ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
የደረሰኝ መልእክት እንቅልፍ የሚነሳ እና የሚረብሽ ነበር። አቅመ ደካማ የሆኑ አይነ ስውራን፦
''በይፋ ሶላት ተከልክለናል፤ መስገድ አልቻልንም። እየተደብቅን ነው ለመስገድ የምንሞክረው። መጅሊሱም በዚህ ጉዳይ ላይ መፍትሄ እንድናገኝ አላደረገም። ጓደኞቻችንም ትምህርት ቤቱን ትተው ወጥተዋል። እኛም ከዛሬ ነገ ይስተካከላል በሚል በትግል በለቅሶ ነው ያለነው። እስካሁን መፍትሄ አላገኝንም። በአዳሪ ት/ቤት እየተማርን ሶላት ተከልክለን ዝም በማለታችሁ ነገ አላህ ፊት እንጠይቃችኋለን'' የሚል ነበር፣ መልዕክቱ በለቅሶ የታጀበና እንቅልፍ የሚነሳ ነበር።
ይህ መልዕክት ከደረሰኝ ጊዜ ጀምሮ ተከታታይ ፕሮግራሞችን ከባልደረቦቼ ጋር እያደርስናችሁ ነው። ነገር ግን በሚያሳዝን መልኩ የነሱን አጀንዳ ጉዳዩ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ቀርቶ መረጃውን እንኳን በማዳረስ የሚያግዝ የለም። ያለንበት ተጨባጭ እጅግ የሚያስደንግጥ ነው።
ማየት የተሳናቸው ወገኖቻችንን ጉዳይ ችላ በማለታችን እንደ ዑማ ያለንበትን ቁልቁለት ቁልጭ አድርጎም የሚያሳይ ነው።
በፋጢማ ቢንት ሙባረክ ወይም በቀየሩት ስሙ በብርሃን የአይነ-ስውራን ት/ቤት የሚማሩ ሙስሊሞች በሶላታቸው ተፈትነው ፈትነውናል። ተመዝነንም ቀለናል። ለማንኛውም ነገ አላህ ፊት የምንጠየቀው እንደ ግል ነውና በአቅማችን ልክ ቅንጣት ወደኃላ ሳንል ወደፊት ጉዟችን እንቀጥላለን! በጌታችን ፍቃድ በዳዮችንም እንቅልፍ እንነሳለን! ያለንበት ሁኔታ ግን እጅግ ያሳዝናል። ለዚህ ቁልቁለት እንዴት ነበር የፈጠንነው..?!
45 የበደል ቀናት
"..የሌሎችም እጣፈንታ ይህ ከመሆኑ በፊት ድረሱላቸው.."
ተማሪ ጀማል በፋጢማ ቢንት ሙባረክ የአይነ ስውራን ት/ቤት ለመማር ሲመጣ ትልቅ ስንቅን አንግቦ ነበር። የአይነ ስውራን ት/ቤት እምብዛም በሌለበት የሀገራችን ሁኔታ ውስጥ መሠል ት/ቤት ማግኘት ከእድልም በላይ ነበር።
ህልሙ ሁሉ እንደተጨናገፈ ለመረዳት ግን 45 የመከራ ቀናት በቂ ነበሩ። ከሶላት ክልከላ እስከ ሀይማኖት ጫና ድረስ ቢደራረብበት ት/ቤቱን ለቆ ለመውጣት ተገደደ። በት/ቤቱ ውስጥ ያሳለፋቸውን የሰቆቃ ቀናት በዚህ ፕሮግራም ውስጥ ዘርዝሮ ተናግሯቸዋል። ከጋዜጠኛ አብዱረሒም አህመድ ጋር ያደረጉትን ይህንን ቆይታ ዛሬ ምሽት 3:00 ጀምሮ ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።
ይጠብቁን...
''ሱረቱል አበሰ'' የቁርኣን ምእራፍ የወረደው አይነ-ስውር በሆነው አብደላ ኢብን ኡሙ መኽቱም ምክኒያት ነው። ዛሬ ማየት የተሳናቸው ወገኖቻችን መሃል ከተማ ላይ በአዳሪ ት/ቤት ሶላት እንዳይሰግዱ ሲከለከሉ ለነሱ ያሳየነው ቸልተኝነት ለኛ ማስተማሪያ ነው።
ረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም የቁረይሽ መሪዎች ሒዳያ ቢያገኙ ለዲኑ ይጠቅማል ብለው አስበው አይነ-ስውር የሆነው አብደላ ኢብን መኽቱምን ችላ ብለዋል ተብለው የተገሰጹበት ምዕራፍ ነው።
እስኪ አንቀጹን ተመልከቱት፧
ሱረቱ ዐበሰ
عَبَسَ وَتَوَلَّىٰٓ
ፊቱን አጨፈገገ፤ ዞረም፡፡
أَن جَآءَهُ ٱلۡأَعۡمَىٰ
ዕውሩ ስለ መጣው፡፡
وَمَا يُدۡرِيكَ لَعَلَّهُۥ يَزَّكَّىٰٓ
ምን ያሳውቅሃል? (ከኀጢአቶቹ) ሊጥራራ ይከጀላል፡
أَوۡ يَذَّكَّرُ فَتَنفَعَهُ ٱلذِّكۡرَىٰٓ
ወይም ሊገሠጽ ግሠጼይቱም ልትጠቅመው (ይከጀላል)፡
أَمَّا مَنِ ٱسۡتَغۡنَىٰ
የተብቃቃው ሰውማ፤
فَأَنتَ لَهُۥ تَصَدَّىٰ
አንተ ለእርሱ (ለእምነቱ በመጓጓት) በፈገግታ ትቀበለዋለህ፡፡
وَمَا عَلَيۡكَ أَلَّا يَزَّكَّىٰ
ባይጥራራ (ባያምን) ባንተ ላይ ምንም የሌለብህ ስትኾን፡
ይህ ልብ የሚነካ መልእክት ደረሰኝ ! ይህን ወንድማችንን አውቀዋለሁ ካሁን ቀደም ኡስታዝ በድሩ ሁሴንም ቪዲዮ ሰርቶለታል :: የህክምና ብሩ አልሞላለትም :: የቻልነውን እንተባበረው
------
As. Wr.wb
ሰላም ወንድሜ? መቼም በጣም እንዳስቸገርኩህ አውቃለሁ ፣ከብዙ ሰዎች ጋር የመገናኘት እድሉ ስላለህ ባገኘኸው አጋጣሚ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንዳደርግ ሚረዳኝ ግለሰብ / ድርጅት ብትጠይቅልኝ ብዬ ነበር
ይህ እንኳን ባይሳካ ትንሽ ሚረዳኝ ሰው ባገኝ
አቅሜም ተዳከመ ደያላይሲስ ላይ ያለ ሰው ብዙ ፕሮቲን ሉዝ ስለሚያደርግ በምግብ መተካት አለበት አለበለዚያ መቋቋም አይችልም፣አሁን ላይከአላህ በቀር ማንም ሚረዳኝ አጣው ባልናግርህ ደስ ይለኝ ነበር ግን አቅም በላይ ሆነብኝ
ለብዙ ሰው መድረስ የምችለው ሰው ዛሬ ላይ ለራሴ ሆድ ራሱ መድረስ አቃተኝ
እኛ ማናውቀው ትልቁ ነገር ጤናችን ነበር ለካ
አላኩሊሃል አልሃምዱሊላህ ...
ማግኘት ለሚፈልገኝ
ስልክ ቁጥር: +251-911791452
ለመርዳት: ስም ‐ ተማም ጀማል አህመድ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ: 1000040276053
ኦሮሚያ ህብረት ባንክ (COOP): 1000036464837
አቢሲኒያ ባንክ: 89064503
ኢቢሲ በነገው እለት የቤኒሻንጉል አሶሳ ስቲዲዮውን እንደሚያስመርቅ ይፋ አድርጓል ። በነገራችን ላይ እንደ ሃሩን ሚዲያ ትልቁ እቅዳችን በየክልሉ ቅርንጫፍ ስቲዲዮ እንዲኖረን ነው ። ለዚህም ከምናስባቸው አካባቢዎች አንዱ ቤኒሻንጉል ነው ። ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ የሚገርም ታሪክ፣የሚገርም እምቅ አቅም ያለው ማህበረሰብ ነው ።
ሃሩን ሚዲያ በአንድ ወቅት ቤኒሻንጉል ለረመዷን ጀዛከላህ ፕሮግራም ሲሄድ የነበረው አቀባበል እጅግ የሚያስገርም የሚያስድመም ነው ።
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱ
ልጆቻችሁን ከሀገር ውጭ አልፎ አቅም ኑሯችሁ ውጭ ሀገር በሚገኙ ታላላቅ ዩንቨርስቲ የማስተማር እድል ያላችሁ ሙስሊም ባለሀብቶች ለልጆቻችሁ ዱንያዊ ትምህርት የምትጨነቁት ያህል ለአኺራቸው ጉዳይም ትኩረት ብትሰጡ መልካም ነው ። ኢስላማዊ ስነ-ምግባራቸውን እንዲጠብቁ ዲናቸውን እንዲያውቁ እንዲተገብሩ በማድረግ በኩል ማገዝ ያስፈልጋል ። በትንሹ ሶላት እና ሂጃባቸውን የተመለከቱ ጉዳዮች ለድርድር ሊቀርቡ አይገባም ።
ነገ እናንተም ወደ አኺራ ስትሄዱ ለነገ ቤታችሁን የሚጠቅማችሁ በዲንም ጭምር ኮትኩታችሁ ያሳደጋችሁት ልጅ ነው ። የአካዳሚክ ትምህርቱ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ፣ሀብት አውርሶ ማለፍ ብቻ ትርጉም ያለው ነገር አይደለም ። ለሁለቱም ሀገር የሚጠቅመውን ነገር በብልህነት በአስተዋይነት ማስኬድ ታላቅነት ነው ።
ይህ መልእክት ሁሉንም ወላጆች ይመለከታል !
አላህ ልጆቻችን በመልካም ስነ-ምግባር በዲን ኮትኩተን የምናሳድግበትን ተቅዋ ይስጠን !
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana