የጥበብ - መንገድ ™

Description
“Art is a step from nature toward the Infinite.”
~ Kahlil Gibran ™🌸📚


@abawassie ✉️
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago

2 weeks, 4 days ago

ለፈገግታ አንብቡ !

ግዙፉ የቻይና ኩባንያ ለሠራተኞቹ በአዞ በተሞላው ሀይቅ ላይ ጉዞ አሰናዳ። እየዋኘ አቋርጦ ከአንደኛው ጫፍ አዞዎችን ተሻግሮ ወደሌላኛው ጫፍ በህይወት ለሚደርስ ሰው አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚሸልም ካምፓኒው ተናገረ።

ሁሉም ሠራተኞች ወደ ሐይቁ መዝለልን ፈሩ። "ውድ ነፍሳችን ዓይናችን እያየ በአዞ ከሚበላ ሺህ ጊዜ ድህነታችን" እያሉ ባሉበት ቆመው ቀሩ።

በድንገት ከመሐላቸው አንዱ ሸሚዙን ከነከረባቱ እንዳጠለቀ ከጀልባው ላይ ዘሎ ወደ ሐይቁ ዘለቀ። በእጆቹ ውሀውን እየቀዘፈ በአዞዎች መሐል ያለ ምንም ፍርሀት  መዋኘቱን ቀጠለ። የስራ ባልደረቦቹ በድንጋጤ ዓይናቸውን አፈጠጡ። ሀይቁን ሲሻገር እየተመለከቱ በአግራሞቱ አንገታቸውን ነቀነቁ።

በዚህ ቅፅበት ያ ምስኪን ሰው ሚሊየነር ሆነ። በቤተሰቡም በመንደራቸውም ነዋሪዎች ዘንድ ዝነናው ሰው ሆነ።

በመጨረሻም ጋዘጠኞች interview እያደረጉ ምን እንደገፋፋው ሀይቁ ውስጥ ያለ ፍርሀት እንዲጠልቅ ምን እንዳነሳሰሰው ስጠየቅ ሚስቱ ሆና ተገኘች። #በጭቅጭቋ በግኖ አጋጣሚውን ተጠቅሞ ራሱን ለማጥፋት አስቦ ኖሯል ዘሎ የገባው።
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ
"ከስኬታማ ወንድ ጀርባ አንዲት ሴት አለች" የሚለው ታዋቂ አባባል የተሰማው የዛኔ ነው ይላሉ።

ምንጩ ፤ Unknown

2 weeks, 5 days ago
3 weeks ago

`በአንድ ወቅት ከጋሽ ስብሃት ገ/እግዚአብሄር ጋር ስለ ሕይወት ጥሪ እና የሞያ ምርጫ የተደረገ ቃለ-መጠይቅ:
፨፨፨ ፨፨፨ ፨፨፨

ጠያቂ፡- አንዳንድ ሠዎች ተሰጥኦዋቸዉ ሌላ ሆኖ እያለ በሌላ ሞያ ይሰማራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ደስተኛ ሳይሆኑ ይቀራሉ፡፡ አንተስ ደራሲነት ጥሪዬ ነዉ ብለህ ታስባለህ? ከሆነስ ደስተኛ ነህ ማለት ነዉ?

ስብሃት፡- ከረጅም ጊዜ በፊት ስሙን ዘነጋሁት መፅሐፍ ላይ ያነበብኩትን ሃሳብ አስታወስከኝ፡፡ በማኔጅመት ዙሪያ የተፃፈ አካዳሚክ መፅሐፍ እንደሆነ ትዝ ይለኛል፡፡ የሠው ልጆች በ 3 ይከፈላሉ ይላል ፀሐፊው፡፡

መሪዎች፣ተመሪዎችና አርቲስቶች በማለት ይከፍላቸዋል፡፡ 85 ፐርሰንት የሚሆነዉ አብዛኛዉ መደዴ ተመሪ ነዉ፡፡ 10 ፐርሰንት የሚሆነዉ መሪ ሲሆን የተቀረዉ 5 ፐርሰንት አርቲስት ነዉ ይላል፡፡ በወቅቱ ሃሳቡ ብዙም አልተዋጠልኝም ነበር፡፡ ቀስ ብሎ ግን ገባኝ፡፡ ለምሳሌ ያለጥሪዉ ተመሪ መሆን ሲገባዉ በኣጋጣሚ መሪ የሆነ ሠዉ ክፉ፤ ተንኮለኛ፤ መሠሪ እና በሠራተኞቹ የሚጠላ አለቃ ይሆናል፡፡ በወሬ የሚያምን ይሆናል፡፡ ስራ ያበላሻል፡፡ መስሪያ ቤቱን ገደል ይከታል፡፡ የሃገር መሪ ሲሆን ደግሞ አስበዉ፡፡ እንደ ሂትለር ወይም ኤዲያሚን ዳዳ ጨካኝ ይሆናል፡፡ አለያም እንደ ዮሃንስ አራተኛ ቀሽም ንጉስ ይሆናል መምራት አቅቶት ገዳም እንደገባዉ መናኝ የሃገራችን መሪ ወይም ደግሞ እንደዘዉዲቱ በቃኝ ብላ ለተፈሪ ዘዉድ እንዳስረከበችዉ፡፡ ያለግብሩ መሪ መሆን ሲገባዉ ወንበዴ አለያም ሌባ የሆነ ደግሞ የማፊያ አለቃ ሆኖ ቁጭ ይላል፡፡ ተይዞ ቢታሰር እንኳ የእስር ቤቱ ካቦ መሆኑ አይቀርም፡፡ አርቲስት ደግሞ መምራትም መመራትም አይሆንለትም፡፡ የሱ ድርሻ መጠበብ ነዉ፡፡ ፈጠራ፡፡ እንደኔ አይነቱ ማለት ነዉ፡፡ መድረስ፤ መተወን፤ መሳል፤ መዝፈን ወዘተ፣ ማለት ነዉ፡፡

ለምሳሌ መክሊታቸዉን በጊዜ ካወቁ እድለኞች መሃል እኔና መለስ ዜናዊን ልትወስደን ትችላለህ፡፡ መለስ ሠቃይ የህክምና ተማሪ ነበር፡፡ ትምህርቱን አቋርጦ 20 አመት ሳፕሞላዉ ጫካ ሲገባ አብዷል ያላለ አልነበረም፡፡ እኔ ግን መክሊቱን አማልክቶቹ ሹክ ብለዉት ነበር እላለሁ፡፡ ፖለቲካዉን ተወዉና በዚህ አድናቂዉ ነኝ፡፡ እኔም ከአሜሪካ የዩኒቨርሲቲ ትምህርቴን አቋርጬ ደራሲ ለመሆን ስመጣ ብዙዎች ጤንነቴን ተጠራጥረዉ ነበር፡፡ ህምምም … እና ምን ነበር ጥያቄህ …. አአአአዎዎ …. ደስተኛ ነኝ ለማለት ነዉ፡፡
.
ጠያቂ፦ፍልስፍና ያሳብዳል ??
.
ስብሃት፦ ፍልስፍና አያሳብድም።አንድ ሰው ፍልስፍና አንብቦ ካበደ መጀመሪያውኑ ለማበድ የሚያበቃ እርሾ በውስጡ ነበር ማለት ነው።
.
ጠያቂ ፦ፍልስፍና ለምን በጥርጣሬ ይታያል??
.
ስብሃት፦ ብዙ ሰዎች ፍልስፍናን በሩቁ ይላሉ ይፈራሉ።መጀመሪያዉኑ የነበራቸው እምነት ጠንካራ ስላልነበር ትንሽ ፍልስፍና እንዳነበቡ ከስር መሰረታቸው ይናጋሉ!ልባቸው በጥርጣሬ ይሞላል።ልብ አድርግ ያናጋቸው ፍልስፍናው አይደለም!ቀድሞ የነበራቸው ደካማ እምነት ነው !`

3 weeks, 5 days ago

እውነት ምንድን ነው? ቀደምት የፍልስፍና ሊቃውንትም ሆኑ ዛሬ በሳይንሳና ቴክኖሎጂ እየታገዙ በርካታ የምርምር ስራወችን የሚያከናውኑ ሊቃውንቶች በጋራ የሚያስማማቸው ነገር ቢኖር እውነት አንፃራዊ ገፅታ ያለው መሆኑን መናገራቸው ነው። የሚለያቸው ነገር ቢኖር ደግሞ ትናንት የቀደሙት የማይለወጥና አለም አቀፋዊ እውነትነት (universal truth) አላቸው ብለው ያፀኗቸው ነገሮች የዛሬው ቴክኖሎጂ ዘመን…

3 weeks, 5 days ago

እውነት ምንድን ነው? ቀደምት የፍልስፍና ሊቃውንትም ሆኑ ዛሬ በሳይንሳና ቴክኖሎጂ እየታገዙ በርካታ የምርምር ስራወችን የሚያከናውኑ ሊቃውንቶች በጋራ የሚያስማማቸው ነገር ቢኖር እውነት አንፃራዊ ገፅታ ያለው መሆኑን መናገራቸው ነው። የሚለያቸው ነገር ቢኖር ደግሞ ትናንት የቀደሙት የማይለወጥና አለም አቀፋዊ እውነትነት (universal truth) አላቸው ብለው ያፀኗቸው ነገሮች የዛሬው ቴክኖሎጂ ዘመን…

3 weeks, 5 days ago

እውነት አንፃራዊ ነች? ስለ እውነት አንፃራዊነት አልያም objectivity ጥያቄን ለመመለስ ከ matter of knowledge እና matter of opinion አንፃር ነገሮችን ከፍለን እስኪ እንመልከታቸው። በእውቀትና በopinion መካከል ደግሞ ሰፊ ልዩነት አለ። በእርግጠኝነት እና በprobability መካከል ያለው ልዩነት ከ እውቀትና opinion ልዩነት ጋር ይያዛል።እናም ከአንደኛው opinion…

1 month ago

አትጠይቅ (?)

"አትመርምር ፣ አትጠይቅ ፣
ልብህ ቢያስብ እንኳን ፣ ምላስህን ጠብቅ፣
"ዝም በል" የሚሉት ቃል ፦
ተመራምሮ ላየው ፣ ብዙ ያስጠይቃል ።

ሲጀመር ፦
አስተዋይ አዋቂ ፣ ጠያቂ...አዕምሮ፣
ከነፍስ ባህርይ፣ በሥጋ አንጎል ቋጥሮ፣
አምላክ ከፈጠረ
ስለምን ዝም ይበል፣ የተመራመረ ?

ሲቀጥል ፦
ልብ የጠየቀውን ፣ አንደበት አውጥቶ ስላልተናገረ፣
የልብብ ሚያውቅ አምላክ፣ እንዳልተጠየቀ እንዴት ተቆጠረ?

ባጭሩ ፦
የሰነፍ አንደበት ፣ ለመልስ ሲቸግረው፣
መርማሪ አዕምሮን፣ "በአትጠይቅ" አሰረው ።

መላኩ አላምረው

1 month ago

ሲያነቃቁን ለምን አንነቃም? ሙተን ይሆን እንዴ?
(አሌክስ አብርሃም)

ለመጀመሪያ ጊዜ self-help book የሚሏቸውን ሳነብ በጣም ነቅቸ ነበር! አስታውሳለሁ የ Rhonda Byrne ን The secret ሳነብ በጣም ከመንቃቴ የተነሳ ለስራ እጀን ከመጠቀም ይልቅ አዕምሮየን ለመጠቀም ወስኘ ነበር። ለምሳሌ መብራት አጥፍቸ ከመተኛት ተኝቸ መብራቱ ልክ እንቅልፍ ሲወስደኝ ይጠፋል ብየ ለራሴ እነግረዋለሁ፤ጧት ስነሳ እንደበራ ባገኘው አልደነቅም፣ ከእንቅልፌ ከመንቃቴ አንድ ደይቃ በፊት በራሱ ጊዜ እንደበራ አምናለሁ። የወሩ የመብራት ሂሳብ ግን የነገረኝ ሌላ ሆነ፤ ተው ወንድሜ በጣም አትንቃ አለኝ። እናም እያጠፋሁ መተኛት ጀመርኩ። ከ1890 ዓ/ም ጀምሮ መብራት ሀይል መብራት ያላጠፋበት ብቸኛ ወር ነበር። ስንነቃ አይወዱ😀

ኦሾን ያነበቡ የኔ ዘመን ወጣቶች ደግሞ "ሐይማኖት ባህል ገለመሌ ከጫነብን ፍዘት ወጣን" አሉና በየመንገዱ ፀጉራቸውን በመፍተል መቆዘም ጀመሩ፤ ይህንንም "ውስጣዊ ንቃት" አሉት። ከአመታት በኋላ ሁሉም ጠበል ገብተው እየጮሁ ከንቃታቸው በጣም ነቁ። በቀን አምስቴ ኡዱ የሚያደርጉ፣ ለጁመዓ የሽቷቸው መዓዛ ከሞያሌ የሚጣራ ፣ እንዴት ያሉ ንፁህ ሙስሊም ወዳጆቸ ሳይቀሩ ጀዝበው ገላቸውን መታጠብ አቁመው ነበርኮ! ስንት ተቀርቶባቸው ተመለሱ። የዛን ሰሞን ወጣቱ ሁሉ ውስጣችን በራልን እያለ ስንት ጨለማ ተከናነበ። ራሳቸውን ያጠፉም ነበሩ። ኦሾና አለቃ ገብርሃና ተረታቸው እንጅ ኑሯቸው አያምርም።

ይሄው በዚህኛው ዘመን ደግሞ አነቃቂወች እንደአሸን ፈሉና "ያሰብከውን ትሆናለህ፣ ነኝ በል፣ አለኝ በል፣ ደርሻለሁ በል፣ እችላለሁ በል፣ በሀሳብህ መኪና አስነሳ፣ አሉ፤ ወጣቱ የሀሳብ መኪና አስነሳ፤ በሀሳብ ሲጋልብ ራሱጋር ተጋጨ፣ ቤተሰቡ ጋር ተጋጨ፣ አገሩ ጋር ተጋጨ፣ፈጣሪው ጋር ተጋጨ ። ከሆነስ ሆነና ለምንድነው በዚህ ዘመን ይሄ ሀሁሉ አነቃቂ ንግግር ያላነቃን? የእውነት የሆነ ጊዜ ያነቃን ነበርኮ፣ እየቆየ ግን እንኳን ሊያነቃን ያስተኛን ጀመረ፤ እኮ ለምን?

የህክምና ባለሙያወች ከተሳሳትኩ አፉ ብለው ያርሙኝና በእነሱ ሙያ Drug tolerance የሚሉት ነገር አለ አሉ፤ በትክክል ከተረዳሁት ለሆነ ህመም የተሰጣችሁ መድሀኒት ከሆነ ጊዜ በኋላ በሽታችሁ ጋር ይግባቡና ፍሬንድ ይሆናሉ። በሽታው መድሃኒቱን ይላመደዋል።ጉቦ እንደበላ ደንብ አስከባሪ በሽታችሁ መንገድ ዳር ሲያሰጣችሁ መድሀኒቱ እንዳላየ ያልፈዋል። ለምሳሌ የእንቅልፍ ችግር ገጠማችሁና በሐኪማችሁ የእንቅልፍ ኪኒን ታዘዘላችሁ እንበል ፤ የመጀመሪያ ሰሞን ድብን ያለ እንቅልፍ ያስወስዳችኋል፤ እየቆየ ሰውነታችሁ ሲላመደው መድሀኒቱን ውጣችሁም ቁልጭ ቁልጭ ስትሉ ታነጋላችሁ። ወይ አይነቱን ወይ መጠኑን ባለሙያ ካልቀየረው በቃ ለውጥ የለም። አይ መጠኑን ራሴ እቀይረዋለሁ ብላችሁ ጨመር አድርጋችሁ ከወሰዳችሁ ደግሞ ትተኙ ይሆናል ግን እንደገና ላትነሱ ትችላላችሁ።

ወደህይወት ስናመጣው እኛ ኢትዮጵያዊያን በአሁኑ ሰዓት ማንኛውንም ማነቃቂያ ከመላመድ አልፈን እንደዘፈን ሸምድደነው አብረን እየደገምነው ነው። ገና ፊቱን ስታዮት አብራችሁ "ብሮሮሮሮሮ" አትሉም?! ለዛ ነው ከነዋሪ መካሪና ዘማሪ የበዛው። የፈለገ ብንመከር ብንዘከር ብንሰበክ ብንወገዝ ወይ ፍንክች። አሁን ሞራል፣ ሐይማኖት፣ የአገርም ይሁን የሰው ፍቅር፣ ይሉኝታ ፣መማር ወዘተ አእምሯችን ተላምዷቸው ተራ ነገር ሁነውብናል።

የሞራል ተቋሞቹ በሞራል ድሽቀት ከተራው ህዝብ ቀድመው ባፍጢማቸው ተተክለዋል፤ የትዳር ሰባኪወቹ ማግባትና መፍታት መድረክ ላይ እንደመውጣትና መውረድ ቀሏቸዋል። እንደውም የጓዳቸውን ውድቀት እንደባንዲራ በአደባባይ እየሰቀሉ እዮልን ባይ ሆነዋል። አሁን እንደህዝብ ሁለት ነገሮች ብቻ ናቸው የሚያነቁን ወይ (((ብር ማጣት))) አልያም (((ብር ማግኘት)))። ይሄ የመጨረሻው ዶዝ(መጠን) ነው! ሰው ክብሬ ገመናየ ማንነቴ የሚለውን ነገር ሁሉ ይዞ ገበያ ከወረደ ምን ይመልሰዋል?! ከዚህ በኋላስ? ምን ያነቃን ይሆን? ምክንያቱም በብር የሚመጣ ንቃት በአንዴ አይረካም፤ እንደአደንዛዢ ዕፅ በየቀኑ መጠኑን እየጨመሩ ካልተወጉት መጨረሻ የለውም። መመለስም መቀጠልም የማንችልበት አውላላ ሜዳ ላይ የሚያስቀር መርገምት ነው!! ምን ላድርግ ቸገረኝ፣ የማደርገው አጣሁ በሚል ሰበብ ከሰውነት ድንበር ከምንርቅ በየግላችን "ይሄንኛው ነገሬ ለገበያ ከሚቀርብ ሞቴን እመርጣለሁ" የምንልለት የሆነ መስመር ልናሰምር ግድ ነው። ሰው ራሱ ወስኖ ያሰመረውን መስመር ከሞት በስተቀር መን ያሻግረዋል?!

1 month ago

መሰልቸትን ማፍቀር አለብህ

“አንድ ስኬታማና ስመጥር አሰልጣኝ አገኘሁና በምርጥ አትሌቶችና በሌሎች ተራ ሰዎች መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?” ብዬ ጠየቅኩት፡፡

“ብዙዎች የማያደርጉትና ውጤታማ ሰዎች የሚያደርጓቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?” አይነት ጥያቄ፡፡

በመጀመሪያ አንተም ልትገምታቸው የምትችላቸውን ነገሮች ዘረዘረልኝ፡፡ ዘረመል፣ እድል፣ ተሰጥዖ፣ ወዘተ፡፡ ከዚያ ግን አንድ ያልጠበቅኩት ነገር ነገረኝ፡፡ “ከሆነ ሂደት በኋላ ግን ወሳኙ ነገር በየቀኑ አንድ አይነት ሊፍት የማንሳትን እና ተመሳሳይ ልምምድ የመስራትን አሰልቺነት የሚቋቋመው ማነው የሚለው ይሆናል።”

መልሱ በጣም አስደነቀኝ፡፡ ምክንያቱም ይህ የሥራ ምግባርን በሌላ አተያይ የሚያይ አመለካከት ነው። ሰዎች በግባቸው ላይ ለመስራት ስለ መበርታት ሲያወሩ እንሰማለን፡፡ በስፓርቱም ይሁን በአርቱ ወይም በንግድ ዘርፍ “አጥብቀህ መፈለግ አለብህ” ወይም “ሁሉም ነገር የጥረት ውጤት ነው” አይነት አባባሎችን ሲናገሩ እንሰማለን፡፡ በዚህም የተነሳ ተነሳሽነትንና ትኩረትን ስናጣ ይደብረናል፡፡ ምክንያቱም ስኬታማ ሰዎች ጥልቀቱ የማያልቅ የጥረትና የፍላጎት ፀጋ ያላቸው እንደሆኑ እናስባለንና፡፡

ይህ አሰልጣኝ እያለኝ ያለው ነገር ግን ውጤታማ ሰዎችም ማንኛውም ሰው የሚሰማውን ያህል ተነሳሽነት የማጣት ስሜት ሊሰማቸው ይችላል ነው። ልዩነቱ እውነተኛ ውጤታማ ሰዎች ከድብርታቸው ተመንጭቀው የሚነሱባቸውን መንገዶች አጥብቀው ፈልገው የሚያገኙ መሆናቸው ነው፡፡

አንድን ነገር በደንብ ማወቅ ልምምድን ይጠይቃል። አንድን ነገር እየደጋገምክ በሄድክ ቁጥር ግን አሰልቺ ይሆንብሃል፡፡ አንድ ጊዜ የጀማሪነትን ጥቅም ከተቀበልንና ምን መጠበቅ እንዳለብን ካወቅን በኋላ ፍላጎታችን እየጠፋ መሄድ ይጀምራል።

ሁላችንም ልናሳካቸው የምንፈልጋቸው ግቦችና ልንተገብራቸው የምንፈልጋቸው ህልሞች አሉን፡ የትኛውንም ለውጥ ለማምጣት ይሁን የምትሰራው ሥራህን የምትፈፅመው ሲመችህ ብቻ ከሆነ ወደ ውጤት የሚያደርስህ በቂ ወጥነት መቼም አይኖርህም፡፡

አንድን ልማድ ለማዳበር አስበህ ብትጀምረውና የሙጥኝ ብለህ እያስኬድከው ያለኸው ቢሆን እንኳን “ተወው” የሚልህ ቀን መምጣቱ እንደማይቀር እርግጠኛ አደርግሃለሁ፡፡ ስትፅፍ መጻፍ የሚሰለችህ ጊዜ አለ፡፡ ስፖርት ስትሰራ መጨረስ የሚሳንህ ጊዜ አለ... ወዘተ። በፕሮፌሽናሎችና በአማተሮች መካከል ያለው ልዩነት እንደዚህ አይነት ስሜት ውስጥ ሆነህና መስራት አስጠሊና አናዳጅ ነገር ሆኖብህም ስራህን መቀጠል ስትችል ነው።

ፕሮፌሽናሎች በጊዜ ሰሌዳቸው መሰረት ሳያዛንፉ ይሰራሉ፤ አማተሮች ግን ከደበራቸው ተወት ያደርጉታል። ፕሮፌሽናሎች  የሚጠቅማቸውን ነገር ያውቁታልና በዓላማቸው ይገፉበታል። አማተሮች ግን በትናንሽ እንቅፋቶች እየተገፉ ከመንገዳቸው ይወጣሉ።

አንድ ልማድ በጣም አስፈላጊህ ከሆነ በየትኛውም ሙድ ውስጥ ሆነህ ልትተገብረው ቆራጥነቱ ሊኖርህ ይገባል። ፕሮፌሽናሎች በመጥፎ ስሜት ውስጥ ሆነውም እንኳን መስራት ያለባቸውን ይሰራሉ፡፡ ደስ ላይላቸው ይችላል፤ ድግግሞሹን ላለማቋረጥ ግን መንገዱን አያቋርጡም፡፡

በአንድ ነገር ላይ እጅግ በጣም ጎበዝ የመሆናቸው ብቸኛ መንገድ አንድ ነገር ማለቂያ በሌለው ሁኔታ እየደጋገሙ በመስራት ደስ መሰኘት ነው። መሰልቸትን ማፍቀር አለብህ፡፡

©Atomic habit

ጄምስ ኪለር

1 month, 1 week ago
```

```
ከሰባት ክፍለ ዘመናት በፊት ሰባት እርግቦች ከጥልቅ ሸለቆ ተነስተው በበረዶ ወደተሸፈነው የተራራ ጫፍ በረሩ። የርግቦቹን መብረር ከተመለከቱ ሰባት ሰዎች መሃል አንዱ
"በሰባተኛው ርግብ ክንፍ ላይ ጥቁር ምልክት አይቻለው" አለ።

ዛሬ በዛ ሸለቆ የሚኖሩ ሰዎች በበረዶ ወደተሸፈነው ተራራ ስለበረሩ ሰባት ጥቋቁር ርግቦች ይናገራሉ።

ካህሊል ጂብራን 📚
```

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 3 weeks, 1 day ago

Last updated 2 weeks, 3 days ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated 1 month ago