Nova'

Description
ከባርነት ነፃነት ትከብዳለች።
ብዙዎች ነፃነትን ሽጠው እስትንፋስ ይገዛሉ።
እኔ ግን እስትንፋሴን በነፃነት እለውጣታለሁ።

!
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 week, 2 days ago

Last updated 4 days, 6 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 weeks, 1 day ago

1 week, 3 days ago

እውነት በዝምታና በመኖር የሚገለጽ ነው ።

የሀገሩ የሮምንና የግሪካዊያንን ፍልስፍና ጠንቅቆ የሚያውቀው ጴንጤናዊው ጲላጦስ የናዝሪቱን እየሱስ የጠየቀው ጥያቄ ነበር "እውነት ምንድን ነው ?" ይህንን ጥያቄ የተጠየቀው ከገዥው ፊት ወንጀለኛ ተብሎ የቆመው ያ ብሩህ ወጣትም ዝም አለ ። ዝምታው ለምን ይሆን ? እውነትን ስለማያውቅ ? ወይስ እውነት በቃላት ስለማትገለፅ ? እውነት በቃላት የሚገለጽ ነገር አይደለም ። በዚህም ሳቢያ እየሱስ ዝም አለ ።

"አንተስ እውነት ምንድን ነው ?" ተብለህ ብትጠየቅ ምን ትመልሳለህ ? በእርግጠኝነት እንደ እየሱስ ክርስቶስ ዝም አትልም ። ምክንያቱም ብዙ የምታውቅ ነው የሚመስልህ እናም ብዙ መልሶች ይኖሩሀል ። የሚያሳዝነው ግን ሁሉም መልሶች የአንተ አይደሉም ከተለያዩ ሰዎችና መፅሐፍት የቃረምካቸው ናቸው ። ስለ እውነት ብዙ ስትናገር እውነት እንዳልገባህ አንዱ ምልክት ነው ። እውነት በዝምታ ፣ እውነት በመኖር የሚገለጽ ነው ።

ስለ እውነት አብዝተው የሚያወሩት እነርሱ ከእውነት በእጅጉ የራቁ ናቸው ። እውነትን የተረዳ ቃላት አጥረውት ለመናገር ይቸገራል ። ሁኖም በኑሮው ውስጥ ፣ በሚያደርጋቸው ነገሮች የገባውን እውነት ይገልጻል ።

ሰራው እሱባለው

.

1 week, 6 days ago

.
.
ውዴ! ስለ አንዲት ወፍ ላጫውትሽ ነው። የእሷን ህይወት አስተውለሽ የእኛን በአያሌው እንድትቆዝሚበት እነሆ! ስለ ብላክ ፖል ላውጋልሽ። ይህቺ ተአምረኛ ብላክ ፖል በእኛ አገር ድንቢጥ የምንላት ዓይነት ነች። የአካሏ ክብደት 20 ግራም ይመዝናል። ያ ማለት የአንቺን አውራ ጣት ነው የምታክለው። ብላክ ፖል በየዓመቱ ከአላስካ እስከ ብራዚል 12,000 ኪሎ ሜትር ትበርራለች። በረራዋን የምትጀምረው ከአሜሪካን ጠረፍ ከአላስካ ነው። 3000 ኪሎ ሜትር እንደበረረች ሃሊፋክስ ዪ  ኤስ ወይም በካናዳዋ ኬፕ ኮድ ደርሳ በሰሜን አትላንቲክ ዳርቻ ዕረፍት ታደርጋለች። በዚህ ረጅም ጉዞ ከአካሏ ላይ የተወሰኑ ግራሞች ቀንሰዋል። ያን የከሳ አካልዋን እንደገና ለመጠገን፣ ለአስራ አምስት ቀናት ባረፈችበት እየበላችና እየጠጣች ትቆያለች።

ቆይታዋ ሁለት ዓላማዎች አሉት ፤ አንደኛው ቀደም ብዬ እንዳወጋሁሽ አካሏን እንዲያገግም ማድረግ እና ከፊት ለሚጠብቃት ብርድ፣ ቅዝቃዜ፣ ጨለማና ረጅም አታካች ጉዞ አካሏን በማሳረፍ ማዘጋጀት ነው። ሁለተኛው በዚያን ወቅት የሚነሳ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ አለ ፤ ይህ ማዕበል ሲነሳ ከሰሜን ምስራቅ የጀምረው ልክ አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ሲደርስ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫን ይይዛል። በዚህ ቅፅበት ያቺ ተአምረኛ ፍጥረት ጉዞዋ ወደ ምስራቅ ስለሆነ ዘልላ ነፋሱ ላይ ጉብ በማለት ሠረገላዋ ታደርገዋለች።

በዚህ የተፈጥሮ ሰረገላዋ ምንም ሳትደክም፣ ክንፏን ሳትጠቀም፣ ሽው ብላ በአያሌው ትበራለች። በተፈጥሮ ሰረገላው ውስጥ ተደላድላ እየበረረች ቀን በፀሐይ ብርሃን፣ ሌት በከዋክብት አማካኝነት አቅጣጫዋን እየለየች የሰመረ ጉዞዋን ታከናውናለች። ማዕበሉ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫን ሲለውጥ ጉዞዋ ወደ ደቡብ ስለሆነ ክንፎቿን በመጠቀም ወደ ብራዚል በረራዋን ታከናውናለች።

ይህ ጉዞ ሥስት ቀንና ሌሊት ይፈጃል። በዚህ በረራ ወቅት ማረፍ የሚባል ሃሳብ በፍፁም የለም። ልረፍ ብትልም 2,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የውቅያኖስ ፅንፍ አልባ መስክ ነው ከሥሯ ያለው። ሁለት ሌሊትና ሁለት መአልት እንደበረረች ከሥሯ የጉንዳን ምላስ የሚያካክሉ የቤርሙዳ ትሪያንግል ደሴቶችን ታገኛለች። ይህቺ ተዓምረኛ ወፍ ግን ግቧ ብራዚል መድረስ ስለሆነ ደሴቱን ቁልቁል እያየች ታልፋቸዋለች። ቤርሙዳ ትሪያንግልን ወደኋላ ትታ 2,000 ኪሎ ሜትር እንደበረረች፣ ከሥሯ የፖርቶሪኮንና አንቲሊስ ደሴቶች ታገኛለች። እነሱንም አልፋ በተጨማሪ 3,000 ኪሎ ሜትር በርራ አትላንቲክ ውቅያኖስን ፉት በማለት የዘር ማንዘሯ መኖሪያ በሆነው ብራዚል ስትደርስ ረጅሙን 12,000 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነውን ጉዞዋን ታጠናቅቃለች። ይህ ምንጊዜም የዓመት አንዴ የምታካሂደው በረራ ነው።

የምወድሽ! ይህቺን ተአምረኛ ፍጥረት አየሺልኝ። ይህ የሰው ልጆችን ሲመታን ድራሻችንን የሚያጠፋንን ማዕበል እንዴት አድርጋ ሰረገላዋ ልታደርገው ደፈረች? በዚያ አስደንጋጭ ፍጥነት ሲፈተለክ እሷ ግን አቅጣጫዋን አሳምራ እየለየች መዳረሻዋ ዘንድ ትደርሳለች። የሰው ልጆች ዘንድ ስንመጣ ብላክ ፖልን ስንት እጥፍ እየበለጥናት ያለንበትን ዓለም ሳናውቀው፣ ሳንፈትሸውና ምን መሆን እንደምንችል ሳንረዳ መደምደሚያችን ላይ እንደርሳለን።

ፍቅሬ! እኔ ግን ብላክ ፖል መሆን አሻኝ። መሆንም ወስኜ እነሆ እየበረርኩልሽ ነው።

*                *                 *

መልህቅ
(ገፅ፡ 370 - 380)
ዘነበ ወላ

2 weeks, 6 days ago

በጓደኞችህ ብዙ እምነት አታሳድር፤ ጠላትህን እንዴት እንደምትጠቀምበት እወቅ!

ጓደኞችህን ስጋ፣ ተጠንቀቅ በፍጥነት ሊከዱህ ይችላሉና በቀላሉ ለቅናት ስለሚጋለጡ። ሞልቃቃ፣ ባለጌና አምባገነንም ይሆናሉና። የቀድሞ ጠላትህን ቅጠረው ከጓደኞችህ የበለጠ ታማኝ ይሆንልሃል ምክንያቱም ማረጋገጥ አለበትና። በእርግጥ ከጠላትህ አብልጠህ መፍራት ያለብህ ጓደኛህን ነው። ጠላት ሚዋጋህ ፊት ለፊት ነው ጓደኛህ ግን ከጀርባህ ይወጋሃል። ጠላት ከሌለህም ጠላት ምታፈራበትን መንገድ ፈልግ።

The 48 Laws of Power.
Robert Green

3 months, 2 weeks ago

መሬት, ፀሓይና ጨረቃ የዘመን መለወጫ ይሠራሉ:: የዘመን መቁጠሪያ ከሰው አቅም ውጭ ነው:: ጨረቃ በ28 ቀናት 12 ከዋክብትን ተከትላ ትዞራለች:: ይህ ወራትና ሳምንታትን ይፈጥራል:: መሬት እና ፀሓይ በ365 ደረጃዎች (ቀናት) የሚዘዋወሩበት ምሕዋር አላቸው:: እነዚህ ሁሉ ያለመዛነፍ ያለማንም ፍጡር ጣልቃ ገብነት ምሕዋራቸውን ጠብቀው ይዞራሉ:: የዓመታት መቁጠሪያ ቀርቶ ሰዓትና ሰኮንድ ከእነዚህ ነው የሚቀዳው:: ምክንያቱም perfect ስለሆኑ:: ሦስቱ አራት ወቅቶች (ክረምት, ፀደይ, በልግና በጋ) ይፈጥራሉ:: ዛሬ የነበሩበት ትይዩ ላይ ለመድረስ አራት ዐመታት ወይም 1,460 ሲደመር 1 ቀን (ዲግሪ) ይፈጅባቸዋል::

ሦስቱም አካላት የማንም የግል ንብረት አይደሉም:: እምነት ቢኖርም ባይኖርም ቆጣሪ ቢፈጠርም ባይፈጠርም ይኸው ሁኔታ ለሚሊዮኖች ዐመታት ነበር:: ይቀጥላል:: በሂጅሪያም ቁጠር በግሪጎሪያ, በሕንድም ቁጠር በዞሮስትሪያ ቆጣሪዎቹ ሰዎች ሳይሆኑ እነዚህ ግዙፍ ፍጡራን ናቸው:: መጋጨት አትችልም:: አይንጋ ብትል ፀሓይ ባንተ እጅ አይደለችም:: ከ12 ወራት በላይ ልጨምር ብትልም አይመጣም:: የሦስቱ አካላት ሽግግር ወደ ቁጥር ለመቀየር የተለያዩ ዘዴዎችን ተጠቅመዋል:: በጀትም ይሁን ጸሎት ጋብቻም ይሁን ውልደት ሳይቀር የእነዚህ ጥገኛ ናቸው:: 12ቱንም የጨረቃ መዞሪያ ቡሩጆች እኩል 30 ቀናት ከሰጠን 5 ዲግሪ (ቀናት) ክፍት ይመጣል:: Perfect ዙር ግን 4 ዓመታት ይፈጃል:: ይህ እንዴት ይቻቻል የሚለው የተለያዩ ሀገራት የተለያየ ዘዴ ተጠቅመዋል:: በአንድ ክብ ላይ የሚመጣው ክፍተት አለ:: ማትስ ጂዖሜትሪ ውስጥ ይወስደናል:: የሦስቱ ክብ አካላት ክፍተት ደግሞ ጳጉሜ አድርገው የሄዱ አሉ:: በየወራቱ የሸጎጡም አሉ::

ለዘመን መለወጫ እየጠፉ ብቅ የሚሉ ከዋክብት የተጠቀሙ ብዙ ናቸው:: ባነበብኩት ግብጾችና ፋርሶች እንዲሁም ከፊል ዐረቦች ሺዕራ (ሲሪየስ) የሚባለውን የንጋት ኮከብ ይጠቀሙና ያመልኩም ነበር:: ግብጾች ሺዕራ ኮከብ ስትቀርብ የዓባይ መነሻ ሀገራት ላይ ክረምት እንደገባ አውቀው ይዘጋጁና ይገብሩ ነበር:: ከሦስቱ አካላት አልፎ ከዋክብትም ምሕዋሩን ጠብቀው ይንቀሳቀሳሉ:: የሕዋው ቋንቋ ቁጥር ነው:: እኛ ሕዳር እንበል ጁላይ ፕላኔቶቹ አያውቁም:: ሰው በ28 ፊደላትና በ7 አናባቢ ይተረጉማቸዋል:: በሌላ አነጋገር እኛ ነን እነርሱን ፕላኔቶቹን ተርጉመን የምንከተለው::

ኢትዮጵያ የምትከተለው ቀመር one of the perfect and ideal ቀመር ነው ይባላል:: የሰዓት አቆጣጠራችንም ልዩ ነው:: ፀሐይ ስትወጣ ጀምረን 1 እንልና ስትጠልቅ 12 እንላለን:: ፈረንጆች ከእኩለ ሌሊት ይጀምራሉ:: የእኛ perfect ነው:: ይህንን ቀመር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቀመር ሆኖ ያገለግላል:: የኢትዮጵያ ዓመታዊ በጀት ዓመቱ የሺዕራ ኮከብ ለምድር መቃረቢያ ሐምሌ ላይ ሲሆን የዘመን መለወጫው ክረምት ሲወጣ መስከረም 1 ላይ ነው:: ጉራጌዎች አሁን ሕዳር አጋማሽ ላይ ናቸው::

እንኳን ለ2017 አደረሳችሁ:: 2018ን በሰላም አደረሳችሁ ለማለት ያብቃን:: በሰላም ስንል በጦ^ርነት የከረሙት ይከፋሉ::

Hassen Injamo

4 months, 4 weeks ago

ኦሾ  ..

የዚህን ሰውዬ መፅሃፍ ካነበብክማ ታብዳለህ (የሚባልለት) ኦሾ  ያነበበዉን  ያክል  መጽሐፍ  ባይጽፍም  ነገር ግን ከ 100 ሺህ በላይ መፅሃፍትን አንብቤያለሁ! በቀን  ውስጥ ቢያንስ ከስድስት ያላነሱ መፅሃፍትን እጨርስ ነበር!  ይላል! "  "Enlightenment" ይለዋል !

የሰው ልጅ ጥልቅ ሃይል እንዳለው በራሱ መንገድ እውነትን ፈልጎ ማግኘት እንደሚገባው በነፃነት መኖር እና ፍቅርን በነፃ ሰጥቶ መቀበል እንዳለበት ያምናል ያስተምራል።

ወሲብ ነፃ መሆን እንዳለበት እና አንድ ሰው ካሻው ከማንኛው ሰው ጋር መመቻቸት እንዳለበት ያምናል "ትዳር" የሚባል ተቋም በጭራሽ እንደማያስፈልግም ያስተምራል ብችል "ትዳር" የሚባለው ተቋም ከምድረ ገፅ ባጠፋው ደስ ይለኛል ይላል! አብዛኛዎቹ የዓለማችን ችግሮች የሚመነጩት ትዳር ከሚባል ቆሻሻ ተቋም ነው ብሎ ሽንጡን ገትሮም ይከራከራል!።

"Meditation" እና "Therapy" የሰው ልጆች ቁልፍ መዳኛ መንገዶች እንደሆኑም ያምናል!
ለዚህ ሰውዬ እዚህ መድረስም መውደቅም ትልቁን አስተዋፅኦ ያበረከተች አንዲት ገራሚ ሴት አለች! "Sheela" ትባላለች በትውልድ ህንዳዊት ናት! ለሷም ፀለየላት "Meditate' አስደረጋት የህይወት ፍልስፍናውን አስተማራት እሷ ግን በነዚህ ነገሮች ብዙም አልተመሰጠችም ሰውየው ያለውን አቅም "ዓለም አቀፋዊ እንዲያደርገው ፈለገች የሰውየው የህይወት ፍልስፍና በወቅቱ ከነበረው የህንድ መንግስት ጋርም ብዙ ሰጣ ገባ ውስጥ እየከተተው ስለነበር ደህንነቱ አሳሳቢ ሆነ! "Sheela" እንዲህ አለችው! ". ...

ለምን ወደ ነፃነቷ ምድር "አሜሪካ" አንሄድም? ለምን "አሜሪካ" ውስጥ ሰፊ መሬት ገዝተን የራሳችንን የተቀደሰች ከተማ አንገነባም? ፍቅር፣ ርህራሄ እና መካፈል የበዛባት ማንም ምንም ነገር ባለቤት የማይሆንባት፣ ስግብግብነት ፅዩፍ የሆነባት፣ የቃል ኪዳን ከተማን አንገነባም? " ብላ መከረችው! ተስማሙ! በአሜሪካ "Oregon" ግዛት "Antelope" የምትባል መንደር ውስጥ 64 ሺህ ሄክታር መሬት ገዙ! አብዛኛዎቹ የ "osho" ፍልስፍና ተከታዮች የተማሩ እና ሀብታም ስለነበሩ ከተማዋን ለመገንባት ብዙ ግዜ አልፈጀባቸውም። የሰውየው "ቃል አቀባይየሆነችው  "Sheela" "osho"ን ለመከተል የመጡትን ባለሃብቶች፣ ኮንትራክተሮች እና አርክቴክቶች አሰባስባ ያለመችውን ከተማ አስገነባቻቸው። የከተማዋን ስምም የ" Rajneesh ከተማ" አሏት። ቀስ በቀስ የራሳቸውን ባንክ፣ የራሳቸውን አየር ማረፊያ፣ ግድብ፣ አውሮፕላኖች፣ ግዙፍ ዘመናዊ እርሻዎች፣ እንስሳት ማርቢያዎች እና ሰው ሰራሽ ሃይቆች ሳይቀር ሰሩ!.....ቀሪውን ፊልሙ ላይ ማየት ነው ....... *** «ናፖሊዮን ሂል 'Think and Grow Rich' የተባለ መፅሐፉን በመሸጥ እንጂ እንደሚያወራው ቀና አስተሳሰቡ አልነበረም ያበለፀገው፡፡ የሀብቱ መነሻ በመላው አለም የሚገኙ የዋሆች መፅሀፉን ስለገዙለት ነበር።» ይለናል Bhagwan Shree Rajneesh Osho ህዝቦቼ አለምን በፌሽታ በደስታ በዳንስ በዜማ እንዲሞሉዋት እፈልጋለሁ።

እኛ አንዳች መንግስተሰማያትን አይደለም የምንፈልገው እኛ የምንፈልገው መንግስተሰማያትን እዚሁ መፍጠር ነው ምክንያቱም እኛ ከሞት በኃላ ስላለ ነገር አይደለም ፍላጎታችን እዚሁ መንግስተሰማያትን መፍጠር ከቻልን በርግጠኝነት በገሀነም ከተገናኘን እዛም መንግስተሰማያትን መፍጠር አያቅተንም

osho

5 months ago

ለአሜን የተፈጠርን
( ካሊድ አቅሉ)

ሰፈራቸው መታጠፍያ ጋር ሆኜ ወደ በራቸው ሳማትር ሰዎች ተባብረው ድንኳን ሲተክሉ አየው ።
ምን ተፈጥሮ ይሆን ብዬ ለማጣራት ወደ ግቢያቸው ስጠጋ እልልታና ጭብጨባ በሙዚቃ መሳርያ ታጅቦ ሌላ ገፅታ አላብሶታል ፤ ለካ አጢነው ከሰሙት " አለምሽ ዛሬ ነው ዛሬ " የሚለው የሰርግ ዜማ ከሙሾ በላይ ያስነባል ነገሩ ዛሬያችን እራሱ ትናንታችን የገፋው ግሳንግስ የሚሆንበት ወቅት አለ አይደል •••

የወደፊትዋ ሚስቴ ብዬ በልቤ መዝገብ አድምቄ የፃፍኳት ልጅ " የአቶ እንትና ባለቤት " ለመባል በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶችን ምትጠባበቅ  እጩ ሙሽራ መሆንዋን ቤታቸው በዜማ ነገረኝ ብዙ ግዜ ያገኘሁት እሷ እስክትመጣ አተኩሬ ያየሁት ደማቅ ጥቁር በራቸው ብዙ እንዳንኳኳሁት አሻራዬን ያላሳረፍኩበት ለመምሰል አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬቱን እያየ "እኔ ምን ላርግ አልከፈትም አልንኳኳም ማለት አልችል !" ያለኝ መሰለኝ ነገሩ እኛስ ህይወት እንደ ከረንቡላ ኳስ ወዳሻት ጉርጓድ ምትወረውረን ከተዘጋጀልን ነገር የማንሸሽ ሰዎች አይደለን ከ "ለምን?"  ይልቅ "ለአሜን" የተፈጠርን። በራሴ እጅ የፃፍኩት ጉም ተስፋ ከተረት ተረት እንዳልዘለልን ተረዳውና ፈጣሪ የከተበልኝን አዲስ ምዕራፍ ለመግለጥ ቤታቸውን ትቼ እራሴን ለማግኘት ጉዞ ጀመርኩኝ ••••••

6 months ago

**ፊት ለፊቴ ተቀምጣለች … ሸገር ባስ ውስጥ መጨረሻ አካባቢ ፊት ለፊት የሚያፋጥጠው ወንበር ተፋጠን ተቀምጠናል … በስርቆሽ ቀና እያለች ታየኛለች … አይኔን ተክዬባታለሁ …ቆንጅዬ ናት …

“ሰዓት ይዘሻል !..”
“እንዴ አንተኮ አስረሃል …!” እየሳቀች
“ኦው …የኔን ሰዓት ስለማላምናት ነው …!”
“እንዴዴዴዴዴዴ ካላመንካት ለምን እጅህ ላይ አሰርካት …!?” ፊቷ ላይ ግርምት ልትቀባ እያኮበኮበች…
“ስለምታምር … ደግሞ በጣም የማከብረው ሰው ሽልማት ስለሆነ …”
“ኦው እንደዛ ከሆነ ጥሩ … በጣም የምታከብረው ሰው መሆን አለበት …!”
“አዎ …ኧረ እንደውም የቴዲ አፍሮ ስጦታ ናት … እሱ ነው ከእጁ አውልቆ የሸለመኝ …” ኮፈስ ብዬ … አይኗ ሲበለጠጥ አየሁ … እግሮቿን ወደኔ አዞረቻቸው … ከንፈሯን በምላሷ ማረጣጠብ … ምናምን ምናምን

“እንዴ የምርህን ነው !.. እስቲ እስቲ … እንዴት ሸለመህ … ማለት አንተም ዘፋኝ ነህ …!” … እጄ ላይ ያለችውን ሰዓት እጄን እያገላበጠች አየቻት ..
“እንደዛ ነገር ….” ኮፈስ ብዬ…” እሱ ባለበት መደረክ ላይ አንድ ሙዚቃውን ተጫወትኩ … መጣና ይህን እኔ በመዝፈኔ እንድቆጭ አደረከኝ …ዘፈኔ ትክክለኛውን ዘፋኝ አገኘ …ብሎ አቅፎኝ አለቀሰ..”
“የምርህን ነው !”
“ያ !... ከዛ እጁ ላይ አድርጓት የነበረችውን እቺን ሰዓት አውልቆ ሸለመኝ….”… አጠገቤ ያለው ሰውዬ ተነስቶ ሲወርድ ባዶ ቦታው ላይ ተሸቀዳድማ አጠገቤ ተቀመጠች … ጠረኗ መቼም ሙት ይቀሰቅሳል … ደስ አለኝ …
“በናትህ ትንሽ አንጎራጉርልኝ …እ!” አይኖቿን በሃዘኔታ አንከባለለቻቸው ….ስታሳዝን
“እዚህ !... ኧረ አይሆንም!... “ ተግደረደርኩ …

“በናትህ አንዴ ብቻ እ!.. ትንሽ ለኔ ብቻ እንዲሰማኝ አድርገህ እ… ደሞ የማደርግልህን አታውቅም … “ (ጉንጭሽን አስሚኝ …ጡትሽን አስነኪኝ ብላት እሺ ትለኛለች …)

“ ሄይ ሰውዬ አይንህን ገልጠህ ታንቀላፋለህ እንዴ !... መጨረሻው ነውኮ … “ የሚፈቀፈቅ ቆርቆሮ ያለው ድምፅ ከሃሳቤ አናጠበኝ … ብንን ብዬ ስነሳ ፊትለፊቴ ባዶዶደዶዶ የቆመ አውቶብስ ውስጥ እኔ ሹፌሩና ቲኬተሩ ተፋጠናል …
(ይሄ አጉል ሃሳቤማ እንኳን ፌርማታ ህይወቴን ያዘልለኛል … የት ልሄድ ነበር የተሳፈርኩት!... ወይኔ ስልኳን ሳልቀበላት** !)

6 months, 1 week ago

ጣምራ ጦር
ደራሲ:- ገበየሁ አየለ
ይዘት:- ታሪካዊ ልቦለድ

.
.

6 months, 1 week ago

የመጽሐፍ ዳሰሳ 3

ጣምራ ጦር
ደራሲ:- ገበየሁ አየለ
ይዘት:- ታሪካዊ ልቦለድ

የታሪክ እና የፖለቲካ መጻሕፍትን እወዳለሁ። የሰው ልጅ ሥነ ጥናት ምን አድማስን ቢዞር ... የመጨረሻ ግቡ ሰው ነው።
ታሪክ እና ፖለቲካ ደግሞ መነሻቸውም ሆነ መድረሻቸው ሰው ነው።

" ጣምራ ጦር " የተሰኘው የገበየሁ አየለ መጽሐፍ ታሪክን መሠረት ያደረገ መጽሐፍ ነው። ታሪኩን ለተደራሲያን ውብ አድርጎ ለማቅረብ ታሪካዊ ልቦለድነትን ተላብሷል።

ታሪኩ መሠረት የሚያደርገው በሃገራችን አቆጣጠር 1969 ላይ በተደረገው የኦጋዴን ጦርነት ላይ ነው። የዚአድባሬ ሱማሊያ ወደ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ወረራ እና የዘመኑን ጀግኖች የአይበገሬነት ትግል ያስቃኘናል።

መጽሐፉ ሙሉ ጦርነቱን አልዘገበም። ከዚያ ይልቅ በሁለት ጓደኛሞች የደርግ ወታደሮች ውጣ ውረድ ላይ ነው ሙሉ ዳሰሳው። በሁለቱ ጀግኖች ሕይወት ላይ የዘመኑን የምስራቅ ኢትዮጵያ ሁኔታ፣ የወረራውን አስከፊነት፣ የህዝቡን ሰቆቃ፣ የመልክዓ ምድሩን አስቸጋሪነት፣ ታማኝነት፣ በወዳጅ መከዳት፣ የሀገር ፍቅር፣ መስዋዕትነት፣ የቤተሰብ ናፍቆት፣ በሞት ጥላ ስር መኖርን ... ያስመለክተናል።

ጣምራ ጦር በውብ አጻጻፍ የተጻፈ፣ እንደ ሌሎች ታሪካዊ ልብወለዶች ማጋነን ያልበረዘው ድንቅ መጽሐፍ ነው።

ገበየሁ አየለ በመጽሐፉ ... ወታደሮች በጦርነት እሳት ውስጥ በምን አይነት ሰቆቃ እንደሚያሳልፉ ቦታው ያለን እስኪመስለን ያሳየናል። ሲያዝኑ አብረን እንድናዝን ሲከፉ አብረን እንድንከፋ የሚያደርግ አስማታዊ አጻጻፍ አለው።
የሰው ልጅ የትዕግስት ልክ የጽናት ጥንካሬ እስከምን እንደሚዘረጋ ስናይ ይደንቀናል።  ሚስቱ እና ልጆቹ በጨካኝ ወታደሮች እጅ የወደቁበት ወታደር ልቡ ምን ያህል እንደሚታመም ... ናፍቆት እንዴት እንደሚያቆስለው ከእውነተኛው ታሪክ በብዕሩ ተቀንጭቦ ስናነብ እናዝናለን።

ለዓላማ ከሚከፈል መስዕዋትነት ትንሽ እርምጃ ራቅ ብሎ አሸናፊነት እንዳለ ስንገነዘብ ... አንዳንዱ ምነው ባልሞተ እና የድል ጣፋጭ ጽዋን ቀምሶ በነበረ ብለን እንመኛለን።

በስተመጨረሻ የኦጋዴን በረሃ ጀግኖች ጽናት ያልተነገረ ያልተዘከረ ታሪካችን ሆኖ እናገኘዋለን።

ድንቅ ታሪክ፣ ፅኑ ልብ፣ አይበገሬ መንፈስ፣ ጀግና ትውልድ፣ ናፍቆት እና መስዋዕትነት ... ሁሉን በውብ አጻጻፍ ከጀግና ወጣት ታሪክ ጋር ጣምራ ጦር ውስጥ እናገኛለን።

አንብቡት። ጋበዝኳቹ።

Pdf ከስር ይለቀቃል።

Nova.

8 months, 1 week ago

ጓድ ዛሬ አይደል እንዴ tik tok ገብቼ የማየው

ምድረ የአረብ ሃገር ሸቃሊት ፖለቲካ ተንታኝ ሆነው የለም እንዴ?

በስድብ መንግሥት እንደሚገለበጥ ነው የሚስቡት እኮ ደግሞ?

ለማን ምን አይነት video መላክ እንዳለባት የማታውቅ ሸቃሊት ... ትተነትነዋለች አልኩህ ይህን ፖለቲካ?

በምን ሰዓት እየሰሩ በምን ሰዓት ነው Live ሚለፋደዱት ግን..?

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 week, 2 days ago

Last updated 4 days, 6 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 3 weeks, 1 day ago