ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana
**ኢማም ትርሚዚ በዘገቡት ሀዲስ ላይ (ሀዲስ ቁጥር 379) የአላህ መልእክተኛ ﷺ "እነዚህ አስራ ሁለት ረከአዎች በየቀኑ የሰገደ ሰው አላህ ጀነት ውስጥ ቤትን ይገነባለታል" ብለዋል።
══ ❁✿❁═══
⓶ ከአስር በፊት አራት ረከአ
➩ ይህ ረዋቲብ ከሆኑትና በጣም ከጠነከሩት ውስጥ ባይሆንም ነገር ግን በሀዲስ የተረጋገጠ ሱና ሰላት ነው።
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
"አላህ ይዘንለት ከአስር በፊት አራት ረከአን የሰገደ"
(ቲርሚዚ 395 ;አልባኒ ሀሰን ብለውታል ሰሒሐል ጃሚእ 3493)
══ ❁✿❁ ══
⓷ ከመግሪብ በፊት ሁለት ረከአ
➩ ከመግሪብ ሰላት በፊት ሁለት ረከአ ሱናን መስገድን በተመለከተ ኡለሞች ኺላፍ ያላቸው ሲሆን ትክክለኛው አቋም ሻፍእዮችና ኢብን ሀዝም ያሉበት ነው እሱም ከመግሪብ በፊት ሁለት ረከአ መስገድ ሱና ነው የሚለው ነው።
ማስረጃውም
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
.
"ከመግሪብ ሰላት በፊት ስገዱ... ሶስት ግዜ ደጋገሙትና በሶስተኛው ለፈለገ ሰው አሉ" (ቡኻሪ 1183)
═ ❁✿❁ ═
⓸ በየትኛው ሰላት አዛንና ኢቃም መሀከል ሰላት አለ
ከላይ ከጠቀስናቸው ሰላቶች በተጨማሪ የየትኛውም ሰላት አዛን ካለ በሗላ ኢቃም እስከሚል ድረስ ሰላትን መስገድ ይቻላል
ማስረጃውም
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
.
"በሁለቱ አዛኖች መሀከል ሰላት አለ.... ሶስቴ ደጋገሙትና በሶስተኛው ለፈለገ ሰው አሉ"
(ቡኻሪ 627 ሙስሊም 838)
.
➩ ስለዚህ ከሰላቱ በፊት ሚሰገድ ቀብልያ የሌለው ሰላት ቢሆን እንኳን በዚህ ሀዲስ መሰረት ሊሰገድ ይችላል ማለት ነው።
.
➩ በመሆኑም ከኢሻ ሰላት በፊትም ሁለት ረከአ መስገድ ሱና ይሆናል ማለት ነው።
══ ❁✿❁ ══
⓹ ሱና ሰላት ሚከለከልባቸው ሶስት ወቅቶች
.
➀ኛ ከሱብሂ ሰላት በሗላ ፀሀይ ወጥታ የተወሰነ ከፍ እስክትል
.
➁ኛ ፀሀይ አናት ላይ ስቶን የተወሰነ እስክትዘነበል
.
➂ኛ ከአስር በሗላ ፀሀይ እስክትጠልቅ
'
➧በሶስቱም ወቅቶች ላይ የመጡ ሀዲሶች ስላሉ
══ ❁✿❁ ═
⓺ ከዋጅብ ሰላት በፊት ሚሰገዱ ያልናቸው ሰላቶች የዛ ሰላት ወቅቱ ከገባ (አዛን ካለ) በሗላ ነው ሚሰገዱት።
═ ❁✿❁ ═
⓻ አራት ረከአ ሚሰገዱ ሱና ሰላቶች በየሁለት ረከአው እያሰላመትን ነው ምንሰግዳቸው
.
ማስረጃው
.
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
"የለሊትም የቀንም ሰላት ሁለት ሁለት ረከአ ነው"
(ቲርሚዚ 597; አቡ ዳውድ 1295; ነሳኢ 1666) .#share_አድርገህ_የአጅሩ_ተካፋይ_ሁን
?click & Join?**
t.me/iqraknow t.me/iqraknow t.me/iqraknow t.me/iqraknow
▒ሱረት አል-ኢኽላስ የወረደበት ምክኒያት▒
----------------------------
ኢማም አል-በይሀቂይ - ኢብኑ አባስ ብለዋል በማለት ተናግረዋል «አይሁዶች ረሱል [ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም] ዘንድ መጥተው 'አንተ ሙሐመድ ሆይ! አንተ የምታመልከውን ጌታ ግለፅልን' በማለት ሲጠይቁ፤ በዚህ ግዜ 'ሱረቱል ኢኽለስ' ለነቢዩ ሷለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ወረደላቸው፦
ﻗﻞ ﻫﻮ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺣﺪ * ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺼﻤﺪ * ﻟﻢ ﻳﻠﺪ ﻭﻟﻢ ﻳﻮﻟﺪ * ﻭﻟﻢ ﻳﻜﻦ ﻟﻪ ﻛﻔﻮﺍ ﺃﺣﺪ *
ከዛም ረሱል [ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም] «ይህ ነው የጌታዬ በህሪ» ብለው መለሱላቸው። ይህም የአይሁዶች ጥያቄ ለእውቀትና ሐቅን ለማወቅ አልነበረም። የዚህ ምዕራፍ ትርጉሙም፦
1- ﻗﻞ ﻫﻮ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﺣﺪ
«ክፍፍልና ብዛትን የማይቀበል፤ በዛቱ (በእውኑ)፣ በበህሪውም ሆነ በድርጊቱ ምንም አጋር የሌለው። ማለትም ማንም የአሏህን በህሪ የሚመስል ያለው የለም» ማለት ነው።
2- اﻟﻠﻪ ﺍﻟﺼﻤﺪ
«ሁሉም ነገራት በእርሱ ፈለጊ ሲሆኑ፤ እርሱ ግን ከማንም ከጃይና ፈላጊ ያልሆነ ጌታ (አሏህ) ነው»።
3- ﻟﻢ ﻳﻠﺪ ﻭﻟﻢ ﻳﻮﻟﺪ
«አይወልድም (ከሱ ሚወጣ ነገር የለም)፤ አይወለድም (ከሌላ የወጣም አይደለም)»።
4- ﻭﻟﻢ ﻳﻜﻦ ﻟﻪ ﻛﻔﻮﺍ ﺃﺣﺪ
«አርሱን በምንም አይነት የሚመስል የለም፤ አምሳያም ሆነ ቢጤ የለውም»
.
ሱረቱል ኢኽላስ ተውሒድን በአጭሩ አጠቃላ የያዘች አንቀፅ ናት። አሏህ ትርጉሟን በተገቢው ካወቁት ያድርገ።
http://t.me/iqraknow http://t.me/iqraknow
ታላቁ መልእክተኛ ሙሐመድ ( ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦ «አንድ ሰው በሚሰራው ወንጀል ምክንያት ሪዝቅን(ሲሳይ) ይከለከላል።»
አላህ ወንጀሎቻችንን የምናይበት ጥበብ ይስጠን።
#ከተኛን በኋላ ንጋት ላይ የምንነሳው እኛ መነሳት ስለቻልን ሳይሆን አሏህ ሌላ አድስ ቀን እንድንኖር ስለፈቀደልን ነው።
አልሀምዱሊላህ!!
http://t.me/iqraknow http://t.me/iqraknow
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።
@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna
#ኢትዮጵያ
Last updated hace 3 semanas, 5 días
Last updated hace 3 semanas
ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ 👉 @Esat_tv_comment_bot
🇪🇹ኢሳት የኢትዮጵያ አይን እና ጆሮ🇪🇹
Last updated hace 1 mes, 1 semana