ETHIO-MEREJA®

Description
Addisababa, Ethiopia🇪🇹

News & Media Company®
.

USA : Washington

.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot ✔
Advertising
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago

4 weeks, 1 day ago
ETHIO-MEREJA®
4 weeks, 1 day ago
**በሸገር ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የእሳት …

በሸገር ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወታቸው አለፈ

ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሸገር ከተማ ፉሪ ክፍለ-ከተማ በመስሪያና መሸጫ ሼድ ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ እናት ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ  ማለፋን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉ በሼድ ዉስጥ ካሉ  ሱቆች መካከል ስድስት የንግድ ሱቆች ተቃጥለዋል። የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሶስት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት አምቡላንሶች ከሰላሳ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማራ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደሌሎች ንግድ ሱቆች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ከንግድ ሱቆቹ መካከል በአንደኛዉ ነዳጅ በፕላስቲክ ጠርሙስ በችርቻሮ የሚሸጥበት ሱቅ በመሆኑ ለሽያጭ የተዘጋጀዉ ነዳጅ ለቃጠሎው መከሰትና መባባስ ምክንያት ሆኗል።

ከስድስት ወር ልጇ ጋር ህይወቷ ያለፈችዉ እናት በእሳት አደጋዉ ከተቃጠሉት የንግድ ሱቆች ዉስጥ በአንደኛዉ ሱቅ የንግድ ስራ ላይ የነበረች መሆኗን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ ያለበት በተፈቀደለትና የአደጋ ደህንነት መስፈርትን ባሟሉ የነዳጅ መሸጫ ጣቢያዎች ዉስጥ ብቻ መከናወን ያለበት በመሆኑ በተለያዩ የንግድ ሱቆች ዉስጥ ነዳጅ ማከማቸትም ሆነ መሸጥ መሰል አደጋዎችን የሚያስከትል በመሆኑ የንግድ ፈቃድ የሚሰጡ አካላት ተገቢዉን ቁጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋልም ሲሉ አክለዋል።

T.me/ethio_mereja ኢትዮ-መረጃ

4 weeks, 1 day ago
ETHIO-MEREJA®
1 month ago
**ትራምፕ ያልተረጋጋ፣ የበቀል አባዜ የተጠናወተው እና …

ትራምፕ ያልተረጋጋ፣ የበቀል አባዜ የተጠናወተው እና በቁጭት የተጨማለቀ ሰው ነው ሲሉ ካማላ ሀሪስ ተናገሩ!

ዴሞክራቷ ካማላ ሃሪስ በዋሽንግተን በተካሄደ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ለተሰበሰቡ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች እንደተናገሩት የሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸው ዶናልድ ትራምፕ ያልተረጋገጠ ስልጣን ይፈልጋሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ሃሪስ በጃንዋሪ 6፣ 2021 ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል እንዲነሳ ያደረጉትን አመፅ በማስታወስ ተናግረዋል። የካማላ ሀሪስ የድጋፍ ሰልፍ በዋይት ሀውስ አቅራቢያ ባለው ቦታ ከ75,000 በላይ ሰዎች ማክሰኞ ምሽት ላይ ታድመዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ማን እንደሆኑ እናውቃለን ያሉት ሃሪስ የቀድሞ ፕሬዝዳንት በ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የደረሰባቸውን ሽንፈት ለመቀልበስ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ታጣቂ ኃይልን ልከው ነበር። "ይህ ሰው ያልተረጋጋ፣ የበቀል አባዜ የተጠናወተው፣ በቁጭት የተጨማለቀ እና ላልተረጋገጠ ስልጣን የሚሻ ሰው ነው" ሲሉ ሃሪስ ከቀጣዩ ማክሰኞ ምርጫ በፊት ተናግረዋል። በፍሎሪዳ ዩኒቨርሲቲ የምርጫ ማዕከል እንደዘገበው በምርጫው ከ53 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን የአለማችን ባለጸጋ እና ኃያል ሀገርን ማን ለቀጣዮቹ ለአራት አመታት እንደሚመራ ለመወሰን የሚደረገው ፍልሚያ ትንቅንቁ እንዳየለ አስነብቧል።

ሃሪስ በመድረኩ ላይ በአሜሪካ ባንዲራዎች ታጅበው በሰማያዊ እና ነጭ ባነሮች "ነጻነት" የሚል ፅሁፍ ቡስፋት ታይተዋል። በዕድሜ የገፉ እና የኮሌጅ ተማሪዎች፣ ከኒውዮርክ እና ከቨርጂኒያ አቅራቢያ የመጡ ሰዎች ታድመዋል። በርካታ ሴቶች በቡድን ተገኝተዋል። ከአሌክሳንድሪያ ቨርጂኒያ የፌደራል የቀድሞ ሰራተኛ ሳውል ሽዋርትዝ “በፕሬዝዳንት ትራምፕ ወደነበሩት አስከፊ ፖሊሲዎች እንዳንመለስ ይህ ድጋፍ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

T.me/ethio_mereja

1 month ago
**በጉራጌ ዞን "ከፋኖ ጋር በተያያዘ” ከ100 …

በጉራጌ ዞን "ከፋኖ ጋር በተያያዘ” ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸው ተነገረ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ከሰኔ 2016 ዓ.ም. ወዲህ ከ100 በላይ የአማራ ብሔር ተወላጆች “በሽብር” ተጠርጥረው ሲታሰሩ ስጋት ያደረባቸው ነዋሪዎች ደግሞ አካባቢውን ለቀው መሸሸታቸውን ለቢቢሲ ተናገሩ።

በዞኑ አበሽጌ ወረዳ ከሰኔ 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ‘ፋኖ ናችሁ፤ የፋኖ ክንፍ ናችሁ፤ ፋኖን በገንዘብ ትደግፋላችሁ’ በሚል የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ እና እንግልትን ጨምሮ “ማንነትን የለየ” እስር እየፈጸሙ መሆናቸውን በመግለጽ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን አመልክተዋል።

የአካባቢው የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ በቁጥጥር ስር የሚገኙት ነዋሪዎች “በመሳሪያ ዝውውር እና እገታ” ወንጀሎች ተጠርጥረው የተያዙ ናቸው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አብሸጌ ወረዳው ካሉት 30 ቀበሌዎች እና ማዘጋጃዎች 16ቱ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ወላጆች እንደሚኖሩባቸው የተናገሩት ነዋሪዎች፤ ካለፈው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ግን ከፋኖ ጋር በተያያዙ ክሶች ምክንያት “እየተሳደድን ነው” ይላሉ።

“ከባለሀብት እስከ ቀን ሠራተኛ፤ ከፖለቲከኛ እስከ ወጣት፤ ከባጃጅ ሹፌር እስከ ሞተረኛ ድረስ” የእስሩ ሰለባዎች እንደሆኑ አንድ አካባቢውን ለቀው የወጡ ነዋሪ ተናግረዋል። የመንግሥት ሠራተኛ የነበሩ አንድ ነዋሪ የታሰሩ ሰዎች ከ140 በላይ (በወልቂጤ 90 ሰዎች እና ዋልጋ ከ50 በላይ ሰዎች) እንደሚሆኑ ጠቁመው እስሩ አሁንም እንዳላቆመ ገልጸዋል።(አዲስ ማለዳ)

T.me/ethio_mereja ኢትዮ-መረጃ

1 month, 1 week ago
ETHIO-MEREJA®
1 month, 1 week ago
ETHIO-MEREJA®
1 month, 1 week ago
ETHIO-MEREJA®
1 month, 1 week ago
ETHIO-MEREJA®
1 month, 2 weeks ago
ETHIO-MEREJA®
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 2 months, 1 week ago

Last updated 6 days, 22 hours ago

ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ ? @Esat_tv_comment_bot

??ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ??

Last updated 2 months, 3 weeks ago