ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
✍
ጠጠር ይዞ ከመቁጠር ሰሀቦች ላይ ጦር እስከ መወርወር በፍጥነት የተምዘገዘገው አፀያፊው የቢድዐ ዕድገት!!
ክስተቱ ዓምር ቢን ሰለማ እንደሚከተለው ያስተላልፈዋል…
ከፈጅር ሰላት በፊት ዐብደላህ ቢን መስዑድ በራፍ ላይ እንቀመጥ ነበር: እሱ ሲወጣ አብረነው ወደ መስጂድ እንሄዳለን።
በአንዱ ቀን አቡ ሙሳ አል_ዓሻሪ መጣና "አቡ ዐብዱረሕማን ወጥቷልን?" አለን። "አይ አልወጣም" አልነው። እስኪወጣ ከኛው ጋ ተቀምጦ ጠበቀው። ልክ ሲወጣ ሁላችንም ተነስተን ወደ እሱ ቆምን።
አቡ ሙሳ……
"አቡ ዐብዱረሕማን ሆይ! አሁን በቅርቡ መስጂድ ውስጥ የሆነ ነገር አየሁኝና ጠላሁት: ግን አልሀምዱ ሊላህ ኸይር እንጂ አላየሁም" አለው።
ኢብኑ መስዑድ……
"ምንድን ነው እሱ?" አለው።
አቡ ሙሳ……
"ከቆየህ ታየዋለህ" አለው።
ቀጠለና……
"መስጂድ ውስጥ ሰዎች ክብ ክብ ሰርተው ተቀምጠው ሰላት ይጠባበቃሉ። በሁሉም ክብ ክብ ላይ አንድ ሰው አለ። በእጃቸው ላይ ጠጠር ይዘዋል። “መቶ ጊዜ አላሁ አክበር በሉ” ይላቸዋል መቶ ጊዜ “አላሁ አክበር” ይላሉ። “መቶ ጊዜ ላ ኢላሃ ኢለላህ በሉ” ይላቸዋል መቶ ጊዜ “ላ ኢላሃ ኢለላህ” ይላሉ። “መቶ ጊዜ ሱብሃነላህ” በሉ ይላቸዋል መቶ ጊዜ “ሱብሃነላህ” ይላሉ።" አለው።
ኢብኑ መስዑድ……
"እና ምን አልካቸው?" አለው።
አቡ ሙሳ……
"ትዕዛዝህን ወይም ሀሳብህን ተጠባብቄ ምንም አላልኳቸውም" አለው።
ኢብኑ መስዑድ……
"ወንጀላቸው እንዲቆጥሩ አታዛቸውም ነበርን? ከመልካም ስራቸው ምንም እንደ ማይጠፋባቸው ቃል አትገባላቸውም ነበርን?" አለው።
ከዝያም ሄደ አብረነው ሄድን። ወደ እነዝያ ክብ ሰርተው የተቀማመጡት ጋ መጣና አጠገባቸው ቆመ።
"እየሰራችሁት የማየው ነገር ምንድን ነው?" አላቸው።
"አቡ ዐብዱረሕማን ሆይ! ጠጠር ናት: ተክቢር፣ ተህሊል እና ተስቢህ የምንቆጥርባት" አሉት።
"ወንጀላችሁን ቁጠሩ፤ ከመልካም ስራችሁ ምንም እንደ ማይጠፋባችሁ እኔ ቃል እገባላችኋለሁ። እናንተ የሙሐመድ ህዝቦች ሆይ! እንደው መጥፊያችሁ ምን አፈጠነው?! እነዚህ የነብያችሁ ባልደረቦች ሞልተው አሉ፣ ይህ ልብሳቸው ነው አላለቀም፣ መጠጫ ዕቃቸውም አልተሰበረም። ነፍሴ በእጁ በሆነችው እምላለሁ: እናንተ ከሙሐመድ በተሻለ የሆነ ቀጥተኛ መንገድ ላይ ናችሁ: ወይም ደግሞ የጥመት መንገድ በመክፈት ላይ ናችሁ"** አላቸው።
"አቡ ዐብዱረሕማ ሆይ! ወላሂ ኸይር እንጂ ሌላ አልፈለግንበትም" አሉት።
"ስንት ኸይርን የሚፈልግ አለ ግን አያገኘውም" አላቸው።
ቀጠለና
"በእርግጥም የአላህ መልእክተኛﷺ ቁርኣን የሚቀሩ ነገር ግን ጉሮሮኣቸው የማያልፍ ሰዎች እንዳሉ ነግረውናል። በአላህ እምላለሁ ምን አልባትም አብዛኞቻቸው ከእናንተ እንደሆኑ አላውቅም።"አላቸውና ትቷቸው ዞር አለ።
የክስተቱ አስተላለፊ የሆነው ዓምር ቢን ሰለማ
"እነዝያ ክብ ክብ ሰርተው ከተቀመጡት አብዛኞቻቸው የነህረዋን ዘመቻ ቀን ከኸዋሪጆች ሆነው ?ሲያጠቁን አይተናቸዋል።" ይላል።
ይህንን ክስተት የተገነዘበና ያስተነተነ በወንጀል እና በቢድዐ ላይ አይቀልድም!!
እንደ መውሊድ "ነብዩን ስለ ምንወድ" በሚል ጅማሬ "ኸይር እንጂ አልፈለግንበትም" ተብለው የሚጀመሩ ፈጠራዎች መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የላቸውም። ብልህ እና ፈጣን የሆነ ሰው ቢድዐን አይዳፈርም።
?{فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَن تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيمٌ}
✍
*ከሱፍይ ጋ ተቀምጠህ ስለ መውሊድ ቢድዐነት የማውራት ምሳሌው;
ከሚስትህ ጋ ተቀምጠህ ሁለት 3 ስለ ማግባት እንደማውራት ነው።*
ይላል አንዱ
✍
ሼኹ ሂጃብ ስለ መልበስ እና መገላለጥ ስለ መተው እያስተማሩ ነው;
አንዷ ጥያቄ አቀረበች: "ያ ሸይኽ እኛ ብቻ ከምንሸፋፈን ወንዶች ለምን አይናቸውን አይሰብሩም?" አለች
ሼኹ: "እቴዋ! በሆነ ዕቃ ላይ ያስቀመጥሽው ማር ቢኖርና ይህ ማር ዝንቦች መጥተው ቢወሩት ዝንቦቹን እንዴት መከላከል ትችያለሽ?" አሏት
"ዕቃውን በመሸፈን" አለች
"እንግዲያውስ ሰውነትሽን ስትሸፍኚ የሰው ዝንቦች ይሄዱልሻል!!" አሏት
✍
**ዕንቁም አልመጣልኝ
ጣጣውም አልነካኝ
ስለ ዕንቁጣጣሽ እኔ ምን አገባኝ??**
*?እንኳን አደረሳችሁ‼️
ማለት አይቻልምን❓*❓
✍የትኛውንም "እስልምናን አቃለሁ" የሚል ሙስሊም “ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶች የባጢል እምነቶች ናቸው” ብሎ ያምናል።
*✍የትኛውንም "ክርስትናን አቃለሁ" የሚል ክርስቲያን “ከክርስትና ውጪ ያሉ እምነቶች የባጢል እምነቶች ናቸው” ብሎ ያምናል።*
አንድ ሙስሊም “ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶች ባጢል ናቸው።" ብሎ እያመነ, የክርስቲያኖችን በዓል አብሮ የሚያከብር ከሆነ፦
ውሸታምና አስመሳይ ነው‼
አንድ ክርስቲያን “ከክርስትና ውጪ ያሉ እምነቶች ባጢል ናቸው።” ብሎ እያመነ, የሙስሊሞችን በዓል አብሮ የሚያከብር ከሆነ፦
ውሸታምና አስመሳይ ነው‼****
የትኛውንም ኡስታዝ መስጂድ ውስጥ "ጀነት ሊገቡ የሚችሉት ሙስሊሞች ብቻ ናቸው። ከዝያ ውጪ ያሉት ከሳሪዎች ናቸው”፣
“አላህ በሚወደው ነገር እንጂ አላህ በማይወደው ነገር መተባበር ወንጀል ነው" ብሎ እያስተማረ፤
ሚዲያና አደባባይ ላይ ሲወጣ “መቻቻል ኢትዮጵያዊነት ነው” እያለ የክርስቲያኖችን በዓል የሚያከብር ከሆነ፦
ይህ ኡስታዝ ሳይሆን አጭበርባሪና ለሆዱ አዳሪ ነው‼****
የትኛውንም ቄስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ “ገነት የሚገቡት ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው (ያመነ የተጠመቀ ይድናል, ሌላው ግን አይድንም)" ብሎ እያስተማረ፤
ሚዲያና አደባባይ ላይ ሲወጣ “መቻቻል ኢትዮጵያዊነት ነው” እያለ የሙስሊሞችን በዓል የሚያከብር ከሆነ
እሱም አጭበርባሪና ሌባ ነው‼****
አዎን‼
ሙስሊም ነኝ። ከእስልምና ውጪ ያሉ እምነቶች በአጠቃላይ ባጢል እንደሆኑ አምናለሁ። ከእስልምና ውጪ ያሉ የሰው ልጆች በአጠቃላይ እስልምናን ተቀብለው ከእሳት ድነው ጀነት እንዲገቡ እመኝላቸዋለሁ። በቻልኩትም እንዲሰልሙ እጥራለሁ።
ያሉበት እምነት ባጢል እንደሆነ ውስጤ እያወቀ ግን “እንኳን አደረሳችሁ” እያልኩ የውሸት ደስታ እየገለፅኩ እነርሱንም እራሴንም መዋሸት አልችልም‼‼
ክርስቲያን ነህ❓ "ከክርስትና ውጪ መዳኛ የለም" ብለህ ታምናለህ❓ ክርስትና አለ መቀበሌ ያሳስብሃል❓
እንግዲያውስ ና! ስለ ክርስትና አስረዳኝ፤ ስለ እስልምና ላስረዳህ‼*
እንጂ፦
ክርስትና ባለ መቀበሌ እያዘንክ ከሆነና "ባጢል ላይ ነህ" የምትለኝ ከሆነ የእስልምና በዓላቶችን ሳከብር እንዴት "*እንኳን አደረሰህ" እያልከኝ የውሸት ደስታ እየገለፅክ ራስህንም እኔንም እንዴት ትዋሻለህ❓❓❓
✍ልብ በሉ‼ አሁንም ልብ በሉ‼*
ይህ ጉዳይ የፖለቲካ አስተሳሰብ አይደለም። የብሄር ውዝግብ አይደለም። የእምነት ጉዳይ ነው። የጀነትና የጀሀነም ጉዳይ ነው። እውነታውን አውርቶ እውነቱን ይዞ የሚኬድበት እንጂ በውሸት መቻቻልና መግባባት የሚኬድበት ነጥብ አይደለም‼***
እሺ! እንዴት እንኗኗር❓❓
?????
በመጀመሪያ የጋራ ሀገር እንጂ የጋራ እምነት የለንም‼️* ሁላችንም ኢትዮጵያዊያኖች ነን።
«*ኢትዮጵያዊ ወንድሞቼ» እንጂ
ሙስሊሞች «ክርስቲያን ወንድሞቼ»፣ ክርስቲያኖች «ሙስሊም ወንድሞቼ» የሚሉበት አግባብ አይኖርም።
እንደ ዜጋ በሀገር ልማት ላይ አብረን የምንሰራቸው ስራዎች ሊኖሩን ይችላሉ፤
እንደ እምነት ግን አብረን የምናከብረው እምነት የለንም።
ሁሉም የሰው ልጆች እስልምና የመቀበል ግዴታ አለባቸው; እስካልተቀበሉ ግን አንድነቱን ይወገዳል።
በማህበራዊ ኑሯችን እንገበያያለን፣ እንበዳደራለን፣ እንተባበራለን።
በእምነታዊ ጉዳይ ግን ከተቻለ ትክክለኛ በሆነው እስልምና አንድ መሆን; ካልተቻለ ግን አብሮ የሚከበር ምንም ዓይነት የእምነት በዓልም ይሁን ስርዓት አይኖርም።
ክርስቲያን ወላጆች፣ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶች ካሉን በዝምድናችን ልክ እንዛመዳቸዋለን እንኗኗራቸዋለን።
በእምነታዊ ተግባራቸው ግን ምንም ዓይነት ተሳትፎ አይኖረንም።
?ከታመሙ እንጠይቃቸዋለን።
?ከቻልን እናግዛቸዋለን።
?ካገኘን እናበላቸዋለን።
?ከተራቆቱ እናለብሳቸዋለን።
?ስጦታም እንሰጣቸዋለን።
?ዝምድናቸውን እንቀጥላለን።
❌እንኳን አደረሳችሁ አንልም።
❌የማክበሪያ ቦታም አናፀዳም።
❌የበዓል ግብዣም አንቀበልም።
?ስሜታችን ሳይሆን የጌታችን ትዕዛዝ ነው?
?{ وَوَصَّيْنَا ٱلْإِنسَٰنَ بِوَٰلِدَيْهِ حَمَلَتْهُ أُمُّهُۥ وَهْنًا عَلَىٰ وَهْنٍ وَفِصَٰلُهُۥ فِى عَامَيْنِ أَنِ ٱشْكُرْ لِى وَلِوَٰلِدَيْكَ إِلَىَّ ٱلْمَصِيرُ (14) وَإِن جَٰهَدَاكَ عَلَىٰٓ أَن تُشْرِكَ بِى مَا لَيْسَ لَكَ بِهِۦ عِلْمٌ فَلَا تُطِعْهُمَا وَصَاحِبْهُمَا فِى ٱلدُّنْيَا مَعْرُوفًا وَٱتَّبِعْ سَبِيلَ مَنْ أَنَابَ إِلَىَّ ثُمَّ إِلَىَّ مَرْجِعُكُمْ فَأُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ(15)}
"ሰውንም በወላጆቹ (በጎ እንዲያደርግ) በጥብቅ አዘዝነው፡፡ እናቱ ከድካም በላይ በሆነ ድካም አረገዘችው፡፡ ጡት መጣያውም በሁለት ዓመት ውስጥ ነው፡፡ ለእኔም ለወላጆችህም አመስግን በማለት (አዘዝነው)፡፡ መመለሻው ወደኔ ነው፡፡(14) ለአንተ በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፡፡ በቅርቢቱም ዓለም፤ በመልካም ሥራ ተወዳጃቸው፡፡ ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡ ከዚያም መመለሻችሁ ወደ እኔ ነው፡፡ ትሠሩት የነበራችሁትንም ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ (አልነው)፡፡(15)
[አል_ሉቅማን:14–15]
በዚህ አንቀፅም ይሁን በሌሎች አንቀፆች ላይ ከእስልምና ውጪ ካሉ ወዳጅ ዘመዶችም ይሁን ከአጠቃላይ ሰዎች ጋ በምን ዓይነት መልኩ መኗኗር እንዳለብን አላህ ያስተምረናል።
?ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል ወደ እስልምና እንጣራቸዋለን።
?የስጋ ዝምድና ወይም ጉርብትና የሚያገናኘን ከሆነ ለእነርሱ መጠበቅ ያለብን መብታቸው እንጠብቅላቸዋለን።
?በቻልነው ያህል ማህበራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ድጋፍና እገዛ እናደርግላቸዋለን።
?እስልምናችንን በሚጋጭ ጉዳይ ላይ ግን በምንም ነገር ቢያዙን አንታዘዛቸውም።
?እምነታቸውን በሚመለከት ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት እገዛም ይሁን ትብብር አናደርግላቸውም።
?ቢታመሙ እንጠይቃቸዋለን፣ ቢራቡ እናበላቸዋለን፣ ቢራቆቱ እናለብሳቸዋለን፤
ቢሞቱ ግን አጥበን ከፍነን አንቀብራቸውም‼
✍️እኛ ሙስሊሞች «በኢትዮጵያ ባህልና ወግ» መሰረት ሳይሆን
«በቁርኣን እና በሐዲስ» ህግጋት መሰረት ነው ህይወታችን የምንመራው‼****
✍
ዱንያ ብትሆን ኖሮ ለደጋጎች ካሳ
ባልጠገቡ ነበር ካፊር ከእንስሳ*
ነብዩ በርሀብ ድንጋይ በሆድ ያስራል
የሀብታሙ ውሻ ስጋ ያማርጣል*
የትግል የስራ የፈተና ሀገር
መሆኑ እወቅና በሰብር ተሻገር!!**
✍
ብልጥ ሁን!!
«العِبَادَةُ في الهَرْجِ كهِجْرةٍ إلَيَّ»
«በፊትና ሰዓት ዒባዳ ማብዛት ወደ እኔ እንደ መሰደድ ነው።»
ይላሉ ነብዩﷺ
እነሱ ይዋኙ: አንተ ወጥር; ወንድ ሁን!!**
مركز السلسبيل لتحفيظ القران الكريم والتربية الإسلامية
✨አስደሳች ዜና ለወላጆችና ለቁርአን ፈላጊዎች በሙሉ
እነሆ መርከዝ ሰልሰቢል የቁረአን ሂፍዝና ተርቢያ ማእከል ተማሪዎችን በተመላላሽ ና በአደሪ የበጋውን ፕሮግራም ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ እርሶን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል እርሶም ቦታዎን ሳይሞላ ፈጥነው ልጆትን ያስመዝግቡ
?መርከዙ ከሚሰጣቸው ትምርቶች መካከል
?ቁርአንን ከማንበብ አንስቶ እስከ ሂፍዝ ማጠናቀቅ
?በተለያዩ ዘርፎች ላይ የኪታብ ትምርቶች
✨እንዲሁም የተርቢያ ትምርቶች ይገኙበታል
?አድራሻ ፉሪ ሰልሰቢል (ወርቃማው)መስጅድ?
ለበለጠ መረጃ
????
0920339222
0944313756
0911784569
?????
https://t.me/alaseriyislamiksenter
✍
በተወለድክ ጊዜ…………
እያለቀስክ ስትመጣ ሁሉም እየሳቁ ተቀብለወህ ነበር:*
በምትሞት ጊዜ……………
ሁሉም እያለቀሱ ሲሸኙህ ስቀህ እንድትለያቸው አሳምረ*ህ ስራ
✍
እቅድህ ላይ
ሞት ጨምርበት!!**
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana