ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ

Description
🥰 እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሄርን ያመስግነው።
መዝ. ፻፶ ፡ ፮
❝በጎንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማነው?
1.ጴጥ 3፡13
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago

1 month ago

**“አካሔድህን አስተካክል”

“ከአፍቃሪያችን ክርስቶስ** ያገኘነው ስጦታ እንዲህ ነው ተብሎ በቃላት መግለጥ የሚቻል አይደለም፡፡ እንዴት ያልን እንደሆነ እኛ በኀጢአት እየተንፏቀቅን I'mባለንበት ወራት እርሱ በምሕረቱ ጐብኝቶናልና፡፡ ኀጢአት ሸክም በሆነችብን ጊዜ እርሱ በእኛ ቦታ ተገብቶ ተሸክሞልናልና፡፡ በዚህ የማይለካ ፍቅሩ ከዲያብሎስ አገዛዝ ወደ መንግሥቱ አፈለሰን /ቈላ.1፡14/፡፡ እኛው ራሳችን ርቀን እርሱ ራሱ አቀረበን፡፡ እኛ ራሳችን በድለን እርሱ ካሠልን፡፡ ተወዳጆች ሆይ! ይህን ሁልጊዜ ከልቡናችን አናውጣ፡፡ የተሠጠንን ነጻ ሥጦታ አንዘንጋ፡፡ከምን እንደወጣን አንርሳ፡፡

ሰው ሆይ! የተጠራኸው ወደ ዘለዓለም ሕይወት ነው፡፡ የተጋበዝከው ወደ ልጁ መንግሥት ነው፡፡ ታድያ አንተእዚህ ስለምን ታንጠራራለህ? ስለምን እዚህ ትቀመጣለህ? ስለምን እዚህ
ትንፏቀቃለህ? ስለ ሥጋህ ድሎት ብዙ ዋጋን ትከፍላለህ፡፡ ታድያ ስለ ነፍስህስ ትንሽ አይገድህምን? ወደ ሕይወት ተጠርተህ ሳለ ስለምን ወደ ሞት ትሮጣለህ? ቢያስፈለግ ይህ
ያገኘኸው ስጦታ ላለማቆሸሽ ብዙ መሥዋዕትነትን መክፈል በተገባኽ ነበር፡፡ ብዙ ሰይፍን መታገሥ በተገባህ ነበር፡፡ ወደ እሳት እንኳ ብትጣል ስለ ድኅነተ ነፍስህ መቋቋም ይገባህ ነበር፡፡
ወዳጄ ሆይ! እስኪ ንገረኝ! የመንግሥተ ሰማያት ዜጋ ለመሆን ተጠርተህ ሳለ ራስህን የዚህ ዓለም ዜጋ ማድረግህ ስለምንድነው? እንደምን ያለ ስንፍና እንደያዘህስ ታስተውላለህን? ይህን
ዓለም የመውደደህ ምስጢር ምቾትን መሻትህ ያሳያል፡፡ በዚህ ዓለም በምቾት መኖርን የሚሻሰው ደግሞ ክርስቲያን መሆን፣ ክርስቲያን ተብሎ መጠራት፣ ክርስቶስን መስሎ መመላለስ
ምቾት ሳይሆን እስር ቤት መስሎ ይታየዋል፡፡ ሁላችንም ወደዚሁ ቈጥ ካስገባን ሰነባብተናል፡፡ ከዚህች ዓለም ጋር የተወዳጀ ግን ምንም ክርስቲያን ቢባልም ምንም በአርባና በሰማንያ ቀኑ የሥላሴን ልጅነት ቢያገኝም ክርስቲያን ክርስቲያን መሽተቱ እየጠፋ ይሔዳል፡፡በዚኽ ዓለም ወጥመድ ተቀፍድዶ ይያዛል፡፡

ወዳጄ ሆይ! ይህን አድምጥና ፍርሐትና ረዓድ ይያዝህ!!! ምንም በቤተ መንግሥት
ብትኖርም፣ ምንም በተሽቆጠቆጠ መኖርያ ቤት ብትኖርም እንደተመቸህ አድርገህ
አትንገረኝ፡፡ አንተ የምትኖርበት ኑሮ ለእኔ ወኅኒ ቤት ነው፤ ያውም ሊፈርስ የተቃረበ ቤት!!!
ይኽ ቤትህ ክረምት ሲመጣ ይፈርሳል፡፡ ክረምት (የመጨረሻይቱ ቀን) ስትመጣ ቤትህ ይፈርሳል፡፡ ክረምት ስላልኩህ ደግሞ “ለሁሉም ሰው ክረምት ከሆነበት እኔ ከማን እለያለሁ” ብለህ አታስብ፤ ይህቺ ቀን ለሁሉም ክረምት አትሆንምና፡፡ ዳግመኛም እግዚአብሔር ሌሊትና
ቀን ብሎ ጠርቷታልና፡፡ ሌሊት የምትሆንባቸው ለኀጥአን ነው፤ ቀን የምትሆንላቸው ደግሞ ለጻድቃን ነው፡፡ እኔም ክረምት ብዬ መናገሬ ከዚህ አንጻር ነው፡፡ ሁላችንም ክረምት ሲመጣ
መብረር እንችል ዘንድ በበጋው ላይ ካላደግን የገዛ እናቶቻችን እንኳ ቢሆኑ ትተዉን ይሔዳሉ እንጂ በዚያ ሰዓት እኛን መሸከም (ማዳን) አይቻላቸውም፡፡ የገዛ እናቶቻችን እንኳ በረሃብ እንሞት ዘንድ ትተዉን ይሔዳሉ፡፡ ቈጡ (ቤቱ) በላያችን ላይ ሲፈርስ እኛን መታደግ አይቻላቸውም ፡፡ እግዚአብሔር ቤቱን ሲያፈርሰው፣ አሮጌው እንደ አዲስ ሲያደርገው፣ እያንዳንዱ እንዳልነበረ ሲሆን እኛን መርዳት የሚችል አንድ ስንኳ አይገኝም፡፡ የዚያን ጊዜ ጌታን በአየር ላይ መገናኘት የማይችሉቱ፣ የመንፈስ ክንፍ ተሰጥቶአቸው መብረር የማይችሉቱ ቤቱ በላያቸው ላይ ይፈርስባቸዋል፡፡ ስቃይ የስቃይም ስቃይ ይሆንባቸዋል፡፡ ስቃዩ
የስቃይ ስቃይ ነው ማለቴ ከ እስከ የሚባል ስለሌለው ነው፤ ለዘለዓለም ስቃይ ስለሆነ ነው፡፡ ክረምት ብዬ መጥራቴ ስለዚሁ ነው፤ ኧረ እንደውም ከክረምት የባሰ ነው፡፡ እንዴት ያልከኝ እንደሆነ በዚሁ፡ክረምት ላይ የሚዘንበው ውኃ አይደለምና፤ እሳት እንጂ፡፡ በዚሁ ክረምት ዙርያህ ጨለማ የሚሆነው ከደመና ብዛት የተነሣ አይደለምና፤ ጽኑ ጨለማ እንጂ፡፡ የብርሃን
ጭላንጭል የሌለው ጨለማ እንጂ፡፡ እዚህ የሚገቡት ሰዎች ተድላ መንግሥትን ማየት
አይቻላቸውም፤ ሰማያትን ማየት አይቻላቸውም፡፡ ከመቃብር ውስጥ የባሰ ጨለማ ይውጣቸዋል እንጂ፡፡
ወዳጄ ሆይ! አሁንስ አትርድምን? ወዴት እየሔድክ እንደሆነ አታስተውልምን? ፊትህንስ ወደ ልጁ መንግሥት አታደርግምን?”… አካሔድህን አስተካክል…

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ )

@Ethiopian_Ortodoks
@Ethiopian_Ortodoks

1 month ago
[**#አማኑኤል\_\_ሆይ**](?q=%23%E1%8A%A0%E1%88%9B%E1%8A%91%E1%8A%A4%E1%88%8D__%E1%88%86%E1%8B%AD)

#አማኑኤል__ሆይ

#አቤቱ_ተወዳጅ_አማኑኤል_ሆይ
የምንኮራበት ክብራችን የምንደምቅበት አክሊላችን አንተ ነህ፤ ቀና ያልንብህ ትምክህታችን ያረፍንብህ ክንዳችን አንተ ነህ፤ እግራችን እንዳይሰናከል የምትጠብቀን እንዳንባዝን የምታረጋጋን አንተ ነህ፤

#አማኑኤል_ሆይ ፍቅርህን የሚመስለው የለም፡፡ እንዳንወድቅ የምትጠብቀን ብንወድቅ የምታነሳን አንተ ነህ፤ እንዳንደክም የምትራራልን ብንደክም የምታበረታን አንተ ነህ፤ እንዳንታመም ባንተ እንታመናለን ብንታመምም ስላንተ ተስፋ አለን፤

#አማኑኤል_ሆይ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? እንዳንሰናከል መላእክቱን ስለእኛ አዘጋጀልህን ጠላቶች እንደበዙብን አይተህ ወዳጆችን አበዛኅልን፤ ፈተናወቻችንን አይተህ መውጫውን ደግሞ አመላከትከን የቀደመውን ፍቅራችንን ብንቀንስ ያንተን ፍቅር አበዛህልን፤

#አማኑኤል_ሆይ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ራቅንህ አንተ ወደኛ ቀረብክ፤ በግብራችን ናቅንህ አንተ ግን እኛን አከበርክ፤ ያለአንተ መኖር እንደማንችል ታውቃለህና ክፋታችንን ሳታይ ራራህልን ስንፍናችንን ሳታይ ቀረብከን ፤

#አማኑኤል_ሆይ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ተወዳጅ ሆይ፦ እንዳንተ ያለ ለእኛ ማን አለን? ማንም የለንምና ክብራችንን አውቀን እንኖር ዘንድ አንተን ሳናስብ የምንውልበት ጊዜ አይኑረን፡፡
#ክብርና_ምስጋና_ላንተ_ይሁን*🙏 #_ሰናይ__ቀን🙏***

1 month ago
**በጨነቃችሁ በችግራችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ አማኑኤል …

**በጨነቃችሁ በችግራችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ አማኑኤል አለሁ ይበላችሁ።

🥰🙏🥰**

3 months, 2 weeks ago
**አርሴማን ጥሩልኝ*****?***

አርሴማን ጥሩልኝ?

በችግራችሁ ጊዜ ማን ከጎናችሁ ነበረ ?

ለኔ ለደካማውና ሃጥያተኛው ፀሃፊ ቅድስት አርሴማ?
በነገራችን ላይ አርሴማ ለኔ
? እናቴ አይደለችም
? እህቴም አይደለችም
? ጓደኛዬም አይደለችም
? ዘመዴም አይደለችም
ለእነዚህ ሁሉ የማይነገር ብዙ ነገር አለ
?ለኔ ለደካማው እስትንፋሴ ነች
? ለኔ ለሀጥያተኛው አእምሮዬ ነች
ከአእምሮ የሚደበቅ እንደሌለ ሁሉ እኔም ከአርሴማ የምደብቀው የለኝም ያለ እስትንፋስ እንደማይኖር ሁሉ እኔም ያለ አርሴማ ኣልኖርም ለዛ ነው በፅሁፌ አርሴማን ጥሩልኝ የምለው

3 months, 2 weeks ago
**አርሴማን ጥሩልኝ*****?***

አርሴማን ጥሩልኝ?
ክፍል ፪
ለካ ትዝ ሲለኝ የፀነስኩት በቅድስት አርሴማ ፀሎት ነው ቶሎ ብዬ ከባሌ ጋር ወደ ለቡ አርሴማ አቀናን እያለቀስኩኝ ወደ ደጇ ገባሁኝ ምነው እናቴ አመስግኜ ሳልጨርስ ብዬ ትንሽ አፈር አፈስ አድርጌ ሆዴን ቀባባሁኝ ወዲያውኑ ሆዴን ይቆርጠኝ ጀመረ በሆዴ ውስጥ ያለው ፅንስ ተገላበጠ በጣም ደነገጥኩኝ ባለቤቴን ልጃችን ተንቀሳቀሰ አልኩት ወዲያው እጆቹን ወደ ሆዴ አደረገ እውነትም ፅንሱ ዘለለ ደስ ተሰኘ በእንባ ቤተመቅደሱን ዞርነው ገና ሆስፒታል እንደደረስን ምጥ ጀመረኝ ማርያም ማርያም እያልኩኝ የአርሴማን ስዕለ አድህኖ ሆዴ ውስጥ አድርጌ በሰላም ወንድ ልጅ ወለድኩኝ ተመስገን ባሌን ልጅ ላሳቅፈው ነው ከማዋለጃ ክፍል ወጥቼ ወደተሰጠኝ ክፍል ስገባ በጣም ደነገጥኩኝ ውዱ ባለቤቴ እግዚአብሔር የሰጠኝ የኔ አዳም በምን ፍጥነት እንደሆነ ባላውቅም ክፍሉን በፅጌረዳ አበባ ሞልቶታል በጂፓስ አይኔን በአይኔ አየሁት … የሚለውን መዝሙር ከፍቶ ከመሀል ደግሞ ትልቅ የቅድስት አርሴማን ስዕል አስቀምጧል እንባዬን መቆጣጠር አልቻልኩም አርሴምዬ ምን ይሳንሻል ግን የኔ አዛኝ እያልኩኝ ወደ ጠዋት ላይ ወደቤታችን ሄድን ስንደርስ የኔ አብሮአደጎቼ ልብሰ ስብሐታቸውን ለብሰው በከበሮ እና በመሰንቆ ታጆበው በእልልታና በዝማሬ ተቀበሉኝ ገና ስገባ እናቴና የባለቤቴ እናት ዝቅ ብለው ስለእኛ እግዚአብሔርን አመሰገኑ በነገራችን ላይ እኔም እሱም እህትና ወንድም የለንም ታዲያ ልጅ በሌለበት ቤት ወንድ ልጅ ሲወለድ እንዴት ደስ አይሰኙ አድርገህልኛልና በቸርነትህ አመሰግንሃለው እልል እልል… ብቻ ምስጋና እና ዝማሬው የቃና ዘገሊላን ሰርግ ቤት ይመስላል ቀናት በቀናት ላይ እየተደራረቡ ልጃችንን ክርስትና ልናስነሳ ሽርጉድ እያልን ነው ሁሉን ነገር አሰናድተናል ……

ይቀጥላል
ብርሃኑ ባውቄ

3 months, 3 weeks ago
3 months, 3 weeks ago

እንደ እባብ ጠቢብ ኹን

እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲል ምን ማለት ነው? እባብ ጭንቅላቱን (ራሱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱ እጅግ በጣም ብዙ ጉዳት ቢደርስበት ይመርጣል፡፡

ስለዚህ እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲልህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን፣ ዝናህን፣ ጓደኞችህን፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ማጣት ካለብህ እንኳን በዚህ ማዘን መቆርቆር የለበህም ሲል ነው፡፡ ሃይማኖትህ ራስህ ነውና - እውነትን የምታውቅበት! እውነት ደግሞ አርነት ያወጣሃል፡፡

ኾኖም እንደ እባብ ጠቢብ መኾን ብቻውን ለእኛ በቂያችን አይደለም፤ እንደ ርግብ ሐቀኞችና የዋሆች መኾንም ያስፈልገናል፡፡ በጎ ምግባር የሚኖረው ጥበብንም የዋህነትንም አስተባብሮ መያዝ ሲቻል ነውና፡፡ ለምን ቢሉ እንደ እባብ ጠቢብ የኾነ ሰው ስለ ሃይማኖቱ ሲል ብዙ መከራዎችን ሊቀበል ይችላል፡፡

መከራ በሚያደርሱበት ላይ ክፉን በክፉ አለመመለስ የሚችለው ግን እንደ ርግብ የዋህ መኾን ሲችል ነው፤ እንደ ርግብ የዋህ መኾን ማለት መከራ በሚያደርሱብን ላይ በበቀል አለመነሣሣት መቻል ማለት ነውና፡፡ የዋህነት በጥበብ ሚዛን ካልተመጣጠነ አንድ ሰው መከራ ሲቀበል መከራ በሚያደርስበት ላይ በበቀል እንዲነሣ ያደርጓልና፡፡ ጥበብ በየዋህነት ሚዛን ካልተመጣጠነም እንደዚሁ አላስፈላጊ ሰማዕትነትን እንዲቀበሉ ያደርጋልና፡፡

ስለዚህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል እንደ እባብ ጠቢብ ኹን፡፡ አብረህም መከራ በሚያደርስብህ ላይ ላለመበቀል ስትል እንደ ርግብ የዋህ ኹን፡፡ ኹለቱንም አዋሕደህ አስተባብረህ ያዝ!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

4 months ago

ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡ የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

?(የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም)?

4 months ago

እግዚአብሔር ይመስገን እሷን ብሎ ማርያም የተሰኘው ልቦለድ ተፈፀመ ቀጣይ ለማቀርብላችሁ ፅሁፍ ያግዘኝ ዘንድ ሀሳብ አስተያየታችሁን እንዲሁም ከፅሁፉ ያተረፋችሁን ፃፉልኝ
❤️
❤️
❤️
❤️
እኔ ደካማ ወንድማችሁን ድክመቴን ሳትንቁ ስለምትሰጡኝ ሃሳብና አስተያየት እግዚአብሔር ያክብርልኝ

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 1 week ago