የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU

Description
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

4 weeks ago
4 weeks, 1 day ago
"እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ …

"እርሱም በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደ ሆነ እናውቃለን።" ዮሐ 4፡42

እንኳን ለመድኃኔዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ሰናይ ሌሊት! መልካም በዓል!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

4 weeks, 1 day ago
1 month ago
1 month, 1 week ago
"ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ …

"ማርያም ሆይ ነበልባል ከሐመልማል ተዋሕዶ ሙሴ በደብረ ኮሬብ ባየ ጊዜ ተአምርሽ በኦሪት ተሰበከ ተነገረ፡ ፡ ምሳሌሽ በሐመልማልና በእሳት አምሳል የታየ ማርያም ሆይ ጽጌ ልጅሽ ኃጢአቴን ያጠፋልኝ ዘንድ በጥላሽ ሥር አስጠጊኝ፡፡” ማኅሌተ ጽጌ

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

1 month, 1 week ago
"የኢየሩሳሌም ቆነጃጂት ሆይ ማርያምን በቁስቋም ተራራ …

"የኢየሩሳሌም ቆነጃጂት ሆይ ማርያምን በቁስቋም ተራራ በጫካውም ካገኛችኋት በመከራ ዓለም በጭንቀት ያለሁ የጎስቋላ አገልጋዩአን ልቅሶ ትነግሯት ዘንድ በኃያሉ አምላክ ስም እለምናችኋለሁ።" ሰቆቃወ ድንግል 7

ሰናይ ሌሊት!

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

1 month, 2 weeks ago
በኢ/ ኦ/ ተ/ ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች …

በኢ/ ኦ/ ተ/ ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ለየአኅጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና ለሰንበት ት/ቤት ክፍል ሐላፊዎች የሁለት ቀን ሥልጠናና የምክክር መድረክ ተከናውኗል።

(የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት) ጥቅምት 11/02/2017 ዓ.ም

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ፵፫ኛውን የሰበካ ጉባኤ ለመካፈል ከተገኙ ከየአኅጉረ ስብከቱ ለመጡ ሥራ አስኪያጆች እና የሰንበት ት/ቤት ክፍል ሐላፊዎች ጋር በሰ/ት/ቤቶች አጠቃላይ እንቅስቃሴ ዙርያ የሥልጠናና የምክክር መድረክ ከጥቅምት 10-11 በጠቅላይ ቤተክህነት በጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ ተከናውኗል።

መርሐ ግብሩ የዳውሮ ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ በተገኙበትና "በምንት ያረትዕ ወሬዛ ፍኖቶ በአቂበ ትእዛዝከ " በማለት " ወጣቶች ያሏት ቤተ ክርስቲያን ነገ ተረካቢ ትውልድ ይኖሯታልና ወጣቱን መጠበቅ የኛ የሁላችን ድርሻ መሆኑን አውቀን ተግተን ልንሠራ ይገባል።" የሚል አባታዊ መልዕክት በማስተላለፍ ተጀምሯል።

በመቀጠልም የማደራጃ መምሪያው ሐላፊ መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወልደ ትንሣኤ በእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክትና ማደራጃ መምርያው እያከናወናቸው የሚገኙ ዋና ዋና ሥራዎችን በማቅረብ የአኅጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና የክፍሉ ተጠሪዎች ከመቼውም ግዜ በላይ ለወጣቶችና ለሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎት ትኩረት በመስጠት ሊሠሩ እንደሚገባ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በሁለቱ ቀን መርሐ ግብር በዲ/ን ዶ/ር ያየህ ነጋሽ "ትኩረት ለሰንበት ት/ቤት ለምን?" እና የሰንበት ት/ቤት አጽተዋጽዎ ለቤተ ክርስቲያን "በሚል ርዕስ በቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኃን ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ስለ ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት መዋቅር አደረጃጀትና ስለ ሥርዓተ ትምህርቱ ምንነትና ዓላማ በዲ/ን ስንታየሁ ምስጋናው በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተ/ም/ሰብሳቢ ለተሳታፊዎች ገለፃ ተደርጓል።

በሁለተኛው ቀን መርሐ ግብር በመገኘት መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ ኢጲፋንዮስ የምስራቅ ጉራጌና የማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ "እንግዲህ እንደተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ኹኑ" (ኤፌ 5፥1) በሚል አምላካዊ ቃል መነሻነት " ወጣቶችና ሕፃናት የነገዎን ቤተ ክርስቲያን የሚያስቀጥሉ የሚረከቡ ናቸውና እናንተ ደግሞ የነሱ መሪ እንደመሆናችሁ ወጣቶችና ሕጻናት የሚመለከቱት እናንተን ነውና ብርሃናቹ በሰው ፊት ይብራ" በማለት አባታዊ መልዕክታቸውን አስተላልፈዎል።

በጉባኤው ማጠቃለያም በሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎትና በማደራጃ መምርያውና የየሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች፤ ሰ/ት/ቤት ክፍል ሐላፊዎች ግንኙነት እና ቀጣይ ሊሰሠሩ ስሚገቡ ሥራዎች የጋራ ውይይት ተደርጎ እንዲህ ዓይነት የጋራ መድረኮች መለመድ እንዳለባቸው በጋራ መግባቢያ ሐሳብ የጉባኤው ፍፃሜ ሆኗል።

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

1 month, 2 weeks ago
የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት -EOTC GSSU
1 month, 2 weeks ago
"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ …

"አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቊርዬውም ቃል በምድራችን ተሰማ።" መኃ 2፥12

የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የማኅበራዊ የትስስር ገጾችን ቤተሰብ ይሁኑ!

ሰናይ ሌሊት!

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)

👉 Youtube

👉 Facebook

👉 Telegram

👉 Tiktok

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago