AYA Media II አያ ሚዲያ

Description
AYA Media II አያ ሚዲያ

ትላንትን ማያ – ነገን ማደሽያ

ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @Haicrosoft ይላኩልን! እናመሰግናለን!

★ አነቃቂ መልዕክቶች
★ ማህበራዊ ጉዳዮች
★ ጠቃሚ መረጃዎች
የሚቀርቡበት ቻናል!

#አያ_ሚዲያ

https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 месяц, 2 недели назад

Last updated 1 неделя назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 месяца назад

2 months, 3 weeks ago

ትችት ለእድገት ወይስ ለክስረት?

በልጆች ላይ ከልክ ያለፈ ትችት ማብዛት በስነ-ልቦናቸው እና በማህበራዊ እድገታቸው ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተጽእኖ ይሳድራል።

ከእነዚህ ተፅዕኖዎች መካከል፡

1. ዝቅተኛ በራስ የመተማመን ስሜት ይፈጥራል፡

ዘውታሪና የማያቋርጥ ትችት የልጆችን በራስ የመተማመን ስሜት እና ችሎታን ይቀንሳል፤ ይህም ልጆች ብቃት እንደሌላቸው እንዲሰማቸው ያደርጋል።

2. ውድቀትን መፍራት፡

ትችት በበዛባቸው ቁጥር ውድቀትን በመፍራት አዳዲስ ነገሮችን ለመሞከርና ኃላፊነት ለመውሰድ ፍርሃት ያድርባቸዋል።

3. ከቤተሰብ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያበላሻል፡

የማያቋርጥ ትችት በልጆች እና በወላጆች መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ክፍተት ሊፈጥር ይችላል፤ ይህም ልጆች በወላጆቻቸው ላይ ያላቸውን የመተማመንን ስሜት እንዲያጡ እና ደጋፊ እንደሌላቸው እንዲሰማቸው በማድረግ ነው።

4. በትምህርታቸው ላይ ተጽእኖ ይፈጥራል፡
ለቋሚ ትችት የተጋለጡ ልጆች በሚፈጠርባቸው ጭንቀት እና ጫና ምክንያት የትምህርት ውጤት ማሽቆልቆል ሊያሳዩ ይችላሉ።

5. ለጭንቀት እና ድብርት ያጋልጣል፡

የማያቋርጥ ትችት ከፍተኛ ጭንቀት ሊፈጥርባቸው አልፎ ተርፎም በልጆች ላይ የመንፈስ ጭንቀት ሊያስከትል ይችላል።

እነዚህን አሉታዊ ተፅእኖዎች ለማስወገድ ትችታችን ገንቢ እና ባህሪያቸውን ለማሻሻል እንጂ ስብዕናቸው ላይ ያነጣጠረ አለመሆኑ ማስተዋል ተገቢ ነው።

በተጨማሪም ትችታችን በአዎንታዊ መመሪያ እና ቀጣይነት ካለው ድጋፍ ጋር ማቆራኘት ተገቢ ነው።

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ
#ስኬታማ_ማክረምት

? የመጪው ትውልድ ኃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

Telegram

Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ

Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya

**ትችት ለእድገት ወይስ ለክስረት?**
2 months, 3 weeks ago

ክረምቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ጠቃሚ ስንቅ!

ወዳጅ ዘመድዎን የሂዳያ ቤተሰብ እንዲሆኑ ይጋብዙ!

የልጆችዎን የክረምት ዕረፍት ስኬታማ በሆነ መልኩ ለማጠናቀቅ የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮች እነሆ፡

1⃣ የጊዜ አጠቃቀም፡-

የመጫወቻ፣ የመማሪያ እና የዕረፍት ጊዜን የሚያካትት ዕለታዊ ወይም ሳምንታዊ ፕሮግራም ያዘጋጁላቸው

2⃣ የንባብ ባህላቸውን ማዳበር፡-

ለልጆች ከዕድሜያቸው ጋር የሚስማሙ አስተማሪና አስደሳች መጽሐፍትን በማቅረብ እንዲያነቡ ያበረታቱ

3⃣ ከቤት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፡-

ልጆች ከቤት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለምሳሌ ብስክሌት መንዳት ወይም በውብ ተፈጥሯዊ ስፍራዎች መራመድ እንዲለማመዱ ማበረታታት

4⃣ እየተጫወቱ መማር፡

የልጆችን ችሎታ፣ ክህሎት እና ዕውቀት ለማሳደግ የሚረዱ ትምህርታዊ ጨዋታዎችን እና በእጅ የሚሰሩ እንቅስቃሴዎችን ማዘጋጀት

5⃣ የበጎ ፈቃደኝነት ስራ፡

ልጆችን የትብብር እና የኃላፊነት መንፈስን ለማሳደግ በበጎ ፈቃድ ተግባራት እንዲሳተፉ ማበረታታት

6⃣ ማህበራዊ ግንኙነት፡

ልጆች ከጓደኞቻቸው እና ከቤተሰብ አባላቶች ጋር በደንብ እንዲግባቡ እና እንዲጫወቱ የዚያራ ፕሮግራሞች ማመቻቸች

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ
#ስኬታማ_ክረምት

? የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው!
መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

Telegram

Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ

Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya

**ክረምቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ጠቃሚ ስንቅ!**
3 months, 3 weeks ago

ከአዲሱ"የሙሊም ልጆች ጋሻ" መጽሐፍ የውስጥ ገጾች በጥቅቲ!

https://t.me/HidayaTerbiyaPro/564?single

5 months, 1 week ago
በልጆች መካከል ፍትሀዊ መሆን

በልጆች መካከል ፍትሀዊ መሆን

በልጆች መካከል ፍትህን ማስፈን እንዲሁም በመካከላቸው ከማዳላትና በደል ፈፃሚ ከመሆን መታቀብ ልጆችን በመልካም ለማሳድግ አንገብጋቢና ወሳኝ ከሚባሉ ምሰሶዎች መካከል አንዱ ነው።

አንድ ወላጅ በልጆቹ መካከል ፍትሀዊ የማይሆን ከሆነ በልጆች መካከል እርስ በእርስ መጠላላት ፣ ምቀኝነትና ጥላቻ እንዲፈጠር ያደርጋል።

በተቃራኒው ደግሞ በመካከላቸው ፍትሀዊ ለመሆን ጥረት ባደረጉ ቁጥር በልጆች መካከል መዋደድና መፋቀር እንዲኖር እንዲሁም ለወላጆቻቸው መልካም እንዲሆኑ ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደርጋል።

ይህን ወሳኝ መርህ አስመልክተው የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል፦

: «فَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْدِلُوا بَيْنَ أَوْلاَدِكُمْ»،

"አላህን ፍሩ! በልጆቻችሁ መካከል ፍትሀዊ ሁኑ" አሉ ።
(አል’ቡኻሪይ ሰሒሓቸው ላይ በቁጥር 2587 ዘግበውታል።)

? "መልካም የልጆች አስተዳደግ" በሚል ርዕስ በሂዳያ ተርቢያ ከተዘጋጀ ያልታተመ መጽሐፍ የተወሰደ!

ምርጥ ወላጅ I #ለወላጆች I
ምርጥ እናት I #ለእናቶች I
ምርጥ አባት I #ለአባቶች I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

5 months, 1 week ago

? አስርቱ የዙልሒጃ ወርቃማ ቀናት

? በሂዳያ ተርቢያ

? ዙልሒጃ 01/12/1445

? #HidayaPublication

⭐️ https://t.me/HidayaTerbiya ⭐️

5 months, 1 week ago
***?*** የዙልሒጃ ሀዲያ ከሂዳያ ተርቢያ! ***?***

? የዙልሒጃ ሀዲያ ከሂዳያ ተርቢያ! ?

https://t.me/HidayaTerbiya

"የዱኒያ በላጭ ቀናት"

አስርቱ የዙልሒጃ ወርቃማ ቀናት ደጃቻችን ቆመዋል..

አስር የንስሐ እና የይቅርታ ቀናት!

የዙልሒጃህ ጨረቃ ከመውጣቱ በፊት ኒያችንን እናድስ!

አስሩን ቀናት በተውበት፣ በፆም፣ በሰላት፣ በዱዓእ ለማሳለፍ በአዲስ መንፈስ እንዘጋጅ!

በተክቢር፣ በተሕሚድ፣ በተህሊል፣ በተስቢሕ ምድርን ከአፅናፍ አፅናፍ ለማድመቅ እንታጠቅ!

እነዚህን አሥርት አላህ ዘንድ በጣም ተወዳጅ የሆኑ ቀናት በስኬት ለማጠናቀቅ የሚረዳ #ቡክሌት ዛሬ ማታ በአላህ ፈቃድ በሂዳያ ተርቢያ የቴሌግራም ቻናል ይዘንላችሁ እንቀርባለን!

ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ወደ ቻናሉ በመጋበዝ እና ሼር በማድረግ የመልካም ሥራ አጋዥ ይሁኑን!

ምርጥ ቀናት I #ዙልሒጃ I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

10 months, 2 weeks ago

https://youtube.com/shorts/mnKOt7tnRCQ?si=L7UpW0VcPZkhTzuW

YouTube

የልብ ንፅህና II ኡስታዝ ሱልጣን ኸድር

AYA Media II አያ ሚዲያ
2 years, 3 months ago
***?***አስደሳች ዜና ለዒልም ፈላጊዎች!

?አስደሳች ዜና ለዒልም ፈላጊዎች!

በኡስታዝ ሱለይማን ዐብደላህ የሚሰጡ ቋሚ ትምህርቶችን በቴሌግራን Live ይከታተሉ።

የሚሰጡ ትምህርቶች፦

? የቁርኣን ተፍሲር

ዘወትር ረቡዕ ከ4:30 እስከ ዙሁር

? አል’ዐርበዑነ ፊ–ል’አሕካም

ቅዳሜ ከዐስር ሰላት በኋላ እስከ 12:00

? ቻናሉን በማስተዋወቅ የኸይር ተቋዳሽ ይሁኑ!

?@ustazsuleyman

2 years, 3 months ago

? የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ ?

ወቅቱ ክረምትና የረፍት ጊዜ እንደመሆኑ መጠን

? ወላጆች ልጆቼ ጊዜያቸውን በምን ያሳልፉ ይሆን? የዲን ትምህርት የት ላስተምራቸው? ብለው የሚጨነቁበት ነው።

? ልጆችም በፊናቸው የትና በምን እንደሚያሳልፉ የሚብሰለሰሉበት ወቅት ነው!

እነሆ! ይህን ጭንቀታችሁን የምታቃልሉበት መፍትሄ ይዘን ከተፍ ብለናል!

ክረምቱን የዲን ዕውቀት ስንቅ የምትሰነቁበት ልዩ ገፀ በረከት!

? የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ!

በአካል ሄደው መማር ለማይችሉ ዕድሜያቸው ከ8 -13 ላሉ ታዳጊዎች የተዘጋጀ አዲስ መጽሐፍ አዲስ የክረምት ኮርሰ በነሲሓ ቲቪ!

? ይህ ኮርስ ለታዳጊዎች እንዲሆን ታስቦ ቀለ ባለና ልዩ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ለኮርሱ መስጫ አጋዥ መጽሐፍም ተሰናድቷል።

መጽሐፉ በውስጡ የዐቂዳ፣ ፊቅህ፣ ሲራ እና አደብ ትምህርቶችን ከመመዘኛ ጥያቄዎችን ጋር አካቶ ይዟል።

የመጽሐፉ ማብራሪያ ፕሮግራም በነሲሓ ቴሌቪዥን ይቀርባል።

? መጽሐፉን፦

ቤተል ነሲሓ ቲቪ ቢሮ እና

በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ቅርንጫፍ ጣቢያዎች ማግኘት ትችላላችሁ!

ለበለጠ መረጃ ስልክ፦
09 30 484284

አዘጋጅ፦ ሂዳያ ተርቢያ ከነሲሓ ቲቪ ጋር በመተባበር!

ምርጥ ትውልድ I #ክረምት #ኮርስ I

I #ሂዳያ #Hidaya #ተርቢያ #Terbiya I

? https://t.me/HidayaTerbiya ?

Telegram

Hidaya Terbiya II ሂዳያ ተርቢያ

Hidaya Terbiya ሂዳያ ተርቢያ የመልካም ትውልድ ማፍርያ! @HidayaTerbiya

***?*** የሂዳያ ስንቅ በነሲሓ ***?***
2 years, 4 months ago

የዐረፋ ቀን ዱዓ

ከዐብደላህ ብን ዐምር ብን አል’ዐስ እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦

وعن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال

((خَيْرُ الدُّعَاءِ دُعَاءُ يَوْمِ عَرَفَةَ ، وَخَيْرُ مَا قُلْتُ أَنَا وَالنَّبِيُّونَ مِنْ قَبْلِي : لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ))

رواه الترمذي ( 3585 ) وحسَّنه الألباني في " صحيح الترغيب " ( 1536 ) .

{ ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ እለት ዱዓእ ነው:: እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩ ነብያት ከተናገሩት መካከል በላጩ ቃል :- ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ፣ እርሱም ብቸኛና አጋር የሌለው ነው  ንግስናም ምስጋናም ለእረሱ ነው እርሱም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው የሚለው ቃል ነው:: }

(ቲርሚዚይ (3585) ዘግበውታል ፤ ኢማሙ አልባኒ ሰሒሕ አት’ተርጊብ (1536) ላይ ሐዲሡን ሐሰን ብለውታል።)

https://t.me/AYAMedia

Telegram

AYA Media II አያ ሚዲያ

AYA Media II አያ ሚዲያ ትላንትን ማያ – ነገን ማደሽያ ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @Haicrosoft ይላኩልን! እናመሰግናለን! ★ አነቃቂ መልዕክቶች ★ ማህበራዊ ጉዳዮች ★ ጠቃሚ መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል! #አያ\_ሚዲያ https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv

የዐረፋ ቀን ዱዓ
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 месяц, 2 недели назад

Last updated 1 неделя назад

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 месяца назад