Exposing Only Jesus ኦንሊ ጂሰስ

Description
ይህ የኦንሊ ጂሰሶች የሀሰት ትምህርትን የሚያጋልጥ ፔጅ ነው

ዮትዩባችንን ሰብስክራይብ አድርገው ይከታተሉ
https://youtube.com/@ExposingOJ

ለማኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት @SDG1517 ላይ ይጻፉልን
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 1 month ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 2 days, 21 hours ago

2 weeks, 2 days ago

የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህንን ያደርጋል ማለት፥ ይህ ሕጻን እንዲወለድ የሚያደርገው ደግሞም በዳዊት ዙፋን ላይ የሚያስቀምጠው እግዚአብሔር ነው ማለት ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርና መሲሁ አስነሺና ተነሺ ናቸው ማለት ነው

እግዚአብሔር መሲሁን በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጥ ዘንድ የሚያስነሳ ሲሆን፤ መሲሁ ደግሞ የዳዊት ሆድ ፍሬ ሆኖ የሚነሳ ወይንም በዙፋኑ የሚቀመጥ ነው ማለት ነው። ስለዚህ የሚወለደው ህጻንና እግዚአብሔር የተለያዩ ማንነቶች ናቸው ማለት ነው።

እግዚአብሔር መሲሁን ያስነሳል ማለት ምን ማለት ነው?

እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ላይ ይቀመጥ ዘንድ መሲሁን ያስነሳዋል ማለት፥ ልጁን በስጋ ይልካል ማለት ነው

በ2 ሳሙ 7:12-16 ላይ እግዚአብሔር በነቢዩ ናታን አማካኝነት ከወገቡ ፍሬ በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥና ያም ልጁ ለዘላለም እንደሚገዛ ለንጉስ ዳዊት ቃል ገብቶለታል። በመጽሐፍ ቅዱስ የወገብ ፍሬ ማለት የስጋ ልጅ ማለት ነው። (1 ነገ 8:19 2 ዜና 6:9)

ስለዚህ እግዚአብሔር መሲሁን ያስነሳዋል ማለት፥ ልጁን ከዳዊት ዘር እንዲሰገው ያደርገዋል ማለት ነው። በመልኩ (መለኮቱ) ሲኖር የነበረውን ልጁን በዚያ ስጋ ልኮታል። ይህ በኢሳ 9:6-7 "የእግዚአብሔር ቅናት ይህንን ያደርጋል" ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ያደርጋል። አብ ልጁን በስጋ ይልከዋል ማለት ነው። ያስነሳዋል የሚለው ትንቢት በዚህ መልኩ ተፈጸመ

" ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን፥ እግዚአብሔር የገዛ #ልጁን #በኃጢአተኛ_ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት #ልኮ አድርጎአልና፤"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:3)

"22፤ እርሱንም ከሻረው በኋላ #ዳዊትን በእነርሱ ላይ እንዲነግሥ አስነሣው፥ ሲመሰክርለትም። እንደ ልቤ የሆነ ሰው ፈቃዴንም ሁሉ የሚያደርግ የእሴይን ልጅ #ዳዊትን አገኘሁ አለ። 23፤ ከዚህም #ሰው #ዘር እግዚአብሔር እንደ ተስፋው ቃል ለእስራኤል መድኃኒትን እርሱም #ኢየሱስን #አመጣ።" (የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 13:22-23)

"ያለው ከቶ ለማን ነው? ደግሞም #በኵርን ወደ ዓለም #ሲያገባ። የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉም ለእርሱ ይስገዱ ይላል።"
(ወደ ዕብራውያን 1:6)

" በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ #ልጁን ወደ ዓለም #ልኮታልና።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:9)

➣ ለዚህም ነው በተለያዩ ስፍራዎች እግዚአብሔርና መሲሁ በአንድ አውድ ላይ ሁለቱም "እግዚአብሔር/ያሕዌ" እና "አምላክ" ተብለው የተጠሩት። የመለኮት አንድነትና የማንነት ሁለትነት በመኖሩ ነው። (ኤር 23:5-6 መዝ 45:6-7)

መደምደሚያ

ስለዚህ ከላይ የቀረቡት ማስረጃዎች በሙሉ፥ ኢሳያስ 9:6-7 "መሲሁ ራሱ እግዚአብሔር አብ ነው" የሚለውን የስህተት ትምህርት እንደማይደግፍ ያሳያሉ።

በተቃራኒው ያ ክፍል እግዚአብሔርና መሲሁ ሁለት መለኮታዊ ማንነቶች መሆናቸውን እንደሚያስተምር ያረጋግጣሉ

ጌታ ይርዳን!

Source : @logostheos111

2 weeks, 2 days ago

? የኢሳያስ 9 ማብራሪያ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች፥ እንደ ኢሳያስ 9:6 በስህተት የሚተረጎም ክፍል የለም። የተለያዩ ወገኖች ይህንን ጥቅስ ከአውዱና ከቋንቋ ህጉ ጋር በተጣላ መልኩ ሲፈቱት ይታያል። ከነዚህ የተሳሳቱ ትርጓሜዎች አንዱ "ኢሳ 9:6 መሲሑ ራሱ እግዚአብሔር አብ መሆኑን ያሳያል" የሚለው ነው

▶️ ዛሬ እግዚአብሔር በፈቅድ ይህንን የተሳሳተ ትርጉም በቃሉ እውነት ለማረም እንሞክራለን

"6 ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። 7፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን ያደርጋል" (ኢሳያስ 9:6)

➣ ይህ ቃል መሲሁ ራሱ እግዚአብሔር አብ መሆኑን ያሳያል የሚሉ ወገኖች የተሳሳቱበት ዋናው ነጥብ "የዘላለም አባት" በሚለው ሀረግ ትርጉም ነው። የዘላለም አባት ተብሎ የተተረጎመው የዕብራይስጥ ቃል "አቪዓድ/אביעד" ሲሆን "የዘላለም ባለቤት፥ ዘላለማዊ" ማለት ነው። የሚወለደው ህጻን መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው እንደሆነ፤ ዘላለማዊነት ባህርይው እንደሆነ የሚያሳይ ቃል ነው።

כי ילד ילד לנו בן נתן לנו ותהי המשרה על שכמו ויקרא שמו פלא יועץ אל גבור #אביעד שר שלום
(Isaiah 9:6)

በዕብራይስጥ ባለቤትነትን ለመግለጽ "አባት" የሚለው ቃል ጥቅም ላይ ይውላል።

ለምሳሌ፦

" #የአቢካኢልም ልጅ ንግሥቲቱ አስቴርና አይሁዳዊው መርዶክዮስ ይህችን ስለ ፉሪም የምትናገረውን ሁለተኛይቱን ደብዳቤ በሥልጣናቸው ሁሉ ያጸኑአት ዘንድ ጻፉ። "
(መጽሐፈ አስቴር 9:29)

አቢካኢል የሚለው ቃል "אֲבִיהַיִל/አቪሃይል" በአወቃቀሩ ከዘላለም አባት ጋር አንድ አይነት ሲሆን ትርጓሜው "የብርታት አባት" ማለት ነው። የብርታት አባት ማለት ብርቱ የሆነ፥ ያ ባህርይ ያለው ማለት ነው። አባት ባለቤትነትን ለማመልከት የገባ ቃል ነው

- Father (i.e #possessor) of might

[ Strong's Hebrew Concordance H32 ]

" ምድርም ተከፈተች ዳታንንም ዋጠችው፥ #የአቤሮንንም ወገን ደፈነች፤"
(መዝሙረ ዳዊት 106:17)

አቤሮን "אֲבִירָם/አቪራም" የሚለው ቃል ከዘላለም አባት ጋር ተመሳሳይ አወቃቀር ያለው ሲሆን የከፍታ አባት ማለት ነው። የከፍታ አባት ማለት ከፍ ያለ፥ የገነነ ማለት ነው። አባት የዚያ ባህሪ ባለቤት መሆኑን ለማሳየት የገባ ቃል ነው

- Father of height (i.e #lofty)

[ Strong's Hebrew Concordance H48 ]

" የምድያምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፌር፥ ሄኖኅ፥ #አቢዳዕ፥ ኤልዳዓ ናቸው። እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።"
(ኦሪት ዘፍጥረት 25:4)

በዚሁ ስፍራም ተመሳሳይ አወቃቀር ያለው ቃል እናገኛለን። አቢዳዕ "אֲבִידָע/አቪዳዕ" ማለት የእውቀት አባት ማለት ነው። የእውቀት አባት ማለት አዋቂ ማለት ነው። አባት ባለቤትነትን ለመግለጽ የገባ ቃል ነው

- Father of knowledge (i.e #knowing)

[ Strong's Hebrew Concordance H28 ]

" እኅቱ መለኬት ኢሱድን፥ #አቢዔዝርን፥ መሕላን ወለደች።"
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 7:18)

በዚሁ ስፍራም ተመሳሳይ አወቃቀር ያለው ቃል እናገኛለን። አቢዔዝር "אֲבִיעֶזֶר/አቪዔዜር" ማለት የእርዳታ አባት ማለት ነው። የእርዳታ አባት ማለት ደግሞ የሚረዳ፥ እረጂ ወይንም ረድዔት ማለት ነው። አባት የዚያን ባህርይ ባለቤትነትን ለመግለጽ የገባ ቃል ነው

- Father of help (i.e #helpful)

[ Strong's Hebrew Concordance H44 ]

" ከሑሺምም #አቢጡብንና ኤልፍዓልን ወለደ።"
(መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 8:11)

ይህ አቢጡብ "אֲבִיטוּב/አቪቶቭ" የሚለው ቃልም ከሌሎቹ ቃላት ጋር አንድ አይነት አወቃቀር ያለው ሲሆን የመልካምነት አባት ማለት ነው። የመልካምነት አባት ማለት ደግሞ መልካም ማለት ነው። አባት የዚያን ባህርይ ባለቤትነት ለመግለጽ የገባ ቃል ነው

- Father of goodness (i.e #good)

[ Strong's Hebrew Concordance H36 ]

➣ ሌሎች ብዙ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል። በዚህ አይነት አወቃቀር አባት የሚለው ቃል ሲገባ፥ ባለቤትነትን ወይንም የዚያ ባህርይ ገላጭ ሆኖ ያገለግላል። ስለዚህ ኢሳ 9:6 መሲሁ ዘላለማዊ መሆኑን ያሳያል እንጂ ራሱ እግዚአብሔር አብ መሆኑን አያሳይም

ይህንንም ሀቅ፤ ክርስትና ከመጀመሩ በፊት የነበሩ አይሁድ አረጋግጠውታል። ብሉይ ኪዳንን ከዕብራይስጥ ወደ አረማይስጥ በተረጎሙበት ታርጉማቸው ላይ፥ የዘላለም አባት የሚለውን ቃል "ለዘላለም የሚኖር" በማለት ነው የተረጎሙት፦

The prophet said to the house of David, For unto us a child is born, unto us a son is given, and he has taken the law upon himself to keep it. His name is called from eternity wonderful, the mighty God who #liveth_to_eternity, the Messiah whose peace shall be great upon us in his days.

[ Targum Johnathan Isaiah 9:6 ]

➣ አዲስ ኪዳንም ይህንን በማጽናት መሲሑ ኢየሱስ ክርስቶስ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ መሆኑን ይናገራል

" ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ። አትፍራ፤ #ፊተኛውና #መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥"
(የዮሐንስ ራእይ 1:17)

" #አልፋና #ዖሜጋ#ፊተኛውና #ኋለኛው#መጀመሪያውና #መጨረሻው እኔ ነኝ።"
(የዮሐንስ ራእይ 22:13)

ስለዚህ መሲሁ የዘላለም አባት መባሉ ዘላለማዊነቱን እንጂ ራሱ እግዚአብሔር አብ መሆኑን አያሳይም። አባት የሚለው ቃል ሕጻኑ የዘላለማዊነት ባህርይ እንዳለው የሚያሳይ ነውና

♦️ሲቀጥል፥ በኢሳይያስ 9:6-7 ሁለት መለኮታዊ ማንነቶችን እንመለከታለን!

እነዚህ ወገኖቻችን ካላስተዋሏቸው እጅግ ዋና ነጥቦች መካከል በኢሳ 9:6-7 ሁለት መለኮታዊ ማንነቶች መኖራቸው ነው። የሚወለደው ሕጻን እና ያንን ያደርጋል የተባለው እግዚአብሔር

"6፤ #ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ #ኃያል_አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል። 7፤ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም ድረስ በፍርድና በጽድቅ ያጸናውና ይደግፈው ዘንድ በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ አለቅነቱ ይበዛል፥ ለሰላሙም ፍፃሜ የለውም። #የእግዚአብሔር ቅንዓት ይህን #ያደርጋል።" (ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 9:6-7)

➣ ነቢዩ ኢሳያስ ሕጻን እንደሚወለድ፥ ያም ሕጻን ኃያል አምላክ እንደሆነ ከተናገረ በኋላ በዳዊት ዙፋን ላይ ለዘላለም እንደሚቀመጥ ይተነብያል። ይህንን የሚያደርገውም የእግዚአብሔር ቅንዓት መሆኑን ይናገራል

2 weeks, 6 days ago

ተወዳጆች እንዴት ቆያችሁ? እስቲ ሠላም እንባባልና ትንሽ ደግሞ እንመካከር በቅርብ ጊዜ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ወደ አገልግሎት እንመለሳለን እና ምን ታስባላችሁ? አገልግሎታችን ላይ ምን አስተያየት አላችሁ?

6 months, 2 weeks ago

የቢሾፕ ደጉን የስህተት ትምህርት ክፍል 8 ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ እየተሰጠበት ነው ይምጡና ይከታተሉ

6 months, 2 weeks ago
We recommend to visit

ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ

Last updated 1 month, 1 week ago

Last updated 1 month ago

ይህ ስለ Manchester United መረጃዎችን የሚያገኙበት የ Telegram ቻናል ነው 🇪🇹
--------------------------------------------------------------
☞︎| ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ትኩስ መረጃዎች
☞| ቀጥታ ስርጭቶች ከየስታድየሞቹ
☞| የዝውውር ዜናዎች
☞| ስለ ማንችስተር ዩናይትድ ታሪኮች

📩 ለማስታወቂያ ስራ DM :- @Marcoabdu

Last updated 2 days, 21 hours ago