Deleted channel

Description
WeCare is Ethiopia’s digital healthcare platform where treatment seekers can discover practitioners to directly book appointments for online consultation or in clinic visits.

[email protected]

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

1 year, 11 months ago

ነባር ሀገራዊ ተቋማትን ማፍረስ
ሀገርን ማፍረስ ነው !!!
----------------------------
(የግል አስተያየት)

ደቡብ ምእራብ ሸዋ ዞን ሶዶ ዳጬ ወረዳ (ከወሊሶ ከተማ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት) በምትገኘው ሀሮ በዓለወልድ ቤተክርስቲያን "ኦሮሚያ ቤተክህነት" አቀንቃኞች በቋንቋ እና በብሔር ማንነታቸው ብቻ "ለተመረጡ" 25 "ኤጲስ ጳጳሳት" ከቤተክርስቲያኒቱ ቀኖና ባፈነገጠ መንገድ ተሹመዋል።

ከአካባቢው እንደተሰማው ምእመናን ይህንን የቀኖና ጥሰት እና ተቋም የማፍረስ አካሄድ ለማስቆም ሲሄዱ ሿሚና ተሿሚዎቹ ታጣቂዎችን አሰልፈው እንደተገኙ እና ጦርነት ለመክፈት ዝግጁ እንደነበሩ ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ለሁለት ተከፍሎ የነበረውን ቅዱስ ሲኖዶስ በእርቅ ወደ አንድነት ለማምጣት ጠቅላይ ሚንስትሩ የሠሩትን በጎ ሥራ እንዳመሠገንነው ሁሉ ዛሬ ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን ለሁለት ሰንጥቆ (ያውም በብሔር አቧድኖ) እንደተቋም ለማፍረስ የተኬደበትን ርቀት በዝምታ ማየቱ፣ የተረከቡትን መንግሥታዊ ሥልጣን ተጠቅመው ከጀርባ ያደራጁ ኃይሎችን አደብ ለማስገዛት ፍላጎት ማጣቱ (ምናልባትም ግፉበት ማለቱ) አሳዛኝም አሳፋሪም ነው።

የኢትዮጵያዊ መልክ እና ሥሪት ያላቸው፣ ከዘር እና ከቋንቋ ማንነት ተሻግረው ዜጎችን አሰባሳቢ እና አስተባባሪ የሆኑ የሃይማኖት ተቋማት መሰንጠቅ፣ ማኮሰስ እና ምእመኖቻቸውን ማዋረድ ዳፋው ለሀገር እንደሚተርፍ ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት አይገባም።

ከሕገመንግሥታዊ ሥርዓት ውጪ "የሽግግር መንግሥት መሥርተናል" የሚሉ ዜጎች በሥውር ካቢኔ ሲያቋቁሙ ቢሰማ መንግሥት ተኝቶ ያድር ነበር? እንደ ሀገር ከምንላቁጥበት የብሔር ፖለቲካ አረንቋ ለመውጣት በምንፍጨረጨርበት ወቅት ሃይማኖትን ያህል ትልቅ ሀገራዊ ተቋም ጎትቶ የብሔር ንትርክ ውስጥ መጨመር አእምሮ ቢስነት ነው።

ይህንን የመሰለ ነውር እና ጋጠወጥነትን ለማረም እና ሕገወጦችን ተጠያቂ ለማድረግ ቀዳሚው ኃላፊነት የሕዝብን ሰላም እና አንድነት የማስከበር እና የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው መንግሥት ነው።

1 year, 11 months ago

“የኢትዮጵያ” ሕገመንግሥት !!!

ኢትዮጵያውያን በተጻፈ የሕገመንግሥት ሰነድ መተዳደር ከጀመርን 92 ዓመታት ተቆጥረዋል። በዚህ የአራት ትውልድ እድሜ ጉዞ አራት የተለያዩ ሕገመንግሥታት በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር በሥራ ላይ ቢውሉም አንዳቸውም “የኢትዮጵያ” ተብለው ለመጠራት የሞራል ልዕልና አልነበራቸውም። የቀደሙት ሁለቱ "የንጉሡ"፣ ሦስተኛው "የደርግ" አራተኛው "የሕወሓት" ሕገመንግሥት በመባል ይታወቃሉ። ለማስታወስ ያህል፦

1) የመጀመሪያው ሕገመንግሥት በ1923 ዓ.ም ከጣልያን ወረራ አስቀድሞ በንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ በሥራ ላይ እንዲውል ተደረገ።

2) ሁለተኛው ሕገ-መንግሥት ኢትዮጵያ ከጣሊያን ወረራ ነፃ ከወጣች በኋላ የ1923ቱን ሕገ- መንግሥት በማሻሻል በ1948 ዓ.ም ጸደቀ፡፡

3) ሦስተኛውና አጭር እድሜ የነበረው ሕገ-መንግሥት በ1979 ዓ.ም. የወታደራዊው ደርግ የፀደቀው ነው፡፡ ይህ ሕገ-መንግሥት በ1983 ዓ.ም የደርግ አገዛዝ ሲወድቅ ተሻረ፡፡

4) አራተኛው እና አሁን በሥራ ላይ ያለው የኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት በ1987 ዓ.ም በህወኃት መራሹ ኢህአዴግ የፀደቀው ነው፡፡

በንጉሡ ጊዜ የነበሩት ሁለቱ የሕገ መንግሥት ሠነዶች ንጉሡ እንደ ሙሴ ከፈጣሪ ተቀብለው ለኢትዮጵያውያን እንዳበረከቱ ተደርገው የሚትርኩ ነበሩ። (በዘመኑ ይሳሉ የነበሩ ሥዕሎችም ሆኑ የመጽሐፉ ሽፋን የሚያሳዩት በንጉሡ ዘመን የተጻፉት ሕገመንግሥታት በዜጎች ስምምነት የተጻፈ ሳይሆን ምልኮታዊ ሰጦታ ተደርጎ ነበር)

የደርግ ሕገመንግሥት በበኩሉ ተምኔታዊውን “የወዝአደሩን መብት” ለማስከበር የተጻፈ ሲሆን አሁን በሥራ ላይ ያለው አራተኛው የህወሓት ሕገመንግሥት ደግሞ ብሔረሰቦችን እንደ ጭራቅ ከተተረከላቸው "የብሔር ጭቆና" ነጻ ለማውጣት በሕወኃት ተጠንስሶ በአጋፋሪዎቿ ጭብጨባ በኢትዮጵያውያን ላይ ተጫነ።

እንደ ሀገር ለዘመናት ከምንታመስበትና ከማያባራው የእርስ በእርስ ጦርነት እንድናርፍ፣ በዓለም ሕዝብ ፊት አንገታችንን ከሚያስደፋን፤ አዋራጅ ከሆነው ችግር እና ችጋር እንድንወጣ፣ ዜጎች በነጻነት እና በክብር የሚኖሩበት ሀገር እንድትኖረን፤ ለሥርዓተ መንግሥት ግንባታ (State Building) ከሁሉም ሀገራዊ ኃይሎች ጋር በትብብር እና በጋራ መሥራት የጠይቃል፡፡

ኢትዮጵያውያን በአሸናፊዎች ጠመንጃ አፈሙዝ የተጻፉ ሕገመንግሥታት ሳይሆኑ ዜጎቸ በየደረጃው ተሳትፈውበት፣ ለኂቃን እና የፖልቲካ ኃይሎች በሰከነ እና በሠለጠነ ውይይት ተገናዝበው የሚጽፉት (የሚያሻሽሉት) "የኢትዮጵያ" የምንለው ሕገመንግሥት ያስፈልገናል።

ይህንን እንደምን ማሳካት ይቻል ይሆን?

ሁሉንም የፖለቲካ ኃይሎች እና ሌሎች ሀገራዊ ተዋንያንን በጠረጴዛ ዙሪያ የሚያሰባስብ እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር ማድረግ ከቻልን በቻ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ የልዩነት እና የግጭት መንስኤ የሆኑ የሕገ መንግሥቱ አንቀጾችን ማረም ስንችል፣ የኢትዮጵያውያን የዘመናት ምጥ የሆነውን “የኢትዮጵያ” የሚባል ሕገመንግሥት ማዋለድ ይቻላል።

ሕገ መንግሥቱ ሲሻሻል

- ዜጎች ያለምንም ስጋት በሀገሪቱ ሉዓላዊ ግዛት እንደልብ የመንቀሳቀስ፣ ሀብት የማፍራት፣ የመኖር መበታችው ይከበርላቸዋል፡፡

- ሀብት፣ ጉልበት እና ዕውቀትን በማስተባበር ለሚሊዮኖች የሥራ ዕድል መፍጠር እንችላለን፡፡

- ባለሀብቶች በፖለቲካ ወገንተኝነት፣ በሚናግሩት ቋነቋ ወይንም በብሔረሰባዊ ማነንታችው ሳይሆን ለሀገር እድገት እና ለወገን ፍቅር ባላቸው ሀቀኛ ተግባር የማይቋረጥ ድጋፍ የተትረፈረፈ ምርት የማምረት እድል ያገኛሉ፡፡

- ከሀገራዊ ፈጆታ የሚተርፈን ምርት ለፋብሪካዎቻቸን ጥሬ ዕቃ እና ለወጭ ምንዛሪ ምንጭ ይሆነናል፡፡

ይህ እንዲሳካ መሥራት፣ መወትወት እና በሚችሉት ሁሉ ማገዝ ሀገርን ከሚወዱ ዜጎች ሁሉ የሚጠበቅ የዚህ ትውልድ ዓይነተኛ ኃላፊነት ነው።

#በትብብር_መሥራት

2 years, 3 months ago

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) አመራሮች ከመስከረም 1- መስከረም 30 ያደረጉትን ቆይታ ይከታተሉ።

የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ ይደረጋል በተባለው የህወሓት እና መንግስት ድርድር ዙሪያ ከሸገር FM 102.1 ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያዳምጡ
https://t.me/ShegerFMRadio102_1/12185

የኢዜማ ትግራይ ክልል አስተባባሪ አንጋው ሲሳይ ይደረጋል በተባለው የህወሓት እና መንግስት ድርድር ዙሪያ ከፋና ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://www.facebook.com/139294240239063/posts/1283347465833729/?app=fbl

የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አንድነት ሽፈራው በ 2014 የነበረው የፖለቲካ ምህዳር እና በ 2015 ሊሻሻሉ ስለሚገባቸው ሁነቶች ከኢሳት ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ
https://youtu.be/mC9whHLRtyA ከ 9፡50 ጀምሮ

የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የአካል ጉዳተኞች መምሪያ ሐላፊ ማዕረጉ ግርማ ይደረጋል በተባለው የሕወሓት እና መንግስት ድርድር ዙርያ ከየኛ ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ

https://youtu.be/NX5Exyby_IE

የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አብርሃም በርታ (ዶ/ር) በሉዓላዊነት ዙርያ ከአሃዱ ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያዳምጡ

https://drive.google.com/file/d/1BOkshBz-X3Nl_DukRvIhf5WyrTIQ-o0I/view?usp=drivesdk

የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ እዮብ መሣፍንት ተመድ በኢትዮጵያ ላይ ያወጣውን የሰብዓዊ መብት ሪፖርት አስመልክቶ ከፋና ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያዳምጡ https://www.fanabc.com/%E1%8B%9C%E1%8A%93-%E1%8B%AB%E1%8B%B0%E1%88%9D%E1%8C%A1/ ከ 26:30-32:00 ያለውን ዘገባ ያድምጡ

የኢዜማ ሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል አወቀ አምዛዬ (ዶ/ር) ለኮሬ ሕዝብ ተደጋጋሚ ግድያ መንስኤው ምንድነው? በሚል ዙርያ ከአሻም ቲቪ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ይመልከቱ

https://youtu.be/BKn9-JPuZgU

የኢዜማ ሀገራዊ ምክክር ኮሚቴ ሰብሳቢ እዮብ መሣፍንት ዓለም አቀፍ ተቋማቶች በኢትዮጵያ ላይ በሚያንጸባርቁት አቋም ዙርያ ከኢፕድ ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ

https://drive.google.com/file/d/1Bn98njomh6SRY2zqBPXBKlz23Ee0JaGF/view?usp=drivesdk እና https://drive.google.com/file/d/1Bqcf0tqHBODLzRmQ4ut7et-eQ-NqBd1Q/view?usp=drivesdk

የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሐላፊ ዶ/ር ሙሉዓለም ተገኘወርቅ በሃገራዊ ጉዳይ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ https://www.ethiopianreporter.com/111076/

የኢዜማ ብሔራዊ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ግርማ ሰይፉ በሙስና እና ሀገራዊ ምክክር ዙሪያ ከሪፖርተር ጋር ያደረጉትን ቆይታ ያንብቡ
https://www.ethiopianreporter.com/111500/

Telegram

ሸገር 102.1(Sheger 102.1FM)

መስከረም 5፣2015 የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ አልቀበልም ብሎ 3ኛ ዙር ጦርነት ውስጥ መግባቱ የታወቀው ሕወሃት የሰላም ድርድሩ ሀሳብን ለመቀበል መዘጋጀቱ ከአለም አቀፍ ድርጅቶች እስከ ፖለቲካ ፓርቲዎች ድረስ በበጎ የመታሰቡ ነገር ከምን የመጣ ይሆን? የኔነህ ሲሳይ #Ethiopia #ShegerWerewoch #ኢዜማ #TPLF #ሰላም ሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች…

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana