዩን የበለጠ አባብሶት የነበረ ቢሆንም ለመኖር ሲባል ለ 7ወር የህል በመምህርነት አገልግያለሁ። ነገር ግን ገቢዬ ፍላጎቴን ለማሟላት በቂ አልነበረም።

አንድ ቀን በታይላንድ ውስጥ የውሂብ ማስገቢያ ኦፕሬተር ለመሆን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የስራ ማስታወቂያ አየሁ።

በጣም ማራኪ መስሎ ታየኝ። በወር 1,000 ዶላር ቃል ገቡልኝ።

ማረፊያ ቦታ እና በቀን 8 ግዜ የምግብ ሰዓት እንደለው ተነገረኝ።

ቤተሰቤን እና ራሴን ከድህነት ለማላቀቅ እና የተሻለ ህይወት ለመኖር ወደ ታይላንድ መሄድ እንዳለብኝ አሰብኩ።

በማስታወቂያው ላይ ያለውን ቁጥር አግኝቼ የመፃፍ ችሎታዬን እና የእንግሊዝኛ ችሎታዬን በቪዲዮ ገመገሙ።

ከዛም ታይላድ ከሄድኩ በኃላ ተወዳደርኩ እና ፈተናውን አልፌ በመቀጠሬ ኩራት ተሰማኝ።

🛬 ስራው ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ ነበር 🛬

በታይላንድ ውስጥ ያለው ስራ ለህልሜ መልስ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር ፤ ለቤተሰቤ እና ለጓደኞቼ የተሻለ ህይወት ይሰጥልኝ ይሆን ብዬም ነበር።

ነገር ግን ያሰብኩት ነገር ቅዠት ሆኖ ተገኘ።

ባንኮክ አየር ማረፊያ ስደርስ አንድ ሰው ወደ መድረሻው በር ወሰደኝና ሹፌሩን እንድጠብቅ ነገረኝ።

ሹፌሩ እኔንና ሌላ ሠራተኛ ጨምሮ እዞን ሄደ።

እዞን የሄደው ማይ-ሶት ወደምትባል የታይላንድ ትንሽ ከተማ (ማይናማር ጋር ትዋሰናለች) ወደዛ ነው።

ያኔ ጨለማ ስለነበር ምን እየሆነ እንዳለ ሙሉ በሙሉ አላውቅም ነበር።

ጥቂት ሰዎች ወደ እኛ መጡ፣ እና በጀልባ እንድንገባ አስገደዱን። ሳንፈልግ ወደ ማይናማር ወሰዱን። ማይናማር ወዳለው ግቢ ስንደርስ ደነገጥኩ፣ ፈራሁ ።

ግቢው ሰፊና በህንጻዎች የተሞላ ነበር።

እያንዳንዱ ሕንፃ አራት ፎቆች ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ወለል 16 ክፍሎች አሉት። እያንዳንዱ ክፍል አራት ተደራቢ አልጋዎች አሉት።

በግቢው ውስጥ አሠሪዎቻችን ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጠሩት።

በሳምንት ሰባት ቀን እስከ 16 ሰአት እንድንሰራ አድርገውናል።

በሥራ ላይ እያለ እንቅልፍ ከተሰማን ወይም እግሮቻችንን ትይዩ ካላደረግን እንቀጣለን።

በግቢዎቹ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ነበሩ።

ከዚያ ቦታ ለማምለጥ ምንም መንገድ አልነበረም። 10 ጫማ ከፍታ ያላቸው ግድግዳዎች በላዩ ላይ ሽቦዎች ነበሯቸው።

ቦታው በታጠቁ ሰዎች ከፍተኛ ጥበቃ ይደረግለት ነበር።

ማይናማር ወደ ባንኮክ መሻገር በጣም አስፈሪ ነበር ነገር ግን የአለህ ፊቃድ ሁኖ ከዛ እስር ቤት ወጣሁ።

ከዚያ መከራ በመትረፌ እፎይታ ተሰማኝ።

በህይወት እወጣለሁ ብዬ አላሰብኩም ነበር። ለዚህ እድል እና እንዲወጣ ለረዱኝ ሰዎች የዘላለም አመስጋኝ እሆናለሁ።

https://www.ethiobookreview.com/book/yeabi-sigat-yeabtsega-ambaw

1 month, 2 weeks ago
የሆነ ደስ የሚል የሆነ የሚጨንቅም ስሜት …

የሆነ ደስ የሚል የሆነ የሚጨንቅም ስሜት አለው ። ሳላውቀው ሁለቱም እጆቼ በግራና ቀኝ ጉንጮቿ ላይ አረፉ ።

ድንገት የቤተ መንግስቱ መብራት ቦግ ሲል ከህልሜ የነቃሁ ይመስለኛል ። አይ ህልም አልነበረም ። ኦክሲ አጠገቤ ነበረች ። ነገር ግን እየተሳሳምን አልነበረም ። ተደናግጠን እየተያየን እንጂ ። መብራት ወደበራበት አቅጣጫ ተመለከትኩ ። ታንዛን ከወታደሮቹ ጋር ቆሞ እየተመለከተን ነበር ።

ለጥቂት ጊዜያት ተፋጠን ቆምን ። ታንዛን ፊት ላይ ያነበብኩት ቁጣን አልነበረም ድንጋጤን እንጂ ። ለካ ንጉስም ይደነግጣል ። ቀስ በቀስ ድንጋጤው ወደ ቁጣ ተቀየረ ።

" ያዟቸው ! " ሲል ወደ እኛ እየጠቆመ ጮሆ ተናገረ።

ምንም ሳላገናዝብ በደመነፍስ የኦክሲን ዕጅ ይዤ ለማምለጥ ሞከርኩ። ነገር ግን ኦክሲ እጄን ጎትታ ለማምለጥ እንደማትፈልግ አሳዬቺኝ። እጇን ለቅቄ ባገኘሁት አቅጣጫ ሮጥኩ ። የወታደር ጋጋታና ሩጫ ከሗላዬ ይሰማኛል ።

" ያዙት እንዳያመልጣችሁ !" የታንዛን ድምፅ ነበር።

በአትክልት ስፍራው ውስጥ ባገኘሁት አንድ ዛፍ ላይ ተንጠላጥዬ የቤተ መንግስቱን አጥር ዘልዬ አመለጥኩ። ከቤተ መንግስቱ አጥር አቅራቢያ መሸሸጊያ ስፍራ ካለ በሚል ማተርኩ። ነገር ግን መሽቶ ስለነበር እምብዛም አከባቢውን ለመለየት አላስቻለኝም ። በደመነፍስ ወደአንዱ አቅጣጫ ለመሮጥ ስሞክር ጉድጉዋድ ውስጥ ተደናቅፌ ወደቅኩ። የወደቅኩበት ጉድጉዋድ ጥልቀት ስለነበረው አንሸራቶ ወደ ውስጥ ወሰደኝ ። በአከባቢው የሚሮጡ ወታደሮች ድምፅ ይሰማኛል።

https://www.ethiobookreview.com/book/mistrawiw-mist-destan-felega-no-3-yeabtsega-ambaw

1 month, 2 weeks ago

የማበልጋት ባለትዳር ነበረች

ዋና ተግባራችን ወሲብ ነው፤ የምንቀጣጠረው ለወሲብ ብቻ ነው የምናወራው ስለ ወሲብ ነው፤ አንዳችን እንዳችንን የምንፈልገው ወሲብ ሲያምረን ነው፡፡

አጠገቤ ሆና ባሏ ደውሎ ያውቃል "ሰውዬሽ ደወለ" ብዬ ስልኳን አቀብያት አቃለሁ። ምንም እንዳልተፈጠረ ስታወራው እርቃኗን አትመስልም ነበር ይገርመኛል ድድብናችን

ነውራችን ስለተደጋገመ ተግባራችን ብልግና መሆኑ ተሰወረብን። ቢሮዋ እሄዳለህ ቢሮዬ ትመጣለች ጓደኛዬ ቤት እኔ ቤት የሆነ ኮስመን ያለ ሰዋራ ቦታ

የሆነ ድብቅ ፅድት ያለ ስፍራ መኪና ውስጥ። ብዙ ብዙ ቦታ ትመጣለች እንዋሰብለን የታሪካችን መነሻ እና መድረሻው ወሲብ ነው። አንድ ቀን በደነገጠ፡ ተስፋ በቆረጠ ድምፅ ባሌ አወቀብን አለችኝ ደነገጥኩ።

ጠፋሁኝ....ጠፋች

ከአስራ ሰባት ቀን በኋላ ጓደኞቼ .. "ገኒ.. ሀዘን ላይ ነች
ሙሉ በሙሉ ከላይ እስከታች ጥቁር ለብሳለች
ከስታለች" አሉኝ

"ምንሆነች?" አልኩ

"ባሏ ሞቶባት ነው፤ራሱን አጥፍቶ ነው የሞተውም" አሉ።

ስደነግጥ፣ፊቴ ሲቀያየር፣እምባዬ ሲያመልጠኝ አዝኜለት ነው የመሰላቸው። እኔ እንደገደልኩት አልጠረጠሩም።

የጥፋተኝነት ስሜት ሊገለኝ ሲል ማምለጫ መፅሃፍ ቅዱስ ገለጥኩ።

"ሰው የሚዘራውን ሁሉ ያንኑ ደግሞ ያጭዳል" የሚለው ከሁሉም ጎልቶ ተነበበኝ ፡
..............
ሰው ይዞ መውደቅ ፤ ማስተካከል የማይቻል አወዳደቅ ፤ ሲያስታውሱት የሚያስነክስ አይነት አወዳደቅ ፤ እነሳለሁ የማይሉት አወዳደቅ ፤ ወድቄ ነበር የማይሉት አወዳደቅ። በግዜ ምክንያት የማይደበዝዝ አወዳደቅ.. እንደዚህ አይነት መውደቅ ሲ..ያ.. ስ..ጠ..ላ!!!

©Adhanom Mitiku

@ethiosecret

1 month, 3 weeks ago

እስኪ ጥቂት እውነታዎች ስለ ማር
አንድ የሾርባ ማንኪያ ? ማር አንድን ሰው ለ24 ሰአታት በህይወት ለማቆየት በቂ መሆኑን ያውቃሉ?
? በአለም ከመጀመሪያዎቹ ሳንቲሞች አንዱ የንብ ምልክት እንደነበረው ያውቃሉ?
? ማር ህይወት ያላቸው ኢንዛይሞችን እንደያዘ ያውቃሉ?
ከብረት ማንኪያ ጋር ሲገናኝ እነዚህ ኢንዛይሞች እንደሚሞቱ ያውቃሉ?
▪️ ማር ለመብላት ምርጡ መንገድ በእንጨት ማንኪያ አንድ ማግኘት ካልቻሉ የፕላስቲክ ማንኪያ ይጠቀሙ
? ማር አእምሮን በተሻለ ሁኔታ እንዲሰራ የሚረዳ ንጥረ ነገር እንዳለው ያውቃሉ?
? በአፍሪካ ንቦች ሰዎችን ከረሃብ እንዳዳኑ ያውቃሉ?
? በንቦች የሚመረተው ፕሮፖሊስ በጣም ኃይለኛ ከሆኑ የተፈጥሮ አንቲባዮቲኮች አንዱ እንደሆነ ያውቃሉ?
? ማር ምንም ያህል ጊዜ ብታስቀምጠው እንደማይበላሺ ያውቃሉ?
? የዓለማችን ታላላቅ ነገስታት አስከሬን በማር ተሸፍኖ የሚቀበረው መበስበስን ለመከላከል እንደሆነ ያውቃሉ?
? "ጫጉላ" (Honeymoon) የሚለው ቃል አዲስ ተጋቢዎች ከጋብቻ በኋላ የመውለድ ችሎታን ለማሳደግ ማር በመመገብ ከሚለው ወግ የመጣ መሆኑን ያውቃሉ?
? ንብ የምትኖረው ከ40 ቀናት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ቢያንስ 1,000 አበቦችን እንደምትጎበኝ እና ከአንድ የሻይ ማንኪያ ያነሰ ማር እንደምታመርት ያውቃሉ። ነገር ግን ለንብ የህይወት ሙሉ ስራ እንደሆነስ ያውቃሉ?

1 month, 3 weeks ago

አሜሪካ ቲክቶክን ዘጋች።

' ቲክቶክ ' የተባለው የአጫጭር ቪድዮ ማጋሪያ እስከ ዛሬ እሁድ ድረስ እንዲሸጥ ካልሆነ ግን እንዲታገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል።

በዚህም ቲክቶክ በመላ አሜሪካ ውስጥ ከዛሬ ጀምሮ እንዳይሰራ ተደርጓል።

መተግበሪያው ገና እግዱ ተግባራዊ የሚሆንበት ሰዓት ሳይደርስ ቀደም ብሎ (ከሰዓታት በፊት) ነው የዘጋው።

በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ስክሪን ላይ ፥ " ቲክቶክን ለማገድ የወጣው ህግ ተግባራዊ ሆኗል በዚህም አሁን ቲክቶክን መጠቀም አይችሉም " የሚል ፅሁፍ ነው የሚታየው።

ቲክቶክ ትራምፕ ስልጣናቸውን ተረክበው ወደ ቢሮ ሲገቡ መፍትሄ ለማበጀት አብረዋቸው እንደሚሰሩ እንደጠቆሟቸው በማመልከትም እስከዚያው ድረስ ተገልጋዮቹ እንዲጠባበቁት ጠይቋል።

ትራምፕ ቲክቶክ መተግበሪያ ካልተሸጠ እንዲታገድ የሚለው ህግ እንዲዘገይ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ከመታገድ ሊያድነቱ አልቻሉም።

ፕሬዜዳንታዊ ስልጣናቸውን ሲረከቡ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ ? የሚለው በቀጣይ ይታያል።

ቲክቶክ 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ነበሩት።

@tikvahethiopia

1 month, 3 weeks ago
ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ግን??

ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ግን??

1 month, 3 weeks ago

ለጥምቀት ያልሆነ ወግ...
(በእውቀቱ ስዩም)

ዓመት በአል በመጣ ቁጥር እልል ያልሁ አማኝ ነኝ፤ ጥምቀትንማ ከልደቴ በላይ ነው የማከብረው፤ ጎረምሳ ሳለሁ እኔና ይሁኔ በላይ አብረን ጥምቀት እንሄድና የጊዮርጊስን ታቦት እናጅባለን፤ ከዚያ የሎሚ ውርወራ ክፍለጊዜ ይቀጥላል ፤

ሎሚ ውርወራን የፈለሰፈው ኢትዮጵያዊ ደብተራ ግን ምንኛ ደንቅ ሰው ነው! ለምሳሌ የስፔን ሕዝብ በአል የሚያከብረው ቲማቲም በመወራወር ነው፤ አንድ ክፍለከተማ የሚመግብ ቲማቲም ሲወራወር ይውልና ፥ ሲመሽ ቀይ ወጥ ውስጥ የዋኘ ይመስል፥ ተጨመላልቆ ወደ ቤቱ ይገባል፤ እኔ ራሴ ባለፈው ዓመት ተሳትፍያለሁ፤ ቱሪስት ነው ብለው ሳይራሩልኝ፥ ያልታጠበ የድግስ ድስት አስመሰለው ለቀቁኝ ! በአልንስ አበሻ ያክብራት!

በጉብዝናየ ወራት፥ የጥምቀት ቀን ፥ ከይሁኔ በላይ ጋራ ሰንተራ ሜዳ ላይ እንሰማራለን፤ እኔ ከትርንጎ ጋራ የተዳቀለ ጠንካራ ሎሚ ታጥቄ ቆነጃጅቱን አማትራለሁ፤ ይሁኔ በላይ እንደኔ የሀብታም ልጅ ስላልበረ፥ ሎሚ afford ስለማያረግ እምቧይ ይወረውራል፤
ከዝያ “ ወርወሬ መታሁት ፥ ጥላሽን በእንቧይ”ብሎ ያንጎራጉራል፤

“ጥላዋን ከመታኸው እንደ ጥላ ስትከተልህ ትኖራለች “ የሚል ፈሊጥ ነበረው’

ሎሚ የምወረውርላቸው ሴቶች ባብዛኛው ይሽኮረመማሉ፤ ትዳር እንኳ ባይሆን ፈገግታ ይለግሱኛል፤ አንደኛዋ ግን ሎሚ ስወረውርላት “ አላማ አለኝ “ አለችና በእግሯ መልሳ ብትለጋው ግንባሬ ላይ ግልገል አናናስ የሚያህል እጢ በቀለ፤

ቅድም፥ ይህንን እያስታወስኩ፥ ሀያሁለት ማዞርያ ላይ፥ ቆሜ አላፊ አግዳሚውን እመለከታለሁ፤የለበስኩት ቲሸርት ከፊትለፊቱ የፋሲል ግንብ ተስሎበታል፤ ከሁዋላ ደግሞ የመጥምቁ ዮሀንስን ምሰል ይዟል፤

ዘናጭ ሴቶች በፊቴ እያለፉ ነው፤

ከሴቶች ጋራ ማውራት ያምረኛል ፤ ግን እንዴት እንደምጀምር ግራ ይገባኛል፤
አንዲቱ አጠገቤ ስትደርስ፥
“ ይቅርታ” ብየ ጀመርሁ፥

“ ምንም አይደል “ ብላኝ መንገድዋን ቀጠለች፤

ቀጣይዋ ከፊቴ ብቅ ስትል፥

“ እናት !” ስላት፥

“ አገር “ አለችኝ፥

ምን አይነቱን ከይሲ ትውልድ ነው ፈትቶ የለቀቀብን ብየ፥ ተስፋ ቆርጨ በማየት ብቻ ተወሰንኩ ፤ ሶስተኛይቱ ባጠገቤ ስታልፍ ዞር ብላ ፈገግ ያለችልኝ መሰለኝ ፤

“ እንኩዋን አደረሰሽ “ አልኳት፤

“ የጆቭሀ ምስክር ነኝ “

1 month, 3 weeks ago

#TikTok?

' ቲክቶክ ' አሜሪካ ውስጥ ከእሁድ ጀምሮ እስከ ወዲያኛው እንዲዘጋ ወይም እንዲሸጥ የሚለውን ውሳኔ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ደገፈ።

ዛሬ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍ/ቤት ' ቲክቶክ ' በአሜሪካ እንዲዘጋ ካልሆነም እዲሸጥ ለሚጠይቀው የፌደራል ህግ ድጋፍ ሰጥቷል።

' ቲክቶክ ' ይግባኝ ቢጠይቅም ውድቅ ሆናል።

ከዚህ ቀደም መተግበሪያው " የአሜሪካውያንን የግል መረጃ ለቻይና መንግሥት አሳልፎ ይሰጣል በዚህ የብሔራዊ ጸጥታ አደጋ ደቅኗል "  በሚል እንዲታገድ ካልሆነም ለአሜሪካ ሰዎች እንዲሸጥ የሚል ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።

ዛሬ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከዚህ ቀደም የተላለፈውን ውሳኔ ደግፏል።

ይህን ውሳኔ ተከትሎ ' ቲክቶክ ' ከእሁድ ጀምሮ ይታገዳል።

የእግዱ ተግባራዊነት ' ቲክቶክ 'ን ከአፕስቶር እና ፕሌይስቶር ላይ እንዲወገድ ያደርጋል።

አዲስ ተጠቃሚዎች ' ቲክቶክ ' ማውረድ አይችሉም ፤ ነባር ተጠቃሚዎች አፕዴት ማድረግ አይችሉም።

ተመራጩ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ' ቲክቶክ ' ን ለመታደግ እና የመታገዱ ውሳኔ እንዲዘገይ ለጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ጠይቀው የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ግን የመጨረሻ ያለውን ውሳኔ አሳልፏል።

እንሆ ስልጣኑ ያበቃው የባይደን አስተዳደር " ህጉን ማስተግበር የቀጣዩ አስተዳደር ኃላፊነት ነው " ብሏል።

የ' ቲክቶክ ' ን እገዳ ለማዘግየት የሞከሩት ትራምፕ ሰኞ ስልጣናቸውን ይረከባሉ። ህጉን ማስተግበርም በሳቸው ላይ ተጥሏል።

ትራምፕ ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በኃላ በሰጡት ቃል " ውሳኔውን እኔው ወስናለሁ ፤ ውሳኔው እኔ ጋር ነው ምን እንደማደርግ ታያላችሁ " ብለዋል።

170 ሚሊዮን ተጠቃሚ አሜሪካ ውስጥ ያለው ' ቲክቶክ ' እስከወዲያኛው ይታገድ ይሆን ? ወይስ ከዚህ በኃላ ትራምፕ ማድረግ የሚችሉት ነገር ይኖር ይሆን ? በቀጣይ ይታያል።

መረጃው ከኤፒ፣ ፎርብስ፣ ሲኤንኤን የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago