ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
ምልከታ
ስለ ቋንቋ የጠለቀ እውቀት ባይኖረኝም ሀሳቤን ግን እናገራለሁ :: የተረዳኝ ካለ ይገዘኝ ስለ እጠይቃለሁ::
አማረኛ ፊደል የተወሰደው ከ ግእዝ እንደሆነ የታወቀነው :: ክብርና ምስጋና ይገባቸውና ለቀደምት አባቶቻችን ለዘለዓለም የሚሆን የፊደልና የቁጥር ስራ ትተውልን አልፈዋል ::
የነሱን ዋጋ የመክፈል አቅም ባይኖረንም ልንጠብቅላቸው የሰጡንን አደራ ለሚቀጥለው ትውልድ በሰጡን ልክ ጠብቀን ልናስረክብ (ልናስተላልፍ) ይገባ ነበር..:: እኛ ግን እያደረግን ያለነው ነገር ግን ይህን አይደለም::...
ከ80 በላይ ቋንቋ ሀገሪቱ ላይ ይነገራል :: ሁሉም ቋንቋወች ግን የ ሀገሪቱን ፊደል ሲጠቀሙ አይታይም ለምን?
የኔ ምልከታ ተማርን የሚሉት ሰወች ለዚህ ተጠያቂወች ናቸው እላለሁ:: የራሳችንን ፊደል ትተን የባእድ ሀገር ፊደል ተጠቃሚ እንድንሆን ያደረጉን ሌላ ማን ተወቃሽ ሊሆን ይችላል ::
የባንዴራ : የባሕል : የቋንቋና ፈደል ጥቅም ያልገባው የማይገባው ትውልድ እንዲፈጠር ያደረጉት ታዲያ እነማን ናቸው ማንን ተወቃሽ እናድርግ <<ተገዝተን እዳንል አባቶቻችን አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው ያቆዩያት ሀገርነች >>አወቅን እናውቅላችሁለን የሚሉት አይደሉም ተጠያቂወች::
ሀገር ሀገር የምትመስለው በራሶ መንገድ ስትሄድ ነው ማንነቶን ምንነቶን ስትጠብቅ ነው:: ይህን ሁሉ የምትገልጥበት ቋንቋዋ ሲበላሽ ደግሞ ምን እንደሚመስል አስቡት እውነት እውነት ባዶ መሬት እያደረግናት ነው ::
ትልቅ የነበረችውን ሀገር እያጠፋን ዝም ብሎ በመጣለት ማንም ሂድ በተባለው መንገድ የሚሄድ የመንጋ ትውልድ እየመሰረትን በስሜት እያስመራን እያጠፋናት ነው:: ለቋንቋው ክብር የለለው ስለሚጠቀመው ፊደል የማያቅ ትውልድ ቆም ብሎ የማይጠይቅ እንሰሳ የሆነ ደመነፍሳዊ ትውልድ እያበዛን ነው::
አብዛኛውን ቋንቋ በማናውቀው በበአድ ሀገር ፊደል እየተቀየረ ነው ግል ልክ ነው ? ልክ ነው የሚል ይኖር ይሆን?::
በዚህ አመት ምን ሰማሁ መሰላችሁ በበዩኒቨርሲቲዎችና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች አማረኛ ትምህርት አይሰጥም የሚል ...ትግራይ ክልል ደግሞ መቆሙን: ይገርማል የተባለው የተደረገውን እየተደረገ ያለውን ...ቋንቋን በበባእድ ሃገር ፊደል የመቀየጥ ስራ ...ፖለቲካ ስለሆነ ልለፈው....! ነገ ፖለቲከኞች ስቀየሩ አብሬሮ ይቀየራል በሚል ተስፋ :: አዝናለሁ የሀገሪቱን ክብር ከሚያጠፍት ትውልዶች ውስጥ እራሴን ስላገኝሁት አዝናለሁ.....
ምልከታየ እንደ አንድ ዜጋ ነው በቋንቋው ከመናገር ከመጻፉና ከማንበብ የዘለለ እማውቀው የጠለቀ እውቀት የለኝም:: በ ቋቋንቋወች ትምህርትን የገፋችሁ ካላችሁ ግን ዝም አትበሉ ተናገሩ ሰሚ ባይኖርም መናገራችሁ ግን ዋጋ አለው:: ተጻፈ:- ከ ማይምራን(ሮሃ)
…የነገር ማሰሪያው
የፀብ ማሳረጊያው የፍቅር ማኖሪያው
ልብ ና ልብ ነው::…
ያልደረቀ ጢናዳም አለ አሉ ሀገሩ ላይ!!
▪️"ዛሬ በዓለም ላይ ሰዎች ትንሽ ሰርተው ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ይጥራሉ። በመንፈስ ለመኖር የሚሞክሩትን ተመሳሳይ ስሜትም ብዙዎችን አስቀርቷል። ቅድስናን ማግኘት ይፈልጋሉ ነገር ግን ምንም ጥረት አያደርጉም "
* ▪️"ዛሬ፣ ጭራሽ አለመሆን ነገሰ። ሁሉም ሰው የሚኖረው በፉደል ሁኔታ ውስጥ ነው፣ በመንፈሳዊ መዝናናት ውስጥ ነው። ምንም አይነት ፍላጎት ቢያሳዩም ወደ ራሳቸው ቦርሳ እንጂ ወደ መልካም ነገር አይመራም። "
* ▪️"ዛሬ አንዱ የሌላውን ቦታ ለመያዝ ይተጋል። እኛም ወደ ሌላኛው ቦታ ገብተን እንድንረዳና ሰላሙን እንድናበዛ ተጠይቀናል። አሁን ሁሉም ስለ ሰላም እያወራ በዛው ልክ ቦምብ (ጦርነት)እያወራ ነው!
* ▪️“እግዚአብሔርን ያልወደደ ሰው ወላጆቹን፣ ጎረቤቶቹን፣ መንደሩን፣ ሀገሩን መውደድ ይተዋል፤ ምክንያቱም ሀገር ቤት አንድ ትልቅ ቤተሰብ ነውና። እንዲህ አይነት ሰው ሙሉ ለሙሉ ከንቱ ይሆናል.
* ▪️“ከዚህ በፊት፣ ማንኛውም ፈሪ ሌይማን ወይም ቄስ፣ ወይም ከዚህ በላይ መነኩሴ በዓለም ላይ እየሆነ ስላለው ነገር ቢጨነቁ፣ በተወሰኑ ግምብ ውስጥ መቆለፍ እንዳለባቸው ያስቡ ነበር። ዛሬ ደግሞ የማያገባችሁ በግምቡ ውስጥ ይቆለፉ ምክንያቱም የክርስቶስ ጠላቶች ሁሉን ሊያጠፉ ይፈልጋሉ። በሐዋርያት ዘመን ክርስቲያኖች ከአለም ሊለዩ ይችላሉ ምክንያቱም አለም ሁሉ ፓጋን ነበር የፓጋን ነበር እናም የፈለጉትን አደረጉ ከታላቁ ቆስጠንጢኖስ በኋላ ግን ነገሩ ተቀይሯል። አለምም ሄደ ክርስቲያን... ቤተ ክርስቲያን ነፃ ሆነች። አሁን ደግሞ ትልቅ ሀላፊነት አለብን። ይሄ ሁሉ የኛ ነው ዛሬ ደግሞ ሁሉንም ነገር ማጥፋት ይፈልጋሉ! ”
* ▪️"አክሱም የተቀደሰውን ታቦት መጀመሪያ አስቀመጠች። ዛሬ አክሱም ያላሰበችውን በኛ ስንፉና መሆን የለለበት ነገር ሆነባት ። እስኪ ተመልከቱት ዛሬ ሰዎች በሁሉም ነገር ወድቀዋል የምድርን ዋጋ ይፈልጋሉ። እኛ (ክርስቲያኖች) ይህን የሐሰት መንገድ መቃወም ይኖርብናል ።
ተጻፈ:- ከ ማይምራን (ሮሃ)
አንዳንዴ መሆን ያምረኛል.... ብቻ ያምረኛል እፈልጋለሁ እመኛለሁ ግን ሣልሆን እቀራለሁ የፈለኩት ካልፈለኩት ያሰብኩት ካላሰብኩት አንሶ እየበልጠ መኖሬ ቀጥሎ መሆኔ ተነነ::
እንዴት ካላችሁኝ እንደዚህ
ተጻፈ:- ከ ማይምራን (ሮሃ)
በል ተሎና ድረስ ከደጃችን
ከፈተን የያዝንበት ሳይዝል እጃችን
16ኛው ሰማይ ምጥቁ ጎዳችን ::
ግብዝ(7)
ግብዝነት ይታገለናል። እጅ ልንሰጥ ወይም ስም ልንቀይርለት ግን አይገባም። ራሳችንን ከሌሎች ጋር ማስተያየት እናቁም፤ ፊታችንን ወደ እግዚአብሔር እናቅና። ዓይናችንን በራሳችን ላይ እንዲገልጥ የእግዚአብሔርን መንፈስ እንማጠን። ማንም የሚያታልለን ሆነን እንዳንቀር፣ ብዙ ማስተዋል እንዲጨመርልን እንጸልይ። ቃሉ እንደሚነግረን፣ እንደ ወንጌል እውነት በቅንነት እንኑር። እንዳንሳብ ከግብዞች እንጠንቀቅ። እውነትን ከሚወዱና ለእውነት ከሚታዘዙ ጋር እንያያዝ። ጌታ አንድ ነው፤ ትልቅ አንድ ብቻውን የሆነ ኃያል እግዚአብሔር ነው። መለዋወጥ በርሱ ዘንድ የለም፣ በመዞርም የተደረገ ጥላ በርሱ ዘንድ የለም፣ እርሱ የብርሃናት አባት ነው፤ ብርሃን ነው፣ ጨለማም በርሱ ዘንድ ከቶ የለም፣ ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን፣ እውነትንም አናደርግም፤ ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፣ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል [ያዕ 1፡17፤1ኛ ዮሐ 1፡5-7] “በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ፤ ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ፤” [መዝ 96፡9]… ተፈጸመ:: የንባብ ህይወት( ምንጭ)
ተጻፈ:- ከ ማይምራን (ሮሃ)
ግብዝ(6)
ማንኛችንም ከግብዝነት የጠራን አይደለንም። እውነትን አውቀን ከእውነት ጋር ካልተጣበቅን፣ እውነትን ከመፍራት ይልቅ እውነትን ካልወደድን፣ ጸጋን ካልተለማመድን በስተቀር ከተገለጠልን እውነት ማፈግፈጋችን አይቀርም። ልንሰማ የምንፈልገውን የሚነግሩንን ብቻ መሰብሰብ እንጀምራለን። ግብዝነት በቅድሚያ ራስን ከማክበር ሰውን ከመፍራት ከሰዎች ጋር ተስማምቶ ለመኖር ከመፈለግ የሚመጣ ነው። ቅንነትና ትኅትና ሲጎድል ነው። እግዚአብሔር አንዱን ዘር ባሕልና ቋንቋ ከሌላው እንደማያበላልጥ ጴጥሮስ ተረድቶ ነበር። “ነገር ግን፣” ይላል ጳውሎስ፣ “ኬፋ [ጴጥሮስ] ወደ አንጾኪያ በመጣ ጊዜ ፊት ለፊት ተቃወምሁት፥ ይፈረድበት ዘንድ ይገባ ነበርና። አንዳንድ ከያዕቆብ ዘንድ ሳይመጡ ከአሕዛብ ጋር አብሮ ይበላ ነበርና፤ በመጡ ጊዜ ግን ከተገረዙት ወገን ያሉትን ፈርቶ ያፈገፍግ ነበርና ከእነርሱ ተለየ። የቀሩትም አይሁድ ደግሞ፥ በርናባስ ስንኳ በግብዝነታቸው እስከ ተሳበ ድረስ፥ ከእርሱ ጋር አብረው ግብዞች ሆኑ። ነገር ግን እንደ ወንጌል እውነት በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ በሁሉ ፊት ኬፋን። አንተ አይሁዳዊ ሳለህ በአይሁድ ኑሮ ያይደለ በአሕዛብ ኑሮ ብትኖር፥ አሕዛብ በአይሁድ ኑሮ ሊኖሩ እንዴት ግድ አልሃቸው? አልሁት” [ወደ ገላትያ ሰዎች 2፥11-14]። ጴጥሮስ ትኁት ሰው ነበረ፤ ከዚህ ሁኔታ ተማረ። በመጀመሪያ መልእክቱ [1፡22]፦ “ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ” ሲል የቀደሙንንና እኛን መከረ። ይቀጥላል... የንባብ ህይወት( ምንጭ)
ተጻፈ:- ከ ማይምራን (ሮሃ)
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana