Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ETHIO-MEREJA®

Description
Addisababa, Ethiopia🇪🇹

News & Media Company®
.

USA : Washington

.
.
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas

1 month ago
ETHIO-MEREJA®
1 month ago
ETHIO-MEREJA®
1 month ago
ETHIO-MEREJA®
1 month, 1 week ago
**A+ Academy ለወላጆች እና ለተማሪዎች

A+ Academy ለወላጆች እና  ለተማሪዎች 
መልካም ዜና ይዞልን መጣ
🤩**

አስጠኝ ይፈልጋሉ?

  1. አዲሱን ሥርዓተ ትምህት መሠረት ያደረገ

2.ከ KG አስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል

3.ልምድ ባካበቱ በተለያየ ት/ ት መስክ በተመረቁ እና በ University ተማሪዎች የሚሰጥ

4.ከ ሰኞ እስከ እሁድ ባሉት ቀናት

ለልጆች ለውጥ የወላጅ ሚና ጉልህ ነው !

ስልክ: 0962804636 ወይም 0942465029**

1 month, 1 week ago
ETHIO-MEREJA®
1 month, 1 week ago
[#CBE](?q=%23CBE)

#CBE

ንግድ ባንክ አጠቃላይ የተወሰደብኝ 801 ሚሊየን ብር ነው ሲል ገለጸ፣ 78 በመቶ የሚሆነውን አስመልሻለሁ ብሏል!!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 06 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት በባንኩ ሲስተም ላይ ባጋጠመው ችግር ያለአግባብ የተወሰደብኝ አጠቃላይ የገንዘብ መጠን 801 ሚሊየን ብር በላይ ነው ሲል ገለጸ።

ከተወሰደበት ገንዘብ ውስጥ 78 በመቶ የሚሆነውን አስመልሻለሁ ሲል ዛሬ መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።

በመጀመሪያው ቀን ብቻ ባደረኩት ጥረት ያላግባብ ብር ከወሰዱብኝ ከ10ሺ 727 ደንበኞቹ አካውንት ውስጥ በቂ ገንዘብ በመኖሩ ከ44 ሚሊየን በላይ አስመልሻለሁ ሲል ገልጿል።

ከዘጠኝ ሺ በላይ የሚሆኑ ያለአግባብ ገንዘብ ከባንኩ ወስደው የነበሩ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ሙሉ በሙሉ መልሰዋል ብሏል።

ከአምስት ሺ በላይ የሚሆኑ ደንበኞቼ በከፊል ያለአግባብ የወሰዱብኝ ገንዘብ መልሰውልኛል ሲል ገልጿል። ባደረኩት ጥረት እስከትላንት መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 623 ሚሊየን የሚጠጋ ብር አስመልሻለሁ ሲል ገልጿል።

ያለአግባብ ገንዘቤን ከወሰዱ ደንበኞቼ መካከል 567 ግለሰቦች ምንም አይነት ገንዘብ አልመለሱልኝም ብሏል።

በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዉስጥ በፍቃደኝነት ገንዘብን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦች ስማቸዉን ጨምሮ ማንነታቸውን የሚገልፅ ምስዕል ከዛሬ ጀምሮ በተለያዩ አማራጮች ይፋ እንደሚያደርግ አስታዉቋል።

-ETHIO-MEREJA-T.me/ethio_mereja

3 months, 1 week ago
**ዜጎች በደህንነታቸው በመንግስት አለመተማመናቸው ስርዓት አልበኝነት …

ዜጎች በደህንነታቸው በመንግስት አለመተማመናቸው ስርዓት አልበኝነት እንዳያነግስ ያሰጋል- ኢዜማ

“በምንም መመዘኛ ቢሆን ንፁሀን ዜጎችን ቤተ እምነት ድረስ ገብቶ መግደል ፖለቲካ ሊሆን አይችልም” ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጥር 16 2016 በጽህፈት ቤቱ በሰጠው መግለጫ ገልጸ።

እንዲህ አይነቱ ድርጊት “ምንም አይነት ግብ የማያሳካ የተራ ሽፍታ የጭካኔ ተግባር ነው” ያለው ኢዜማ፤ በዚህ መልኩ የንፁሀንን ሰላምና ደኅንነት መንጠቅ ቂም ከማትረፍና የመጠፋፋት አዙሪትን ከማክረር ያለፈ አንዳችም ፋይዳ እንደማይኖረው መገንዘብ እንደሚያስፈልግ ገልጿል።ፓርቲው የተወሰኑ ማሳያዎችን በመጥቀስ “ብቻቸውን አገሪቷ ስላለችበት የሰላምና ደኅንነት ቀውስ ብዙ ነገሮችን የሚጠቁሙ ናቸው” ሲል አሳስቧል። 

በዚህም ምክንያት በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን “የባሰ አታምጣ” ብለው ወደ ፈጣሪያቸውን ከመጸለይ አልፈው መንግሥት ከዚህ አደጋ ዜጎችን መጠበቅ እንደተሳነው በማመን እንቅስቃሴያቸውን ገትተው እንደሚገኙ ጠቁሟል።ይህ የዜጎች አረዳድ ውሎ አድሮ “የሚጠብቀኝ መንግሥት የለም” የሚለውን ሥሜት እያሰረጸ በመንግሥት ላይ እምነት ማጣት እና ሥርዓተ አልበኝነትን የሚያነግስ ሁኔታን ሊፈጥር እንደሚችልም ፓርቲው ስጋቱን ገልጿል።

በንጹሀን ዜጎች ላይ ከተፈጸሙ ጥቃቶች መካከል በቄለም ወለጋ ዞን፣ ጊዳሚ ወረዳ በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ኅዳር 14 ቀን 2016 የታጠቁ ቡድኖች በፈጸሙት ጥቃት በዘጠኝ የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ላይ “የጅምላ ግድያ” መፈጸሙን አንስቷል።

-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja

3 months, 1 week ago
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ላይ አቃቤ ህግ …

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ።በቅርቡ በቤተ ክርስቲያን መርሃ ግብር ላይ ያደረጉት ንግግር በተለያዩ ማህበራዊ የትስስር ገፆች በብዛት ሲሰራጭ የታየውና በበርካቶች ዘንድም መነጋገሪያ ሆነው የሰነበቱት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 እና 251 ድንጋጌ ተላልፈዋል በሚል በፍትሕ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጀነራል ዐቃቤ ሕግ ክስ እንደመሰረተባቸው ተሰምቷል።

ክሱ የቀረበባቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ሕገ መንግስታዊና በሕገመንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት መሆኑን የዘገበው ኤፍ ቢሲ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 247 (ሐ) እና አንቀጽ 258(ሀ) ስር የተደነገገውን ድንጋጌ እንዲሁም የወንጀል ህግ አንቀጽ 251 (ሐ) እና አንቀጽ 258 ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚሉ ሁለት ክሶች የተመሰረቱባቸው መሆኑን ነው የዘገበው።

በተጨማሪም ተከሳሽ በፀረ ሰላም ሃይሎች የሚፈፀሙ የወንጀል ተግባሮችን ተከትሎ መንግስት ፈፃሚዎቻቸውን ለሕግ ለማቅረብ እና ሕግ ለማስከበር የሚያደርግባቸው ጥረቶችን ለማደናቀፍ እና ህዝብ መንግስት ላይ እምነት እንዲያጣ ማነሳሳታቸው በክሱ ተመላክቷል ብሏል።

የክስ ዝርዝሩ የደረሰው ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ጥር 27 ቀን 2016 ዓ.ም እንዲቀርቡ ትዕዛዝ በመስጠት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja

3 months, 1 week ago
ቦይንግ ኩባንያ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን እንዳያመርት …

ቦይንግ ኩባንያ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን እንዳያመርት ታገደ

ቦይንግ በበኩሉ የባለስልጣኑን ትዕዛዝ እንደሚያከብር እና ከደንበኞቹ ጋር የደህንነት ውይይቶችን እንደሚያደርግ አስታውቋል

በአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጠን የተጣለው ይህ እገዳ ጊዚያዊ ነው የተባለ ሲሆን ኩባንያው ተጨማሪ የደህንነት ማረጋገጫ እርምጃዎችን እንዲወስድም ተጠይቋል።በአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የተጣለው ጊዜያዊ እገዳ ንብረትነቱ የአላስካ እና ዩናይትድ አየር መንገዶች የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በበረራ ላይ እያለ መስኮቱ መገንጠሉን ተከትሎ እንደሆነ ኤፒ ዘግቧል።

ይህን ተከትሎም ቦይንግ ሰራሽ የሆኑ 737 ማክስ 9 አውሮፕላኖች እንዳይበሩ ተደርጓል።የአሜሪክ አቪዬሽን ባለስልጣን ሀላፊ ማይክ ዌታከር እንዳሉት የማክስ 737 አውሮፕላኖች ከዚህ በፊት የነበረባቸውን የደህንነት ችግር ተፈቷል በሚል ዳግም ወደ በረራ እንዲመለሱ አድርገን ነበር ብለዋል። ይሁንና አሁን ደግሞ ሌላ የደህንነት ችግር በማጋጠሙ ምክንያት ማክስ 737 አውሮፕላኖች ምርት በጊዜያዊነት እንዲቆም ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja

3 months, 2 weeks ago
ኢጋድ ለሶማሊያ ሉዓላዊነትና አንድነት ቁርጠኛ መሆኑን …

ኢጋድ ለሶማሊያ ሉዓላዊነትና አንድነት ቁርጠኛ መሆኑን ገለጸ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ)ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ የሶማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር እሳሰበ።

ኢጋድ ከጉባዔው በኋላ ምሽቱን ባወጣው መግለጫ የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ "ሉዓላዊነትን፣ አንድነትን እና  የግዛት አንድነትን ማክበር  የግድ ነው ብሎ፤ ማንኛውም ስምምነት ወይም ዝግጅት በሶማሊያ መንግሥት ፈቃድ መሆን አለበት ብሏል።

አገራቱ በመካከላቸው ውጥረትን ከሚያባብሱ ድርጊቶች እንዲቆጠቡ እንዲሁም ገንቢ ውይይት እንዲያርጉ ኢጋድ አሳስቧል።

ዛሬ በዩጋንዳ አስተናጋጅነት የተደረጉው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት 42ተኛ አስቸኳይ ጉባዔ ላይ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እንዲሁም የሱዳን መንግሥታት ተወካዮች ባልቱገኙበት የተደረገ ነው።

-ETHIO-MEREJA-T.me/ethio_mereja

We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated hace 1 día, 17 horas

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot

🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹

Last updated hace 5 días, 6 horas

Last updated hace 5 días, 19 horas