ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 2 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago
[ኢብኑ_ሰማክ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ዱንያ ሁለ ነገሯ ጥቂት ናት፣ ከሷም ውስጥ አሁን የቀረው ጥቂቷ ነው፣ ከቀረው ጥቂት ውስጥ ላንተ የሚደርስህም ጥቂት ነው፣ ከደረሰህ ጥቂት ውስጥ አሁን የቀረህ ጥቂቷ ናት።»
? ۞ سير أعلام النبلاء【8/330】۞
───────────
https://t.me/Tewhid_and_Sunahhttps://t.me/Tewhid_and_Sunah](https://t.me/Tewhid_and_Sunahhttps://t.me/Tewhid_and_Sunah)
ክፋት ለማንም አይጠቅምም አትክፉ‼️
«አንዳንድ ሰው‼️»
?በኑረዲን አል-አረብ
*ኢብኑ_ዑሰይሚን ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -
«ማንም ቢሆን የሰዎችን ልቦና ሊጠብቅ ይገባል። የአንድ ሰው ልብ ከተሰበረ በሚችለው ለመጠገን ይጣር። ምክንያቱም በዚህ ውስጥ ትልቅ ትሩፋት አለና።»
? ۞ شـرح بلـوغ المـرام【11/333】۞
───────────*https://t.me/Tewhid_and_Sunahhttps://t.me/Tewhid_and_Sunah
?አዝካሩ ሰባህ (የጠዋት ዚክር)? "አልሀምዱሊላህ"
ነግቶ ከተነሳሁ ከትንሿ ሞት
እድልን ካገኘሁ ዛሬም ለተውበት ምስጋና ይገባው ለአርሹ ባለቤት
ሚስኪኒቷን ነፍሴን ህያው ላደረጋት‼️**
ክፍል ___ 1
***➲ ˝ተውሂድ እና ሽርክ˝
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬
✅ተከታታይ አድሰ ፅሁፍ
➨ ክፍል-አንድ˝⓵
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
መግቢያ:-
➧በአላህ ስም እጅግ በጣም ርሕሩሕ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። ምስጋና ሁሉ
ለአላህ ነው። እናመሰግነዋለን እገዛን እንጠይቀዋለን፣ ምህረትንም እንጠይቀዋለን። ከነፍሳችን ተንኮል፣ ከመጥፎ ስራዎቻችንም በአላህ እንጠበቃለን። አላህ የመራውን ሰው የሚያጠመው የለም ያጠመመውን የሚመራው የለም።
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ حَقَّ تُقَاتِهِ وَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُونَ
(ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 102)
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገቢውን መጠንቀቅ ተጠንቀቁት። እናንተም ሙስሊሞች ኾናችሁ እንጅ አትሙቱ።”
[አሊ ዒምራን፡ 102]
يَا أَيُّهَا النَّاسُ اتَّقُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُم مِّن نَّفْسٍ وَاحِدَةٍ وَخَلَقَ مِنْهَا زَوْجَهَا وَبَثَّ مِنْهُمَا رِجَالًا كَثِيرًا وَنِسَاءً ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ الَّذِي تَسَاءَلُونَ بِهِ وَالْأَرْحَامَ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلَيْكُمْ رَقِيبًا
(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 1)
“እናንተ ሰዎች ሆይ! ያንን ከአንዲት ነፍስ (ከአደም) የፈጠራችሁን ከእርስዋም መቀናጆዋን
(ሀዋን) የፈጠረውን ከእነርሱም ብዙ ወንዶችንና ሴቶች የበተነውን ጌታችሁን ፍሩ። ያንንም
በርሱ የምትጠያየቁበትን አላህንና ዝምድናዎችንም (ከመቁረጥ) ተጠንቀቁ። አላህ በእናንተ
ላይ ተጠባባቂ ነውና።”
(አን-ኒሳእ ፡ 1)
يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَقُولُوا قَوْلًا سَدِيدًا
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 70)
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ፍሩ፡፡ ትክክለኛንም ንግግር ተናገሩ፡፡
يُصْلِحْ لَكُمْ أَعْمَالَكُمْ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ ۗ وَمَن يُطِعِ اللَّهَ وَرَسُولَهُ فَقَدْ فَازَ فَوْزًا عَظِيمًا
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 71)
ሥራዎቻችሁን ለእናንተ ያበጅላችኋልና፡፡ ኀጢአቶቻችሁንም ለእናንተ ይምርላችኋል፡፡ አላህንና መልክተኛውን የሚታዘዝም ሰው በእርግጥ ታላቅን እድል አገኘ፡፡
(አል አሕዛብ፡ -71)
➧በመቀጠልም ከንግግር ሁሉ በላጭ የአላህ ንግግር ነው ምርጥ የሚባለው መመሪያ የሙሐመድ صلى الله عليه وسلم መመርያ ነው፤ ከነገሮች ሁሉ የከፋው (በዲን ላይ) ፈጠራ ነው፤ ፈጠራ የተባለ ሁሉ ቢድዐ ነው፤ ቢድዐ ሁሉ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።
✅ይህች አጠር ያለች መፅሐፍ በአላህ ፍቃድ ስለ ተውሒድ ምንነት፣ ወሳኝነት ለተውሒድ ባለቤቶች አላህ ያስቀመጠውን ሽልማት በአጭሩ የዘረዘርኩባት በተቃራኒው የሽርክን ምንነት አደጋውን፣ የሽርክ ባለቤቶች ላይ የተዛተውን ዛቻም አጠር ባለ መልኩ ያስቀመጥኩባት ናት። ማስረጃዎቼን ከስህተት ከፀዳው የአላህ ቃል ቁርኣን፣ የአላህ ጥበቃ
ከማይለያቸው መልክተኛው صلى الله عليه وسلمሱና፣ ከመልካም ቀደምቶች እና የነሱን መልካም አርዓያ የተከተሉትን አስተምህሮት ለማድረግ መርጫለሁ። ምክንያቱም ከጥመት የመዳኛው
ብቸኛው መንገድ ይህ ስለሆነ። የአላህ ባርያዎች ሆይ! አላህ ዲንን እንዲያስገነዝበን እየለመንኩ የሰው ስራ ከስህተት አይጠራምና መፀሐፉን አስመልክቶ ስህተት ካገኛችሁ በሚከተለው የኢሜል አድራሻዬ ብትጠቁሙኝ ደስተኛ ነኝ።[email protected] ✅˝ተውሒድ እና ሺርክ˝
⓵,. የተውሒድ እውቀት ከየትኛውም እውቀት በፊት ይቀደማል!!
አላህ ለነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ይላቸዋል፡-
فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مُتَقَلَّبَكُمْ وَمَثْوَاكُمْ
(ሱረቱ ሙሐመድ - 19)
“እነሆ ከአላህ ሌላ በሃቅ የሚመለክ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ። ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን። አላህም መዘዋወሪያችሁን መርጊያችሁንም ያውቃል።” [ሙሐመድ፡ 19]
➨ ከታላላቅ የኢስላም ሊቃውምት ውስጥ ተውሒድን “ታላቁ እውቀት” /ፊቅሁል አክበር/
ብለው የጠሩት አሉ።
ይህም ይህ የእውቀት ዘርፍ ያለውን የላቀ ደረጃ አመላካች ነው።
ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንዳሉት “አላህ መልካም የሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል።
?[ቡኻሪና ሙስሊም]
?የአምልኮ ሁሉ ቁንጮ ተውሒድ ከሆነ ከእውቀት ሁሉ ቁንጮው ደግሞ የተውሒድ እውቀት ነው።
⓶. ተውሒድ ምንድን ነው?
በቋንቋ ደረጃ ተውሒድ ማለት ፡- የሆነን ነገር አንድ ማድረግ ማለት ነው። በሸሪዓዊ ትርጉሙ ደግሞ፡- ተውሒድ ማለት አላህን ብቸኛ በሆነባቸው ሐቆቹ በብቸኝነት መነጠል ነው። ለምሳሌ አላህ በጌትነቱ፣ በፈጣሪነቱ
በአስተናባሪነቱ ህያው በማድረጉ በመግደሉ በተመላኪነቱ፣ ለእርሱ ምሉዕ የሆኑ ስምና መገለጫዎች
በመኖራቸው ላይ ያለ አጋር ብቸኛ ነው።
✅ተውሒድ አልኡሉሂያ ማለት
ደግሞ አላህን በእርሱ ላይ ማንንም ምንንም ሳያጋሩ አምልኮን ለርሱ ብቻ መፈፀም ነው። እስቲ የሚከተለውን የተውሒድ ቃላት ውስጡ በዝርዝር ምን እንደያዘ እንይ፦
“ላኢላሃ ኢልለ-ሏህ ወህደሁ
ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል-ሙልኩ ወለሁል-ሐምዱ ዩሕይ ወዩሚቱ
ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር።”
ትርጉም:-
“ከአላህ በስተቀር በሃቅ የሚመለክ አምላክ የለም። ብቸኛ ነው። አጋር የለውም። ንግስና (ባለቤትነት) ለእርሱ ናት። ምስጋናም ለእርሱ ነው።
ህያው ያደርጋል።ይገድላልም። ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ ነው።”
ይህቺ ቃል የያዘችው መልእክት፡-
ጌትነቱ (ተውሒድ አርሩቡቢያህ) ፡- ብቸኛ ፈጣሪና ሁሉን አድራጊ አስተናባሪ ንግስና
በጠቅላላ የእርሱ ነች፣ ህያው ያደርጋል፣ ይገድላል፣ ሁሉን በማድረግ ላይ ቻይ መሆኑን
ማረጋገጥ ነው። ይህ የተውሒድ ክፍል ተውሒድ አርሩቡቢያህ ይባላል። ከሶስቱ የተውሒድ ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው።
✅አምላክነቱ (ተውሒድ አልኡሉሂያ)
➧ከአላህ በስተቀር በሃቅ የሚመለክ አምላክ የለም
አላህ ብቸኛ ተመላኪ መሆኑን ማረጋገጥ። ይህ የተውሒድ ክፍል ተውሒድ አልኡሉሂያ ይባላል። ከሶስቱ የተውሒድ ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው።
➨ ስምና መገለጫዎቹ (ተውሒድ አልአስማእ ወስሲፋት) ፡-
“ቻይ” ገዳይ” ህያው አድራጊ” የሚሉት ምርጥ ምርጥ የአላህ ስሞችና መገለጫዎቹ ሲሆኑ ሌሎችም አላህ ለራሱ
ወይንም መልክተኛው صلى الله عليه وسلم ለርሱ ያረጋገጧቸውን መልካም ስሞችና መገለጫዎች
ትርጉሙን ሳንቀይር፣ ሳናራቁት፣ ሁኔታው እንዲህ ነው ሳንል (ከይፍያ ሳንሰጥ) ሳናመሳስል፣ ትርጉሙ አይታወቅም ሳንል (ተፍዊድ ሳናደርግ) በመጣበት እውነታ ማፅደቅ ይገባል።
?ይህ የተውሒድ ክፍል ተውሒድ አልአስማእ ወሰስሲፋት ይባላል። ከሶስቱ የተውሒድ ክፍሎች ውስጥ አንዱ ነው።
➳ኢንሻአሏህ
ይቀጥላል.....
ዝግጅት:-ሳዳት ከማል አቡ መሪየም
? አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰዉ ያደርጋል!!
ወ ዴ ቻ ና ላ ች ን ይ?️ላ?️ ሉ*
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/Tewhid_and_Sunah
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
አድሚናች ልንሰራቸው የሚገቡ ስራዎች እንደ ሃሳብ
☪☪☪የግሩፕ እንቅስቃሴን በተመለከተ
1⃣✅ በመጀመሪያ ሰወችን አድ የማድረግ ዘመቻ መክፈትና አሁን ካለንበት ቢያንስ በእጥፍ ማሳደግ በተላይ የሱና ቻናሎች ላይ በምታውቋቸው በኹረልአይን ቻናሎቻችሁ ላይ ማስተዋወቅ
2⃣✅ የግቱርፑን ጥንካሬ ለወደፊት ሊጠቁም የሚች በኡስታዞች ዳእዋ ማስደረግና ዳእዋውን በተለያዩ ቻናሎች በዘመቻ መልክ ሸር ማድረግ ወይንም ማስደረግ
3⃣✅ መፃፍ የምትችሉ ወንድም እና እህቶች ከእንቶ ፎንቶ ፖለቲካ የፀዱ ተውሂድን እና ሱና የሚያስተምሩ በተለይ መንሃጅ ነክ የሆኑ ምንጫቸው የሚታወቁ የሆኑ ኡለማዎችን በማጣቀስ ፅሁፎችን በንባብ መልክ ማስቀመጥ ወንዶች ደግሞ በድምፅም ቢሆን ችግር የለውም
4⃣✅ በየቀኑ የማያቋርጥ ተከታታይ የሆኑ ደርሶችን በተለይ አቂዳ ነክ የሆኑ ደርሶችን እንዲሁም መንሃጅን በግልፅ የሚያስተምሩ ደርሶችን በተከታታይ ለአድማጭ መልቀቅ
5⃣✅ አሪፍ አሪፍ የሆኑ የቆዩም ሆኑ አድስ የሱና ኡስታዝ ሙሃደራዎችን በሊንክ ሸር እንዲደረግ በማድርግ በማዘጋጀት ለአድማጭ ማብቃት
☪☪☪ፋይናንስን በተመለከተ
1⃣❎ ወደፊት በጣም ብዙ በፋይናንስ ጉዳይ ላይ የሚጠበቁብን ወጭ ነክ የሆኑ ነገሮች ስለሚጠብቁን ፋይናንስን ማጠንከር ቢያንስ በቀን ከሶስት አኽለል ኸይር በላይ እንድቀላቀለን ማድረግና ማስነየትና የነየቱትን ገቢ እንዳደርጉ ሳይሰላቹ ማስታወስ
2⃣❎ በፋይናንስ የስራ ዘርፍ ላይ የተመደባችሁ እህቶች የራሳችሁን አካሄድ በመጠቀም ስራችሁን በደንብ መወጣት
3⃣❎ ፋይናንሳችን እንያድግልን ፕሮግራም ይዞ የገቢ ማሰባሰቢያ ቀን በማመቻቸት ኡስታዞች እንዲመሩት ሃላፊነቱን ለእነሱ ሰቶ ፕሮግርም ማዘጋጀት
4⃣❎ የጨረታ ፕሮግራም ልምድ ባላቸው ወንድምና እህቶች እንዲመራ ፕሮግራም ይዞ ማካናወን
5⃣❎ ከተራቁጥር 1⃣ ጋር ተመሳፋይ ሃሳብ ቢሆንም የድጋፍ ቦታችንን ሸር በማድረግ ማጠናከር
☪☪☪ መሬት ላይ የሚሰሩ ስራዎችን በተመለከተ
1⃣? ሰወችን ተውሂድን በማስተማር አላህንና መልእክተኛውን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰላምን እንዲያውቁና የወደፊት ሃገራቸው እንዲያምርላቸው ሃቁን በማሳወቅ መገንባት
2⃣? በጭረቻ ዙሪያዎች ባሉ ቦታወች መድረሳወችን በመክፈትና ቂርአት እንዲስፋፋ ልፋት ማድረግ
3⃣? ለመድረሳዎች የሚሆኑ ግብአቶችን ማሟላት
4⃣? ሌላ ተጨማሪ መስጅድ መጨመር አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አቅምን አጣናክሮ መስጅድን መገንባት
5⃣? ዳእዳዋዎችን በሱና ኡስታዞች ቢያንስ ከሁለት ወር ባልበለጠ ርቀት ዳእዋ ማስደረግ
ከእነዚህ ከተዘረዘሩት ውስጥ በተለይ በኦላይን እንቅስቃሴ እኔ ይህንን እወጣለሁ የሚል ቁጥሩን በመምረጥ በሃላፊነት መስራት እና ማጣናከር
ሌሎች ደግሞ ስራ ያልተሰጣችሁ አባል የሆናችሁ ሰወችን አድ በማድረግና የፋይናንስ ተጠሪዎችን በማገዝና ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥም በመምረጥ እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅብናል
አላህ የበለጠውን ያውቃል ለስራችንም መልካም የሆነችዋን መንገድ ይምራን ሃቅን በሃቅነቱ ያሳውቀን የምንቀበለው ያድርገን ባጢልን ባጢልነቱን ያሳውቀን የምንርቀውም ያድርገን
የቀረ ካለ እናንተ ጨምሩበት
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
ሱረቱል አህዛብ (33: 56)
اَللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيْمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيْمَ إِنَّكَ حَمِيْدُ مَجِيْدٌ، اَللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيْمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيْمَ إِنَّكَ حَمِيْدُ مَجِيْدٌ.
‘አልሏሁምመ ሶልሊ-ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ አሊ ሙሐመድ፣ ከማ ሶልለይተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ አሊ ኢብራሂም ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡ አልሏሁምመ ባሪክ ዐላ ሙሐመዲን ወዐላ አሊ ሙሐመድ ከማ ባረክተ ዐላ ኢብራሂመ ወዐላ አሊ ኢብራሂመ ኢንነከ ሐሚዱን መጂድ፡፡አላህ ሆይ! በሙሐመድ ላይና በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይ እዝነትህን አውርድ በኢብራሂምና በኢብራሂም ቤተሰቦች ላይ እዝነት እንዳሰፈንከው፡፡ አንተ ምስጉን የላቅክ ነህና፡፡ አላህ ሆይ! በሙሐመድ ና በሙሐመድ ቤተሰቦች ላይ ረዴዔትህን አውርድ በኢብራሂምና በኢብራሂም ቤተሰቦች ረዴዔትህን እንዳወረድክ ሁሉ፡፡ አንተ ምስጉንና የላቅክ ነህና፡፡
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated 2 months, 2 weeks ago
Last updated 2 months, 2 weeks ago
ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች
📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu
Last updated 1 month, 1 week ago