Nejashi Printing Press

Description
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana

hace 2 meses, 2 semanas

መፃሕፍትን እቤትዎ ወይም ሥራ ቦታዎ ድረስ እናምጣልዎ

ፕሌይ ስቶርን በማውረድ ወደ Nejashi Bookstore  ወይም በዌብሳይታችን WWW.NEJASHIBOOKS.COM በመግባት
የመፃሕፍት ዝርዝሮች በማየት የፈለጉትን መጽሐፍ ይምረጡ። ዋጋው እዚያው አለላችሁ ።

ከዚያም ወደ 0945858585 በመደወል የመረጡትን መጽሐፍ ይዘዙ።
ለአዲስ አበባ ደንበኞች
የትራንስፖርት 50 ብር ብቻ ይከፍላሉ ።

ወደ ክልሎች በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ

https://t.me/NejashiPP

hace 3 meses, 2 semanas

መፃሕፍትን እቤትዎ ወይም ሥራ ቦታዎ ድረስ እናምጣልዎ

ፕሌይ ስቶርን በማውረድ ወደ Nejashi Bookstore ወይም በዌብሳይታችን WWW.NEJASHIBOOKS.COM በመግባት
የመፃሕፍት ዝርዝሮች በማየት የፈለጉትን መጽሐፍ ይምረጡ። ዋጋው እዚያው አለላችሁ ።

ከዚያም ወደ 0945858585 በመደወል የመረጡትን መጽሐፍ ይዘዙ።
ለአዲስ አበባ ደንበኞች
የትራንስፖርት 50 ብር ብቻ ይከፍላሉ ።

ወደ ክልሎች በፖስታ ቤት በኩል እንልካለን።

ነጃሺ መፃሕፍት መደብር
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ

https://t.me/NejashiPP

hace 4 meses

ሶባሐል ኸይር !

ሁለት አዳዲስ መፃሕፍት ልጠቁማችሁ ነው።

1- የሰዒድ ሽፈራውን ሐላልን ፍለጋ መጽሐፍ አንብባችኋል?

አዎ አሁን ደግሞ "ሐቢብ" ብሎ መጥቶላችኋል፡፡ ወይም ደግሞ "ሐላልን ፍለጋ ቁጥር 2" ልትሉት ትችላላችሁ፡፡
መጽሐፉ ኢስላማዊ ታሪክ ወይም ልቦለዳዊ ነው፡፡ ከኢስላማዊ እሴትና አደብ ሳይወጣ ተጨባጭ የሕይወት ታሪካችንን ይዳስሳል፡፡

ታይፓችሁ የሆነ እነሆ ….

2- ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመርን ታውቁት የለ..
አዎን የርሱን መፃሕፍት ካላነበባችሁ ብዙ ነገር አምልጧችኋል፡፡ ጥንቅቅ ጥንፍፍ ያለ፣ በመረጃና ዕውቀት የዳበሩ፣ ብዙ የተደከመባቸው ዝግጅቶች ናቸው፡፡

"አርዓያ" የተሠኘው ምርጥ መጽሐፉን ካነበባችሁ አሁን ደግሞ “አርዓያ ቁጥር 2” በተሠኘ መጥቶላችኋል፡፡
መጽሐፉ የታላቁ አርዓያችንን የነቢያዊውን የሕይወት ዘይብ ይዳስሳል ። ብዙ ብዙ ትማሩበታላችሁ።

ሁለቱንም መፃሕፍት ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኟቸዋል፡፡

https://t.me/MuhammedSeidAbx

hace 4 meses, 3 semanas

.......የፈራ ማልዶ ይነሣል፡፡ እወድቃለሁ ብሎ የሠጋ በርትቶ ያጠናል። የድህነትን ክፋት የፈራ በርትቶ ይሠራል፡፡ በጊዜ ሂደትም ድህነትን ይገላገላል፡፡ እውቅናን ማግኘት ዓላማው የሆነ ሰው መግባት መውጣት፤ መቆም መነሣት ፤ በአደባባይ መታየት ከፊት ለፊት መገኘት ያዘወትራል፡፡ በዚህም ከጊዜያት በኋላ የሃሣቡን ያሣካል፤ የኒያውም ይሞላለታል፡፡ ለብር የቋመጠ ሰው በእንቅልፍ ልቡ ሲዞር ያድራል፤ በጧት ተነስቶ ይሮጣል፤ በቀን አብዝቶ ይደክማል፤ ምሽቱን ገፍቶ ይተኛል፤ ኋላም ሀብት ያገኛል፡፡ ለትዳር የተመኛትን ከእጁ ማስገባት የፈለገ ሰው መላዎችን ያውጠነጥናል፤ ዘዴዎችን ይቀይሣል፤ በዚህም በዚያም ይጥራል፤ ከብዙ ድካምና ልፋት በኋላም የሀሣቡን ያሣካል የምኞቱን ያገኛል፡፡ የሰው ልጆች እንዲህ ለዱኒያዊ ስኬቶች እንለፋለን፡፡ ለዓለማዊ እድገቶችም በብዙ መልኩ ስንጥር እንታያለን፡፡ የጥረትን ውጤት የድካምን ፍሬ እናውቃለንና ብዙ የምንደክምላቸው ነገሮች አሉ፡፡ ለብር እንደክማለን፡፡ ለትምህርት እንደክማለን። ለእውቅና እንደክማለን፡፡ ለጥሩ ትዳር እንደክማለን፡፡ የምንደክምላቸው ነገሮች ብዙ ከመሆናቸው ጋር የዋጋውን ያህል ያልደከምንለት አገር ቢኖር ጀነት ነው፡፡ ጀነት ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች በላይ ሁሉ ውድ ሆኖ ሳለ ብዙም ግምት የሰጠነው አይመስልም፡፡ አብዛኞቻችን ተዘናግተናል፡፡ ኑሮአችንም የደመነፍስ ሆኗል.......

ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ ሣለን በዚህች ዓለም ላይ የተሠጠን እድሜ አልቆ ቆይታችንም አብቅቶ ያ ስሙ እንኳ እንዲነሳ የማንፈልገው ሞት ድንገት 'መጣሁ' ቢለን ያኔ ምን ሊውጠን መሸሻችን ወዴት ነው… መጠጊያችንስ ከየት ይሆን? ሰማይ እንደሆነ ሩቅ ነው፡፡ መሰላል ተይዞ አይወጣ፡፡ መሬት እንደሆነች ክብ ናት ብንዞርም አንለያት፡፡ ወይ ወደ እናት ማህፀን አይመለሱ ነገር። 'አፈር በሆንኩ' ም አይጠቅም፡፡

ስለሆነም አሁኑኑ በአጭሩ እንታጠቅ፡፡ ለአኼራችን በወጉ እንሰንቅ፡፡

ብንኮራ መሬት ላንሰምጥ የተራራን ያህል ላንረዝም ምነው መንጠባረር መወጠሩ… ሞት ላይቀር ነገር ምን ቢኖሩ!!
-----
'ልብ ላላሉ ልቦች' ከሚለው የMuhammad Seid Abx መፅሃፍ የተወሰደ

https://t.me/MuhammedSeidAbx

hace 4 meses, 3 semanas

የርሃብ ጥቅም

ኢማም አልገ-ዛሊ - ኢሕያእ ዑሉሚዲን በተሠኘው መጽሐፋቸው ውስጥ ስለ ርሃብ ጠቀሜታ ሐዲሦችን፣ የሶሐቦችንና የደጋግ ሰዎች አባባሎችን አስፍረዋል፡፡

መጽሐፉ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ነጃሺ መፃሕፍት መደብር ያገኙታል፡፡

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) “ከሰው ሁሉ የሚልቅ ማነው?” ተብለው ሲጠየቁ፦ “ምግቡና ሳቁ የተመጠነ፣ ኃፍረተገላውን የሚሸፍንበትን ነገር የወደደ ነው” ብለዋል።

ዓኢሻ (ረ.ዐ.)፣ “መጥገብ ብንሻ ኖሮ እንጠግብ ነበር፤ ነገር ግን ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ.) የሰውነታቸውን መራብ ይመርጡ ነበር፡፡” ብላለች።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)፣ “ምግብና መጠጥ በማብዛት ቀልቦችን አትግደሉ፤ ቀልብ ውሃ ሲበዛበት እንደሚሞት ተክል ነው::” ብለዋል።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ ብለዋል፡- “የሰውን ልጅ የሆዱን ያህል የተሸከመው ስልቻ የለም። ጀርባውን የሚያቆምበት የተወሰኑ ጉርሻዎች ይበቁታል፤ የግድ ከሆነ ደግሞ አንድ ሦስተኛውን ለምግብ፣ አንድ ሦስተኛውን ለመጠጡ፣ አንድ ሦስተኛውን ለእስትንፋሱ መተው አለበት።”

ዑመር (ረ.ዐ.) እንዲህ ብለዋል፦ “አደራችሁን ከልክ በላይ ጠግባችሁ አትመገቡ፤ ጠግቦ መብላት በምድር ላይ ለሰውነት ክብደት ያጋልጣል፤ በሞቱ ጊዜም ጥንብነት ነው።”

በሌላም መልዕክታቸው፣ “ሸይጧን፣ በሰው ልጅ ደም ውስጥ ይዘዋወራል፤ መዘዋወርያውን በርሃብ አጥቡበት::” ብለዋል። (ኢብኑ አቢ ዱንያ ዘግበዉታል፡፡)

በሌላም መልዕክታቸው፣ “ሙእሚን በአንድ ሆድ ነው የሚመገበው፤ ሙና ፊቅ ግን በሰባት አንጀቶች ነው የሚበላው” ብለዋል።
ይህም፣ ካፊር ሙእሚን ከሚመገበው ሰባት እጥፍ ይመገባል እንደ ማለት ነው። ወይም ደግሞ የመመገብ አምሮቱ ሰባት እጥፍ ነው ማለት ነው። የስሜት መነሻው ደግሞ ሆድ ነው፤ ሆድ ሲጠግብ ስሜት ይከተለዋልና። እንጂ በተጨባጭ ሰባት አንጀቶች በሆዱ ውስጥ አለ ማለት አይደለም።

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ.) እንዳስተላለፉት፣ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ለሦስት ተከታታይ ቀናት ቤተሰቦቻቸውን የስንዴ ዳቦ አጥግበው አያውቁም፤ ይህችን ዓለም እስኪለዩ ድረስ።” (ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት፡፡)

ሉቅማን ልጃቸዉን ሲመክሩ “ ልጄ ሆይ ሆድ ሲሞላ ማሰላሰል ይሞታል፣ ጥበብ ይሰናከላል፣ ሰውነት ከዒባዳ ይተሳሰራል ፡፡” ብለዉታል፡፡

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ ለራሱ እንዲህ ይል ነበር፣ “ነፍሴ ሆይ ምንድነው የምትፈሪው? እራባለሁ ብለሽ ትሰጊያለሽን?! እሱን አትፍሪ፤ አንቺ አላህ ዘንድ ከዚያ በታች ዋጋ ነው ያለሽ፤ ሙሐመድ እና ቤተሰቦቻቸው እንኳን ይራባሉ።”

ሰህል ኢብኑ ዐብዱላህ አት-ቱስቱሪ፣ “በአመጋገብ ሥርዓት የአላህ መልዕክተኛን (ሰ.ዐ.ወ.) ፈለግ በመከተል ትርፍ መመገብ መተውን የበለጠ የትንሳኤ (ቂያም) ዕለት ሚዛንን የሚሞላ መልካም ሥራ የለም፡፡” ብለዋል።

እንዲህም ብለዋል፡- “ ለዲንም ሆነ ለዱንያ ከመርራብ በላይ ጠቃሚ የሆነ ነገር የለም፡፡”
በሌላም ንግግራቸው፡- “ለአኺራ ተማሪዎች ምግብ ከማብዛት በላይ ጎጂ የለም፡፡” ብለዋል፡፡

እንዲሁም “ጥበብ በዕውቀትና በርሃብ፤ ኃጢኣት ደግሞ በመሃይምነት እና በጥጋብ ውስጥ ይገኛል፡፡” ብለዋል፡፡

“ራሱን ያስራበ ሰው የሰይጣን ጉትጎታ ከሱ ይወገዳል፡፡” ብለዋል፡፡

https://t.me/NejashiPP

hace 4 meses, 4 semanas

የደጋግ ሰዎች ንግግሮች - ስለ ዱንያ

 ዐብዱላህ ኢብኑ ሙስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ይላሉ፡-
‹ይህች ዱንያ አገር የሌለው ሰው አገር፤ ገንዘብ የሌለው ሰው ገንዘብ ናት፡፡ እሷን የሚሰበስባትም ዐቅል የሌለው ነው፡፡›

 ሱፍያን አስ-ሠውሪይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ (የቅርቢቱ ዓለም) ዱንያ የተባለችው ቅርብ ስለሆነች ነው፡፡ ማል (ገንዘብ) ማል (ዘንባይ) የተባለው ባለቤቱን ወደራሱ እንዲያዘነብል ስለሚያደርግ ነው፡፡›

 ወህብ ኢብኑ ሙነበህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ ለብልሆች መስሪያ አገር ናት፡፡ መሃይማን ደግሞ በሷ ላይ ተዘናግተዋል፡፡ ከሷ እስኪለቁ ድረስ ስለሷ ምንም አላወቁም፡፡ ወደኋላ ለመመለስ ፈልገው ቢጠይቁም መመለስ አልቻሉም፡፡›

 አል-ሐሰን አል-በስሪ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አራት ነገሮች የዕድለ ቢስነት ምልክቶች ናቸው፡፡ የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ረጅም ምኞት እና በዱንያ ላይ ለመቆየት መስገብገብ፡፡›

 ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ለዱንያ ባለህ ሀሳብና ጭንቀት ልክ ለአኺራ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡ ለአኺራ ባለህ ጭንቀት ልክ ለዱንያ ያለህ ሀሳብ ከውስጥህ ይወጣል፡፡›

 ማሊክ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህም ብለዋል፡-
‹ለዱንያ በተደሰትክ ልክ የአኺራ ጥፍጥና ከልብህ ውስጥ ይወጣል፡፡›

 አል-ፉዶይል ኢብኑ ዑያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
‹አምስት ነገሮች የዕድለቢስነት ምልክቶች ናቸው፡- የቀልብ መድረቅ፣ የዐይን እንባ ማጣት፣ ጥሩ ጓደኛን አለመምረጥ፣ ለዱንያ ማዘንበል እና ረጅም ምኞት፡፡ አምስት ነገሮች ደግሞ የደስታ ምልክቶች ናቸው፡- በቀልብ በአላህ ላይ እርግጠኛ መሆን፣ በዲን አላህን መፍራት፣ ከዱንያ መብቃቃት፣ ሐያእ እና እውቀት ናቸው፡፡”

 አል-ፉዶይል ረሒመሁላህ እንዲህም ብለዋል፡-
‹ዱንያ ከነሙሉ ግሳንግሷ በመጨረሻው ዓለም የማልመረመርባት ሐላል ሆና ብትቀርብልኝ፤ አንዳችሁ ጥንብ ባየ ጊዜ እንዳይነካው እንደሚጠየፈው ሰው ሁሉ ተጠይፌያት በራቅኩ ነበር፡፡›

 ሰለመህ ኢብኑ ዲናር ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹በዱንያ አንድም የሚያስደስትህ ነገር አይኖርም በሌላ በኩል የሚያስከፋህ ነገር የተጣበቀበት ቢሆን እንጂ፡፡›

 ዐብዱላህ አርራዚ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የዒባዳን ጥፍጥና ማግኘትና የጥፍጥናው ጣሪያ መድረስ ከፈለግክ ባንተና በዱንያ ስሜቶች መካከል ከብረት የሆነ ግድግዳ አብጅ፡፡›

 ሰዕድ ኢብኑ መስዑድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹አንድ ሰው ዱንያው ስትጨምርና አኺራው ስትቀንስ እሱም ይህን ሁኔታውን ወዶ የሚኖር መሆኑን ካየህ የዚህ ዓይነቱ ሰው የተታለለና ሳያውቅም በራሱ የሚጫወት መሆኑን እወቅ፡፡›

 ከሢር ኢብኑ ዚያድ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያችሁን በአኺራችሁ ሽጡ፡፡ ወላሂ ሁለቱንም ታተርፋላችሁ፡፡ አኺራችሁን በዱንያ አትሽጡ ወላሂ ሁለቱንም ትከስራላችሁ፡፡›

 ዑበይድ ኢብኑ ዑመይር አልለይሢይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ዱንያ የተወሰነ ዕድሜ አላት፡፡ አኺራ ደግሞ ዘላለማዊ ናት፡፡›

 ዐውን ኢብኑ ዐብደላህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡-
‹የዱንያን ማማር አትመልከቱ፡፡ እሷ በየትኛውም ጌጥ ብትዋብና ብታሸበርቅ ውሸት ናት፡፡ ትልቅ ትርፍና ሀብት የሚገኘው ነገ በአኺራ ነው፡፡ እኛ ደግሞ በቀደሙትና ወደ ኋላ በቀሩት ሰዎች መካከል ነን፡፡›

 ጥበበኛው ሉቅማን ልጃቸውን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፡-
‹ልጄ ሆይ! ወደዚህች ምድር ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ ለዱንያ ጀርባህን እየሰጠህ ነው፡፡ አኺራ ደግሞ እየመጣች ነው፡፡ አንተም ርቆ ከሄደው ይልቅ እየቀረበ ላለው ቅርብ መሆንህን አስተውል፡፡›

https://t.me/NejashiPP

hace 8 meses

የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ እንዲህ ይላሉ፡-

“ከታላላቅ ከንቱ ተስፋዎች መካከል፣ ሳይፀፀቱ በወንጀሎች ውስጥ በመቆየት የአላህን ይቅርታ መጠበቅ ነው። ያለ አንዳች መታዘዝ ተግባራትን ሳይፈጽሙ ወደሱ መቅረብን መመኘት፣ የእሳት ዘር እየዘሩ የጀነትን ፍሬ መጠበቅ፣ በኃጢአት ዉስጥ ተዘፍቀው የታዛዦችን አገር መመኘት፣ ሳይሠሩ ምንዳን ማሰብ፣ በእጅጉ ተዘናግተው እያሉ አላህ ላይ አጓጉል ምኞት ማሳደር ነው።”

https://t.me/NejashiPP

hace 8 meses, 3 semanas

ለወላጅ ቅን መሆን

ምንጭ - የወላጆች ሐቅ መጽሐፍ
አዘጋጅ ፥ ዐብዱልመሊክ ቃሲም
ትርጉም ፥ ሑሴን ኸድር

ለቤተሰበም ሆነ ለዘመድ ተገቢውን ክብር መስጠት፣ በሠናይ ሥነ-ምግባር አጋርነትን ማሳየት፣ በፍቅርና በእዝነት መቅረብ ተገቢ ነው፡፡

አል-ሐሰን አል-በስሪይ እንደሚሉት፡-
“ቢርር” ወላጆች በአላህ አለመገዛት እስካላዘዙ ድረስ እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትን ነገር በሙሉ ያለማመንታት መታዘዝ ሲሆን በአንጻሩ “ዑቁቅ” ወላጆች ክብርና እንክብካቤ ‘በሚፈልጉበት ወቅት ከነሱ በመራቅ ቸል ማለት ነው ’”

አል-ቁርጡቢ በበኩላቸው፡-
“ዑቁቅ" ወላጆችን በመቃረን ከመብትና ፍላጐታቸው ውጭ መፈጸም ሲሆን
“ቢርር” ደግሞ ይህንኑ ፍላጐታቸውን እንደፈለጉት መፈጸም ነው፡፡ ስለዚህ ወላጆች ወይም ከሁለት አንዳቸው ትዕዛዛቸው በአላህ ማጋራት እስካልሆነ ድረስ” ልጆቻቸው እንዲያደርጉላቸው የሚፈልጉትን አንዳች ነገር እንደሚፈልጉት መታዘዝ ግድ ነው፡፡

“አቡበክር የተባሉት ታላቅ ዓሊም ‘ዛዱል ሙሳፊር’ በተሰኘው መጽሐፋቸው ‘አንዳች ነገር በመሥራቱ ወላጆቹ የተቆጡት ወይም ያለቀሱበት (ሰው) በፍጥነት አንዳች የሚያስደስታቸውን ወይም የሚያስቃቸውን ነገር ማድርግ አለበት፡፡’ ይህ ማለት ወላጆች አንዳች የሚያስፈልጋቸው ነገር ሲያዙ ፈጥኖ በመታዘዝ አክብሮትን ማሳየት ነው፡፡ ማንኛዉንም ትዕዛዛቸውን በፍጥነት መፈጸም ማንኛውንም የማይፈልጉትን ነገር መተው ተገቢ ነው፡፡

በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲስ እንደተዘገው ደግሞ፤
ሰውየው ወደነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣና ለጂሃድ ፍቃድ ጠየቃቸው ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) “ወላጆችህ በሕይወት አሉ?” አሉት “አዎን!” አለ “ተመለስና እነሱን አገልግል” አሉት፡፡ (ቡኻሪ ዘግበውታል።)

ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)” እንዲህ ብለዋል፡-
‘አላህ የተደሰተበት ወላጆቹ የተደሰቱበት ነው፡፡ አላህ የተቆጣበት ደግሞ ወላጆቹ የተቆጡበት ነው።’

አቡ ደርዳእ “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዘጠኝ ነገሮችን እንዳደርግ አዘውኛል (እነርሱም)፡-
“አላህን ያለ አንዳች ማጋራት ተገዛው፡፡ ብትማረክም ሆነ በምርኮ ወቅት ብትሰቃይ ከአላህ ውጭ ምንንም አትገዛ፡፡ ግዴታ የሆኑትን ሶላቶችን እያወቅክ በጭራሽ አትተው፡፡ ሶላት የተወ ሰው በኢስላም የሚደረግለት ጥበቃ ይነሳበታል፡፡ በጭራሽ አስካሪ መጠጥ መጠጣት የለብህም፡፡ መጠጥ የወንጀሎች ሁሉ ቁልፍ ነው፡፡ ለወላጆች ታዛዥ ሁን የውርስ ድርሻህን ቢከለክሉህም እንኳን….” ብለዋል። (ቡኻሪ ዘግበውታል።)

ሙሐመድ ኢብኑ ዐሊ አክለው እንደሚገልጹት “መጥፎ የሆኑ ልጆች ወላጆቻቸውን በዳይ ይሆናሉ፡፡ መልካም ያልሆኑ ወላጆች ደግሞ ክብራቸውን ያጋንናሉ፡፡ አላህ ወላጆችን ለልጆቻቸው መልካም አርአያ ሆነው እንዲታዩ አስጠነቅቋቸዋል፡፡

በመሆኑም ወላጆች በልጆቻቸው መጠቃቀምን እንዳይከጅሉ ያሳስባል፡፡ ሆኖም አላህ ልጆችን ለወላጆቻቸው በጐ እንዲውሉ ያዛል፡፡
ወላጆች ለልጆቻቸው ታዛዥ እንዲሆኑ በማያሻማ ሁኔታ ያላዘዘበት ሁለት ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛው አላህ በወላጆች ልብ ውስጥ እዝነትን በማድረጉ ሲሆን ሁለተኛው ልጆችም በተወሰነ መጠን የወላጆቻቸውን የተወሰነ ነገር ስለሚወርሱ ለወላጆቻቸው ፍቅርና እዝነት ስለሚያሳድሩ ነው፡፡ ይህ እውነታ በሁሉም ፍጡራን የሚከሰት ነው፡፡ በአውሬ እንኳ ሳይቀር፡፡ ጥቂት መልካምነት ያለው ለዘርማንዘሮቹ ይተርፋል፡፡
ኢስላም ወላጆች የልፋታቸውን ውጤት በልጆቻቸው እንዲካሱ ያዛል፡፡ ብልህ ልጆች የወላጆቻቸውን ውለታ በድጋፍና እንክብካቤ እንደሚፈልጉት በመታዘዝ ይወጣሉ፡፡ ከዕብ ኢብኑ ኡጅራህ እንደተረኩት፡፡
“ሰውየው በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) በኩል ተፍ ተፍ እያለ አለፈ፡፡ ሶሐቦች በትጋቱና በጥንካሬው በጣም ተገረሙ፡፡ እንዲህም አሉ፡፡ ‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይህ ጉልበቱንና ኃይሉን በአላህ መንገድ ቢያደርገው ኖሮ› የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሲመልሱ ‘ትናንሽ ልጆቹን ለመርዳት ብሎ የተጓዘ እሱ በአላህ መንገድ ላይ ነው፡፡ አዛውንት ወላጆቹን ለመረዳት ብሎ የተጓዘ እሱ በአላህ መንገድ ላይ ነው፡፡ (ልመናን በመጥላት ክብሩን ጠብቆ) ራሱን ለመርዳት የተጓዘ እሱ በአላህ መንገድ ላይ ነው፡፡ ለታይታና ለኩራት የሚጓዝ እሱ በሰይጣን መንገድ ላይ ነው”
(አጥ- ጠበራኒ ዘግበውታል)
ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዳወሩት፣
“አንዲት ሴት ወደኔ መጣች፡፡ ሁለት ሴት ልጆች አብረዋት አሉ፡፡ እንድረዳት ጠየቀችኝ፡፡ አንዲት ተምር ብቻ ነበረችኝና እሷን ሰጠኋት፡፡ ተምሯን ለሁለት ከፍላ ለልጆቿ ሰጠቻቸው፡፡ እሷ ቅንጣት እንኳ አልቀመሰችም፡፡ ከዚያም ሄደች፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሲመጡ ሁኔታውን ነገርኳቸው፡፡ እሳቸው እንዲህ አሉ፣
“በነዚህ ሴቶች ልጆች ባንዳች ነገር የተፈተነ፣ ለነሱም በጐ የዋለ፣ ለእሳት ግርዶሽ ይሆኑለታል፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐውፍ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፡-
“አንድ ሰው መጣና የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! አንድ ወጣት እያሟሟትነው ሳለ <ላ ኢላሀ ኢልለላህ (ከአላህ በቀር አምልኮ የሚገባው ሌላ አምላክ የለም) ማለት አቅቶት ተቸግረናል አላቸው፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ወጣቱ በመሄድ ‘ላ ኢላሀ ኢልለላህ’ አሉ፡፡ ወጣቱ ‘አልቻልኩም’ አላቸው፡፡ መልዕክተኛውም (ሰ.ዐ.ወ) ‘ለምንድነው ያልቻልከው’ ቢሉት ‘ልቤ ተደፍኗል፤ ለወትሮ ደጋግሜ እለው የነበረ በልቤም እመላልሰው የነበረ ቃል ነው፤ አሁን ግን አቃተኝ!> ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‹ለምን› ሲሉ በድጋሚ ጠየቁት፡፡ ወጣቱም ‹ለናቴ አሳያት በነበረ ያልተገባ ባህሪ ምክንያት› አለ፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደናትየው ላኩባት፡፡ እንደመጣችም ‹ልጅሽን ለአላህ ስትይ ይቅር በይው አለበለዚያ እንጨት አስመጥቼ ላቃጥለው ነው› አሏት፡፡ ‹አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! እኔ ለአላህ ብዬ ይቅር ብዬዋለሁ› አለች፡፡ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹አላህና መልዕክተኛው ምስክሮቼ ናቸው ይቅርታ አድርጌልሃለሁ በይው› አሏት ‹አላህና መልዕክተኛው ምስክሮቼ ናቸው ልጄን ይቅር ብዬዋለሁ› አለች፡፡”
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ ልጁ ዞረው ‹ላ ኢላሃ ኢልለላህ በል› አሉት፡፡ ልጁም ‹ላ ኢላሃ ኢልለላህ ዋሕደሁ ላሸሪክለሁ (ከአላህ በቀር አምልኮ የሚገባው ፈጣሪ የለም አንድ ነው ብጤ (አጋር) የለው) አለ፡፡ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹ጌታዬ ጥራት ይገባው ከእሳት አዳነህ› አሉት (አጥ-ጠበራኒይ ዘግበውታል)
ኢብኑ ዐባስ (ረ.ዐ) እንደዘገቡት፡-
“አላህ ሁለት የጀነት በሮችን ለሁሉም ሙስሊም ክፍት አድርጐ ይተዋቸዋል፡፡ በሮቹ ለእናት ወይም ለአባት በሽልማት የተሰጡ ናቸው፡፡ በአንደኛው በር ቤተሰቡን በቅንነት ያገለገለ ወይም ያገለገለች ይገቡበታል፡፡ ከወላጆቹ አንዳቸው ያዘኑበት ወላጆቹ ይቅር እስኪሉት አላህም ያዝንበታል” ሰውየው ጠየቀ ‹ልጁ ሳያስበው ባጠፋው ጥፋትም ቢሆን?› ‹ሳያስበው ጠፋውም ቢሆን› (አል-በይሀቂ)

ልጆቻቸው በመልካምና በጐ ለዋሉላቸው ወላጆች እንዲሸከሙ አላህ የጀነትን በሮች ክፍት አድርጐላቸዋል፡፡ ለአቅመ-አዳም የደረሱ ልጆች ከቤቶቻቸው በመውጣት የራሳቸውን ኑሮ ይመሠርታሉ፡፡ ታዲያ አላህ (ሱ.ወ) እነዚህን የጀነት በሮች በመክፈት ለወላጆቻቸው ያሳዩ በነበሩት መልካም ባህሪና ታዛዥነት ምንዳቸውን እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል፡፡ ከሁለት አንዳቸው በልጃቸው ያዝኑ ከነበረ ግን አላህም በድርጊታቸው በመቆጣት የጀነቱ በር እንዲዘጋባቸው ያደርጋል፡፡ ከቶም በሥርዓቱ ወላጆቻቸውን ያናግሩ ያልነበሩ ያመናጭቁ ያጉላሉ የነበሩ የዚህ አደጋ ተቋዳሾች ናቸው፡፡ ከዚህ

hace 9 meses, 3 semanas

ዐሽረል አዋኺር (አሥርቱ ቀናት)

ትርጉም -
በተባረከው የረመዷን ወር ዉስጥ የሚገኙ አሥሩ የመጨረሻ ቀናት ናቸው፡፡ በነኚህ ቀናት ዉስጥ አምልኮም ሆነ ማንኛዉም መልካም ሥራ የተወደደና ከፍ ያለ ደረጃ ያለው ነው፡፡

ጅማሮ -
አሥርቱ ቀናት የሚጀምሩት በረመዷን 21ኛው ምሽት ላይ ነው፡፡ ወሩ ሙሉ ከሆነ እስከ ረመዷን 30ኛው ቀን ምሽት ይቆያሉ፡፡

ምሽቶቹን ምን ልዩ ያረጋቸዋል?

ለይለቱ ቀድር የምትባል ምሽት ከአሥርቱ ቀናት በአንዱ ዉስጥ አለች፡፡ ይህችን ቀን በነኚህ ቀናቶች ዉስጥ በርትተን እንድንፈልግ ነቢዩ ሶ.ዐ.ወ. መክረዉናል፡፡

ለይለቱል ቀድር ምንድናት?

ከሺህ ሌሊቶች የምትበልጥ ትልቅ ደረጃ ያላት ምሽት ናት፡፡

ቀኗ በትክክል ይታወቃል?

በትክክል አይታወቅም፤ ነገርግን በተለይም ዋናነት በምሽቶቹ ነጠላ ቀናት ዉስጥ ማለትም በ21፣ በ23፣ በ27፣ በ29 ዉስጥ ፈልጉ ተብሏል፡፡
ለይለቱል ቀድር የሚባል ዱዓ ይኖራል? - እናታችን አላህ ለይለተል ቀድርን ከወፈቀኝ ምን ልበል? በማለት የአላህን መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ ጠይቃቸው “ አልሏሁም ኢንነከ ዐፉዉን ቱሒቡል ዐፍው ፈዕፉ ዐንኒ” በይ ብለዋታል፡፡ “አላህ ሆይ አንተ ይቅር ባይ ነህ፤ ይቅር ማለትን ትወዳለህ፤ ይቅር በለኝ፡፡” ማለት ነው ትርጉሙ፡፡

ነቢዩ ምን በነኚህ ቀናት ዉስጥ ምን ያደርጉ ነበር?

በነኚህ ቀናት ዉስጥ ነቢዩ ሶ.ዐ.ወ. በአምልኮ ከሌላው ጊዜ በበለጠ በእጅጉ ይበረቱ ነበር፡፡ ቤተሰቦቻቸዉንም ያነቁ ነበር፡፡ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ይለግሳሉ፡፡ ሌሊቱን በዚክር እና በዒባዳ ያሳልፋሉ፡፡ ኢዕቲካፍም ይገባሉ፡፡

ኢዕቲካፍ ምንድነው?

ኢዕቲካፍ ማለት አምልኮና ወደ አላህ መቃረብን በማሰብ ራስን ከዓለማዊ ጉዳዮች አርቆ ለተወሰነ ጊዜ፣ ሰዓታት፣ ቀን ወይም ሌሊት መስጂድ ዉስጥ መቆየት ነው፡፡ ኢዕቲካፍ ነቢያዊ መንገድ ነው፡፡ በአሥርቱ ቀናት ዉስጥ እስከሚሞቱ ድረስ ኢዕቲካፍን አልተዉም ነበር ብላለች እናታችን ዓኢሻ፡፡

የኢዕቲካፍ ጥቅሙ ምንድነው?

ኢዕቲካፍ ከዓለማዊ ጉዳዮች ያርቃል፣ ሙሉ በሙሉ ቀልብን ወደ አላህ በመመለስ ከአላህ ጋር መገለልን ያስገኛል፡፡ ነፍስን ያጠራል፣ መንፈስን ያድሳል፣ ቀልብን ያንፃል፡፡ ራሣችን እንድንፈትሽና እንድንገመግም ዕድል ይሠጠናል፡፡

በኢዕቲካፍ ጊዜ ምን ይወደዳል?

በኢዕቲካፍም ሆነ በአሥርቱ ቀናት ዉስጥ ሶላት ማብዛት፣ ኢስቲግፋር (አላህን ምህረትን መለመን) ማብዛት፣ ቁርኣን መቅራት፣ ዚክር ማድረግ፣ ሶደቃ መስጠት፣ ዱዓ ማድረግ፣ መልካም ሥራዎችን ማብዛት ይወደዳል፡፡ በአጠቃላይ ማንኛዉንም መልካም ነገር ሁሉ ሳይሠለቹ አብዝቶ መሥራት ይወደዳል፡፡

https://t.me/NejashiPP

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 3 semanas, 5 días

Last updated hace 3 semanas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 1 mes, 1 semana