ዝክረ ተማሪ

Description
ይህ ዝክረ ተማሪ የተሠኘው ቻናላችን ነው። በዚህም ቻናል ስለ ጥንታዊ ቆሎ ተማሪዎች እናወሣለን ። ይከታተሉ ።

https://www.instagram.com/zkre_temari?igsh=MThoZDRteWhvNjlvbw==
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago

3 weeks, 1 day ago
**የየካቲት ኪዳነ ምህረት ክብረ በቃል ቀለም …

https://youtu.be/MiDA3hsdlJM?si=NNPRex3_VmgsmPre

የየካቲት ኪዳነ ምህረት ክብረ በቃል ቀለም በሊቀ ጠበብት ቀለመ ወርቅ ልይህ

3 weeks, 2 days ago
የተማሪው ረጅም ጉዞና በደረሠበት የትምህርት ቤት …

የተማሪው ረጅም ጉዞና በደረሠበት የትምህርት ቤት አቀባበል
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
አንድ ተማሪ ትምሕርቱን ለመቀጠል ከመላው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ግዛቶች ተነሥቶ 10 ወይም 15 ቀን  በእግር ከተጓዘ በኃላ በትጋት ከሚያሥተምሩ መምሕራን  በለጋሥነት ከታወቁ ምዕመናን ከየሚገኙባቸው ሀገራት ወደ ፈቀደው አንዱ ይሄዳል። በደረሠም ጊዜ  የትምህርት ቤት ወዴት እንዳለ ይጠይቃል ......
ምን ያጋጥሙው ይሆን 😕 በቀጣይ ..
@zkretemari

ተቀላቀሉ☝️☝️☝️
https://t.me/zkretemari

ወዲያው  ከሥፍራው ከደረሠ በሗላ ግማሾቹ ዜማውን ንባቡን ሌሎቹም በአቅማቸው ሲማሩ ድምፃቸውን በሰማ ጊዜ ወደነሱ ተጠግቶ በፍርሃት ይቆማል እነሱም ከትምህርታቸው ተነሥተው በአክብሮት አንዱ አኮፋዳውን አንዱ ደሞ በትሩን ይቀበለዋል  ሌሎቹ ደሞ ማረፊይውን ያዘጋጁለታል በመቀጠል አንዱ ለእግሩ ውሀ ሲያመጣ ሌላዉ ደሞ እግሩን ያጥባል የተቀሩትም ስለ መሥተንግዶው ጥሬ ይቆላሉ።
🔅🔆🔅🔆🔅🔆🔅🔆🔅🔆
ይህም የሚያሳየው ጥንታዊው ተማሪ የቀለሙን ትምርት ብቻ ሳይሆን ሚቀስመው ትህትናን እና ወዳጅነት ጭምር እንደሆነ ነው።
🔆🔅🔆🔅🔆🔅🔆🔅🔆🔅
https://t.me/zkretemari

እንግዳው ተማሪ የትምህርት ሠዐት ደርሶ ጉባኤው እሥኪነሣ ይጠብቅና በእረፍት ሠዐት ለ መምህር ይነገርለታል ።
እርሱም ለ መምህሩ ቀርቦ የመጣበት ቦታ እና  ምን ሊማር እንደመጣ ያሥረዳል ።
እንግዳውም ከ ተማሪዎቹ እና አካባቢውን እሥኪላመድ  በቅርብ ከሚገኙ መንደሮች ተከፍሎ እንዲሠጠው ይደረጋል ።
ለጊዜው ይታዘዝለት እንጂ ተማሪዎቹ ሥለእንግዳነቱ ክብር ፫ _፬  ወር እየለመኑ ሥለሚመግቡት ወደ ልመና አይሠዱትም ።
ጥንታዊ የቆሎ ተማሪ በየሄደበት ትምህርት ቤት እንደዚህ ያለ አቀባበል  ይደረግለት ነበር  አሑንም አለ ።     
👉https://t.me/zkretemari

📌ጥንታዊ ተማሪና ችግሩ    
                    በትምህርት ቤት 📌
በሚቀጥለው ጊዜ📖

3 weeks, 5 days ago
የአብነት ትምህርት በአካል በመገኘት መማር ለምትፈልጉ …

የአብነት ትምህርት በአካል በመገኘት መማር ለምትፈልጉ ከጀማሪ ጀምሮ ........

4 weeks ago

🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢

*🔺*አእዱግ ወበቅል እንዘያወጽኡ
               ስሳ...
በአንድ ወቅት የቅኔ መስፍን እየተባለ ይደነቅ የነበረው የዋድላው ሊቅ መምህር ሲራክና የአክሱም ጽዮን ሊቃውንት እርስ በእርስ ቅኔ በመዘራረፍ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ሲፎካከሩ ነበር።

ይህ የሆነው ሲራክ የቅኔ መስፍን በመምህርነት ለመቀጠር ሲል ከጓደኞቹ ጋር ወደ አክሱም ጽዮን በሄደበት ወቅት ነው።

ሲራክና ጓደኞቹ ሥራ ለመቀጠር አክሱም የደረሱት በአጋጣሚ ለኅዳር ጽዮን በዓል ቀን ነበርና በቅኔ ችሎታው ዝነኛ ለሆነው ለሲራክ ዋዜማ ቅኔ እንዲቀኝ ይሰጠዋል።

ሲራክም በወቅቱ ከተቀኘው ቅኔ ውስጥ "ዐውዳ ለጽዮን"የሚል ሐረግ ይገኝበታል።ትርጉም "የጽዮን ዙርያዋ"ማለት ነው።

ካህናቱ ግን አሽሙረኛና ተሣላቂ መሆኑን በመረዳት የጽዮን ሰነፎች አውደልዳዮች ብሎ ሰደበን በሚል ይወርፉታል።እንዲያውም የቅኔ ትምክህቱ ፣በራስ የመተማመን ጉልበቱ
እንዲበርድለት በሚል የአክሱም ካህናት የሲራክ ጓደኞች በዓመት ስድሳ ስድሳ ብር እሱን ግን በዓመት ሠላሳ ብር ሒሳብ ይቀጥሯቸዋል።

እርሱ ግን ልቡ በቅኔ ፍልስፍና የተሞላ ስለነበር ....*🔻*አእዱግ ወበቅል እንዘያወጽኡ  ስሳ፣

ሲራክ አምላከዋድላ ተሰይጠ ሠላሳ።**

ብሎ ተቀኘባቸው....

ትርጉም:-አህዮችና በቅሎዎች ጓደኞቸ ስድስ ስድሳ ብር ሲያወጡ የዋድላው አምላክ ሊቁ ሲራክ ግን በሠላሳ ብር ተሸጠ ማለት ነው።ይህም ራሱን እንደ ክርስቶስ፣ጓደኞቹን ደግሞ በአህያና በበቅሎ መስሎ መዝረፉን ያመለክታል።

📱 https://t.me/Geezz12

4 weeks ago
እሑድ በዐውደ ፋጎስ

እሑድ በዐውደ ፋጎስ

" መጽሐፈ ሄኖክ በውጭው ዓለም የሚጠናባቸው ምክንያቶች" ======================================
በዶ/ር አባ ዳንኤል አሰፋ (በመጽሐፈ ሄኖክ ዙሪያ ጥልቅ ምርምር ባደረጉ ምሁር) እሑድ የካቲት 09.2017 ዓ.ም በዐውደ ፋጎስ የውይይት ክበብ ይቀርባል። በሰዓቱ ይገኙ።

ግዕዝን በቀላሉ ለመማር
✈️https://t.me/geeZzlekulu

4 weeks ago
ዝክረ ተማሪ
4 weeks ago
እንዴት አደራችሁ እግዚአብሔር ይመስገን***🙏***

እንዴት አደራችሁ እግዚአብሔር ይመስገን🙏

ተዘከር ቃለከ ዘአሰፈውኮ ለገብርከ ፤
ወይእቲ አስተፍስሐተኒ በሕማምየ ፤ እስመ ቃልከ አሕየወኒ

ለባርያህ ተስፋ ያስደረግኸውን ቃልህን አስብ፤
ቃልህ ህያው አድርጎኛልና ፤ ይህች በመከራዬ ደስ አሰኘችኝ።
- መዝ ዳዊት ም 118 ቁ (49,50)

join - https://t.me/zkretemari
🌿🌿🌿🌿እውነተኛ ታራክ 🌿🌿🌿🌿🌿

ሔንሪ ሽቭርኔል የሚባል የኮሎምቢያ ሰው ቹሩቡሾ በተባለ ቦታ በሜክሲኮ ጦርነት ላይ ሲዋጋ ሰኔ 20 ቀን 1847 ዓ.ም ከደረቱ ላይ በጥይት ተመታ ።
        ጥይቲቱ የመታችው በልቡ አኳያ ሲሆን ጥይቲቱ ደረቱ ላይ ይዞት ከነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰጥማ በመቅረቷ ሔንሪ በመጸሐፍ ቅዱሱ ሰበብ ከመሞት ዳነ መጽሐፍ ቅዱሱ ባይኖር ግን ልቡ ይመታ እንደ ነበር ጓደኞቹ መስክረዋል።

-ምንጭ ጳውሎስ ኞኞ

🧐እኛስ መጽሐፉን ስላልያዝን በስንት አይነት ጥይት ልባችን ተመቶ ይሆን ??

🌿https://t.me/zkretemari
https://t.me/zkretemari🌿
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
Join share

4 weeks, 1 day ago
***🌿******🌿****ዘመነ ነነዌ ፈጠራ ወረብ* ***🌿******🌿***

🌿🌿ዘመነ ነነዌ ፈጠራ ወረብ 🌿🌿

በሊቀ ጠበብት ቀለመ ወርቅ ልይህ ።

እምልሳነ ሊቃውንት አስተዳለወ ስብሐተ ዘኮነ ሰማያዊ ።

subscribe and share እያረጋችሁ😌

https://youtu.be/na1QlcqyMUw?si=1b5c8ZVvcQM5IkKQ

🌿https://t.me/zkretemari
https://t.me/zkretemari🌿
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
Join share

1 month ago
''[እውነት በሌለበት አለም ለመኖር አልወለድም](https://t.me/geazlekulu)''

''እውነት በሌለበት አለም ለመኖር አልወለድም''

«እሺ ፡ መሬት ፡ አለሽ? »
«የለኝም»
«ቤት  እለሽ ?»
«የለኝም ።»
«ትምህርት እለሽ ?»
«የለኝም ።»
«ታዲያ ፡ ምን ፡ አለሽ ?»
«ምንም ፡ የለኝ ።»
«ታዲያ፡ ድህነት፣ በሽታንና ድንቁርናን ልታወርሺኝ ፡ ነው ፡ ተወለድ የምትይኝ?»
«ዕድልህን ፡ እንዴት ፡ አውቀዋለሁ ፡ ልጄ?» አለች ፡ በትካዜ።»
.
.
አልወለድም

©አቤ ጉበኛ

✈️https://t.me/geazlekulu

1 month ago

የተማሪ ወግ

አንድ ሴትዮ ከባሏ ተደብቃ መብላት የለመደች እንደተለመደው ባሏ ሳይመጣ ልበላ ቂጣዋን ስትጋግር  'ተሜ' ከደጃፍ 'በእንተ ስማ ለማርያም' በማለት ቁራሽ ልመና ይቆማል ። በዛው ተከትሎ ባለቤቷም በድንገት ይመጣባትና  ምን እያረግሽ ነው ቢላት ተሜ ዱቄት አምጥቶ አነጉችልኝ ቢለኝ ያጸድቀኛል ብዬ አነጉታለው አለችው።
ተማሪውም ይህን ሲሰማ ቆይቶ ባለቤቱ ሲወጣ ሽልጦዬን ሳታሰጡኝ አይሂዱ ብሎ ይማጸናቸዋል ። ሰውየውም ሚስቱን ለተማሪው ሽልጦውን ስጭው ቢላት ትኩስ ነው አኮፋዳውን ያቃጥልበታል ይብረድለት ብዬ ነው ፤ ሂድ አንተ እሰጠዋለው ትለዋለች።
ይሄኔ ነገሩ የገባው ተማሪ ሰውየውን ሽልጦዬን ሳያሰጡኝ እንዳይሄዱ በእግዚአብሔር ስም ይዤዎታለው ይላቸዋል። ሰውየውም ሴቲቱን በቁጣ ቃል እንድትሠጠው  ያዟታል። ሴቲቱም ያለ ውድ በግድ አንከብክባ አምጥታ ሽልጦውን ከአኮፋዳው ትከታለች። በዚህ በጣም የተቆጨችው ሴትዮ ተሜን በኋላ ኋላ እየተከተለች ቀጥሎ ያለውን መርገም እና በረከት ተለዋወጡ ይባላል።

🌿https://t.me/zkretemari🌿

ሴትየዋ - ይነቅህ አለችው😡
ተሜ -
😌ውሃ እጠጣለው
ሴትየዋ - ይቁረጥህ እለችው
😡
ተሜ -
😌ግራዋ እጠጣበታለው
ሴትየዋ - ከቤትህ አያድርስህ
😡
ተሜ -
😌በመንገድ አድራለው አላት
ሴትየዋ - ለናትህ ልጅ አትሁናቸው አለችው
😡
ተሜ -
😌ለአባቴ እሆናለው

እያለ እርግማኗን ወደ በረከት በመለወጥ ምላሽ አሳጥቶ አሳፍሮ መለሳት።
ምንጭ - ጥንታዊ የቆሎ ተማሪ

መልካም ዕለተ ሰንበት 🙏😌

🌿https://t.me/zkretemari
https://t.me/zkretemari🌿
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
Join share🫵

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 3 weeks ago

Last updated 2 months, 2 weeks ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 1 month, 2 weeks ago