ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 day, 23 hours ago
Last updated 3 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 1 day ago
**ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ በኦሮሚያ ክልል የሚያደርገዉ የአጀንዳ ልየታ መርሐ ግብር በይፋ ተጀመረ
👉በዚህም ከ356 ወረዳዎች የተወጣጡ ከሰባት ሺሕ በላይ የህብረተብ ክፍሎች ይሳተፋሉ ተብሏል**
ታሕሳስ 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የሚያደርገዉ የአጀንዳ ልየታ መርሐ ግብር ዛሬ ታሕሳስ 7 ቀን 2017 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል፡፡
ኮሚሽኑ ከዛሬ ጀምሮ ባሉ አምስት ተከታታይ ቀናት ከክልሉ 356 ወረዳዎች ከአስር የማህበረሰብ መሰረቶች የተመረጡ ከ7 ሺሕ በላይ የማህበረሰብ ወኪሎች አጀንዳዎቻቸውን በምክክር እንደሚለዩ አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ከእሑድ ታሕሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ፤ የህብረተሰብ ወኪሎችን ጨምሮ 1 ሺሕ 700 የክልል ባለድርሻ አካላት ለተከታታይ ሦስት ቀናት በክልሉ አጀንዳዎች ዙሪያ ተመካክረው እንደሚያደራጁ አመላክቷል፡፡
በውይይቱ በርካታ አካላት እንደሚሳተፉ የተገለጸም ሲሆን፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የተወጣጡ ከሰባት ሺሕ በላይ ተወካዮች፣ አንድ ሺሕ 700 የክልሉ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም 48 የሥራ አስተባባሪዎችን ጨምሮ ከ150 በላይ በጎ ፍቃደኞች እንደሚሳተፉ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዐያ ተናግረዋል።
ዋና ኮሚሽነሩ አክለዉም በኦሮሚያ ክልል የሚደረገዉ የአጀንዳ ልየታ መርሀ ግብር ሁለት ምዕራፎች እንዳሉት የገለጹ ሲሆን፤ አንደኛዉ ከወረዳ የተወጣጡ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሳተፉ እንዲሁም፤ በሁለተኛዉ ምዕራፍ ደግሞ የክልል ባለድርሻ አካላት አጀንዳዎችን የሚለዩ መሆኑን አብራርተዋል።
በተጨማሪም ከተለያዩ ወረዳዎች የተወጣጡት ተወካዮች በአስር የማህበረሰብ ክፍሎች የተከፈሉ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ መምህራን፣ አካል ጉዳተኞች፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጨምሮ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች እንደሚሳተፉ አጽዕኖት ሰጥተዋል።
በዛሬው ዕለት የተጀመረው መርሃ ግብር በአባ ገዳዎች የምርቃት ሥነ-ስርዓት የተከናወነ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ መሪ ኮሚሽነር ዶ/ር አምባዬ ኦጋቱ እና ሌሎች የምክክር ኮሚሽኑ የበላይ አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል።
በመድረኩም አባ ገዳዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እንዲሁም የተለያዩ የኦሮሚያ ክልል የተወጣጡ ተወካዮች፣ የክልሉ ባለድርሻ አካላትን ጨምሮ ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ታድመዋል።
መርሀ ግብሩ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስቴድየም ላይ እንደሚካሄድም ተገልጿል።
በፅዮን ይልማ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በኢትዮጵያ 500 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ከመርሳት በሽታ ጋር እንደሚኖሩ ተገለጸ
ታሕሳስ 7/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) አሁን ላይ ካለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ውስጥ አረጋውያን 5 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍኑ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል 500 ሺሕ የሚሆኑት ከመርሳት በሽታ (አልዛይመር) ጋር እንደሚኖሩ አልዛይመርስ ኢትዮጵያ ገልጿል፡፡
የአልዛይመርስ ኢትዮጵያ መስራች እና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ያሬድ ዘነበ "የአልዛይመር ወይም የመርሳት በሽታ ብዙ ሰዎች ሕመሙ ሳይታወቅላቸው 'የጤናማ እርጅና ምልክት ነው' እየተባሉ ከሕመሙ ጋር ሲቆዩ ይስተዋላል" ብለዋል።
አክለውም፤ ይህ በሽታ በብዛት እድሜቸው ከ70 እስከ 80 ዓመት በሚደርስ ሰዎች ላይ እንደሚከሰት ገልጸዋል።
ጤና ሚኒስቴር "2 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው ይጠቃሉ ተብሎ ይታመናል" የሚል መረጃ ቢያስተላልፍም፤ ማህበራቸው እያከናወነው በሚገኘው ጥናታዊ መረጃ ግን እስከ 40 በመቶ የሚሆኑ ሰዎች በበሽታው ይያዛሉ ተብሎ እንደሚታመን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
"በዚህ ጥናት የደም ናሙና በመስጠት 400 የሚሆኑ ሕመሙ ያለባቸው ታማሚዎች ይሳተፋሉ" ያሉም ሲሆን፤ "በዚህም ሕመሙ ያለባቸው ሰዎችን ሕመሙ ከሌለባቸው ሰዎች የመወዳደር ሥራ እየሰራን ነው" ብለዋል።
አክለውም ከ10 በላይ የሳይንስዊ ጥናት የሚመሩ የሚያግዙ እና የሚደግፉ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ባለሙያዎች መኖራቸውን በመግለጽ፤ ከዓለም አቀፍ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ጥናቱ እየተሰራ ስለመሆኑ ተናግረዋል።
ነገር ግን በተያዘለት ጊዜ ጥናቱን እንዳይጠናቀቅ የዩኒቨርስቲዎች አሰራር እንዲሁም የማህበረሰቡ ግንዛቤ አነስተኛ መሆን ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
"በዋናነት በእኛ ሀገር ለጥናት እና ምርምር ማህበረሰቡ ውስጥ ያለው የእውቀት ማነስ እንዲሁም፤ በምናደርገው ጥናት ላይ ለመሳተፍና የደም ናሙና ለመስጠት ፍቃደኛ ያለመሆን በከፍተኛ ደረጃ ችግር እየሆነብን ይገኛል" ሲሉ አስረድተዋል።
አያይዘውም "የዩንቨርስቲዎች አሰራር ፕሮጀክቶዎች ሲመጡ ለማስፈፀምና ማህበረሰቡን ለማስተባበር የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ትብብር ስለማያደርጉ ከፍተኛ ተፅዕኖ አሳድሮብናል" ብለዋል፡፡
"አሁን የፕሮጀክቱ መጠናቀቂያ ጊዜ ነበር፡፡ ወደ 2 ዓመት የፈጀብን ማህበረሰብ በማስተማር እና የወረቀት ሥራዎችን መጨረስ ስለነበረብ ነው፡፡" ያሉት ሥራ አስኪያጁ፤ በመንግሥት እና በዩንቨርስቲዎች በኩል ጥናት እና ምርምር ከመደገፍ አንፃር ብዙ ክፍተቶች መኖራቸውን ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡
አክለውም "ለጥናቱ የሚውል ገንዘብ ሲመጣ ዩንቨርስቲው አላስፈላጊ ላልሆኑ ወጭ ይቀንሳል" ያሉ ሲሆን፤ ለሚመለከተው ፕሮጀክት የመጣ በጀት ከግማሽ በላይ አላስፈላጊ ለሆነ ወጭ እየወጣ በመሆኑ ጥናቱን ለማከናወን እንደ ትልቅ እንቅፍት ሆኖብናል" ሲሉ ተናግረዋል።
በዓለም ላይ በ3 ሰከንድ 1 ሰው በመርሳት በሽታ እንደሚያዝ የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል።
በህይወት ጌትነት
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ኮሚሽኑ ሁሉም የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲተገበር መጠየቁ ትክክለኛ ነው ሲል ገለጸ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የቀድሞ ተዋጊዎችን በመመለስ ሂደት ውስጥ ሁሉም የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ መፈፀም እንደሚገባው መጠየቁ ትክክለኛ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዐቢይ ኮሚቴ በማቋቋም ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ተስፋዓለም ይህደጎ፤ የቀድሞ ተዋጊዎች በተለይም በግብርና፣ በጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም በተለያዩ ሥራዎች ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያደርግ ተግባር መጀመሩን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ይሁን እንጂ ከተለያዩ ተቋማትና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች 'ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመመለሱ ሥራ ግልፅ አይደለም' ተብሎ የሚነሳው ጉዳይ፤ ኮሚሽኑ ግልፅ ነው ብሎ እንደማያምን ገልጸዋል፡፡
ይህ የተሃድሶ ሥራ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አንድ አካል መሆኑን ያነሱት አቶ ተስፋዓለም፤ "ይህም ተፈፃሚ እንዲሆን ጥረት እየተደረገ ይገኛል" ብለዋል።
በተለይም የተፈናቃዮች ጉዳይ እና የሌሎች ሀገራት ታጣቂዎች ከትግራይ ክልል ያለመውጣት የመሳሰሉት ጉዳዮች ተፈፃሚነታቸው ላይ ጥያቄ መነሳቱ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡
"በስምምነቱ መሰረት የፌደራል መንግሥት እና የጊዜያዊ አስተዳደሩ በመነጋር በመጠለያ ጣቢያ ያሉ ተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው የመመለስ ሥራ እንዲሰራ ጥሪ እያቀረብን እንገኛለን" ሲሉም ገልጸዋል፡፡
አክለውም "የቀድሞ ታጣቂዎችን መመለሱ እንዳለ ሆኖ፤ ሌሎች የስምምነቱ ውሎች እንዲፈፀሙ መጠየቅ ይገባል። አግባብ ነውም" ብለዋል፡፡
ከፌደራል መንግሥት ጋርም ቀጣይነት ያለው ንግግር በማድረግ በጊዜያዊ አስተዳደሩና የፌደራል መንግሥቱ መካከል መተማመን መፍጠር እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡
" 'የቀድሞ ታጣቂዎችን ወደ ማህበረሰቡ የመመለሱ ስራ ተገቢ አይደለም' የሚል ፓርቲም ይሁን ሌላ አካል ቆም ብሎ ማሰብ አለበት" ሲሉም አሳስበዋል።
ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በክልሉ የተጀመረው የተሃድሶ ሥራ በበጎ ጎኑ የሚነሳ መሆኑን ቢያነሱም፤ ነገር ግን ሁሉም የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነቶች መተግበር አለባቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተለይም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሰፋፊ ቦታ በሌሎች ሃይሎች ቁጥጥር ሥር መሆኑ ጥርጣሬ እየፈጠረባቸው መሆኑንም ለአሐዱ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
የፌደራል መንግሥት ባሳለፍነው ሳምንት የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባደረገው ውይይት፤ በተለይም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደቀያቸው የሚመለሱበትን ሁኔታና ታጣቂዎችን ወደ መደበኛ ሕይወት የመመለስ ሂደት በትኩረት የሚሰራበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት መደረሱን ገልጿል፡፡
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት 43 ሺሕ ወታደሮቿን አጥታለች" ዘለንስኪ
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎደሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ሙሉ ለሙሉ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፤ ሀገራቸው በጦር ሜዳ 43 ሺሕ ወታደሮቿን አጥታለች ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዘለንስኪ ቀደም ሲል "የዩክሬን የተጎጂዎችን ቁጥር የሕዝብን ሞራል ሊያዳክም ስለሚችል፣ ጥብቅና ሚስጥራዊ ናቸው" በማለት፤ መረጃውን ከማውጣት ተቆጥበው መቆየታቸው ይታወቃል።
ነገር ግን ከተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በፓሪስ ከተገናኙና ትራምፕ በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ያለው ጦርነት መቆም እንዳለበት ካሳሰቡ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ፤ ቀደም ሲል "ከፍተኛ ሚስጥራዊ ነው" ብለው የያዙትን የሟቾች ቁጥር ይፋ አድርገዋል።
በዚህም "ሙሉ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ዩክሬን በጦር ሜዳ 43 ሺሕ ወታደሮችን አጥታለች" ያሉ ሲሆን፤ 370 ሺሕ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለው የሕክምና ዕርዳታ እያገኙ መሆኑን በኤክስ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።
ሩሲያ 750 ሺሕ የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብላ እንደምታምን የገለጸች ሲሆን፤ "ይህ ከፍተኛ መጠን ያለው ጥፋት በክሬምሊን የእግረኛ ጦር" በዩክሬን ምሽጎች ላይ የደረሰ ነው" ብላለች።
ዘለንስኪ በዩክሬን እና በሩሲያ የተጎጂዎች ቁጥር መካከል ያለውን ልዩነት ለመለየት የሞከሩም ሲሆን፤ የዩክሬን መረጃ ቀላል ጉዳቶችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
"በእኛ ሰራዊት ውስጥ በጥቃት ከቆሰሉት ወታደሮች ውስጥ ግማሽ ያህሉ በኋላ፤ ወደ ጦር ሜዳ እየተመለሱ ነው" ሲሉም ተናግረዋል።
በፈረንጆቹ 2019 በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ክፉኛ የተጎዳው የሮተርዳም ካቴድራል ዕድሳት ተደርጎለት ዳግመኛ በተከፈተበት ሥነ ስርዓት ላይ፤ ከሌሎች የዓለም መሪዎች የተገኙት ዘለንስኪ ቅዳሜ ዕለት በፈረንሳይ ፓሪስ ከትራምፕ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ከውይይቱ በኋላ ትሩዝ ሶሻል በተሰኘው የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፤ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
አክለውም “በዩክሬን ጦርነት ብዙ ሞቷል፣ ብዙ ቤተሰብ ፈርሷል እስካሁን የሆነው በቂ ነው፣ ጦርነቱ ሊቆም ይገባል” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
“ፕሬዝዳንት ዘለንሰኪ እና ዩክሬን የሰላም ስምነምነት በቅርቡ እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል፣ ይህ እብደት መቆም አለበት” ሲሉም ትራምፕ አሳስበዋል፡፡
አንድ ሥማቸው ያልተጠቀሰ የዩክሬን ባለስልጣን ለዋሽንግተን ፖስት በሰጡት ቃል፤ ስብሰባው ውጤታማና መሰረት ያለው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ "ሁላችንም ይህን ጦርነት በተቻለ ፍጥነት ማቆም እንፈልጋለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
"የግሪሳ ወፍ ምልክት በተስተዋልባቸው አካባቢዎች ላይ የኬሚካል ርጭት ለማከናወን ግብረ-ኃይል ተቋቁሟል" የግብርና ሚኒስቴር
ሕዳር 30/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይና በአማራ ክልሎች የግሪሳ ወፍ እየተስተዋለ መምጣቱን ተከትሎ፤ አፋጣኝ መፍትሔ ለመስጠት ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የመከላከል ሥራው እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በሚኒስቴሩ የአዝርእት ጤና ክትትል ኃላፊ አቶ በላይነህ ንጉሴ በቅርቡ በሁለቱም ክልሎች ተከስቶ የነበረውን የግሪሳ ወፍ በግብርና ምርቶች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለማስከተሉን የገለጹ ሲሆን፤ ክልሎቹ ባቀረቡት ጥሪ መሰረትም ከፌደራል መንግሥት ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ለአሐዱ ተናግረዋል።
ሚኒስቴሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአዝእርት ተባይንና የግሪሳ ወፍን ለመከላከል ከክልሎች ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
አርሶ አደሩ በባሕላዊ መንገድ መከላከል የሚችልባቸው ሁኔታዎችና የኬሚካል ስርጭት ዙሪያም በትኩረት እየተሰራበት ስለመሆኑ ኃላፊው ተናግረዋል።
ቀደም ሲል በአማራ ክልል ተቀስቅሶ የነበረው የግሪሳ ወፍ በተወሰኑት አካባቢዎች ላይ እየተስተዋለ መሆኑም ተገልጿል።
በቅርቡም በደቡባዊ የትግራይ ክልል የግሪሳ ወፍ በስፋት መከሰቱን ከትግራይ ክልል ግብርና ቢሮ ማስታወቁን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፤ ይህንንም ተከትሎ በአውሮፕላን የተደገፈ የኬሚካል ስርጭት መከናወኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ልማት ቢሮ ገልጿል።
በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
እየተስፋፋ የመጣው የበይነ መረብ ንግድ በምጣኔ ሐብቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ ተገለጸ
ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ እንደቴሌግራም፣ ኢንስታግራምና ፌስቡክ በመሳሰሉት የበይነ መረብ አውታሮች በመጠቀም የሚሸጡና የሚለውጡ ነጋዴዎች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ተከትሎ፤ ከግብይቶች መንግሥት ማግኘት ያለበትን ታክስ እያሳጡት መሆኑን የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩቱ በዘርፉ አደረኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ "የበይነ መረብ አውታር ግብይቶች የመንግሥት ገቢ ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ መምጣታቸውን አረጋግጫለሁ" ብሏል።
በኢትዮጵያ እየተስፋፉ የመጣውን የበይነ መረብ ንግድ ለወደፊቱ በአግባቡ ካልተያዘ፤ በምጣኔ ሐብቱ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ መፍጠሩ እንደማይቀር ኢንስቲትዩቱ በጥናቱ ገልጿል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢ-መደኛ መልኩ የሚንቀሳቀሱ የበይነ መረብ ነጋዴዎች ተመዝግበው እንዲሰሩ ጥሪ ቢቀርብም፤ የሚመዘገቡና ግብር የሚከፍሉ ነጋዴዎች ቁጥር አነስተኛ መሆኑንም ተናግሯል።
በተለይም ከታክስ ስወራ ጋር ተያይዞ ዘርፉ ተግዳሮት እየሆነ መምጣቱን የግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤትን ጨምሮ ከሚመለከታቸው አካላት የተገኘው መረጃ ጥናቱ መዳሰሱንና፤ ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንቅፋት ሊሆን ይችላል የሚል እምነት መኖሩን የኢንስቲትዩቱ የምጣኔ ሐብት ተመራማሪ አቶ ሰለሞን አክሊሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ኢንስቲትዩቱ የበይነ መረብ ንግድን በተመለከተ ለዘርፉ የሕግ ማእቀፍ እንዲዘጋጅ ውትወታ እያደረገ መሆኑን፤ ለዚህም የፖሊሲ ግብአቶችን በማቀናጀት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ለዚህም ከጎረቤት አገራት ጋር ተወዳዳሪ የበይነ መረብ ሕግ እንዲዘረጋና የንግዱ ስርዓትም በዚሁ ልክ እንዲስፋፋ ያስፈልጋል መባሉን የምጣኔ ሐብት ተመራማሪው አቶ ሰለሞን አክሊሉ ለአሐዱ ገልጸዋል።
ጥናቱ በሌሎች አገራት ያለውን ተሞክሮ ተከትሎ እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅሰው፤ በአገር ዓቀፍ ደረጃ እየተዘጋጀ ባለው ፓሊሲ ለማካተት ጥረት እየተደረገ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የበይነ መረብ ንግድ እየተስፋፋ መምጣቱን ተከትሎ፤ ሕግና መመርያ ሊደረግለት መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡ ሆኖም ይህ የበይነ መረብ ንግድ በትክክል ግብር የሚከፍሉ የንግድ ማሕበረሰቦች ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑ ተነግሯል።
ከውጭ አገራት የሚገቡ ምርቶች ጥራት ጉዳይ ያልተረጋገጠ በመሆኑ፤ በተጠቃሚው ላይ ተፅእኖ እየፈጠሩ መሆናቸውን የፓሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በጥናቱ አሳስቧል።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያልተረጋገጡ መድኃኒቶች እየተበራከቱ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ በሕብረተሰቡ ላይ ጤናን ጨምሮ አጠቃላይ ማሕበረ- ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እየፈጠሩ እንደሚገኙም አደረኩት ባለው ዳሰሳ አመላክቷል።
"ኢ-መደበኛ የበይነ መረብ ነጋዴዎች ወደ መደበኛው የንግድ ስርዓት እንዲመጡና ከሚመለከተው የመንግሥት መስሪያ ቤት ፍቃድ ወስደው እንዲሰሩ የሕግ አካላት የበኩላቸውን ማድረግ ይኖርባቸዋል" ሲልም ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል።
በአማኑኤል ክንደያ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ምርጫ ቦርድ ለምክር ቤቱ ዕዉቅና ከመስጠት ውጪ አማራጭ የለዉም ሲል የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ
ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምክር ቤቱ ዕዉቅና ከመስጠት ዉጪ አማራጭ የለዉም ሲል የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገልጿል፡፡
የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በምርጫ ቦርድ የተመዘገበ ተቋም ለማድረግ የሕግ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዉ በርካታ ጥረቶች ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዲሱ ሊቀመንበር የሆኑት የከፋ ሕዝቦች አረንጓዴ ፖርቲ ፕሬዝዳንት ሰለሞን አየለ፤ ዕዉቅና ያለዉ ተቋም እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡
ሊቀመንበሩ "ሕግ የለም ማለት አይቻልም" ያሉ ሲሆን፤ የተለያዩ ማዕቀፎችና መተዳደሪያ ደንቡ ለጋራ ምክር ቤቱ ቀርቦ መጽደቁን ገልጸዋል።
"ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ለጋራ ምክር ቤቱ እዉቅና ከመስጠት ዉጪ አማራጭ የለውም" ሲሉ የምክር ቤቱ ሊቀመንበር ተናግረዋል።
አክለውም፤ አዲሱ አመራርም ሆነ ሥራ አስፈፃሚ ከቦርዱ ጋር በመሆን ያሉበትን ችግሮች ለመፍታት በጋራ እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ የቤት ኪራይ ተከራይቶ እንደሚያስተዳድረዉ ቢገልፅም "እዉቅና ነፍጎኛል" ሲል ግን ተደምጧል።
ይህንንም በተደጋጋሚ በደብዳቤ ቢያሳውቅም ምላሽ ማግኘት አለመቻሉንም መግለፁ ይታወሳል። ይህንን በሚመለከት ከዚህ ቀደም ጥያቄ አንስተንላቸዉ የነበሩት የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ ዉብሸት አየለ፤ "ቦርዱ እዉቅና መስጠት ኃላፊነቱ አደለም" ብለዋል፡፡
"ምክር ቤቱ አሁን ባለበት መንገድ የሚቀጥል እንጂ፤ ፖርቲዎችን የማስተዳደር ኃላፊነት የተሰጠዉ ለምርጫ ቦርድ ብቻ ነው" ሲሉም ምክትል ሰብሳቢዉ ተናግረዋል።
ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ "እውቅና የመስጠት ኃላፊነት የለኝም" እያለ ቢገልጽም፤ የጋራ ምክር ቤቱ ሊቀመንበር "አማራጭ የለውም" ሲሉ ለአሐዱ ተናግረዋል።
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
**በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተፈረደበት
👉2ኛ ተከሳሽ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል**
ሕዳር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል ዓደዋ ከተማ በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው አንደኛ ተከሳሽ ላይ የሞት ፍርድ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በትግራይ ክልል የመቀሌ ከተማ መካከለኛ ፍርድ ቤት በታዳጊ ማህሌት ተክላይ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች ላይ ዛሬ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
የ16 ዓመት ታዳጊዋ የዓድዋ ከተማ ነዋሪ ማህሌት ተክላይ መጋቢት 10 ቀን 2016 ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች ከነበረበት ታግታ ተወስዳ ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ ተገድላ መገኘቷ ይታወሳል፡፡
አንደኛ ተከሳሽ አንገቷን አንቆ በመያዝ፣ ሁለተኛ ተከሳሽ ደግሞ በባጃጅ አግቶ በመውሰድ ለ30 ደቂቃ ያክል በጫማ ማሰሪያ ገመድ አሰቃይተው እንደገደሏት የመቀሌ ከተማ ዐቃቤ ሕግ ገልጿል።
አንደኛ ተከሳሽ ግድያውን ከፈጸመ በኋላ ወደ ሥራ እንደገባ፤ ገድለው ከቀበሯት ከሦስት ቀናት በኋላም አባቷ ተክላይ ግርማይን 3 ሚሊየን ብር እንደጠየቀው ተገልጿል።
ሁለተኛ ተከሳሽም ከአንደኛ ተከሳሽ እኩል የወንጀሉ ተባባሪ መሆኑን ያስረዳው ዐቃቤ ሕግ፤ ይህ የግድያ ወንጀል ጭካኔ የተሞላበት በመሆኑን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ማስረጃ የመረመረው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾች የፈጸሙት የወንጀል ድርጊት ጭካኔ የተሞላበት መሆኑን በማረጋገጥ የፍርድ ውሳኔ ሰጥቷል።
በዚህም ታዳጊዋ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀመው 1ኛ ተከሳሽ በሞት፣ 2ኛ ተከሳሾች ደግሞ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል።
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ችግር ዋና ምክንያት የግዚያዊ አስተዳደሩ በአግባብ ሀላፊነቱን ባለመወጣቱ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ገለጹ
ሕዳር 17/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደርን በዋናነት ህወሓት ሰዎች ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠሩት ቢሆንም፤ ከዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ቡድን ውስጥ ህወሓት የነሱ ብቻ አድርገው የሚቆጥሩት እንዳሉ የባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዮሴፍ በርሄ ተናግረዋል፡፡
በዚህም "ግዚያዊ አስተዳደሩ ወደታች ወርዶ ወረዳ ድረስ መስራት ባለመቻሉ ሌላኛው ቡድን የቀድሞ ህወሓቶች ወረዳዎች ላይ ላይ ያላቸውን ተቀባይነት በመጠቀም በመቆጣጠራቸው ግዚያው አስተዳደሩ መስራት ሳይችል ቀርቷል" ብለዋል፡፡
"ግዚያዊ አስተዳደሩ ክልሉ ላይ ተንጠለጥሎ በመቅረቱ የተነሳ እንዲሁም ባለበት ጫና ምክንያት በሚገባ እያስተዳደር አይደለም" ሲሉም ገልጸውታል፡፡
በግዚያዊ አስተዳደሩና በህወሓት መካከል የተፈጠረው ችግር እየተካረረ መሄዱን ተከትሎ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር "መፈንቅለ መንግሥት ሊደረግብኝ ነው" የሚል ቅሬታዎችን እያሰማ ይገኛል፡፡
ይህንና ሌሎች በክልሉ እየተካረሩ የሄዱ ጉዳዮችን በመመልከት "በተለይም ክልሉ አሁን ገና ከጦርነት ያገገመ እንደመሆኑ የፌደራል መንግሥት መፍትሄ አያስፈልገውም ወይ? ሲል አሐዱ ጠይቋል፡፡
ይህንን በሚመለከት የሳልሳይ ወያነ ትግራይ ፓርቲ ሊቀመንበር አሉላ ሀይሉ፤ "ጣልቃ ገብነት በተለይም እርምጃ መውሰድ ችግሩን ማባባስ ነው" ይላሉ፡፡
ቀደም ተብሎ የተነሳውን አሳብ የሚጋሩት የባይቶና አባይ ትግራይ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ዮሴፍ በርሄ በበኩላቸው "የፌደራል መንግሥት ጣልቃ ገብነት የሚያስፈልገው ችግር የለም" ያሉ ሲሆን፤ "ነገር ግን ጠንካራ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲፈጠር ማድረግ ይችላል" ብለዋል፡፡
ችግሮችን ከሚያባሱ ጉዳዮች አንዱና ዋነኛውን የፕሪቶሪያው ውል በአግባቡ ያለመተግበሩ በመሆኑ በትኩረት ስምምነቱ ላይ መስራት ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ እሁድ ዕለት የክልሉን ወቅታዊ የፖለቲካ፣ የደህንነት እና የማህበራዊ ጉዳዮች አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ በሰጡበት ወቅት፤ በህወሓት አመራሮች መካከል የተፈጠረው መከፋፈል ተባብሶ መቀጠሉን ገልጸዋል።
አክለውም "የፌደራል መንግሥት ውስጣዊ ችግራችንን እንድንፈታ እየገለጸ ነው" ነው ያሉ ሲሆን፤ "ካልተቻለ ግን የማስተዳደር ስልጣኑን ብልፅግና በብቸኝነት እንደሚይዘው ግልፅ አድርጎልናል" ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።
በአቤል ደጀኔ
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
ትክክለኛዎቹን የአሐዱ ራዲዮ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ!
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/ahaduradio
ድረ ገጽ፡- https://ahaduradio.com/
ዩትዩብ፦ http://shorturl.at/cknFP
ቲክቶክ ፡- www.tiktok.com/@ahadutv.official
አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት በ7545 አጭር የፅሁፍ መልክት ይላኩ
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 1 day, 23 hours ago
Last updated 3 days, 5 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated 2 weeks, 1 day ago