ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago
"ከነሀሴ 28 ጀምሮ ወደ አስመራ የሚደረገው በረራ ተቋርጧል" - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ነሐሴ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚያቋርጥ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ በረራውን የሚያቋርጠው "በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር" ነው ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው መልዕክት አስታውቋል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለበረራ ትኬት የቆረጡ መንገደኞች ያለምንም ተጨማሪ ወጪ በሌሎች አየር መንገዶች ጉዟቸውን እንዲያደርጉ ጥረት እንደሚያደርግ አሳውቋል።
አየር መንገዱ በበረራው መቋረጥ ምክንያት ለሚፈጠረው መጉላላትም ይቅርታ ጠይቋል። #EthiopianAirlines
ሩሲያና ዩክሬን ከ100 በላይ የእስረኛ ልውውጥ አደረጉ።
ዩክሬን 115 እስረኞችን የተረከበች ሲሆን፣ ሩሲያም 115 እስረኞችን ተረክባለች።
በጦርነት ውስጥ የሚገኙት ሁለቱ ሀገራት የእስረኛ ልውውጥ ያደረጉት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አደራዳሪነት ነው።
ሀገራቱ የእስረኛ ልውውጥ ሲያደርጉ ይህ ለ55ኛ ጊዜ ነው። #pbsnews
"የኢትዮጵያ ወታደሮች በሰላም ማስከበር ተልዕኮው አይቀጥሉም" - ጠ/ሚ አብዲ ባሬ
ከሶማሌ ላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ካልተሰረዘ በስተቀር የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ በሚሰማራው የአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር ድጋፍ /AUSSOM/ ውስጥ እንደማይካተቱ ሶማሊያ ገልፃለች።
የሶማሊያ ጠ/ሚኒስትር ሀምዛ አብዲ ባሬ፣ በሞቃድሾ በተደረገ ስብሰባ ላይ "ኢትዮጵያ ራሷን ከስምምነቱ ካስወጣች ወታደሮቹ ይቆያሉ፤ ካልሆነ ግን ለቀው ይወጣሉ" ሲሉ ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ኬንያ፣ ኳታርና ሳዑዲዓረቢያ እንድያሸማግሉ ጠይቃ የነበረ ቢሆንም እኛ ውድቅ አድርገነዋል ብለዋል። #voanews
አረብ ኤምሬት ለጎልደን ቪዛ ፕሮግራም አዲስ መስፈርት አወጣች።
የተባበሩት አረብ ኤምሬት ከቪዛ ጋር በተያያዘ ባወጣችው አዲስ ህግ በሀገሪቱ ቋሚ የመኖሪያ ፍቃድ ለማግኘት ወርሃዊ ገቢ 30 ሺሕ ድርሃም መሆን እንዳለበት አሳስባለች።
ወርሃዊ ገቢው ጥቅማጥቅም እና የትራንስፖርት ክፍያዎችን እንደማያካትት ተገልጿል።
በቪዛ ላይ በተደረገው ለውጥ መሠረት መስፈርቶችን የማያሟሉ ሰዎች በሀገሪቱ ለ10 አመት መኖር የሚያስችለውን የጎልደን ቪዛ ማግኘት አይችሉም። #dailyausaf
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 1 week ago
Last updated 6 days, 22 hours ago
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot
??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??
Last updated 2 months, 3 weeks ago